Documents Authentication and Registration service

Call Directions Website Contact the organization

Documents  Authentication and Registration service ምንግዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

ክብርት ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ የኢፌድሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።እንኳን ደስ ያለዎት!!የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆ...
08/10/2026

ክብርት ወ/ሮ ሃና አርአያስላሴ
የኢፌድሪ ፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል።
እንኳን ደስ ያለዎት!!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች መልካም የሥራ ዘመን እንዲሆንልዎ ይመኛሉ!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት
ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

የመልካም ምኞት መግለጫ!!!!እንኳን ደስ ያላችሁ!- እንኳን ደስ ያለን!የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና  እና ሠራተኞች፣ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒ...
05/10/2026

የመልካም ምኞት መግለጫ!!!!

እንኳን ደስ ያላችሁ!- እንኳን ደስ ያለን!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና እና ሠራተኞች፣ ክቡር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በድጋሚ በመመረጣቸው የተሰማንን ደስታ እየገለጽን፣ መጪው የሥራ ዘመን የስኬት እንዲሆንላቸው እንመኛለን!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት

ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

05/10/2026
መልካም የኢሬቻ በዓል!Baga Ayyaana Irreechaan nu gahe!Happy Irrecha!የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ Authentication an...
02/10/2026

መልካም የኢሬቻ በዓል!
Baga Ayyaana Irreechaan nu gahe!
Happy Irrecha!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት
ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ
Authentication and Registration service

ጠቃሚ መረጃ :የሥራ ቅጥር ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፣ (የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1 አዋጅ ቁጥር 1156/2011) በተቋሙ ትኩረት የሚሰጥባቸው ነጥቦች1.-በሥራ ቅጥር ውል ወቅት ስራው ልዩ ሙያ ...
30/09/2026

ጠቃሚ መረጃ :

የሥራ ቅጥር ውል ሰነድ አረጋግጦ ለመመዝገብ፣ (የፍ/ብ/ህ/ቁ/ 1 አዋጅ ቁጥር 1156/2011) በተቋሙ ትኩረት የሚሰጥባቸው ነጥቦች

1.-በሥራ ቅጥር ውል ወቅት ስራው ልዩ ሙያ የሚጠይቅ እንደ ህክምና፣ ምህንድስና፣ የተመሰከረለት የሂሳብ ስራ ባለሙያ፣ አሽከርካሪ እና የመሳሰሉትን ከሆነ ተቀጣሪው (ተቀጣሪዎች ) ምን ጊዜም የሙያ ፈቃድ ወይም የብቃት ማስረጃ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሆኖም ግን ሌሎች ስራዎችን በተመለከተ እንደሁኔታው እየታየ አገልግሎት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

2.- በሥራ ቅጥር ውል ወቅት ተቀጣሪው የሚያቀርበው የትምህርት ወይም የሞያ ብቃት ማስረጃ የተሰጠው ከግል ወይም ከውጭ ሀገር ተቋማት ከሆነ ማስረጃው በሃገር ውስጥ በሚመለከተው አካል ዕውቅና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡

3.-ተቀጣሪው የውጭ አገር ዜጋ ከሆነ የመጠቀሚያ ጊዜው ያላለፈ የመኖሪያ ፈቃድ፤ ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የስራ ፈቃድማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

4.- የውጭ ሃገር ዜጋ የሥራ ቅጥር የውሉ ጊዜ የሚወሰነው በተሰጠው የሥራ ፈቃድ ላይ ባለው ጊዜ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የውጭ አገር ዜጎች የስራ ቅጥር ውል ከሦስት አመት የሚበልጥ መሆን የለበትም፡፡

የጥልቅ ሃዘን መግለጫ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ቅርንጫፍ 14 ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ተዋበች አንዳርጌ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካ...
27/09/2026

የጥልቅ ሃዘን መግለጫ

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ቅርንጫፍ 14 ጽ/ቤት የስራ ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ ተዋበች አንዳርጌ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል::

የነፍስኄር ወ/ሮ ተዋበች አንዳርጌ ስርዓተ ቀብር በአዲስ አበባ ከተማ ዘነበወርቅ አካባቢ በሚገኘው ቅዱስ አቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን ዛሬ መስከረም 17 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 5:00 ላይ ይፈጸማል።

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት አመራርና ሰራተኞች በባልደረባችን ህልፈት የተስማንን ጥልቅ ሀዘን እየገልጽን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መጽናናትን እንመኛለን::

ውድ ተገልጋዮቻችን ፣እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ! መልካም በዓል ይሁንልዎ!የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባአገልግሎት ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋዮች
25/09/2026

ውድ ተገልጋዮቻችን ፣
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!
መልካም በዓል ይሁንልዎ!

የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባአገልግሎት

ምንጊዜም ቅድሚያ ለተገልጋዮች

ውድ ተገልጋዮች የንግድ ማህበር ቃለ ጉባኤ ሰነድ አረጋግጠው ለማስመዝገብ የሚከተሉትን ማዘጋጀት ይኖርብዎታል።1. የቃለ ጉባኤው ሰነድ·በህጉ መሰረት የተዘጋጀ መሆን አለበት።· በኦንላይን ሲስተ...
24/09/2026

ውድ ተገልጋዮች የንግድ ማህበር ቃለ ጉባኤ ሰነድ አረጋግጠው ለማስመዝገብ የሚከተሉትን ማዘጋጀት ይኖርብዎታል።

1. የቃለ ጉባኤው ሰነድ
·በህጉ መሰረት የተዘጋጀ መሆን አለበት።
· በኦንላይን ሲስተም ተሞልቶ የመከታተያ ቁጥር ማግኘት አለበት።

2. የፈራሚዎች መታወቂያ
·ውሉን የሚፈርሙ ሰዎች መታወቂያ ማቅረብ አለባቸው።

3. የማህበሩ ሰነዶች
የመመስረቻ ጽሑፍ
· የንግድ ምዝገባ ወይም የታደሰ የንግድ ፈቃድ
· እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ እና መተዳደሪያ ደንብ
ማቅረብ አለብዎ።

4. የጉባኤ ጥሪ እና ኮረም
· ጥሪው በመመስረቻ ጽሑፍ፣ በመተዳደሪያ ደንብ ወይም በህግ መሰረት መደረጉን ማረጋገጥ።
· ኮረም መሟላቱን ማረጋገጥ

5. የፈራሚው ስልጣን
·ፈራሚው ስልጣን ያለው መሆኑን ማረጋገጥ።
· ለአክስዮን ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ከሆነ፣ አባሉ የውክልና ቅጽ (Proxy) ፈርሞ ውክልና የሰጠበት ማስረጃ ማቅረብ አለበት።

6. አዲስ አባል የንግድ ማህበር ከሆነ
የመመስረቻ ጽሑፍ
· የንግድ ምዝገባ ወይም የታደሰ ፈቃድ
· እንደአስፈላጊነቱ ቃለ ጉባኤ
ማቅረብ አለበት።

7. አዲስ አባል ንግድ ያልሆነ ማህበር ከሆነ
ጊዜው ያላለፈበት የምዝገባ ምስክር ወረቀት
· መተዳደሪያ ደንብ
· ኃላፊነትን የሚያሳይ ከመዝጋቢ መንግስታዊ አካል የተጻፈ ደብዳቤ
ማቅረብ አለበት።

8. አዲስ አባል አካለ መጠን ያልደረሰ ከሆነ
የልደት ሰርተፍኬት
· የወላጆች የጋራ ፈቃድ ወይም የውክልና ማስረጃ
· ወይም የፍርድ ቤት የሞግዚትነት ማስረጃ
ማቅረብ አለበት።

9. የስም ለውጥ ካለ
ከንግድ ሚኒስቴር/ቢሮ የተሰጠ ደብዳቤ ማቅረብ አለብዎ።

10. በአይነት መዋጮ ካለ
· የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ማቅረብ አለብዎ።

11. ንብረቱ እግድ አለመኖሩ
· ከንብረት መዝጋቢ አካል ማስረጃ ማቅረብ።
· በተቋሙ መረጃ ቋት እግድ አለመኖሩን ማረጋገጥ።

12. የባለንብረቱ የጋብቻ ሁኔታ
· ያላገባ ከሆነ፡ ያላገባ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ።
· ያገባ ከሆነ፡ የጋብቻ ማስረጃ እና የትዳር አጋር የፈቃድ ስምምነት።

13. በአይነት መዋጮ ለኢንቨስትመንት ከሆነ
· የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሆነ፡ ከክልል/ከከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ቢሮ የድጋፍ ደብዳቤ።
· የሚንቀሳቀስ ንብረት ሲሆን ከቀረጥ ነፃ የገባ ከሆነ፡ ከሚመለከተው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለብዎ።

14. የአክስዮን/ድርሻ ሽግግር ካለ
· ማህበሩን ለማፍረስ ዕግድ አለመኖሩን ማረጋገጥ።
· ለሽግግሩ የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ አለብዎ።



15. በአይነት መዋጮ ከአዲስ አበባ ውጭ ከሆነ
· ከዚህ ቀደም እግድ እንደሌለበት የሚገልጽ፣ በተቋሙ አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ አለብዎ።

በአጭሩ ማስታወሻ

· ሰነዱ በህግ መሰረት መዘጋጀቱን
· በኦንላይን መመዝገቡን
· ፈራሚዎች መታወቂያና ስልጣን ማረጋገጣቸውን
· የማህበሩ ሰነዶች
· የጉባኤ ጥሪና ኮረም
· እንደ ጉዳዩ የአባልነት፣ የንብረት፣ የጋብቻ፣ የቀረጥና የእግድ ማስረጃዎች
መቅረብ አለባቸው።

ማስታወሻ፦
ከላይ የተዘረዘሩት ሰነዶች ካልተሟሉ ወይም መረጃው ካልተረጋገጠ፣ ምዝገባው ሊዘገይ ወይም ተጨማሪ ማስረጃ ሊጠየቅ ይችላል።

ለተጨማሪ መረጃ ወይም እርዳታ ወደ ተቋሙ የደንበኞች አገልግሎት ክፍል ይቅረቡ።

16/09/2026

የንግድ ማህበራት የተለያዩ አጀንዳዎችን የቃለ ጉባዔ ሰነድ ለማጽደቅ መሟላት ያለባቸዉ ነጥቦች ቅድመ ሁኔታዎች:-

መስከረም 6 ቀን 2019 ዓ.ም

1-ካፒታል ማሳደግ ሲሆን፣

ሀ. ከማህበሩ የትርፍ ክፍፍል በማድረግ፣

ለ. በጥሬ ገንዘብ ወይም የዓይነት መዋጮ በማድረግ፣

ሐ. ማህበሩ ያለበትን የዕዳ ሰነዶች ወደ አክስዮን በመለወጥ፣

መ.ማህበሩ ያሉበትን የመክፈያ ጊዜአቸው የደረሱ ዕዳዎችበአክስዮንበማቻቻል፣

ሠ. የማህበሩ መጠባበቂያ ገንዘብ ወይም ማህበሩ ሊያዝባቸው የሚችሉ ሌሎች ገንዘቦችን ወደ ዋና ገንዘብ በመጨመር፣

ረ. የነባር አክስዮኖችን ዋጋ (Par value)በመጨመር መሆን አለበት

2-ካፒታል መቀነስ ሲሆን

የንግድ ማህበር ካፒታል መቀነስ የሚችል ሲሆን የመቀነሻ መንገዶቹም የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. በአክስዮኖች ላይ የተጻፈውን ዋጋ /Par value/ በመቀነስ፣

ለ. የነባር አክስዮኖችን ዋጋ ሳይቀንስ ቁጥራቸውን በመቀነስ ይሆናል፡፡

3-የንግድ ማህበራት ውህደት ሲሆን፣

ሀ. በተናጠል ተረጋግጦ የተመዘገበ ቃለ ጉባኤ፣

ለ. የሚዋሀዱት ማህበራት ዕዳና ዕገዳ የሌለበት መሆን አለበት፣

ሐ. የንግድ ማህበሩ ጠቅላላ ካፒታል በህግ ከተቀመጠው መነሻ ገንዘብ በላይ ሲሆን አግባብ ካለው አካል ውህደቱን የሚፈቅድ ደብዳቤ መቅረብ አለበት፣

መ. የሚዋሀዱት የንግድ ማህበራት ለእያንዳንዳቸው የገቢዎች ክሊራንስ መቅረብ አለበት፣

ሠ. የሚዋሃዱት የንግድ ማህበራት የየራሳቸውን ነባር የመመስረቻ ጽሁፍ፤ የንግድ ምዝገባ እና ቀደም ሲል የተመዘገበ ቃለጉባዔ እንደአስፈላጊነቱ መቅረብ አለበት፣

4-የንግድ ማህበር ለውጥ ማድረግ ሲሆን፣

ሀ. ነባር የመመስረቻ ጽሁፍ፣ የንግድ ምዝገባ ፤እንደአስፈላጊነቱ ቃለጉባዔ፣

ለ. የሚለወጠው የማህበር ዓይነት የስያሜ ደብዳቤ

ሐ. ከገቢዎች ክሊራንስ፣

መ. ዕዳና ዕገዳ የሌለበት መሆን አለበት ፣

ሠ. ፈራሚዎች ከህግ፤ ከውል ወይም ከፍርድ ቤት ውሳኔ የመነጨ ስልጣን ያላቸው መሆን አለባቸው ፣

5-የንግድ ማህበር መፍረስ ሲሆን፣

የቃለጉባዔ ሰነድ ለመመዝገብ በመመሪያው የተዘረዘሩት መስፈርቶችን መከተል በቂ ነው፡፡

6-የውጭ ሀገር ዜጎች በነባር የንግድ ማህበር የሚገቡ ሲሆን መሟላት ያለባቸው ቅድመሁኔታዎች ፣

ሀ. ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተሰጠ የድጋፍ ደብዳቤ፣

ለ..በኢንቨስትመንት አዋጁ መሠረት ለማህበሩ ሊከፈል የሚገባው መዋጮ ፣

ሐ. አዲስ ገቢው የውጭ ሃገር የህግ ሰውነት ያለው አካል ከሆነ በማህበሩ ውስጥ ለመግባት መወሰኑን የሚያሳይ በሀገሩ ህግ መሠረት የተረጋገጠ ቃለጉባዔ ወይም ደብዳቤ ወይም ተመሳሳይ ሰነድ ማቅረብ አለበት፣

መ. ማህበሩ ከተቋቋመበት ሀገር ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት ማረጋገጫ ሰነድ ማቅረብ አለበት ፣

እንኳን አደረሳችሁ እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሠላምና በጤና አደረሳችሁ መጪው ዘመን የመተሳሰብና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::መልካም አዲስ ዓመት!የሰነዶች ማረጋገጫና  ምዝገ...
10/09/2026

እንኳን አደረሳችሁ

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲሱ ዓመት በሠላምና በጤና አደረሳችሁ መጪው ዘመን የመተሳሰብና የስኬት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን::

መልካም አዲስ ዓመት!
የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት
ምንግዜም ቅድሚያ ለተገልጋይ!

Address

Addis Ababa
29935

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Documents Authentication and Registration service posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Documents Authentication and Registration service:

Share