Ethiopian Media Authority - ኢመብባ

Ethiopian Media Authority - ኢመብባ

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Media Authority - ኢመብባ, Public & Government Service, Addis Ababa.

This is the official page of the Ethiopian Media Authority of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, a government body with a mission of Promoting Pluralistic and Responsible Media through enabling Regulation, Capacity Building, and Partnership.

Photos from Ethiopian Media Authority - ኢመብባ's post 01/06/2026

በኢትዮጵያ የሕዝብ፣የንግድ፣ የበይነ-መረብ፣የማህበረሰብ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ሰፊና ከፍተኛ ሽፋን ያለው የዘገባ ሥራ እያከናወኑ ይገኛል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ይህን ታላቅ ሀገራዊ ሂደት መገናኛ ብዙሃኑ ተደራሽ እያደረጉ ስለመሆናቸው ለማረጋገጥ የሚያስችል የሚዲያ ይዘት ክትትል እያደረገ ይገኛል።


29/05/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት መገናኛ ብዙኃን ለሀገር ሰላም፣ ደህንነት፣ ለብሔራዊ ጥቅምና የወል ትርክት ግንባታ ያላቸውን ሚና እንዲያጠናክሩ ተከታታይ የአቅም ግንባታ ስራዎች በስፋት እያካሄደ ይገኛል። እነዚህ የአቅም ግንባታ ስራዎችና የጋራ ምክክር መድረኮችም አበረታች ውጤቶች እያስገኙ ያሉ ናቸው።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ


28/05/2026

"አዲሱ የቴክኖሎጂ ስርዓት በዋናነት የሚዲያ ተቋማት እና ባለሙያዎች አጠቃላይ መረጃ መያዣን፣ የሚዲያ ሪጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓትን፣ እንዲሁም የሚዲያ ይዘት ክትትል፥ ጥቆማና ቅሬታ መቀበያዎችን፥ የሚዲያ የደረጃ ስርዓትን አቀናጅቶ እንዲይዝ መደረጉ በዘርፉ እየተካሄደ ያለው የሬጉላቶሪ አሰራር ከማንዋል ወጥቶ ወደ ዘመናዊና የተቀናጀ የሚዲያ ሬጉላቶሪ የአስተዳደር ስርዓት እንዲሸጋገር ያደረገ ነው" የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ


28/05/2026

" የተቀናጀ የሚዲያ ሪጉላቶሪ እና አስተዳደር ስርዓት ቴክኖሎጂ የሚዲያ ዘርፉን የሬጉላቶሪ እና ሌሎች ሥራዎች እጅግ ዘመናዊ ወደሆነ እና ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ነው" ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የብሔራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ጄኔራል ዳይሬክተር እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ቦርድ ሰብሳቢ


28/05/2026

የማሳወቅ ግዴታ

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 አንቀፅ 45 ንዑስ አንቀፅ (1)እንደሚያስረዳው የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ እንደአግባብነቱ የሚከተለትን ለውጦች ሲያደርግ ለውጦችን ባደረገ በ14 ቀናት ውስጥ ለኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን በጽሁፍ የማሳወቅ ግዴታ አለበት

ሀ) የሥርጭት አገልግሎቱ ሲጀመር፤
ለ) የሥርጭት አገልግሎቱ ሲቋረጥ፤
ሐ) የመርሀ ግብር ለውጥና የሥርጭት ሰዓት ለውጥ ሲያደርግ፤
መ) የጣቢያው ሥም፣ ምልክትና አድራሻ ላይ ለውጥ ሲያደርግ፤ እና፣
ሠ) የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ ወይም የቦርድ አባል ወይም የፕሮግራም ኃላፊ ላይ ለውጥ ሲያደርግ፡፡


26/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1 ሺ 447 ኛው የኢድ-አል አድሃ (አረፋ) በዓል አደረሳችሁ!!


26/05/2026

የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁጥር 1238/13 አንቀፅ 45 እንደሚያስረዳው የብሮድካስት አገልግሎት ባለፈቃድ የሚከተለትን ለውጦች ከማድረጉ በፊት ለባለሥልጣኑ በጽሁፍ ማሳወቅና ፈቃድ ማግኘት አለበት፡-

ሀ) የጣቢያውንም ሆነ የጣቢያውን የአክስዮን ባለድርሻዎች የአክስዮን ድርሻ መጠን ለመጨመር፣ ለመቀነስ፣ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ፣ ሌላ የመገናኛ ብዙኃን የንግድ ማኅበርን ለመግዛት፣ ለመዋሀድ ወይም መሰል ለውጥ ለማድረግ ወይም
ለ) የውጪ ሀገር ብሮድካስት አገልግሎቶች የሚያሠራጩትን ፕሮግራም ተቀብሎ ለማሠራጨት፡፡


26/05/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት እንደሚከተለው ቀርቧል።

እንኳን ለ1447ኛው የዒድ አል አድሐ በዓል አደረሰን፣ አደረሳችሁ!

ስለዒድ አል-አድሐ "ዐረፋ በዓል ስናስብ ሦስት ነገሮች ቀድመው ይታወሱናል። መስዕዋትነት፣ መታዘዝ እና መተጋገዝ። አባት ልጁን ለመስዕዋት ያቀረበበት፥ ልጅ የአባቱን ትዕዛዝ የፈጸመበት፣ ሙስሊሞች የመተጋገዝን እሴት ለዓለም የገለጡብት በዓል ስለሆነ “ዐረፋ በሕዝበ-ሙስሊሙ ዘንድ ትልቅ ትርጉም አለው።

እስማኤል ለነብዩ ኢብራሂም የመጀመሪያ እና ተወዳጅ ልጃቸው ነው። አላህ (ሱ.ወ.) ይሄን ተወዳጅና የመጀመሪያ ልጅ እንዲሠዉለት ሲጠይቃቸው ታዘዙ እንጂ ወደኋላ አላሉም። ለመታዘዝ የሞከሩት ነገሩ ቀላል ሆኖ አይደለም። ልጅን ያህል ነገር መስዕዋት ማድረግ ምኑ ይቀላል? የአባትነት ስሜት ይተናነቃል። የሰይጣን ሹክሹከታ ይፈታተናል። የቤተዘመድን ወቀሳ እና የጎረቤትን አስተያየት መቋቋምም ይከብዳል። ነብዩ ኢብራሒም፡ በዚህ ሁሉ አጣብቂኝ ውስጥ አንድ ሐቅ ተገልጦላቸዋል። ከራስ ስሜት፣ ከሰው ሐሜት እና ከወዳጅ ፍላጎት የሚልቅ ታላቅ ዓላማ እንዳለ አምነዋል። ስለዚህም በፈተና ውስጥ ጸንተው ቆሙ; ቆራጥነታቸውም በተግባር ታየ።

ሀገር የምትገነባው ከራስ ጥቅም በላይ በሚያስቡ እና ከግላዊ ፍላጎታቸው በላይ ለመፈጸም በቆረጡ ዜጎች ነው። የሚወዱትን ነገር እንኳን ሳይቀር ለመሠዋት ዝግጁ የሆኑ ዜጎች ሲበዙላት ሀገር ትበረታለች። እስማኤላቸውን ለመስጠት የማያመነቱ ዜጎች የሞሉባት ሀገር ጽኑ ናት።

የለመድናቸው፣ የምንወዳቸው፣ የራሳችን ገንዘብ ያደረግናቸው ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ከእነዚህ የሚበልጥ ዓላማ ግን አለ፣ እሱም “ሀገርነት እና ሉአላዊነት” ይሰኛል። ሀገርነት የሚገነባው ከመውሰድ ይልቅ በመስጠት ነው። ሉአላዊነት የሚጸናው በፈተና ሳይወድቁ በመቆም፣ በወጀብ ሳይናወጡ መጓዝ በመቻል ነው።

የእውነት ኢትዮጵያ ሲያልፍላት ማየት የምንሻ ከሆነ ምኞታችን በተግባር ይገለጥ። የሀገር ኩስመና ካሳሰበን ለማዝፈቷ እንድከም። ያጎበጣትን የድህነት ቋጥኝ ለመሸከም ትከሻችንን እናመቻች። ጎተራዋ እንዲሞላ እጃችን አፈር ይንካ። የጠየመ ገጽዋ እንዲፈካ በሥራ ሌት ተቀን እንሰለፍ። የተቀማ ክብሯ እስኪመለስ ድርሻችንን እንወጣ። ሀገር መውደዳችን ከልብ ከሆነ መስዕዋት ለመሆን እናመንታ።

የዐረፋ በዓል የመታዘዝና የመስዕዋት ብቻ ሳይሆን የመደጋገፍና የመተጋገዝ በዓል ጭምር ነው። በዐረፋ ከሚከናወነው እርድ አንድ ሦስተኛው ለምስኪኖች እንዲሰጥ የእስልምና አስተምህሮ ያዛል። በዐረፋ ሕዝበ-ሙስሊሙ ደስታና ሐዘኑን እየተጋራ በዓሉን ያከብራል። የዐረፋ እለት አንድም ሰው ተከፍቶ አያሳልፍም፤ በዐረፋ ሰሞን ማንም ሰው ተርቦና ተጠምቶ አያድርም። በዓሉ ትርጉም የሚሰጠው ሕዝበ-ሙስሊሙ ያለውን ተካፍሎ ሲያከብረው ነው። ሰዎች አስቸጋሪ ሁኔታን የሚሻገሩበት መፍትሄው መተሳሰብና መተጋገዝ እንደሆነ ከዐረፋ እንማራለን። ሀገርም ከፈተናዎችዋ በላይ እንድትሆን እኒህ እሴቶች ወሳኝ ናቸው።

ዐረፋ ማኅበረሰባዊ በዓል የሚባለው ለዚህ ነው። ሰዎች በግላቸው የሚያከብሩት አይደለም። ቤተሰቡ፣ ጎረቤቱ፣ ሠፈሩ፣ ከተማው የሚያከብረው በዓል ነው። ያላቸውና የሌላቸው፤ የሚችሉና የማይችሉ፣ ታላላቆችና ታናናሾች፣ ባለ ሥልጣናትና ተራ ዜጎች፣ በአንድነት የሚያከብሩት በዓል ነው። ሰው የሚኖረው በቤቱ ውስጥ አይደለም። በማኅበረሰቡ ውስጥ ነው።

ማኅበረሰባዊ ትሥሥርና ትብብር ለዜጎች እና ለሀገር ደኅንነት ወሳኝ ናቸው። ማኅበረሰባዊ ትሥሥር ስለሌሎች እንድናስብ፣ ስለሌሎች እንድንሠራ እና ስለ ሌሎች ዋጋ እንድንከፍል ያደርገናል። ራሳችንን በሌሎች ጫማ ላይ አቁመን እንድናይ ያስችለናል። የሁላችንም ሰላም፣ የሁላችንም ደኅንነት እና የሁላችንም ጥቅም ካልተከበረ በቀር የሣላችንን ብቻ ልናስከብር እንደማንችል ያስገነዝበናል። ስለዚህም ማኅበራዊ ግዴታን እንደ ዜግነት ግዴታ ወስደን እንድንሠራ ያደርገናል።

ምርጫ ማኅበራዊና ዜግነታዊ ግዴታዎችን ከምንወጣባቸው የዴሞከራሲ መገንቢያ መሳሪያዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ዴሞክራሲ አይሳካም። ያለ ምርጫም የሕዝብ ተሳትፎ ምሉዕ አይሆንም። የዴሞከራሲያችን መሰረት ጥንካሬው የሚለካው በተሳትፎአችን መጠን ነው።

የዘንድሮ ሀገራዊ ምርጫ ሀገረ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን የሚጠነከርበት መሰረት ነው። የዴሞክራሲ ልምምዳችን አንድ ደረጃ ከፍ የሚልበት፣ የቀጣይ ዓመታት የሀገራችንን እጣ-ፈንታ የምንበይንበት፤ ከምንም በላይ ብዝሃ-ድምጽ የሚሰማበት የሕግ መወሰኛ ምክርቤት የምንመሰርትበት ወሳኝ አጋጣሚ ነው። በመሆኑም በዓሉን ስናከብር ዜግነታዊ ግዴታችንን ለመወጣት ብቻ ሳይሆን በካርዳችን ዴሞክራሲያዊ መብታችንን ለማረጋገጥ እየተዘጋጀን እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ።

በድጋሚ መልካም የዐረፋ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ!

ዒድ ሙባረክ!!

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርከ!


23/05/2026

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከባለሥልጣኑ ቦርድ አመራሮች ጋር በመሆን የኢቢኤስ ቴሌቪዥን የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።


23/05/2026

"የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን አጅግ ዘመናዊ የሚዲያ ኮምፕሌክስ ከመገንባት ባሻገር ብሔራዊ የኢትዮጵያ ጣቢያነቱን የሚመጥን በይዘትም በቴክኖሎጅም በጣም የላቀ እና ብቃት ያለው መሆኑን አይቻለሁ"
የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ኃይማኖት ዘለቀ ከባለሥልጣኑ የቦርድ አመራሮች ጋር ተቋሙን በጎበኙበት ወቅት ከተናገሩት የተወሰደ


Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Addis Ababa
43142