05/06/2026
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር የሚሰጠው የካፍ ኤ ላይሰንስ ስልጠና ሦስተኛ ሞጁል ስልጠና በትላንትናው ዕለት በአዲስ አባባ የካፍ የልህቀት ማዕከል ተጀምሯል።
ስልጠናው ለቀጣይ 10 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናውን በበላይነት በካፍ ኤሊት ኡንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና ሌሎች ተጋባዥ ኢንስትራክተሮች አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
05/06/2026
የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እና ማላዊ አሰልጣኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እና ማላዊ አሰልጣኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.
05/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል።
ቡድናችን ከማላዊ የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ነገ ግንቦት 29 በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውን የጅቡቲ ዳኞች ይመሩታል።
ተጋጣሚያችን የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ የገባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ልምምዳቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ
04/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በድሬዳዋ የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል።
የቡድናችን አባላት በዛሬው ዕለት ወደ ድሬዳዋ ማምራታቸው የሚታወቅ ሲሆን ጥቂት እረፍት ካደረጉ በኋላ ከ11፡40 ጀምሮ ልምምዳቸውን አከናውናዋል። በስብስቡ የሚገኙት 21 ተጫዋቾችም በተሟላ ሁኔታ ልምምዳቸውን አከናውነዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር በስፍራው በመገኘት የብሔራዊ ቡድናችንን ልምምድ ተከታትለዋል።
04/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድሬዳዋ ደርሷል።
የልዑክ ቡድናችን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ሲደርስ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ጀማል ኢብራሂም (ኢ/ር)፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሸነር አቶ ካሊድ መሐመድ፣ የድሬዳዋ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዲሁም የከንቲባ ጽሕፈት ኃላፊ አቶ ከድር አሊዬ በተገኙበት በፖሊስ ማርሽ ባንድ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።
ቡድናችን ማረፍያውን ታቴኖ ሮያል ሆቴል ያደረገ ሲሆን አመሻሽ ላይ በድሬዳዋ የመጀመርያ ልምምዱን ያከናውናል።
03/06/2026
የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች እና ሴቶች ውድድር ከሐምሌ 5 - ነሐሴ 3 በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።
03/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአዲስ አበባ የመጨረሻ ልምምዱን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል።
ቡድናችን በነገው ዕለት 6፡35 ላይ ወደ ድሬዳዋ የሚያመራ ሲሆን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታ ቅዳሜ፣ ሁለተኛው ደግሞ ማክሰኞ ይከናወናል።
02/06/2026
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በ10 ክለቦች መካከል ከሰኔ 7-21 በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ መረጃዎችን ለማግኘት ማህበራዊ ገፆች ይከታተሉ
————————————————
Telegram -
Facebook - facebook.com/ethiopiaYF
X - twitter.com/EthiopiaLYFL
02/06/2026
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ቡሩንዲን በድምር ውጤት 4-2 አሸንፎ ወደ መጨረሻው ዙር ማለፉ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶም አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን መግለጫ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ቡሩንዲን በድምር ውጤ...