23/05/2026
Ethiopian National Theatre
Information about Ethiopian National Theater
23/05/2026
14/05/2026
ታላቁ አርቲስት ፍቃዱ ተ/ማርያም ሀውልት የቆመለት።
ከልብ እናመሠግናለን!!
ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ/ም
የኪነጥበቡ ዓለም ጀግናችን ፍቃዱ ተክለማርያም (1948-2010 ዓ.ም)
የጥበቡ ዘርፍ ታላቁ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም
በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ የተወለደው አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ትምህርቱን ሚያዚያ 27 እና አጼ ናዖድ ትምህርት ቤቶች ተከታትሏል፡፡
በ1967 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቲያትርና ባህል አዳራሽ የመቀጠር ዕድል አጋጠመው:: አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ የመሪ ተዋናይነት ሚና ያገኘው በአባተ መኩሪያው "እሳት ሲነድ" ነበር። ከዛ በኋላም ፍቃዱ ለበርካታ ዓመታት በመድረክ፣ በሬዲዮ፣ በቴሌሺዥን እና በፊልም በርካታ ገፀ ባሕርያትን እየወከለ ተጫውቷል፡፡
የአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም ሥራዎች.......
1. ትረካዎች መካከል ውስጥ ጥቂቱን.......
- ሞገደኛው ነውጤ
- ጥቁር ደም
- ሳቤላ
- ወንጀለኛው ዳኛ
- ግራጫ ቃጭሎች
2. የመድረክ ወጥ እና ትርጉም ተውኔቶች...
- ኦቴሎ
- ኤዲፐስ ንጉሥ
- ሐምሌት
- ቴዎድሮስ
- ንጉሥ አርማህ
- መቃብር ቆፋሪው እና የሬሣ ሳጥን ሻጩ
- የሠርጉ ዋዜማ
- አቡጊዳ ቀይሶ
- ባለካባ ባለዳባ
- መልዕክተ ወዛደር
የቃቄ ውርድወት
3. የቴሌቭዥን ድራማዎች.......
- ባለጉዳይ
- ያልተከፈለ እዳ
- የአበቅየለሽ ኑዛዜ
- ገመና
ፍቃዱ በኋላም በፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥም በርካታ ፊልሞች ላይ ተውኗል።
ከተወነባቸው ፊልሞች መካከል “ቀይ ስህተት” በተባለው ፊልም የተዋጣለት ፊልም ለመሥራት በመብቃቱ መኪናም ለመሸለም በቅቷል።
ፍቃዱ እጅግ ገናና ከሆነበት "ቴዎድሮስ" ቴአትር በተጨማሪ በ"ኤዲፐስ ንጉስ"፣ "ሐምሌት" እና "ንጉስ አርማህ" ተውኔቶች ላይ ንጉሥ ሆኖተጫውቷል።
አርቲስት ፍቃዱ ተክለ ማርያም ባደረበት የኩላሊት ሕመም ሳቢያ ውጪ ሀገር ሄዶ ለመታከም ገንዘብ ቢሰበሰብለትም ከተሠበሰበው ገንዘብ 200 ሺህ ብር ለአንዲት ኩላሊት ታማሚ ወጣት መሥጠቱ የሚታወስ ነው።
ሐምሌ 25ቀን 2010 በኩላሊት ሕመም ምክንያት አርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም በ62 ዓመቱ ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል።
ታላቁ አርቲስት ፍቃዱ ተክለማሪያም የተሳተፈበትን ፤ በጣም የወደዳችሁትንና የማትረሱትን ተውኔት እናንተም አስታውሱን ?
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Addis Ababa
Addis Ababa
