FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት, Government Organization, General Mulugeta Buli Street, Addis Ababa.

Seeing a modern defense force that is absolutely faithful to the constitution, government and people of our nation, center of excellence and love who can put an end to war, and who can safely and effectively succeed at the national and international duty

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 03/06/2026

የሁርሶ ዕጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ታሪክ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

በኢትዮጵያ የዕጩ መኮነንነት ስልጠና ታሪክ የመጀመሪያው ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ1927 ዓ.ም የተመሰረተው ሆለታ ገነት የሚገኘው የያኔው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ጦር ትምህርት ቤት የአሁኑ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው በ1950ዎቹ የተቋቋመው የሀረር ጦር ትምህርት ቤት ነው፡፡ ሶስተኛው የዕጩ መኮንን ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ደግሞ ከረዥም የሥልጠና ታሪክ ውስጥ ጉልህ ሚና ካላቸው ማሰልጠኛ ተቋማት የሁርሶ ጦር ትምህርት ቤት ነው።

ከ1977 - 1983 ዓ.ም. ድረስ በነበሩት ስድስት ዓመታት ብቻ ለእናት ሀገራቸው አንድነትና ሉዓላዊነት መከበር ሲሉ ላባቸውን የጠመቁ፣ ደማቸውን ፣ያፈሰሱና አጥንታቸውን የከሰከሱ ከ22,000 ሽህ በላይ ጀማሪ መኮንኖች በማስመረቅ የጦር ሜዳ ጀግኖች አፍርቷል።

ይህ የማይረሳው፣ ፈፅሞ ፣የማይዘነጋው ስለ ዝነኛው የበረሃው የሥልጠና ማዕከል የሆነው የያኔው የሁርሶ ጦር ትምህርት ቤት የአሁኑ የሁርሶ እጩ መኮንን ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ነው፡፡

የተነሳነው ከድሬዳዋ ከተማ በስተ ምዕራብ 30 ኪሜ. ርቀት ላይ፣ ከባሕር ወለል በላይ 1130 ሜትር ከፍታ ላይ ስለምትገኘው፣ በቀድሞው አጠራር በድሬዳዋ ኢሣና ጉርጉራ አውራጃ፣ በኋላም በድሬዳዋ ራስ ገዝ አሁን ደግሞ በሶማሌ ክልል ሺኒሌ ዞን አስተዳደር ሥር ስላለችው የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት ስለሚታፈስባት ሁርሶ ነው።

የሁርሶ ነዋሪዎች በዋናነት የሰርካማ ወንዝን በመጠቀም በመስኖ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በማልማት የሚተዳደሩ ሲሆኑ ከዚህ በተጨማሪ በአካባቢው የኢሳና የኦሮሞ አርብቶ አደሮች ይገኛሉ። ሁሉም በጋራና በፍቅር ተሳስበው ይኖራሉ፡፡

የ1969 ዓ.ም የዚያድ ባሬ የዕብሪት ወረራ የሶማሊያ ጦር ድሬዳዋ ከተማን በምዕራብ አቅጣጫ ለመክበብ ራሱ አስቀድሞ በአደራጃቸው ምንገደኞቹ በምዕራብ ሶማሌ ነፃ አውጭ ወንበዴዎች እየተመራ 1970 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ሰርጎ ገብ ጦሩን በሁርሶ ደቡብ ምዕራብ በሚገኘው የአሰሊሶና አሊቾ ተራራ ተረተር በኩል አስርጎ በማስገባት ወደ ኤረር ሸለቆ ተሻግሮ እስከ አዋሽ ድረስ በመዝለቅ የባቡር ሐዲዶችና ድልድዮች ላይ ጉዳት አደረሰ፡፡

በ1970 ዓ.ም አብዮታዊ ሠራዊት በመደበኛውና በሚሊሺያ ጦር ተጠናክሮ በጀግናው አየር ኃይላችን እየታገዘ በጠላት ላይ በወሰደው ፈጣን የመልሶ ማጥቃት ዘመቻ፤ በድሬዳዋ ግንባር በጀልዴሣ፣ በሐረዋ፣በሁርሶ፣ በሐወሌ፣ በሺኒሌ፣ በሐመርካ፣ በአልባሕና በአይሻ መሽጎ ይርመሰመስ የነበረውን የሶማሊያ ወራሪ ሠራዊት እያሳደደ በመምታት ዳግም እንዳያንሰራራ አድርጎ አከርካሪውን ሰባብሯል።

ታሪኩ ወደ ሶማሊያ ወሰደን እንጅ ያለነው ሁርሶ ላይ ነው። ዋናው የወገን ኃይል በከፍተኛ ሞራልና ወኔ በማጥቃት ወደፊት ሲገሰግስ ቀሪው ደግሞ የኋላ ወረዳውን በአስተማማኝ ሁኔታ በማስጠበቅ በሁርሶ፣ጀልዴሳና ሺኒሌ ላይ ተጠናክሮ ተቀመጠ፡፡ በዚሁ ጊዜ በተዋጊ ኃይል ለተመናመኑ የወገን ጦር ክፍሎች ማሟያ የሚሆን ጦር ሁርሶ ላይ የማሠልጠን ሀሣብ ተወሰነ፡፡

ሁኔታው ከዚህም በላይ ርቆ በመጓዝ መንግሥት በተለይ የሁርሶ አካባቢ በረሃማ የአየር ፀባይ ለወታደራዊ ሥልጠና (ልምምድ) አመቺ ሆኖ ስላገኘውና በአቅራቢያውም የሰርካማ ወንዝ ያለማቋረጥ ከአመት እስከ አመት ስለሚፈስ የውኃ ችግር እንደማይኖር በመታመኑ፤ ሰላም ከተመለሰ በኋላ የተፈናቀሉትን የሁርሶ ነዋሪዎችን ወደ ሶደሬና ሌላም አካባቢ በማስፈር፤ ሁርሶ የቀደመ ታሪኩ ተለውጦ በርካታ የሠራዊት አባላትን የሚያስተናግድና የሚያሰለጥን ጦር ሠፈርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት ሆነ፡፡
ይቀጥላል.......

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 03/06/2026

ማሥታወቂያ

ደረጃቸውን የጠበቁ የግንባታ ግብዓቶችን የቤትና የቢሮ ፈርኒቸሮችን መግዛት ይፈልጋሉ ?

እንግዲያውስ ወደ መከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት ጎራ ይበሉ፤

✅ ድርጅታችን የቤት እና የቢሮ ፈርኒቸሮች፤ ማለትም ፦

✅ ደረጃቸውን የጠበቁ የምግብ ጠረጴዛ እና ወንበሮች፤

✅ ገራሚ ጥንካሬ ያላቸው ሶፋዎች እና የተለያዬ መጠን ያላቸው ቁም ሳጥኖች፤

✅ ሜትር ከሃያ፣ ሜትር ከሃምሳ እና ሜትር ከሰማንያ አልጋዎች፤

✅ ሌሎች የእንጨት ሥራ ውጤቶችን በጥራት እያመረተ ለደንበኞችና ለተጠቃሚዎች ያደርሳል።

የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት

❇️ ✅ በኮንስትራክሽን ዘርፍም በተለያዩ ደረጃ የአርማታ ውህድ ወይም ኮንክሪት ሚክስ፤

✅ የተለያዩ መጠን እና ደረጃ ያላቸው ክፍት እና ድፍን ቦሎኬቶች እና ፌመንት ታይል፤

✅ የውሃ ፍሳሽ ማሥወገጃ የኮንክሪትና የብረት ቱቦዎች፤

✅ የብረት አልጋዎች እና ወንበሮች

✅ ለህንፃዎች ማጠናቀቂያ አገልግሎት የሚውሉ የእንጨት የብረት እና የአልሙኒየም ምርቶች፤

✅ ለጤና እና ለትምህርት ተቋማት እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎት የሚውሉ የቤተ ሙከራ ቤንቶች፤

✅ የጠጠር ምርቶች እና የመሳሰሉትን በማምረት ላይ እንገኛለን።

ይዘዙን ይምጡና ይጎብኙን በተፈለገው ደረጃ በምናመርተው ምርት እና በአገልግሎታችን ጥራት ይደሰታሉ።

አድራሻችን ፦
❇️♦️ ቃሊቲ መናሃሪያ ወደ 08 በሚወስደው መንገድ ከአቃቂ ቃሊቲ ስታዲየም ጀርባ

❇️♦️ ስልክ ቁጥር፦ +251 114-35-21-48 /49/50/51

❇️♦️ ፋክስ፦ +251 114-34-17-29 /34-28_93/34-68-20

የመከላከያ ግንባታ ግብዓቶች ማምረቻ ድርጅት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 03/06/2026

የሠላም አሥከባሪ ሻለቃ አመራሮች የሕፃናት የመብት አያያዝ በተመለከተ ውይይት አካሄዱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ አመራሮች ስለ ቀጠናው የፀጥታ ሁኔታና የሕፃናት የመብት አያያዝ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያዩ።

‎የዌስተርን ኢካቶርያ ስቴት ምክትል አስተዳዳሪ የዜጎች ሠላም ለማፅናትና የሕፃናት መብት አያያዝ ለመጠበቅ የተከናወነው ስራ በቀጠናው የተሠማራው የኢትዮጵያ
‎ሠላም አስከባሪ ከሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጋር በጋራ በመሆን ላደረገው ስኬታማ እንቅስቃሴ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ተልዕኮውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

‎የደቡብ ሡዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ ሌተናል ጄነራል አሻብ ኩሚስ ባለፈው ዓመት በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት የቀጠናው የሠላም ሁኔታና የሕፃናት መብት አያያዝ እንደገመገሙና መሻሻል እያሣየ መሆኑን ገልፀው ውጤቱ የተገኘው የኢትዮጵያ ሠላም አስከባሪ ሠራዊት ከባለድርሻ አካላትና ከማሕበረሰቡ ተናቦ በመስራቱ እንደሆነ አብራርተዋል።

‎የ21ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አሥከባሪ ሻለቃ አዛዥ ኮሎኔል እንዳለ እሸቱ ቀደም ሲል የሰላም አስከባሪው ለግዳጅ ሲንቀሳቀስ ለማደናቀፍ ይሞክሩ የነበሩ ጥቂት ሀይሎች አሁን ላይ ሠራዊቱ የዜጎችን ሠላም በመጠበቅ ረገድ ያመጣውን አወንታዊ ለውጥ በመገንዘባቸው ለሠላም አሥከባሪው መልካም ትብብር እያደረጉ ይገኛሉ ብለዋል።

‎በውይይቱ የዩናሚስ የበላይ ሀላፊዎች ፣የደቡብ ሡዳን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ፣ የፀጥታ ሀይሎችና የሲቪል ማሕበረሰብ ተወካዮች ተገኝተዋል።

‎ዘጋቢ ፍፁም ተካ
‎ፎቶ ግራፍ ግርማቸው አብረሀ

‎የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ለሠራዊቱ መኖሪያ ቤት.... 03/06/2026

ለሠራዊቱ የመኖሪያ ቤት

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም

ለሠራዊቱ መኖሪያ ቤት.... Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 02/06/2026

ወደ ዕዙ ለተቀላቀሉ መሠረታዊ ወታደሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተጠናቀቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

በመሠረታዊ ወታደሮች ስልጠና ማጠናቀቂያ ዝግጅት ላይ ተገኝተው የሥራ መመሪያ የሠጡት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ዋኘው አለሜ ዕዙ በጀግንነቱ እና በሚፈፅማቸው ግዳጆች የሀገር ባለውለታ መሆኑን አውስተው ፣ ስልጠናው ፕሮፌሸናል ሠራዊት በመገንባት የጠላትን ሴራ በመበጣጠሰ ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥና ጠንካራና ተተኪ መሰረታዊ ወታደሮችን ለማፍራት ያስቻለ መሆኑን ገልፀዋል።

የሠላም እንቅፋት የሆኑ ተላላኪ ባንዳዎች የኢትዮጵያን የልማትና የዕድገት ጉዞ ለማደናቀፍ ቢሞክሩም በጀግናው ሠራዊትና በደጀኑ ህዝብ ጥረት ሴራቸው እየከሸፈ መምጣቱንም አንስተዋል።

ህገ -መንግስታዊ ተልዕኳችን በውጭ ጠላቶችና በሀገር ውስጥ ባንዳዎች ሴራ በምንም መልኩ አይደናቀፍም ያሉት ምክትል አዛዡ የዕዙ ሠራዊት ከአጎራባች ዕዞች ጋር በመናበብ የጠላትን ምኞተ ተስፋ እያጨለመ ሠላምና ልማትን እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።

ከጀግኖች አባቶቻችን የተረከብናትን ሀገር ሰላሟን፣ አንድነቷና ሉዓላዊነቷን አስጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ የማስተላለፍ ታላቅ ሀገራዊ አደራ ተቀብለን ግዳጃችንን በአኩሪ ሁኔታ እየተወጣን እንገኛለን ሲሉም መልዕክት አሥተላልፈዋል።

ተመራቂዎችም ከፍተኛ የማሸነፍ ሰነ ልቦና በመታጠቅ በታማኝነትና በቆራጥነት ከጀግኖቹ ነባር የሠራዊት አባላት ተሞክሮ በመውሰድ በጋራ የሚሰጣቸውን ግዳጅ በላቀ ሁኔታ እንዲወጡም አሳስበዋል።

ዘጋቢ ይሁን አሻግሬ
ፎቶግራፍ እያሱ ጃርሶ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 02/06/2026

ክፍለጦሩ የሀገር አፍራሾችን ሴራ እያከሸፈ እንደሚገኝ ተገለፀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ምስራቅ ዕዝ ስር የሚገኝ አንድ ክፍለጦር የተሰጠውን ግዳጅ በሚገባ በመፈፀም የሀገር አፍራሽ ቡድኖችን ሴራ እያከሸፈ እንደሚገኝ ተገለፀ።

የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል ጠጁ ሙላት ሬጅመንቶች በተሰማሩበት ቀጠና በመንቀሳቀስ በወቅታዊ የግዳጅ አፈፃፀም እና በወታደራዊ ዝግጁነት ጉዳዮች ላይ ከሠራዊት አባላቱ ጋር ተወያይተዋል።

የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የሚያሰማሯቸው የውስጥ ፅንፈኛ ተላላኪዎች የህዝቡን እሴት ንደው ሀገር የማፍረስ ግባቸውን ለማሳካት ያላሰለሰ ጥረት ማድረጋቸውን የጠቀሱት አዛዡ የክፍለጦሩ የሠራዊት አባላት በታላቅ ሀገራዊ ፍቅር እና ጀግንነት ግዳጃቸውን በመፈፀም የባንዳዎችን ሴራ ማኮላሸት መቻላቸውን ገልፀዋል።

አዛዡ በውይይቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ያረጋገጣችሁት ወታደራዊ ዝግጁነት እና የተገነባችሁበት የጀግንነት እሴት ጠላቶቻችሁ ከሩቅ የሚፈሯችሁ የማትጨበጡ የእሳት ነበልባል እንድትሆኑ አስችሏችኋል ሲሉ የሠራዊት አባላቱን ፅናት አድንቀዋል።

ሰራዊታችን በተሰማራበት የግዳጅ ቀጠና ግዳጁን ከመወጣት ባሻገር ከራስ በፊት ለህዝብና ለሀገር ቁልፍ እሴቱ መሰረት ማህበረሰቡን እየረዳና እያገዘ መሆኑን አውሰተዋል። የክፍለጦሩ የድል ሰራዊትነት እና ለማንኛውም ጠላት የማይበገር መሆኑን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ዘገባው የሄኖክ አባይነህ ነው ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 02/06/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ ሰጡ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሰላምን መንገድ የመረጡ የፅንፈኛው ታጣቂዎች በወረዳው ለሚገኘው የኮማንዶ ሻለቃ ከነ ሙሉ ትጥቃቸው እጅ መሰጠታቸውን የሻለቃው አዛዥ ሻምበል ወንድምነህ በስፋት ገልፀዋል።

እጅ የሰጡ አባላትም እየሄዱበት ያለው መንገድ የተሳሳተ ህዝብን የሚጎዳ ለጥቂት አመራር ነን ባዮች ሀብት መሰብሰቢያ ዕድል የፈጠረ ከምንም በላይ የአካባቢውን ብሎም የሀገርን ሠላም የሚጎዳ መሆኑን ተናግረዋል። ዘገባው የአየር ወለድ ክፍለ ጦር የሠራዊት ስነ ልቦና ግንባታ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

02/06/2026

የህዝብ ዋይፋይ እና የደህንነት ስጋቶች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

የህዝብ ዋይፋይ ምንድን ነው?
የህዝብ ዋይፋይ (Public Wi-Fi) በካፌዎች፣ ሆቴሎች፣ አየር መንገዶች፣ ቤተ-መጻህፍት ባሉ የጋራ የህዝብ መገልገያ ቦታዎች የሚገኝ የገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት ነው።

ይህ አገልግሎት ለተጠቃሚዎች አንዳንድ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ የህዝብ ዋይ ፋይ የደህንነት መጠበቂያ (Encryption) እጥረት ስላለባቸው ለሳይበር ጥቃቶች እጅግ የተጋለጡ ናቸው።

አጥቂዎች በዚህ አውታረ መረብ ውስጥ ተጠቃሚው የሚያስተላልፈውን እንደ የይለፍ ቃል፣ የተጠቃሚ ስም እና የግል መልዕክቶች የመሳሰሉትን ሚስጥራዊ መረጃዎች በቀላሉ በመጥለፍ ሊሰርቁት ይችላሉ። ይህ ጥቃት በወታደራዊ ተቋማት ሊሰነዘር የሚችል ሲሆን በቅድሚያ አጥቂዎች የግል መሳሪያዎችን የድምጽ መቅረጫዎች እና ካሜራዎችን በርቀት በመቆጣጠር ለስለላ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

በሁለተኛ ደረጃ በህዝብ ዋይፋይ የተጠለፈ መሳሪያ ወደ ወታደራዊ ውስጣዊ ኔትወርክ (Intranet) ሲገናኝ እንደ "ትሮጃን ፈረስ" ሆኖ አደገኛ ቫይረሶችን ወደ ሰርቨሮችና ሲስተሞች ያስገባል።

በሶስተኛ ደረጃ የሰራተኞች የጂኦ-ስፓሻል (GPS) መረጃ በመስረቅ የወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን ወይም የተቋማትን አቀማመጥ ለጠላት አሳልፎ የመስጠት አደጋ ይፈጠራል።

የጥቃት ስልቶች
ሳይበር ወንጀለኞች በህዝብ ዋይፋይ ላይ ጥቃት ለማድረስ በዋናነት የሚጠቀሙባቸው ዘዴዎች በተጠቃሚው መሳሪያ እና በዋይፋይ ራውተሩ መካከል በመቀመጥ የሚተላለፉ ሚስጥራዊ መረጃዎችን የሚሰርቁበት፣ ህጋዊ የሚመስል የውሸት የዋይፋይ መስመር በመክፈት ተጠቃሚዎችን የሚያታልሉበት፣ እንዲሁም ልዩ ሶፍትዌሮችን በመጠቀም በኔትወርኩ ላይ የሚተላለፉ የውሂብ ጥቅሎችን መጥለፍ የሚያስችላቸው መንገዶች ናቸው። እነዚህ አጥቂዎች መረጃው ሳይመሰጠር ሲተላለፍ በቀላሉ መቆጣጠር፣ መቅዳት ወይም መለወጥ ይችላሉ።

የመከላከያ ስልቶች እና የጥንቃቄ እርምጃዎች
በህዝብ ዋይፋይ መጠቀም የግድ አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ደህንነትን ለመጠበቅ የኢንተርኔት ትራፊክን በቪፒኤን (VPN) ምስጢራዊ ማድረግ፣ የሚያስሷቸውን (የሚጎበኙትን) ድረገጾች "https://" መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ የፋይል መጋራት (File Sharing) እና የራስ-ሰር ግንኙነትን (Auto-Connect) ማጥፋት እንዲሁም ባለ ሁለት ደረጃ ማረጋገጫ (2FA) መጠቀም እንደ ባንክ አካውንት ያሉ ሚስጥራዊ መረጃዎችን አለመክፈት ይገባናል።

በፀጥታና ደህንነት፣ በሌሎች ቁልፍ ቦታዎች የተሰማሩ ሰዎች የህዝብ ዋይፋይን ከመጠቀም ይልቅ ደህንነቱ የተጠበቀ የሞባይል ዳታ ቢጠቀሙ ይመከራል፣ ከዚህ በተጨማሪ የስርዓት ክወናዎችና የፀረ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን በየጊዜው በማዘመን የመከላከያ እርምጃዎችን መውሰድም ይገባል።
የመከላከያ ሳይበር ማዕከል

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወታደራዊ ማርች ባንድ 02/06/2026

ወታደራዊ የማርች ባንድ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ወታደራዊ ማርች ባንድ Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

Photos from FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት's post 01/06/2026

የዕዙ ደረጃ 3 ሆስፒታል የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የዊልቸር ድጋፍ አደረጉ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል የሠራዊት አባላትና ሲቪል ሠራተኞች የአካል ጤና መጓደል ለገጠማት ህፃን 359 ሺ ብር የሚያዋጣ ዘመናዊ ዊልቸር ገዝተው ድጋፍ አድርገዋል።

የሆስፒታሉ የሠራዊት አባላትና ሲቭል ሰራተኞች እንዲሁም ከሁሉም ዕዞች፣ ከአየር ሃይል፣ ከባህር ሃይል፣ ከልዩ ዘመቻዎች ተውጣጥተው በሆስፒታሉ የነርስ ትምህርት እየተከታተሉ ያሉ የ9ኛ ዙር አባይ ኮርስ የነርስ ተማሪዎች 359 ሺህ 275 ብር በማዋጣት በኤሌክትሪክ የሚሰራ ትራክ ዊልቸር ገዝተዉ አስረክበዋል።

ህፃን አርሴማ ጌታሁን የ8 ዓመት ከ8 ወር እድሜ ያላት ስትሆን ስትወለድ ጀምሮ ባጋጠማት የአካል ጤና መጓደል ምክንያት ሁልጊዜ በቤተሰቦቿ ታቅፋና ታዝላ የምትንቀሳቀስ ሲሆን አሁን ላይ ዕድሜዋ እና ክብደቷ እየጨመረ በመምጣቱ ከጓደኞቿኗ ከአቻዎቿ ጋር እኩል ማህበራዊ ግንኙነቷን ለማስቀጠል የተደረገላት ድጋፍ ወሳኝ መሆኑ ተነግሯል።

የህፃኗ ቤተሰቦችም የሆስፒታሉ የሠራዊት አባላትና ሲቭል ሠራተኞች ላደረጉላቸዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

ህፃን አርሴማ ቋሚ የዳይፐር ተጠቃሚ ስለሆነች የምስራቅ ዕዝ ደረጃ 3 ሆስፒታል ማኔጅመንት እንዲሁም ከፍተኛ መኮንኑ ተወያይቶ ባሳለፈዉ ዉሳኔ መሠረት ልጅቷን በዘላቂነት የዳይፐር ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጿል። ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


General Mulugeta Buli Street
Addis Ababa