Addis Ababa Electric Service Administration Authority

Directions Website

Addis Ababa Electric Service Administration Authority This is Official Page of Addis Ababa Electric Service Administration Authority/
ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ይፋዊ ገፅ ነው

ባለሥልጣኑ የ2019 ኢሬቻ በዓል ያለምንም የመንገድ መብራት መቆራረጥ እንዲከበር  የሚያስችል ተግባራትን እያከናወነ ነው።የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የፊታችን ቅዳሜ...
28/09/2026

ባለሥልጣኑ የ2019 ኢሬቻ በዓል ያለምንም የመንገድ መብራት መቆራረጥ እንዲከበር የሚያስችል ተግባራትን እያከናወነ ነው።

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የፊታችን ቅዳሜ መስከረም 23/ 2019 ዓ.ም የሚከበረውን ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ያለምንም የመንገድ መብራት መቆራረጥ እንዲከበር የሚያስችል ተግባራትን እያከናወነ ነው።

የእዚሁ ተግባር አካል የሆነው የከፍተኛ ዋት ተሸካሚ የመብራት ተከላ በባለስልጣኑ አማካኝነት በኢሬቻ ፓርክ ተከናውኗል።

የባለሥልጣኑ የግንባታና ኮንትራት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙሉጌታ ወዳጆ በኢሬቻ ፓርክ የተተከለው መብራት 360 ዲግሪ (ዙሪያውን) ረዥም ርቀት ብርሃን መስጠት የሚችል መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም በዓሉን ለሚያከብረው ተሳታፊ ደህንነት ተጨማሪ ምቾት የሚፈጥርና ያለምንም ስጋት በዓሉን እንዲከውኑ የሚያስችል መሆኑንም አውስተዋል።

በበዓሉ ማክበሪያ፣ በኮሪደር ልማት ስፍራዎችና በወንዝ ዳርቻ አካባቢዎች ቀደም ብለው የተተከሉ ዘመናዊ መብራቶች ፍተሻና ቅየራ በባለስልጣኑ እየተደረገ ይገኛል።

የዘንድሮዉ የመስቀል ደመራ በዓል በርካታ ህዝብና ቱሪስቶች በተገኙበት እጅግ ባማረ እና በደመቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ ተከብሯል !በዓሉ በደምቀት እሴቱን ጠብቆ  እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀ...
27/09/2026

የዘንድሮዉ የመስቀል ደመራ በዓል በርካታ ህዝብና ቱሪስቶች በተገኙበት እጅግ ባማረ እና በደመቀ መልኩ በመስቀል አደባባይ ተከብሯል !

በዓሉ በደምቀት እሴቱን ጠብቆ እና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ አካላት ሁሉ ምስጋና ይገባችሁል።

መልካም በዓል !

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስ...
26/09/2026

እንኳን ለደመራና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን!

የከተማችን ድምቀት ከሆኑ የአደባባይ በዓላት አንዱ ለሆነውና በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና ባህል ድርጅት ዩኔስኮ በማይዳሰስ ቅርስነት ለተመዘገበው ለመስቀል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳቸሁ!!

በዓሉ ሃይማኖታዊ እሴቱን ጠብቆ በባህላዊ አልባሳቶቻችን ደምቆ፣ የቱሪዝም ስበት ሆኖ የሀገራችንን መልካም ገጽታ በሚያጎላ መልክ ይከበራል።
እንደ ወትሮዉ ሁሉ በአሉን ስናከብር እንደ ዳመራዉ በአብሮነት ተደምረን ፣በትብብር ፣በመተሳሰብ እና በፍቅር እንድናከብር መልካም ምኞቴን አገልጻለሁ።

በድጋሚ እንኳን ለደመራ እና መሰቀል በዓል በሰላም አደረሳቸሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ !
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ባለሥልጣኑ የህብረተሰቡን ከቤት ውጭ ያሉ የመብራት ጥያቄዎች እየፈታ ነው።የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የረዥም ጊዜ የህብረተሰብ ጥያቄ የነበረውን አራት ኪሎ ግንፍሌ ...
26/09/2026

ባለሥልጣኑ የህብረተሰቡን ከቤት ውጭ ያሉ የመብራት ጥያቄዎች እየፈታ ነው።

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የረዥም ጊዜ የህብረተሰብ ጥያቄ የነበረውን አራት ኪሎ ግንፍሌ የትራንስፖርት ተርሚናል የመብራት መሠረተ ልማት በመዘርጋት የመብራት ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል።

በባለሥልጣኑ የግንባታና ኮንትራት አስተዳደር ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሙሉጌታ ወዳጆ ግንፍሌ የትራንስፖርት ተርሚናል ጨለማ በመሆኑ የትራንስፖርት ተጠቃሚ የከተማዋ ማህበረሰብ በምሽት ለተለያዩ ችግሮች የሚዳረጉበትና ተደጋጋሚ የመብራት ጥያቄ የሚያቀርብበት እንደነበር አስታወሰዋል።

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በጥናት በመለየት ከመሰረቱ ጀምሮ የመብራት መሰረተልማት ግንባታ በከተማዋ እያከናወነ ሲሆን ግንፍሌ ተርሚናል የዚሁ አካል መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙ የህብረተሰቡን ጥያቄ በመለየት እየፈታ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ተቋሙ በ2019 በጀት አመት በጥናት የለያቸው የህብረተሰቡ የመብራት መሰረተ ልማት ጥያቄዎችን እየፈታ እንደሚሄድ ተናግረዋል።

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል።...
26/09/2026

ለመስቀል በዓል እንኳን አደረሳችሁ

የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊና ባህላዊ በሆነ መንገድ በመላው ኢትዮጵያ የሚከበር በዓል ነው። በዓሉ ቤተሰባዊ እና ማኅበራዊ ቀለም አለው። ቤተሰብ ይገናኝበታል። ሠፈሩ ይሰባሰብበታል። ከተማውና አካባቢው ወደ አንድ አደባባይ ይተምበታል። ከእንጨት እስከ ደመራ ያለው መሰባሰብም የመደመርን ኃይል የሚያሳይ ተምሳሌት ነው።

በዓሉን በምናከብርበት ጊዜ ሁሉ የኢትዮጵያን ዐቅሞች እያሰባሰብንና እየደመርን ታላቅ ሀገራዊ ዐቅም ለመፍጠር እንትጋ።
በድጋሚ መልካም በዓል ይሁን።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው  ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!!!ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ው...
24/09/2026

ሁሉም ቀና ቢያስብ፣ ሰው ለሰው ቢፋቀር፣ ሁሉም ቢተባበር የት እንደርስ ነበር!!!

ለዓመታት ነዋሪዎቻችን የጎርፍ እና የእሳት አደጋ ደጋግሞ እየጎበኛቸው በከፍተኛ ሰቀቀን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ ነበር።

ዛሬ ግን የዜጎቻችንን ክብር ወደ ጠበቀ ውብ የመኖሪያ ቤትና ስፍራ ተሸጋግረው በደስታ ሲኖሩ ማየት ወደር የሌለው ደስታ ይሰጣል።
ግን ዋናው ጥያቄ በሀገራችን ዋና ከተማ ውስጥ እንዴት ብዙ ዜጎቻችን እንደዛ አይነት አስቸጋሪ አኗኗር ውስጥ ለዓመታት ኖሩ? ዛሬስ ሁሉም በዚህ ፍጥነት እየተለወጠ ያለው እንዴት ነው? የሚለው ነው፡፡

መልሱ ፡- ይህን ስራ እውን ያደረግነው ብዙ አካላትን በማስተባበርና በመደመር ነው። ከያለበት ያለውን እውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ሳንሰስት ደምረናል። የተወሰኑት በፋይናንስ ሲደግፉን፣ ሌሎቹ ደግሞ በእውቀታቸው፣ በጉልበታቸው፣ በዲዛይን እና በግንባታ ስራው ላይ በንቃት በበጎ ፍቃድ ተሳትፈዋል። ነዋሪዎቻችንም ለተሻለ ልማት የለውጥን ተስፋ ሰንቀው ትልቅ ትብብር አድርገዋል።
ይህ ሁሉ ጥረት አንድ ላይ ተደምሮ ትልቅ አቅም በመሆን ይህን የመሰለ የመኖሪያ መንደር እና አካባቢን ፈጠረ። ቅጠል ተራም ታሪኩ ተቀየረ።

ውድ ወገኖቼ፤ አንድ ላይ ተደምሮ ይህንን አዲስ ሰፈር የፈጠረው መሬት፣ ሰዉም፣ ገንዘቡም፣ እውቀቱም የእኛው ነው። ትርጉሙ አንድ ቦታ ላይ ንፁህ የመኖሪያ ስፍራ ከማግኘት እጅግ የላቀ ነው። ይልቁንም ለጋራ ራእይ እየተባበርን፣ በቅንነት፣ በትጋት እና እውነተኛ አገልጋይነት አብረን ስንሰራ ብዙ ሀብቶቻችን ተደምረው የሁላችንንም የጋራ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጡ፣ የዜግነትን ክብር የሚያልቁ ፣ አዳዲስ እድል እና ሀብት ይፈጥራሉ።

ስለዚህ በማንኛውም ነገር በጋራ እንቁም፤ ትብብራችንንም ይበልጥ እናጠናክር። ለበለጠ ሀገራዊ ስኬት በመተማመን አብረን እንትጋ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን፣ በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላ...
24/09/2026

ከፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌ እና ከአሊኮ ዳንጎቴ ጋር በመሆን፣ በጅቡቲ ዳመርጆግን ከኢትዮጵያ ደወሌ የሚያገናኝ እና ታላቅ ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት የሆነውን አዲስ የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታን ዛሬ ይፋ አድርገናል።
‎
‎ ፕሮጀክቱ በሁለቱም ጫፎች ላይ በሚገነቡ የማከማቻ ተርሚናሎች የተደገፈ ሲሆን፤ ይህ ታሪካዊ መሰረተ ልማት በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በዳንጎቴ ግሩፕ ጥምረት የሚተገበር ነው።
‎
‎የሎጂስቲክስ ወጭንና መዘግየትን በመቀነስ፣ የኢነርጂ ዋስትናን ያጠናክራል፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የንግድ መስመርን ፍጥነት እና ዘላቂነትን ያሳድጋል።
‎
‎መሰረተልማቱ ከነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ በላይ፣ የአፍሪካውያንን ኢንቨስትመንት እና በጋራ መልማትን ማዕከል ያደረገ፣ ለዘላቂ እድገት፣ ለቀጣናዊ ትስስር እና ይበልጥ አስተማማኝ ለሆነ የጋራ ኢኮኖሚያዊ እጣ ፈንታ የሚደረግ ሰፊ ኢንቨስትመንት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ 24 ግራር ሰፈራ እና ገርጂ 5 ኮንዶሚኒየም የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የውስጥ ለውስጥ መብራት በመዘርጋቱ መደሰታቸውን ገለጹ።የአዲስ አበባ ከተማ  ...
23/09/2026

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በተለምዶ 24 ግራር ሰፈራ እና ገርጂ 5 ኮንዶሚኒየም የሚኖሩ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው የውስጥ ለውስጥ መብራት በመዘርጋቱ መደሰታቸውን ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የምስራቅ ሪጅን ባከናወነው የውስጥ ለውስጥ የመብራት ሥራ የአካባቢው የምሽት እንቅስቃሴ መሻሻሉን ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ በፊት በምሽት አካባቢው ጨለማ በመሆኑ እንቅስቃሴያቸው የተገደበ እንደነበር ጠቅሰው አሁን መብራት በመዘርጋቱ በምሽት በተሻለ ሁኔታ መንቀሳቀስ እንደቻሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም የተከናወነው የመብራት ሥራ ለአካባቢው ደህንነትና ለከተማዋ ውበት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የባለስልጣኑ ምስራቅ ሪጅን በበኩሉ የመብራት መሠረተ ልማትን ከማስፋፋትና ከመጠገን ባለፈ ህብረተሰቡ መሠረተ ልማቱን እንዲጠብቅ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ጎተራ ማሳለጫና በተለያዩ አከባቢዎች የነበረውን የመብራት ችግር   በአካል በመገኘት አይተው በትኩረት አፅኖት ሰተው ችግሩን በመፍታት ላ...
20/09/2026

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ጎተራ ማሳለጫና በተለያዩ አከባቢዎች የነበረውን የመብራት ችግር በአካል በመገኘት አይተው በትኩረት አፅኖት ሰተው ችግሩን በመፍታት ላይ ይገኛል።
በ11ም ክ/ከተማ የጥገና ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰብስብ ሁሴን አስታወቁ ።

ባለስልጣኑ ባለፉት ሦስት ወራት ከ6 ሺህ በላይ ያረጁ የሶዲየም አምፖሎችን ወደ ኃይል ቆጣቢና ዘመናዊ (ኤልኢዲ/LED) አምፖሎች የመቀየር ስራ መከናወኑን ገለፀ።የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት ...
17/09/2026

ባለስልጣኑ ባለፉት ሦስት ወራት ከ6 ሺህ በላይ ያረጁ የሶዲየም አምፖሎችን ወደ ኃይል ቆጣቢና ዘመናዊ (ኤልኢዲ/LED) አምፖሎች የመቀየር ስራ መከናወኑን ገለፀ።

የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን (ዶ/ር)
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተቋቁሞ ወደ ሥራ ከመግባቱ እና የኮሪዶር ልማቱ በከተማዋ መከናወን ከመጀመሩ በፊት በከተማዋ የመንገድ ዳር መብራት ሽፋን አነስተኛ እንደነበር አስታውሰዋል።

በዚህም ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የከተማዋ የዋና ዋና እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች በጨለማ የተዋጠ እንደነበር ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ይህም የሆነው የመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማቱን በባለቤትነት የሚያስተዳድረው አካል በውል ባለመታወቁ ሀይ ባይ አጥቶ በመዘረፉ መሆኑን ገልጸዋል።

እንዲሁም የተበላሹና አደጋ የደረሰባቸው መሠረተ ልማቶችንም በወቅቱ ተጠግነው ወደ አገልግሎት አለመግባታቸው ለሽፋኑ ዝቅተኝነት ምክንያት መሆናቸውን አስረድተዋል።

ተቋሙ የከተማዋን የመንገድ ዳር መብራት መሠረተ ልማት እንዲያስተዳድር በአዋጅ ሥልጣንና ኃላፊነት ተሰጥቶት ሲቋቋም አዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣን ሲያስተዳድራቸው ከነበሩት 29 ሺህ የዋና መንገድ ዳር መብራት ምሰሶዎች ውስጥ ከ12 ሺህ 500 በላይ የሚሆኑት አይሠሩም ነበር።

ከዚህ ውስጥ በ2018 በጀት ዓመት ባለሥልጣኑ 14 ሺህ የሚጠጉ የዋና መንገድ መብራቶችን የድግግሞሽ ጥገና ጭምር በማከናወን ሁሉንም የመንገድ ዳር ምሰሶዎች (29 ሺህ) ወደ አገልግሎት ማስገባቱን ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቀደም ሲል በከተማዋ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይመሩ ከነበሩ 35 ሺህ የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ዳር አምፖሎች ውስጥ ብርሃን የሚሰጡት አምስት ሺህ (16 በመቶ ) ገደማ የሚሆኑት ብቻ እንደነበሩ አመልክተዋል።

እነዚህን የውስጥ ለውስጥ አምፖሎች ባለሥልጣኑ ተረክቦ ማስተዳደር በጀመረ ባለፉት ሦስት ወራቶች ውስጥ ብቻ ከስድስት ሺህ በላይ ያረጁ የሶዲየም አምፖሎችን ወደ ኃይል ቆጣቢና ዘመናዊ (ኤልኢዲ/LED) አምፖሎች በመቀየር ወደ ሥራ አስገብቷል።

ቀሪዎቹን የማይሠሩ አምፖሎች ደግሞ ወደ ኃይል ቆጣቢና ዘመናዊ አምፖሎች በመቀየር በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ በጀት ተመድቦ በትጋት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለጻ፤ የማይሠሩ ነባር መሠረተ ልማቶችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ከማስገባት እና በተለይ በኮሪዶር ልማቱ ስማርት የመንገድ ዳር መብራቶችን በመትከል ቁጥሩን ከመጨመርና ከማዘመን ባሻገር ደግሞ በከተማዋ ያሉ 41 ሺህ 160ዎቹንም የመንገድ መብራት ምሰሶዎችን ወደ ጂአይኤስ (GIS) ሥርዓት በማስገባት ሁሉንም በአንድ ማዕከል መቆጣጠር የሚያስችል በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋት ተችሏል።

በዚህም አሁን ላይ 24 ሰዓት የትኛው ምሰሶ ላይ ምን አይነት ችግር እንደደረሰ አንድ ማዕከል ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለሚፈጠረው ችግር አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል የአሠራር ሥርዓት መዘርጋቱን አብራርተዋል።

Address

Piyassa
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Electric Service Administration Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share