18/05/2026
የስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ የመዋቅሮችን የ10 ወር የተግባር አፈፃፀም እየገመገመ ነዉ
ድጋፍና ክትትሉ መዋቅሮች አቅደዉ ባከናወኗቸዉ በርካታ ተግባራት የሚታዩ ጥንካሬዎችን ለማላቅና ጉድለቶችን ለማረም ታቅዶ የተዘረጋ ሲሆን
ከዚህ በተጨማሪም መጪዉ የአረፋ በአልን ምክንያት በማድረግ የሚደረጉ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪዎችንና ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ለማረም ነዉ።
08/05/2026
የኑሮ ውድነት ለማረጋጋት አቅርቦትን ከአምራቾች በቀጥታ የገበያ ትስስር መፍጠር ዋነኛው መፍትሔ ነው።የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት
30/2018-ወራቤ
ለወራቤ ከተማ አስተዳደር ሸማቾች የሚሆን የሽንኩርት እና የድንች ምርት ከአርሶአደሮች:ሌሎች አምራቾችና ጅምላ አከፋፋዮች በቀጥታ ለቅዳሜ ገበያ
ትስስር መፍጠር ተችሏል።
በመሆኑም የከተማችን ሸማቾች ለነገው ቅዳሜ ገበያ ከሁልበረግ ወረደ ከቢላወንጃ ቀበሌ የአርሶአደሮች ምርት ቀርቧል ::
የመኪና ድገፍ የወራቤ ከተማ አስተዳደር መዘገጃ ቤት በመሸፈን ምርቱ ወራቤ ቅዳሜ ገበያ የደረሰ በመሆኑ በፍላጎታቹ ልክ በተመጣጠኝ ዋጋ መሸመት የምትችሉ መሆኑን እናበስራለን።
የምርት ጥራቱን የንግድና ገበያ ባለሙያዎች በአካል በማሳው ተገኝተው ተረጋግጧል።
👉የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤትን ከልብ እናመሠግናለን።
#የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት-ወራቤ
29/04/2026
ወቅታዊዉ አለምአቀፋዊዉ ሁኔታ ያልበገረዉ የምርት አቅርቦት!!
በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ ረግዲና ማዞርያ ላይ የሚገኘዉ የማክሰኞ ሰንበት ገበያ አሁን ላይ የሚታየዉ የትራንስፖርት አቅርቦት መስተጓገል ሳይበግረዉ ልክ እንደወትሮዉ ጥራትና ብዛት ያላቸዉን የሰንበት ገበያ ምርቶች በቀጥታ ከማሳ ወደገበያ በማቅረብ ሸማቹን በማስጠቀም ላይ ይገኛል።
እንደ ዞን የሰንበት ገበያዎች የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይገጥማቸዉ እጥረት የሚቲይበትን ነዳጅ ቅድሚያ ሰጥቶ በማመቻቸት በአምራችና በሸማች ማህበራት አማካኝነት ተከታታይ ምርት እንዲያቀርቡ በማስቻል የዋጋ ንረቱን ትርጉም ባለዉ መንገድ ለመከላከል እየተሰራ ነዉ።
17/04/2026
ህገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ የንግድ ስሮዓቱንና ማህበረሰቡን በሚያውኩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሁልባረግ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ!
ሚያዝያ 08/2018 ሁልባራግ ኮሙኒኬሽን -ኬራቴ
በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ ቤት ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ በነዳጅ እና በሌሎች ሸቀጦች ከልክ ያለፈና የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች እርምጃ እየወሰደ መሆኑን አስታውቋል።
የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ዋበላ ሹኩሬ ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋ መጨመርን ምክንያት በማድረግ በሌሎች እቃዎች ላይ የሚደረገው የዋጋ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሸማቹን ማህበረሰብ ኑሮ የሚፈታተንና የሚያናጋ መሆኑን ጠቅሰው ድርጊቱን ለማስቆምና ህገወጦችን ለማጋለጥ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥብቅ ክትትል ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።
ወቅታዊ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪውን መነሻ በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እንዳይኖር የተጠናከረ የክትትልና ቁጥጥር ስራ መጀመሩን የገለጹት ኃላፊው በየደረጃው ያለው የንግዱ ማህበረሰብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል።
ያልተገባ ጥቅም ለማግኘትና በአቋራጭ ለመበልፀግ በማሰብ ህገወጥ የዋጋ ጭማሪ በደረጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ ዋበለ ሹኩሬ ህገወጦችን በማጋለጥ ረገድ የማህበረሰቡ ሚና የጎላ በመሆኑ ጥቆማው በቀጣይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
በወረዳው ውስጥ በየትኛውም አካባቢ በህገወጥ መልኩ የሚነግዱና ከተሰማሩበት የንግድ ስራ ውጭ በሆነ ዘርፍ ተሰማርተው ቀጣይ ዋጋ ሊጨምር ይችላል በሚል ሰበብ ምርት የሚያከማቹ፣ የመሸጫ የንግድ ማዕከላትን የሚዘጉ እና ተገቢ ያልሆነ ዋጋ በመጨመር የሚሸጡ እንዲሁም የዕቃ መሸጫ የዋጋ ዝርዝር በግልጽ ቦታ የማይለጥፉ ፣ የድጅታል ሚዘን የማይጠቃሙ ፣ የወፍጮ ቤት ግራም ቅነሳ ፣የእህል መሸጫ ፣የዳቦ ግራም የመቀነስ ፣ወቅቱ ያለፈበት የፈብሪካ ዕቃ የሚሸጡ ነጋዴዎች የንግድ ህጉን እየጣሱ መሆኑን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የሁልባረግ ወረዳ ን/ገ/ል/ፅ/ቤት ነው
06/04/2026
ምክንያት ያሌላቸው የምርት የሽያጭ ዋጋ ጭማሪዎች ተቀባይነት የላቸውም!!
በአለም ኃያላኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በአለም የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለት ና የንግድ እንቅስቃሴ ላይ በተፈጠረው መስተጓገል ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ ተጠባቂ የዋጋ ንረቶች ቢኖሩም እርሱን እንደ ሽፋን በመጠቀም ትርፍ ለማጋበስ የሚሰሩ ስግብግብ ነጋዴዎች መኖራቸውን የሚገመግም መድረክና በቀጣይ በሚወሰደው የመፍትሔ እርምጃ ዙሪያ መዋቅሮች በግብረሐይል ደረጃ ውይይት እያደረጉ ሲሆን
በዚህም መድረኩ ተፈጥሮ ነባራዊ ሁኔታ ተገምግሞ አቅጣጫ ከተቀመጠባቸው መዋቅሮች ውስጥ ወራቤ ከተማ፣ቅበትና አልቾ ውሪሮ ወረዳዎች ይገኙበታል።
ግብረሐይሎቹ ወትሮውኑ በመደበኛ የዋጋ ንረት እየተፈተነ ያለው ዝቅተኛ ገቢ ያለው የማህበረሰብ ክፍል ሰው ሰራሽ ጭማሪዎች በላዩ ላይ ሲጫኑበት የመኖር ህልውናው አደጋ ውስጥ እንደሚገባ በማሰብ ጠንካራ ክትትልና ቁጥጥር ከህግ ማስከበር ጋር በማጀብ የሰፊውን ሸማች ጥቅም ለማስከበር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እንደሚሰራ በማረጋገጥ የቀጣይ ስምሪቶችን ሰጥተዋል።
02/04/2026
ከስር በምስሉ የሚታየው ማደያ አይደለም
ይልቅኑ በዞኑ አልቾ ውሪሮ ወረዳ በትስስር መልኩ ከቅበት ኦላ ማደያ የመጣውን ቤንዚን በወጣለት ታሪፍ መሰረት ለባለሁለት ና ሶስት እግር አሽከርካሪዎች አየቤንዚን አገልግሎት ሲሰጥ የሚያሳይ ምስል ነው።
መሰል ውጤታማ የትስስር ተግባራት በሌሎች መዋቅሮችም በተጠናከረ መንገድ እየተሰራበት ሲሆን ትስስሩን በተሟላ መንገድ ተግባራዊ በማያደርጉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ያስገድዳል
በዚህም ዞኑ ማደያ ያለባቸውን መዋቅሮች ማደያ ከሌላቸው መዋቅሮች ጋር በማስተሳሰር የሚታየውን የነዳጅ አቅርቦት ችግር ለመቀነስና በፍትሐዊነት ለማዳረስ የሚሰራው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ።
31/03/2026
በኢራን_እስራኤል ጦርነት ምክንያት የነዳጅ አቅርቦት መስተጓገልን እንደሽፍን በመጠቀም የተጋነነ ዋጋ ባቀረቡ ድርጅቶች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።
በዚህም በቀን 22/7/2018 በአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ዩኒት አማካኝነት በተደረገው የወጭ እንስፔክሽን 55 ንግድ ድርጅቶችን እንስፔክት በማድረግ በተለያዩ ምርቶች ላይ ዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 9 ንግድ ድርጅቶችን የማሸግና አስተዳደራዊ እርምጃ የመውሰድ ስራ ተሰርተዋል።
የዞኑ ንግድና ገበያ ልማት መምሪያም በቀጣይ መሰል ጠንካራ ክትትልና ህግ የማስከበር ስራዎችን በመስራት ምክንያት የሌላቸውን የዋጋ ጭማሪዎችን ለማስቀረት እንደሚሰራ ገልፀዋል።
17/03/2026
የከተማው የህገወጥ ንግድ መከላከል ግብረ-ኃይል የጋራ የውይይት መድረክ አካሄደ!
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
መጋቢት 8፣ 2018 [ወራቤ ኮሙኒኬሽን] የወራቤ ከተማ አስተዳደር የህገወጥ ንግድ መከላከል ግብረ-ኃይል በዛሬው ዕለት ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል።
የነዳጅ አጠቃቀም በተመለከተ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተቀመጠው የአሰራር ስርዓት መሠረት ብቻ ተግባራዊ እንዲደረግ የጋራ አቋም የተያዘ ሲሆን በሌላ በኩል በከተማ አስተዳደሩ የሚደረግ ማንኛውም ህገወጥ የንግድ እንቅስቃሴ ላይ የተቀናጀ እና ፈጣን እርምጃ እንዲወሰድ የጋራ አቅጣጫ ተቀምጧል።
ህገ ወጥ የነዳጅ እንቅስቃሴ ለመግታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር አስፈላጊ መሆኑም ተነስቷል።
ነዳጅ በሚዲያዎች ታሪፍ ጨምረው በሚሸጡ ባለቤቶችና ሰራተኞች ህጋዊ እና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ በቁጥጥር እና በክትትል ስርዓት በማጠናከር የሚባክን የነዳጅ ሀብትን በመቀነስ አላስፈላጊ የሚፈፀሙ ድርጊቶችን ማስቆም እንደሚገባ ተጠቁሟል።
የነዳጅ ግብይት ላይ የሚደረገው ግብይት ስርዓት ቁጥጥር እና ክትትል የሚያደርግ የንግድ ባለሙያዎች ከአንድ ፖሊስ በጋራ በመሆን ማታ 12:30 ተለክቶ በማሸግ በማሸግ በነጋታው ጠዋት 12:30 በጋራ ተለክቶ እንዲከፈት በተቀመጠው አሰራር መሰረት በጥብቅ እንዲተገበር ውይይት የተደረገ በመሆኑ ይህንን ተላልፎ የተገኘ ማንኛውም አካል አዋጅ1363/2017 መሰረት እርምጃ መውሰድና ከትስስር ማስወጣት።
በመጨረሻም በከተማ አስተዳደሩ ግብረሃይል በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 1500ሊትር ነዳጅ በህገወጥ መንገድ ሲሸጥ የተገኘ በመሆኑ ተወርሶ መሠረታዊ ለሆኑ ለመንግሥት አገልግሎቶች እንዲውል ተወስኗል።
17/03/2026
መንግስት በተወሰኑ ቀናት ልዩነት ውስጥ “የነዳጅ ቆጥቡ” ጥሪን ለሦስተኛ ጊዜ አቀረበ፤ አጭር ጉዞዎችንም “በእግርና ብስክሌት አድርጉ” ሲል መክሯል
ማክሰኞ፣ መጋቢት 08 ቀን 2018 ዓ.ም ( )
የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በዓለም አቀፍ ደረጃ እየታየ ነው ያለውን የነዳጅ ገበያ መዋዠቅ ለመቋቋም፣ የሀገሪቱን የትራንስፖርት ዘርፍ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይልና ወደ ተፈጥሮ ጋዝ ለማሸጋገር የሚያስችል የነዳጅ ቁጠባ ሀገራዊ ጥሪ አቀረበ።
ሚኒስቴሩ ዛሬ ይህን የነዳጅ ቆጥቡ ማሳሰቢያውን ከማስተላለፉ በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ በተመሳሳይ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) “ሀገርን ከውጭ ጥገኝነት ለማላቀቅና የራስን የተፈጥሮ ጸጋ ለመጠቀም ከዓመታት በፊት ቀርጸውታል” ያለው ስትራቴጂያዊ ውሳኔ፤ “በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምስራቅ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት ሊመጣ የሚችለውን የኢኮኖሚ አደጋ ለመከላከል ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተረጋግጧል” ብሏል።
“መንግስት በስንዴ ልማት ያስመዘገበውን ታሪካዊ ስኬት በነዳጅ ዘርፍም ለመድገም በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን” ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የቴክኖሎጂ ሽግግርን በተመለከተ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መጠቀምን እንደ ሀገራዊ ባህል ማሳደግ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን፣ በነዳጅና በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖች ነዳጅን ትተው የኤሌክትሪክ ኃይልን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።
በተጨማሪም እስከ 20 ቶን የሚሸከሙ የጭነት ተሽከርካሪዎች ወደ ኤሌክትሪክ፣ ከዛ በላይ የሆኑት ደግሞ ወደ ተፈጥሮ ጋዝ እንዲቀየሩ ከመንግስትና ከግል ዘርፉ ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ አክሎም፣ በፌዴራልና በክልል ደረጃ የሚገኙ ሁሉም የመንግስትና የፕሮጀክት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ እንዲቀየሩ በማድረግ የተጀመረው እቅድ ወደ ተሟላ ትግበራ እንደሚሸጋገር አስታውቋል።
የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች በተለይም ባቡሮችና አውቶብሶች ተገቢውን ታሪፍና መርሃ-ግብር ጠብቀው ያለ መቆራረጥ አገልግሎት እንዲሰጡ ጥብቅ ክትትል እንደሚደረግም በመግለጫው ተመልክቷል።
በሌላ በኩል፣ ዜጎች ከአንድ ቤት ውስጥ ብዙ መኪኖችን ይዞ ከመውጣት ይልቅ በጋራ የመጠቀም ልምድን እንዲያዳብሩና አጭር ጉዞዎችን በእግርና በብስክሌት በማድረግ “አረንጓዴ ጉዞን” እንዲያዘወትሩ ሚኒስቴሩ ጥሪ አቅርቧል። አሽከርካሪዎች ነዳጅንና የካርቦን ልቀትን የሚቀንስ የ“Eco-driving” የማሽከርከር ስልጠና እንዲወስዱና ተሽከርካሪዎቻቸውን በኦሪጅናል መለዋወጫዎች በመጠገን የነዳጅ ብክነትን እንዲከላከሉ ይመከራል።
የጥራት ቁጥጥርን በተመለከተ፣ ሁሉም ተሽከርካሪዎች በኢትዮጵያ ስታንዳርድ የጸደቁ የነዳጅና የጭስ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙና የጭስ ልኬት መመሪያን 100 በመቶ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል።
ይህ ሀገራዊ ጥሪ የሀገርን የውጭ ምንዛሬ ለማዳንና ዜጎች በዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ መዋዠቅ እንዳይጎዱ ለማድረግ የታለመ በመሆኑ፣ ሁሉም አካላት በኃላፊነት ስሜት እንዲንቀሳቀሱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አሳስቧል።
ተጨማሪ ዜናዎችንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የማሕበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ይጎብኙ፦
16/03/2026
በዞኑ ምዕራብ አዘርነት በርበሬ ወረዳ በህገ ወጥ ንግድ በተሰማሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን የምዕ/አ/በ/ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት አስታወቀ።
በህገ ወጥ ንግድ እና ድብልቅ ንግድ /ዘርፍ ቀላቅለው/ በሚሰሩ ነጋዴዎች እንዲሁም በህገ ወጥ የነዳጅ ችርቻሮ ንግድ ላይ በተሰማሩ ነጋዴዎች የተለያዩ እርምጃዎች ተወስዷል ።
ከዚህ ጎን ለጎንም የ መደበኛ የሚዛን ምርመራ የተደረገ ሲሆን የንግዱ ማህበረሰብ የሚዛን ቅሸባ እንዳያደርግ ክትትል ማድረግ የተባለሸው እንዲውረስ በማድረግ የዲጂታልሚዛን የሌላቸውን ሙሉ በሙሉ የዲጂታል ሚዛን እንዲጠቀሙ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል።
የንግድ ህጎችን የማስከበር ስራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ግብረሐይሉ አሳስበዋል።