01/11/2018
በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል ያለው የዘርፉ የስራ ግንኙነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ
አዲስ አበባ፡ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም
በከተማ ልማት ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የከተማ ልማት ዘርፍ እንዲሁም የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ስራዎች አፈጻጸምን ውጤታማ ከማድረግ አኳያ ግልጽ የሆነ የግንኙነት አግባብ የሚፈጥር የጋራ ውይይት መድረክ ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ተካሂዷል፡፡
የውይቱ ዓላማም በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን የዘርፉን የዕድግትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በማናበብ ወጥና ተናባቢ የመረጃ ልውውጥ የአሰራር ስርዓት ላይ መግባባት ላይ ለመድረስ እና የጋራ እቅድ በማዘጋጀትና ሚናን በመለየት በመደጋገፍና አመርቂ ውጤት በማስመዝገብ የዜጎችን እርካታ ለማሳደግ እንዲሁም የጋራ ተግባቦት ለመፍጠር የሚሉት ዋናዋና ዓላማዎች ናቸው፡፡
በጌታቸው ኃይሉ
26/09/2018
ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !
የፌደራል ከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር
25/09/2018
አዲስ አበባ፡ መስከረም 14 ቀን 2011 ዓ.ም
ክቡር ሚኒስትሩ በዋና ዋና ስራዎች እንዲሁም የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ አድርገዋል
በቆይታቸውም በ2010 በጀት ዓመት በዘርፋችን በነበሩ ዋና ዋና ስራዎች ማለትም፡
የስራ ዕድል ፈጠራና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ሥራዎች
የከተማ ፕላን ዝግጅትና አፈጻጸም ሥራዎች
መሬት ልማትና ማኔጅመንት ሥራዎች
የቤቶች ልማትና አስተዳደር ሥራዎች
የከተማ ካርታ ማምረት፣ ቅየሳና የመሬት አጠቃቀም መብት ምዝገባ ሥራዎች
የከተሞች የአረንጓዴ ልማትና የፅዳት ማሻሻያ ሥራዎች
የተቀናጀ የከተሞች መሠረተ ልማት አቅርቦት ሥራዎች ወዘተ…በነበሩ ዋናዋና ክንውኖች፣አፈጻጸም እና ተግዳሮቶች እንዲሁም በ2011 በጀት ዓመት የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ከፋና ብሮድ ካስቲንግ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡
19/09/2018
የህጋዊ ካዳስተር መረጃ መኖር ጠቀሜታው
1/ የይዞታ ባለቤትነትን ከማረጋገጥ እና መብትን፣ ክልከላን እና ኃላፊነትን ግልጽ በማድረግ ክርክሮች ቢነሱ እንኳን በአጭር ጊዜ እልባት እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤
2/ የይዞታ ባለመብትነት አስተማማኝ በማድረግ መሬትን ለማልማት ትልቅ እምነት በመፍጠር የመሬት ማልማት ተነሳሽነትን ይጨምራል፤
3/ በመሬትና የመሬት ነክ ንብረት ልውውጥ ሂደት ውስጥ መረጃን የማጣራት ረጅም ሂደትን በማሳጠር፣ ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ እና በጣም አስተማማኝ ያደርገዋል፤
4/ ለመሬትና ቋሚ ንብረት ታክስ ሥርዓት መነሻነት ከተሞች ለልማት ‘ወጪን በገቢ መደገፍን’ እንዲተገብሩ የሚያስችል ግብአት ይሰጣል፤
5/ አካባቢ ጥበቃ ላይ የሚደርሱትን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቆጣጠር ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤
ማንኛውም የሥርዓት ግንባታ መነሻው የሕግ ማዕቀፍ፣ ስታንዳርድ እና እንዲመጣ የሚፈለገው የአገልግሎት አይነት ጥናት ከመሆኑ አንፃር የሚገነባው ፍላጎት ጥናቱ ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
በመሆኑም የሕግ ማዕቀፉ ሀገራዊ ተፈጥሮ እና አተገባበር ይዞ፤ ይህን ማስተግበሪያ አቅም እንዲኖረው በማድረግ በዘመናዊ የመረጃ ስርዓት መደገፉ አስፈላጊ ነው፡
የመሬት ይዞታ ምዝገባ ዓላማዎች
ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲችሉ በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖ በማስቻል አንድ የኢኮኖሚ ማህበረሰብ የመገንባቱን ሂደት ማገዝ፤
ይዞታ መብትን በምዝገባ በማረጋገጥ፣ የባለይዞታውን የመሬት ይዞታ ተጠቃሚነት ዋስትና እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነት መብትን እውቅና በመስጠት የከተሞችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማሕበራዊ እና አካባቢያዊ ልማትን ማፋጠን፤
ከተሞች ያላቸውን መሬት ቆጥረው ማወቅ እንዲች በማድረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተናባቢ የሆነ የመሬት ይዞታ መረጃ እንዲኖር ማድረግ፤
መረጃው የፌደራል መሬትና መሬት ነክ፣ንብረት ምዝገባ ኤጀነሲ ነው
13/09/2018
ለሁሉም የሚዲያ ተቋማት
ጉዳዩ፦ የሚዲያ ሽፉንን ይመለከታል ፣
የከተሞች ተቋማዊና የመሰረተ ልማት ማስፉፊያ ፕሮጀክት (ULGDP 1 እና 2) አፈፃፀምና የሶስተኛው ዙር መርሃ ግብር (UIIDP) በቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስመልክቶ ለሚዲያ አካላት ለማሳወቅ ጋዜጣዊ መግለጫ ስለሚሰጥ መስከረም 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 8 ስዓት ላይ ብሄራዊ አካባቢ በሚገኘው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ 8ኛ ፎቅ በመገኘት የተለመደውን የዜና ሽፉን እንድትሰጡልን እንጠይቃለን ።
10/09/2018
ለመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች በሙሉ
===================================================++++++++
እንኳን ለ2011 አዲሱ አመት አደረሳችሁ
የፌደራል ከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ የመደመርና የአንድነት ዘመን እንዲሆንልን መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
ዓላማችን ከተሞቻችንን የልማት፣ የሰላምና የመልካም አስተዳደር ማዕከላት ማድረግ ነው !!
06/09/2018
በከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ (UIIDP) ፕሮግራም ለሚሳተፉ 117 ከተሞች ስለፕሮግራሙ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ
አዲስ አበባ፡- ነሃሴ 30 ቀን 2010 ዓ.ም
ሦስተኛው ዙር የከተሞች ተቋማዊና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮግራም መርሃ ግብርን በማስመልከት ከዚህ በፊት በፕሮግራሙ ከታቀፉት 44 ከተሞች በተጨማሪ በአዲስ ለሚቀላቀሉት 73 ከተሞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከነሀሴ 29ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት በአዳማ ከተማ ተሰጠ፡፡
ስልጠናው የሚያተኩረውም ወደ መርህ ግብሩ ለመግባት የሚያስችሉ 8ቱ የመመዘኛ መስፈርቶች/ነጥቦች/ ላይ ሲሆን በተለይ ደግሞ አዳዲስ የተቀላቀሉ ከተሞች ከመጋቢት ወር ጀምሮ ሲሰጣቸው የነበረውን ቴክኒካልና በስራ ላይ ስልጠና ውጤታማ ለማድረግና በቀጣይ ጥቅምት 2011 ዓ.ም ለሚደረገው የከተሞች አመታዊ ግምገማ አፈጻጸም ግብዓት እንዲሆን ታስቦ ነው፡፡ በስልጠናውም የክልል ከተማ ልማት ቢሮ ምክትል ሃላፊዎች፣የከተማ ስራ አስኪያጆች እና ድጋፍ የሚሰጡ ባለሞያዎች ተሳትፈዋል፡፡
05/09/2018
በከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ 16ኛው ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልሎች የአፈፃፀምና ግምገማ መድረክ ተካሄደ
==========================================================
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር በከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ የ 2010 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀምና ግምገማ መድረክ ነሀሴ 24/2010 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ደኤታ ወ/ሮ ሂሩት ቢራሳ እንደገለፁት፡- ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ልዩ ድጋፍ የሚሹ ክልል ህዝቦችን የልማትና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ፤ ብሎም በከተሞች ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የሚያስችል የማስፈፀም አቅምን ለመገንባት ዘርፈ ብዙ የሆኑ ድጋፎችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ የ2010 በጀት ዓመት አፈፃፀም በከተማ ልማትና መሬት ማኔጅመንት፤ በከተሞች መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ፤ በመኖሪያ ቤቶች ልማትና አስተዳደር፤ በከተማ ፕላንና ዝግጅት ትግበራና ክትትል፤ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ እና በከተሞች መሰረተ ልማት ማሻሻያ አሃድ ስራዎችን በተመለከተ የአፈጻጻም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጨረሻም ልዩ ድጋፍ ለሚሹ ክልሎች የሚደረገው ድጋፍ በክልሎቹ የሚፈለገውን ያህል ለውጥ እንዲያስገኝ የድጋፍ ስራው ከዕቅድ ባለፈ በተጠናከረ መልኩ መተግበር ይኖርበታል የሚል ሀሳብ ከመድረክ የተንፀባረቀ ሲሆን ሚኒስቴር ደኤታዋ በበኩላቸው በቀጣይ የድጋፍ ስራዎችን በእቅድ፤ የተያዙ ግቦችን፤ በሙሉ አቅም በመተግበርና የስራዎችን አፈፃፀም በጋራ በመገምገም፤ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ለጋራ ስኬት መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የበላይ አመራሩ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ወሳኝነት አለው ብለዋል፡፡
05/09/2018
በ16 ኛው የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ ላይ ተሳታፊ የነበሩ አካላት የችግኝ ተከላ ፕሮግራም በአዳማ ከተማ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ሲያከናውኑ
05/09/2018
የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር 16 ኛውን የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ አካሄደ
==========================================================
በከተማ ልማት ዘርፍ በ 2010በጀት ዓመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለመገምገምና በግማሽ ዓመቱ የተከናወኑና ያልተከናወኑ ተግባራትን ለመለየትና የወደፊት አቅጣጫ ለማስቀመጥ የሁሉም ክልሎች አመራርና ባለሙያዎች እንዲሁም ዘርፉ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር 16ኛውን የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ መደበኛ ጉባኤ ከነሃሴ 25 ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት በአዳማ ከተማ አካሂዷል፡፡
በጉባኤው ላይ የተገኙት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት ከተሞች ብዙ ህዝብ በአንድ ቦታ ላይ ተጠጋግቶ የሚኖርባቸው፤ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው፤ ከገጠር ይልቅ ለኑሮ የሚመረጡ በመሆናቸው በእቅድ ካልተገነቡና በፕላን ካልተመሩ የማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ብሎም ፖለቲካዊ ቀውስ ማዕከላት ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡
ሃገራችን በያዘችው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን የዕቅድ ዘመን ዘርፈ ብዙ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደምትገኝ የጠቅሱት ሚኒስትሩ ከተጠናቀቀው በጀት ዓመት ጀምሮ የከተሞችን ልማት የሚያፋጥኑ ስትራቴጅዎችና ህግ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ እየተደረጉ ሲሆን ከተማ ፕላን ዝግጅትና ትግበራን ሳይሸራረፍ ወጥነት ባለው መልኩ መፈፀም እንዲቻል 18 የህግ ማዕቀፎች ማንዋሎችና ጥናቶች ስራ ላይ እንዲውሉ መደረጉን ተናግረዋል ፡፡
በከተሞች የመኖሪያ ቤት እጥረትንለመፍታትና ህዝቡን የቤት ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ፤ ነገር ግን የዜጎችን የቤት ፍላጎት በሚፈለገው መጠን ለማርካት በእድገቱ ልክ አቅምን የሚጠይቅ በመሆኑ ውስንነት ይታይበታል ያሉት ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠልና በክልል ከተሞችም በከተማ ቤት ፖሊሲና ስትራቴጅ ማዕቀፍ የተለያዩ የቤት አማራጮች ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
05/09/2018
“በከተሞች የሚታዬውን የመሬት ወረራ ለመቆጣጠር የካዳስተር ስርዓቱን በቁርጠኝነት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል” አቶ ጃንጥራር አባይ-የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር
16ኛው የከተማ ልማትና ቤቶች ሴክተር ጉባኤ በአዳማ ከተማ ተካሂዷል
የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ሴክተር ጉባኤ በአዳማ ከተማ በተካሄደበት ወቅት የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ለተሳታፊዎች እንደገለፁት፣ በከተማ መሬት አስተዳደር ላይ እየታየ ያለውን ብልሹ አሰራር ለመቅረፍ የህጋዊ ካዳስተር ስርዓቱን በሙሉ አቅም ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡ የከተማ መሬት አስተዳደር ስርዓቱን የዘመነ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋ ለማድረግ የህጋዊ ካዳስተር ስራ ቁልፍ ስራችን ይሆናልብለዋል፡፡
መንግስት የከተማ መሬት አስተዳደር ስርዓቱን የዘመነ ለማድረግ የህጋዊ ካዳስተር ስርዓትን በሀገር ደረጃ ወጥና ተናባቢ በሆነ መልኩ በከፍተኛና መካከለኛ ከተሞች ለመተግበር ይችል ዘንድ በሁለተኛው ዕደገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን በእቅድ አካቶ መያዙ የሚታወቅ ነው፡፡ሆኖም የበላይ አመራሩ ለስራው የሰጠው ትኩረት አናሳ በመሆኑ ስራው የሚፈልገው ግብዓት በወቅቱ ባለመሟላቱ የዜጎች የይዞታ ዋስትና የማረጋገጥ ስራዎች በሚፈለገው ደረጃ እየተከናወኑ እንዳልሆነ በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡
በመሆኑም በሚቀጥሉት አመታት የህጋዊ ካዳስተር ስርዓቱን በከተሞች ተግባራዊ በማድረግ በመሬት ዘርፍ የሚታዩ ብልሹ አሰራሮችን ለማስዎገድ ከመቸው ጊዜ በላይ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
በ2010 በጀት አመት በሀገራችን በ14 ከተሞች 107,208 /አንድ መቶ ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ስምንት/ ይዞታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ ሥራ የተከናወነ ሲሆን በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በ6 ከተሞች (ባህር ዳር፣ ጎንደር፣ ደብረ ማርቆስ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ እና ደብረ ብርሃን) 2,783 ይዞታዎች፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ/ ክልል በሚገኙ 6 ከተሞች (ወላይታ ሶዶ፣ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና፣ ዲላ ፣ አርባ ምንጭ፣ ሐዋሳ እና ሳውላ) 9,343 ዞታዎች፣ በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ ብቻ 840 ይዞታዎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 94,242 ይዞታዎች ላይ የይዞታ ማረጋገጥ ስራዎች ተከናውነዋል፡፡
በሌላ በኩል በሰባት ከተሞች ለ69,758 ዜጎች የይዞታ ዋስትና ምዝገባ የተካሄደ ሲሆን በደቡብ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት በሚገኙ 5 ከተሞች (በሃዋሳ፣ ዲላ፣ አርባምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ እና ሆሳዕና) 3,754 የመሬት ይዞታዎች ፣ በአማራ ክልል 1 ከተማ (ደ/ማርቆስ) 20 የመሬት ይዞታዎች፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር (በማነዋል- 26,299 እና በሲስተም 39,685 የመሬት ይዞታዎች) በድምሩ 65,984 ይዞታዎች የይዞታ ዋስትና ምዝገባ ተካሂዷል፡፡
የይዞታ ማረጋገጥና የምዝገባ ስራዎቻችን ከታቀደው አንፃር ሲታዩ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው ሲሆን ለዚህም በምክንያትነት የሚጠቀሱት ስራውን አቅሎ በማየት በቅድመ ዝግጀት ሥራ ላይ አጥርቶ ባለመስራት የገጠሙ ፈተናዎች መበራከት፤ የምዝገባ ተቋም በማቋቋም ወደ ስራ ያለመግባት፣ በከተማ የምዝገባ ተቋሙ በሰው ሃይልና በግብአት ያለመሟላት እና ከመብት ሰጪው ተቋም የይዞታ ሰነዶች ተደራጅተው እንዲቀርብ ማድረግ ባለመቻሉ እና በዋናነት ግን የአመራሩ ተረጋግቶ አለመቀመጥና የፖለቲካ አመራሩ ለዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ትኩረት አለመስጠት ናቸው፡፡ ለአብነትም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ወደ ተግባር ያለመግባት፣ በሐረሪብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ተቋሙ በተደራጀ አግባብ ያለማቋቋም፣ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር በቂ የሆነ የሰው ኃይል እና የግብአት አቅርቦት ያለመሟላት፣ ኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከአዳማ ከተማ ውጪ ቀሪዎቹ ወደ ስራ ያለመግባት ይጠቀሳሉ፡፡
16ኛውን የከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ ሴክተር ጉባኤን የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ ቢሮ ሀላፊዎች፣ የኤጀንሲ ሀላፊዎች፣ የዘርፉ ባለሙያዎችና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመውታል፡፡
05/09/2018
ሚኒስቴር መስሪያቤቱ የከተሞች ተቋማዊና መሠረተ ልማት የማስፋፊያ ፕሮግራም(UIIDP) የማስጀመሪያ ወርክሾፕ በአዲሰ አበባ አካሄደ
አዲስ አባበ፦ ነሃሴ 28 ቀን 2010 ዓ.ም አዲሱ ፕሮግራም በዓለም ባንክና በፈረንሳይ መንግስት የታገዘ ሲሆን 860 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ተመድቦለታል ።
የወርክሾፑ ዓላማ የከተሞችን መሠረተ ልማት በሚገባ ለመገንባት ግንባር ቀደም ተዋናይ ለሆኑት አመራሮች ግንዛቤ ለማስጨበጥ መሆኑን የከተማ ልማት እና ቤቶች ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።
በአዲሱ የUIIDP ፕሮግራም ቀደም ሲል የULGDP ፕሮጀክት ተጠቃሚ የነበሩ 44 ከተሞች ቀጥተኛ ተጠቃሚ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ከተሞች ደግሞ በመመዘኛ እየተፈተሹ በጀት የሚለቀቅላቸው ይሆናል። በሃገሪቱ የሚከናወነው የመሠረተ ልማት ግንባታ የከተማና የገጠር ዕድገትን ተመጋጋቢ እና ተደጋጋፊ በማደረግ አንዱ እድገት ሌላውን የሚጫነው እና የሚጠልፈው መሆን እንደሌለበትና የከተሞችና የገጠሩ ትስስር ጤናማ መሆን እንዳለበት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ምኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን ገልጸዋል።
አዲሱ ፕሮጀከት ለአምስት አመታት የሚቆይ እና 117 ከተሞችን በማቀፍ ወደ 7 ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ።