29/05/2026
This is our current statement translated into English for the international community who cannot read Amharic.
This is an official page of Ethiopian Social-Democratic Party.
ይህ የፌስቡክ ገ?
29/05/2026
This is our current statement translated into English for the international community who cannot read Amharic.
25/05/2026
ቀደም ሲል በተያዘው ውጥን መሠረት ኢሶዴፓ ከ7ኛው አገር አቀፍ ምርጫ ውጭ ተደርጓል።
ዝርዝር ሁኔታውን እና የወደፊት አቅጣጫን በተመለከተ ፓርቲው በቀጣይ ሰፋ ያለ መግለጫ የሚሰጥ መሆኑን ይገልጻል።
እስከዚያ ሁላችንም የምርጫ ቅስቀሳ አቁመን፣ በተረጋጋና ጠንካራ መንፈስ ከሕዝባችን ጋር እየመከርን፣ ለእውነትና ፍትሕ ድሞፅ እንደሆንን እንቀጥላለን።
መላው የኢሶዴፓ አባላት እና ደጋፊዎች፣ ሕገ-መንግሥታዊ የመመረጥና የመምረጥ መብት ልትተገብሩ እጅግ በርካታ ማነቆችን እና የማያስችሉ ሁኔታዎችን እያለፋችሁ፣ ጽኑ በሆነ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌትነታችሁ ዛሬ ላይ ለደረሳችሁ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እጅግ የከበረ አድናቆትና ምስጋና አለን።
ፓርቲያችን ኢሶዴፓ የሰላማዊ ትግል ተምሳሌት የሆነ አንጋፋ የሕዝብ ፓርቲ እንደመሆኑ ለዚህ ለ7ኛው አገራዊ ምርጫ በነበረው ካምፔይን ሁሉ ያሳየው አፈጻጸም:- ካለፈው ተሞክሮ ትምህርት የተወሰደበት፣ ከምን ጊዜም በላይ በተሻለ ሁኔታ ሕዝባዊነቱንና ሰላማዊነቱን ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ለዓለም ሁሉ ያስተዋወቀበት አጋጣሚ ነው። ዛሬ ላይ ሕዝባችን አማራጩንና የመምረጥና የመመረጥ መብቱን እየተቀማ ያለ ቢመስልም ፅናቱና ተስፋው እጅግ አስደማሚ ሆኗል። ይህም የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲከ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) እንደፓርቲ፣ ሕዝባችንም እንደጉዳዩ ባለቤት ሕገ-መንግሥታዊ፣ ሰብዓዊ እና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣ የዓለም አቀፉ ስምምነቶች ስለሚከበሩበት ሂደት የበኩላችንን ለመወጣት የመፍትሔው የመጀመሪያው ደረጃ ላይ እንድንቆም አስችሎናል።
በፌዴራል ሰበር ችሎት ያለው የፍትሕ ጥያቄ አቤቱታችን ዛሬም እንደተለመደው ሁሉ ለነገ 8:00 ሰዓት ተቀጥሯል። ሆኖም ግን ቢዘገይም ፍትሐዊ ውሣኔ ይሰጣል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ኢሶዴፓ እንደሀገራዊ አንጋፋ የፖለቲካ ፓርቲ በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች፣ ለአገሪቱ ሰላምና የሕዝቧ ደህንነት የበኩልን ድርሻ እንዳይወጣ ሥርዓቱ ስልታዊ በሆነ መንገድ/ሲስተማቲካሊ ፓርቲውን ከምርጫው ውጭ ያደርጋል ብለን ለማሰብ እንቸገራለን።
ስለሆነም በቅርቡ ሁሉን አቀፍ መግለጫ የምንሰጥ ሲሆን የማንነታችን መገለጫ የሆነውን ሰላማዊ ትግላችሁን እንድትቀጥሉ በአክብሮት እንጠይቃለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝባችንን ይባርክ!!!
05/05/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርዱ ከአዋጁና ከመተዳደሪያ ደንባችን ውጭ በዚህ ልክ በውስጥ ጉዳያችን ገብቶ በነአጫሞ ቦቄ አቅራቢነት (ቦርዱ ከነአጫሞ ጋር በትብብር) ያዘጋጁአቸውን ዕጩዎችን አቅርበው፣ ዝርዝርዠሩ ላይ ፓርቲው አስተያየት እንዲሰጥበት መላኩ "የሕግ ጥሰቱንና የጣልቃ ገብነቱን ልክ" በጥቂቱም ቢሆን ለሕዝባችን፣ ለመንግሥት እና ለሚዲያው በግልጽ ሊነገር ይገባል። ስለሆነም ከተላኩልን ሠነዶች ውስጥ ጥቂት ማሳያዎችን ብቻ አያይዘናል።
እንደምታዩት:- ጥያቄው ከነአጫሞ ይሁን እንጂ ሌላ መስፈርት አያስፈልግም የሚል በሚመስል መልኩ፣ ቦርዱ የፓርቲውን ሕጋዊ ወረቀት (headed paper) ፣ ማህተምም ሆነ የሕጋዊ ተወካይን ፊርማ አይጠይቅም።
እንደኢሶዴፓ:- መላው ሕዝባችን ለፍትሐዊ፣ ነፃና ተዓማኒ የዴሞክራሲ ተቋማት ግንባታ በቁርጠኛነት መታገልና የየበኩላችን የማዋጣት ቁርጠኛነት የግድ እንደሆነ በፅኑ ያምናል።
16/04/2026
TikTok · ተስፋሁን ኢሶዴፓ ሐረር 119 likes, 5 comments. “ ”
06/04/2026
TikTok · ተስፋሁን ኢሶዴፓ - ሐረር 1057 likes, 32 comments. “ ”
29/03/2026
TikTok · ተስፋሁን ኢሶዴፓ - ሐረር 42 likes, 3 comments. “ ”
| Monday | 08:30 - 17:00 |
| Tuesday | 08:30 - 17:00 |
| Wednesday | 08:30 - 17:00 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:00 |