01/06/2026
በምሽት ተሰልፈው ለሚገኙ መራጮች ወ/ሮ መሪማ ታደሰ በነፃ ምግብና ውኃ እያቀረቡ ነው
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 ነዋሪ የሆኑት ወ/ሮ መሪማ ታደሰ፤ የምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ማራዘሙን ተከትሎ በምሽት ተሰልፈው ድምፃቸውን ለመስጠት እየተጠባበቁ ላሉ ነዋሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት ምግብና ውኃ በነፃ እያቀረቡ ነው፡፡
ወ/ሮ መሪማ መራጩ ሕዝብ ሳይሰለችና ሳይደክም የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ ለማበረታታት ቆሎ፣ ውኃ፣ ዳቦ እና ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡
በአሁኑ ወቅትም በክፍለ ከተማው የምርጫ ክልል 28 ሥር በሚገኙት የምርጫ ጣቢያዎች በርካታ መራጮች አሁንም ድረስ ተሰልፈው ተራቸውን እየተጠባበቁ መሆናቸው ታውቋል፡፡
01/06/2026
ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው!
7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ከሌሊት ጀምሮ በመውጣት ሲመርጡ ለነበሩ የከተማችን ነዋሪዎች፥ በተፈጠረው የምርጫ ሂደት መዘግየት ምክንያት፣ የድምፅ መስጠት ሂደት ባልተጠናቀቅባቸው የምርጫ ጣቢያዎች እስከ ምሽት 6 ሰዓት ማራዘሙን ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።
ይህን ተከትሎ፥ መላው የከተማችን ነዋሪዎች በማለዳ በነበረው ከፍተኛ መነሳሳት የሚስተካከል፣ በታላቅ ሃላፊነት እና ትዕግስት አሁንም በዚህ ሰዓት በየድምፅ መስጫ ጣብያዎች ተሰልፎ ድምፅ እየሰጠ ይገኛል። ለዚህም ላቅ ያለ አድናቆት ይገባዋል።
!
01/06/2026
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
ከማለዳ ጀምሮ ድምፁን በመስጠት ላይ የሚገኘው የከተማችን ክንደ ብርቱ ህዝብ አሁንም በተፈጠረው የሲስተም መስተጓገል ሳይበገር፣ ምርጫ ቦርድ በሰጠው የሰዓት ማሻሻያ በመጠቀም ድምፁን ለመስጠት በየምርጫ ጣቢያው በፅናት እንደቆመ ነው::
ይህም ዲሞክራሲ የማፅናት ተምሳሌትነት ጉዞ ማሳያ ነው::
#ኢትዮጵያእየመረጠችነው
#አዲስአበባእየመረጠችነው
01/06/2026
በድጋሚ የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት 12:00 ሰዓት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ እንደነበር ይታወቃል። ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት ተመልክቶ የሚከተለውን ወሥኗል።
በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) መሠረት ቦርዱ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ብሎ ካመነ የድምፅ መስጫ ሰዓቱን ሊያራዝም እንደሚችል በግልጽ ይደነግጋል። በመሆኑም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ ያሳውቃል።
ማሳሰቢያ: የተመዘገቡ መራጮች መርጠው የተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ ያስታውሳል።
01/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት በማስፈጸም ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ 12:00 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እንደሚቀጥል ያሳውቃል።
ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።
01/06/2026
የኢትዮጵያን መፃዒ እድል ለመወሰን ወሳኝ የሆነዉ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ሂደት አንደቀጠለ ነዉ፡፡
የኢትዮጵያን መፃዒ እድል ለመወሰን ወሳኝ የሆነዉ ይህ ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳዉ 12 ሰዓት የተጀመረዉ 7ኛዉ ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ድምቸዉን እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
01/06/2026
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በሚወዳደሩበት ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን ሰጡ
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል፡፡