01/06/2026
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት በማስፈጸም ላይ መሆኑ ይታወቃል። ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ 12:00 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እንደሚቀጥል ያሳውቃል።
ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።
01/06/2026
የወላድነት ድካም ስሜት ያልበገራቸው እናት፤
ወ/ሮ መሰረት ወሌ በወለዱ በ3ስዓት ልዩነት ድምጻቸውን ሰጡ።
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 የሚኖሩት ወ/ሮ መሰረት ወሌ፣ ወንድ ልጅ በሰላም በተገላገሉ በ3 ሰዓታት ልዩነት ውስጥ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
ወ/ሮ መሰረት በወረዳው በሚገኘው "ጉሊት ምርጫ ጣቢያ" በአካል በመገኘት ነው ሀገራዊ መብትና ግዴታቸውን የተወጡት። የእናቶች እና የህጻናት ጤና ጥበቃ እንዲሁም ከወሊድ በኋላ የሚኖረው ከባድ የድካም ስሜት ሳይበግራቸው፣ ህጻኑን ልጃቸውን በሰላም ተገላግለው ገና የ3 ሰዓት አራስ ሳሉ ወደ ምርጫ ጣቢያው ማምራታቸው በቦታው በነበሩ ታዛቢዎችና መራጮች ዘንድ ከፍተኛ አድናቆትን አትርፏል።
ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ በሰጡት አጭር አስተያየት፣ የወላድነት ስሜቱና ድካሙ ቢኖርም፤ ለሀገር መፃኢ እድል ወሳኝ በሆነው በዚህ የታሪካዊ ምርጫ ወቅት ላይ አሻራቸውን ማሳረፍ በመቻላቸው ታላቅ ደስታና ኩራት እንደተሰማቸው ገልጸዋል።
ይህ የእናትነት እና የዜግነት ቁርጠኝነት፣ በምርጫ ጣቢያው የነበረውን ህዝባዊ መነሳሳት ይበልጥ ያደመቀውና ለሌሎች መራጮችም ትልቅ አርአያነትን ያሳየ ክስተት ሆኗል።
ቦሌ ኮሙኒኬሽን
ግንቦት 24/2018
01/06/2026
የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ በ7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ምርጫ ጣቢያ 2 ድምፃቸውን ሰተዋል።
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
ቦሌ ኮሙኒኬሽን
ግንቦት 24/2018
01/06/2026
ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው !
እኔም መርጫለሁ!!
01/06/2026
ኢትዮዽያ እየመረጠች ነው !
እኔም መርጫለሁ!!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ
01/06/2026
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በበሻሻ ድምፅ ሰጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በትውልድ ቀያቸው በሻሻ ድምፅ ሰጥተዋል።
01/06/2026
የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ነዋሪዎች በማለዳ በመውጣት የሕዝብ ሉዓላዊ የስልጣን ባለቤትነትን በሚያረጋግጥ መልኩ ድምፅ እየሰጠ ይገኛል።
የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው።
በምርጫ ብቻ!
ኢትዮጵያ እየመረጠች ነው!
01/06/2026
በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 በአምስቱም የምርጫ ጣቢያዎች የድምፅ መስጠት ሥነ-ስርአቱን ለመጀመር ዝግጅቶቻቸውን እያጠናቀቁ ነው
31/05/2026
ኢትዮጵያ ትመርጣለች !
የሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር ይረጋገጣል!!
ምርጫ የሕዝብ ሉዓላዊነት እውነተኛ መገለጫ፣ የዜጎች የባለቤትነት እና የውሳኔ ሰጪነት መብት በተግባር የሚረጋገጥበት ወሳኝ መድረክ ነው።
እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚገነባውም፣ የሕዝብን ፍጹም ውሳኔ ሰጪነት በመቀበልና በማክበር ላይ ብቻ ነው። ሕዝብን "በምርጫ አትሳተፉ፣ አትምረጡ" በማለት ለማስፈራራት መሞከር፣ እንዲሁም “እኔ አውቅልሃለሁ" በሚል የተሳሳተ የሞግዚትነት መንፈስ የዜጎችን ነፃ ፈቃድ ለመቀማት መሻት ለሕዝብ ያለን ንቀት የሚያሳይ፣ ከዘመኑ የሕዝብ የፖለቲካ ንቃተ ሕሊና ጋር የማይሄድ ኋላ ቀር አካሄድ ነው።
ሕዝባችን ግን ከእነዚህ ሁሉ የተዛቡ የፖለቲካ አመለካከቶች እጅግ ልቆ የሄደ፣ የሚበጀውንና የማይበጀውን ጠንቅቆ የሚያውቅ፣ እንዲሁም የሀገሩን የወደፊት ዕጣ ፈንታ በራሱ ሚዛናዊነት መወሰን የሚችል እጅግ አስተዋይና እውነተኛ ዳኛ ነው። ለዚህም አንዱና ዋነኛው ማረጋገጫ፣ ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ከወዲሁ በንቃት በመመዝገብ የሀገራቸውን ብሩህ መጻኢ ዕድል ለመወሰንና የሚበጀውን ለመምረጥ ያሳዩት ከፍተኛ ዝግጁነትና ታሪካዊ ቁርጠኝነት ነው።
ስለሆነም፣ የሕዝብን ነፃ ምርጫ ማክበር የዲሞክራሲያዊነታችን መለኪያ ብቻ ሳይሆን የሀገራዊ ሕልውናችን እና የአንድነታችን ፅኑ መሠረት ነው። ይህ 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ለሀገራችን ብቻ ሳይሆን፣ በመላው የአፍሪካ አህጉር የእውነተኛ ዲሞክራሲንና የሕዝብን የውስጥ አቅም በተግባር ለማሳየት የሚኖረው አዎንታዊ አንድምታ እና ምሳሌነት እጅግ የላቀ ነው።
#ዲሞክራሲ
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ