የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን - Ethiopian Heritage Authority

የኢትዮጵያ ቅርስ  ባለስልጣን - Ethiopian Heritage Authority

Share

The page promotes the rich Cultural and Historical resources of Ethiopia to all people across the Globe.

Photos from የኢትዮጵያ ቅርስ  ባለስልጣን - Ethiopian Heritage Authority's post 14/10/2025

በጦርነት የተጎዱ ቅርሶችን መልሶ ለማልማትና ለመጠበቅ የጣልያን መንግስት 1.7 ሚልዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር የፕሮጀክት ውል ተፈራረሙ፡፡

ጥቅምት 4፣2018ዓ.ም
አዲስ አበባ

በትግራይ ክልል ውቅሮ ገኽርላታ ቤልት በሚል በጦርነት የተጎዱ ቅርሶችን መልሶ ለማልማትና ለመጠበቅ የጣልያን መንግስት 1.7 ሚልዮን ዩሮ ድጋፍ ለማድረግ ከኢትዮጵያ ጋር የፕሮጀክት ውል ተፈራረሙ፡፡

ይህ ለሁለት ዓመት የሚቆየው ፕሮጀክት በኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴርና በጣልያን የልማት ትብብር ተወካይ መካከል ነው የተፈራረሙት፡፡ ፕሮጀክቱም በትግራይ ክልል ውቅሮ ገኽርላታ ቤልት ማህበረሰብን በቱሪዝም እና ቅርስ መልሶ ማልማት በሚል ድጋፍ የተዋዋለ የድጋፍ ፕሮጀክት ነው ተብሏል፡፡

Ethiopia and Italy Launch €1.7 Million Project to Boost Post-Conflict Resilience and Heritage Conservation in Tigray’s Wukro-Gheralta Belt

The Ministry of Finance (M*F) and the Italian Agency for Development Cooperation (AICS) have signed a landmark agreement launching a two-year initiative titled “Supporting Community Resilience through Community-Based Tourism and Heritage Conservation in the Wukro-Gheralta Belt, Tigray, Ethiopia.”.

The agreement was signed by H.E. Semereta Sewasew, State Minister at the Ministry of Finance, and H.E. Agostino Palese, Ambassador of Italy to Ethiopia. The €1.7 million project marks a renewed phase of cooperation between the two nations, aiming to promote sustainable livelihoods, peacebuilding, and cultural preservation in post-conflict areas.

H.E. Semereta Sewasew highlighted that the initiative carries both symbolic and strategic value, representing another milestone in the long-standing friendship between Ethiopia and the Italian Republic, rooted in shared history and sustained by mutual cooperation.

መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር ማህበራዊ ገፅ የተገኘ ነው፡፡

Photos from የኢትዮጵያ ቅርስ  ባለስልጣን - Ethiopian Heritage Authority's post 13/10/2025

በመላው ሀገሪቱ ለሰንደቅ ዓላማ ክብርና ለሀገር ሉዓላዊነት ደሙን ያላፈሰሰ፤ ነፍሱን ያልገበረ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ የለም፡- አበባው አያሌው(ረ/ፕ)

ጥቅምት 3፣ 2018ዓ.ም

አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ከመላው የተቋሙ ሰራተኞች እና ከፌዴራል ፖሊስ አባላት ጋር በመሆን 18ኛውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን "ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ለብሔራዊ አንድነታችን እና ለኢትዮጵያ ህዳሴ" በሚል መሪ ቃል አክብሯል።

አበባው አያሌው (ረ/ፕ) የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የተቋሙ ሰራተኞች የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ባከበሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት፡- በመላው ሀገሪቱ ለሰንደቅ ዓላማ ክብርና ለሀገር ሉዓላዊነት ደሙን ያላፈሰሰ፤ ነፍሱን ያልገበረ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ የለም ብለዋል፡፡

ቀኑን የምናከብረው ለብሔራዊ ኩራት፣ ለሉዓላዊነታችንና የሁላችን ዓርማ ለሆነው ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ ሕይወታቸው የሰዉ ውድ ዜጎቻችን ለማሰብ ነው ያሉት ዋናው ዳይሬክተሩ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ሳትደፈር ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ እና ህዝቦቿም ቀና ብለው እንዲኖሩ ለነፍሳቸው ሳይሰስቱ ለተዋደቁ ጀግኖች ክብር ይገባቸዋል ብለዋል።

አክለውም ለዓመታት ለሰንደቅ ዓላማ የሚሰጠው ክብርና እይታ ቀንሶ የነበረ መሆኑን ጠቅሰው ፤ ነገር ግን ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ትኩረት በመስጠት ማከበር በመጀመሩ በህዝቦች ዘንድ የኢትዮጵያዊነት መንፈስና አብሮነት እየዳበረ መጥቷል ብለዋል።

18ኛው የሰንደቅ ዓላማ ቀን ክብረ በዓል ኢትዮጰያ በሁሉም ዘርፍ ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሸጋግራ በማንሰራራት የከፍታ ብስራት ዘመን ላይ ሆና ማክበር መቻሏ ከወትሮው ለየት የሚያደረግ ቀን ነው።

በሁለንተናዊ ለውጥና ልማት የታጀበው መንግስት ለሰንደቅ ዓላማ ክብር ዳግም እንደ ኢኮኖሚው ማንሰራራት የጀመረበት ወቅት ነው። ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፤ ለብሔራዊ አንድነታችን እና ለኢትዮጵያ ህዳሴ በሚል የሚከበረውም ይህንኑ ሃሳብ ለማስረፅ ነው ብለዋል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


National Museum
Addis Ababa