የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication

የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication

Share

ይህ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።

ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ።

Photos from የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ Addis Ababa City Communication's post 31/05/2026
Photos from የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication's post 29/05/2026

የፀጥታ አካላት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት እና የሸገር መና አቢቹ ክፍለ ከተማ የፀጥታ አካላት ጋር 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።

በዕለቱ ተገኝተው ለፀጥታ አካላት ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ “ከዚህ ቀደም የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ እንዳደረግነው ሁሉ፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው “መላው የፀጥታ መዋቅራችን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሁልጊዜውም ዝግጁ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት ከፀጥታ መዋቅሩና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልፀዋል።

በስምሪት መርሃ ግብሩ ላይ የሸገር ሲቲ መና አቢቹ ክፍለ ከተማ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ለፀጥታ አካላቱ አስፈላጊውን የቁሳቁስና የግብዓት ድጋፍ ተደርጓል።

28/05/2026

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
👉የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
👉የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ

2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
👉የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
👉የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
👉ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::

27/05/2026
Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Telephone

Address


Ferensay Legasion
Addis Ababa