03/06/2026
Ethiopian Ministry of Industry
The Ethiopian Ministry of Industry is one of The Ethiopian Federal Democratic Republic Gov
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሀገራችንን ኢኮኖሚ በመምራት የማይናጋ የኢኮኖሚ ስርዓት በመገንባትና ቀጣይነት ያለው አድገትና የስራ እድል ፈጠራን እውን ለማድረግ የአስር ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ አዘጋጅቶ፡-
👉ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ የኢኮኖሚ ድርሻ ከ 6.8 በመቶ በ2022 በጀት ዓመት መጨረሻ ወደ 17.2 በመቶ ማሳደግ፣
👉የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም ከ 50% በ2022 ወደ 85% ማድረስ፤
👉ስትራቴጂክ ገቢ ምርት የሚተኩ አምራች ኢንዱስትሪዎች በማስፋፋት በመነሻ ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ በ2022 ወደ 60 በመቶ ማድረስ፤
👉በአጠቃላይ በማኑፋክቸሪንግ
03/06/2026
02/06/2026
02/06/2026
ኢትዮጵያውያን መርጠዋል፤ ኢትዮጵያ አሸንፋለች!
.....
ኢትዮጵያ ከዜጎቿ የፈለገችዉን ሁሉ በፈለገችው ጊዜና ሁኔታ የምታገኝ ሀገር ናት፡፡ ለሀገራቸዉ የተጠየቁትን ሁሉ ለመስጠት ወደኋላ የማይሉ ዜጎች ስላሏት በእጅጉ ኮርታለች፡፡ ከዓድዋ እስከ ሕዳሴ ግድብ፣ ከወገን ለወገን መረዳዳት እስከ አረንጓዴ ዐሻራ የዜጎቿን ተሳትፎ ጠይቃ፣ ከመሻቷ በላይ ተሳትክቶላታል፡፡ ዛሬ የተደገመዉም ይኸው ነው፡፡
ኢትዮጵያ ኢትዮጵያዊ ዴሞክራሲን ማንበር፣ በግልጽና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ መንግሥትን መምረጥ፣ ሕገ መንግሥታዊነትን ፅኑ መሠረት ማስያዝ ትሻለች፡፡ ለዚህ ደግሞ 7ኛዉን ሀገራዊ ምርጫ እንደ ትልቅ አጋጣሚ መጠቀም አስፈልጓት ነበር፡፡
በምላሹም ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለመራጭነት ተመዝግበው የዛሬዋን ቀን ሲጠባበቁ ቆይተዋል፡፡ እነሆ የእናት ሀገር ጥሪን በመቀበል ዜጎች በነቂስ ወጥተው ሲመርጡ ውለዋል፤ ሌሊቱንም አጋምሰዋል፡፡ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ ዜጎች ለረዥም ሰዓታት ተሰልፈዉ ድምፅ የሰጡበት ልዩ ምርጫም ነው፡፡
ምርጫዉ እንዳይካሄድ ባዳ እና ባንዳ ተቀናጅተዉ ያልቆፈሩት ጉድጓድ፣ ያልደረደሩት እንቅፋት አልነበረም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጠራችው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ የማይቻል ነገር አልነበረምና በስኬት ተጠናቅቋል፡፡ ኢትዮጵያውን በሰላማዊ መንገድ መርጠው ኢትዮጵያ አሸንፋለች፡፡
የኢትዮጵያን የዴሞክራሲያዊ ምርጫ ጥሪ ተቀብሎ ከንጋት እስከ ምሽት በመምረጥ ምላሽ ለሰጠው ሕዝብ፣ ሕገ መንግሥታዊ ሥርዐቱ እንዲጸና እና ዜጎች በሰላም እንዲመርጡ ምቹ ዓውድ ለፈጠሩ የፀጥታ አካላት፣ ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃ በየደቂቃዉ ሲያደርሱ ለነበሩ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማት እንዲሁም የምርጫዉን ሂደት ለመሩ፣ ላስተባበሩ እና ለታዘቡ ሁሉ ኢትዮጵያ ታመሰግናለች፡፡
የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ግንቦት 25 2018፣አዲስአበባ፣ኢትዮጵያ
01/06/2026
ከ54 ሚሊዮን በላይ ኢትዮጵያውያን የምርጫ ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ::
29/05/2026
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ለስራ ጉብኝት አፋር ብሔራዊ ክልል ሰመራ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው
“የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”
http://linktr.ee/fdremoi
29/05/2026
“የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”⚙️
linktr.ee/fdremoi
28/05/2026
🎯 ዛሬን በአዲስ መንፈስ፡ ከትንሽ ተነስተው ትልቅ ለሚሆኑት!
እያንዳንዱ ትልቅ የኢኮኖሚ ስኬት እና የፈጠራ ታሪክ መነሻው አንድ ነው—ከትንሽ መጀመር!
አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች (SMEs) የሀገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ፣ የስራ እድል በመፍጠር እና አዳዲስ አሰራሮችን በማስተዋወቅ ረገድ የሚጫወቱት ሚና በቀላሉ የሚገመት አይደለም።
እያመረታችሁ፣ እየፈጠራችሁ እና እንቅፋቶችን ሁሉ አልፋችሁ ወደፊት እየተራመዳችሁ ያላችሁ ስራ ፈጣሪዎች የሀገራችን እውነተኛ የኢኮኖሚ ሞተሮች ናችሁ።
ዛሬ አዲስ ቀን ነው! አዲስ ቀን ደግሞ አዲስ እቅድን ለመተግበር፣ አዳዲስ ደንበኞችን ለመድረስ እና ምርታማነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ እድል ይዞ ይመጣል።
ዛሬ የምታደርጉት ጥረት የነገው ትልቅ ተቋም መሠረት ነው።
በየቀኑ የምታሳዩት ቀጣይነት ከውድድር መስመር ያስቀድማችኋል።
የምርታችሁ ጥራትና ታማኝነት የደንበኞቻችሁ የዘላቂነት ዋስትና ነው።
ውድ ስራ ፈጣሪዎች እና አምራቾች፤ ቀናችሁን ስትጀምሩ በታላቅ ተነሳሽነት፣ በልዩ ትኩረት እና ምርጥ አቅማችሁን ለመጠቀም ዝግጁ ሆናችሁ ይሁን። ለሀገር ውስጥ ምርት እድገትና ለኢንተርፕራይዞች ስኬት በቁርጠኝነት የምንሰራበት ፍሬያማ የሥራ ቀናት ይሁንልን!
linktr.ee/fdremoi
https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment
28/05/2026
“የፀና ቃል፤ የላቀ እመርታ!”⚙️
ኢትዮጵያ ታምርት ሲባል አሁን ባየነው ውጤት ልክ በፈጠነ ጊዜ የምርት አይነት ሰፍቶ ጥራት አድጎ የኢትዮጵያን ፍላጎት በዚ ልክ ይመልሳል ብለው የሚያምኑ ሰዎች ጥቂቶች ሊሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የአምናውን የአቻምናውን ኤክስፖ መጥቶ የጎበኘ ማንኛውም ሰው የዘንድሮውን ሲጎበኝ ኢትዮጵያ ምን ያክል በጥራትና በአይነት እያደገች እንዳለች ለመገንዘብ ለመማር ለማወቅ አይቸገርም ፡፡
linktr.ee/fdremoi
26/05/2026
ኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ አምራቾችን ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ያሳድጋል የተባለለትን የመጀመሪያውን የንግድ ፖሊሲ አፀደቀች
======================================
ግንቦት 18/2018 ዓ.ም (ኢሚ )የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሀገሪቱን የንግድ ሥርዓት በዘመናዊ መንገድ ለመምራት ያስችላል ያለውን “የኢትዮጵያ የንግድ ፖሊሲ” በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።
የፖሊሲው አስፈላጊነት፡-
▪️ የገበያ ክፍተቶችን ለመሙላት፦ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓትን በአግባቡ ለመምራት፣
▪️ የወጪ ንግድን ለማዘመን፦ በግብርና ላይ ብቻ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ የውጭ ገቢን ለማሳደግ፣
▪️ ፍትሐዊ አሰራርን ለመዘርጋት፦ የምርት ደህንነትን ለማረጋገጥና ሕገወጥ ውድድርን ለመግታት እና
▪️ ኢንዱስትሪዎችን ለማጠናከር፦ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርታማነትና ተወዳዳሪነት እንዲያድግ ለመደገፍ።
ፖሊሲው ከዛሬ ግንቦት 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ ተፈጻሚ እንዲሆን ምክር ቤቱ ወስኗል፡፡
የንግድ ፖሊሲው መጽደቅ ሀገራችን ለዘመናት ንግድን በተበታተኑ ሕጎች ስትመራበት የነበረውን አሰራርን ከመሠረቱ በመቀየር የሀገር ውስጥና የወጪ ንግድን የተቀናጀ፣ ተገማችና በሕግ ማዕቀፍ ወደሚመራ አስተዳደር የሚያሸጋግር እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡
linktr.ee/fdremoi
26/05/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Address, Adwa Street
Addis Ababa
Opening Hours
| Monday | 08:30 - 17:30 |
| Tuesday | 08:30 - 17:30 |
| Wednesday | 08:30 - 17:30 |
| Thursday | 08:30 - 17:00 |
| Friday | 08:30 - 17:30 |
