ክርስቲያኑም አለ: መለሰም

ክርስቲያኑም አለ: መለሰም

Share

ይህ 'ፔጅ' በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እና በክርስቲያናዊ አስተምህሮዎች ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች በመረጃ ላይ የተመሰረቱ መልሶችን ይሰጣል:

List of English translated personal names - Wikipedia 21/05/2024

የአምላክ ስም ጉዳይ:-
============
🌍 በድሮ ጊዜ ስሞች ተተርጉመው ጥቅም ላይ ይውሉ ነበር።
🌍በዘመናዊው አለም የግል ስሞች አይተረጎሙም:ከህግ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ።
🌍በጥንት ዘመን እና በመካከኛው ዘመን የግል ስምችን ከአንድ ቋንቋ ወደ ሌላው ቋንቋ እየተረጎሙ የመጠቀም ልማድ ነበር።ይህም ሲሆን በመጀመሪያ በነበረው ስም ላይ ሙሉ ለውጥ ወይም የተወሰነ ለውጥ ይደረግ ነበር።
ምሳሌዎች:-
🌍Ali Ibn Al-Ḥusayn Ibn-'Abdillāh Ibn-Ḥasan Ibn-Sīnā(አረቢኛ)=Avicenna(ወደ እንግሊዝኛ).....ሙሉ ለውጥ
🌍Wilhelm Alexander (ጀርመንኛ)=Bill Alexander("ወደ እንግሊዝኛ)....የተወሰነ ለውጥ
🌍Lucius Sergius Catilina (ላቲን)=Catiline(እንግሊዝኛ)....የተወሰነ ለውጥ
🌍Cristóbal Colón (ስፓኒሽ)=Christopher Columbus(ወደ እንግሊዝኛ)
🌍Cristoffa Corombo (ሊጉሪያን)=Christopher Columbus(እንግሊዝኛ)
🌍Kǒng Qiū (孔 丘),ወይም (Kǒng Fūzǐ (孔 夫子) :(ቻይኒኛ)=(Confucious...እንግሊዝኛ)...ሙሉ ለውጥ እና ወዘተ። ....ምንጭ:-
https://en.m.wikipedia.org/wiki/List_of_English_translated_personal_names
🌍በዚህም መሠረት የአምላክ ስም በዕብራይስጥ "ያህዌ":በግሪክ "ቴዎስ":በእንግሊዝኛ "God" በአማርኛ "እግዚአብሔር" እና ወዘተ።
🌍ከዚህ በተረፈ ግን "አላህ" የሚለው ቃል "አል" እና "ኢላህ" ከሚሉ ሁለት ቃላት የተገኘ ሲሆን እንደሚታወቀው "አል"=the:"ኢላህ"="አምላክ" በመሆኑ: አላህ =አንድ የታወቀ(definite) የሆነ አምላክ ማለት ነው።ስለዚህም "አላህ" የአምላክ ...የግል መጠሪያ ስም(Proper noun) አይደለም።

🌍" ኢላህ"(አራማይክ"): እና "አላህ"(አረቢኛ)🌍🌍

🌍 አራማይክ ቋንቋ አሁንም በሶሪያ ተወላጆች ይነገራል።
🌍በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን የነበረው የአምላክ መጠሪያ ስም በአራማይክ ቋንቋ "ኢላሃ" ነው።ሆኖም በዘመናዊ አራማይክ "አላሃ" ነው።ይህም ከአረቢኛው "አላህ" ጋር ተመሳሳይ ነው።
🌍የአምላክ ስም በሌላ የጥንት የሶሪያ ቋንቋ " አላሃ" ነው።
🌍የእስልምና "አምላክ" መጠሪያ ስም "አላህ" የሚለው ቃል የተገኘው "አል-ኢላህ" የሚለውን ቃል በማሳጠር እንደሆነ በቀጣዩ ሊንክ ላይ ተመልከት። "አላህ" የሚለው ቃል "ኢላህ" እና "አላሃ" ከሚሉት ቃላትም ጋር ተመሳሳይነት እንዳለው እንዲሁ:-
🌍Allah (/ˈælə, ˈɑːlə, əˈlɑː/;[1][2][3] Arabic: ٱللَّٰه‎, romanized: Allāh, IPA: [ʔaɫ.ɫaːh] ⓘ) is the common Arabic word for God. In the English language, the word generally refers to God in Islam.[4][5][6] The word is thought to be derived by contraction from al-ilāh, which means "the god", and is linguistically related to the Aramaic words Elah and Syriac ܐܲܠܵܗܵܐ (ʼAlāhā) and the Hebrew word El (Elohim) for God.[7][8]
https://en.m.wikipedia.org/wiki/Allah
🌍በአረብ አገር ያሉ ክርስቲያኖች በቋንቋቸው የአምላክ ስም ተተርጉሞ ሲቀርብ የነበረው አማራጭ/አቻ ቃል "አላህ" በመሆኑ ቃሉን ይጠቀሙበታል።
🌍አንዳንድ ሙስሊም እግዚአብሔር ስለሚለው ስም የሚናገረው አፍራሽ ነገር የሚያሳየው ስለ ቋንቋ ያለውን አናሳ ግንዛቤ ነው። ስለ ቋንቋ ጠቅለል አድርገን ብንነጋገር ቋንቋ ስምምነት በመሆኑ በቋንቋ ውስጥ የምጠቀማቸው ቃላትም እንዲሁ ስምምነት ናቸው።ስለዚህም አንድ ሰው አምላክን ለማመልከት በየቋንቋው "ያህዌ"(ዕብራይስጥ) :"God":"እግዚአብሔር" :"ቴዎስ"(በግሪክ":" ዲዮስ"(ስፓኒሽ) እና ወዘተ ቃላትን ሊጠቀም ይችላል።
🌍እላይ እንዳልነው ቋንቋ ስምምነት ነው።ሰለዚህ ለአንድ ነገር የተሰጠው ስምም እንዲሁ ስምምነት ነው።እናም እንደ ምሳሌ" አላህ" የሚለውን ቃል ብንመለከት በጥንት ዘመን ጣዖትንም ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሎ ነበር:- https://en.m.wikipedia.org/wiki/Allah_as_a_lunar_deity #:~:text=The%20postulation%20that%20Allah%20(God,he%20called%20a%20lunar%20deity.
....ሆኖም በሌላ መልኩ ፈጣሪንም ለማመልከት ጥቅም ላይ ውሏል።

List of English translated personal names - Wikipedia This is a list of personal names known in English that are modified from another language and are or were not used among the person themselves.

Jami` at-Tirmidhi 2562 - Chapters on the description of Paradise - كتاب صفة الجنة عن رسول الله صلى الله عليه وسلم - Sunnah.com - Sayings and Teachings of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) 17/05/2024

🌍 ለክርስቲያን በሰማይ ጋብቻ የለም።ሙስሊም የሚጠቅሰው "መቶ እጥፍ" ጥቅስ ማጣመም ነው። የሙስሊሞች ነብይ መሀመድ ሴትን በተመለከተ ላለው ፍላጎት ገደብ የለሽ ንባብ ለራሱ አስቀምጧል።ኢየሱስ እንደዚህ አልተናገረም።የሙስሊሞች ሀዲስም ሙስሊሞች በገነት 72 ደናግላን እና 80,000 አገልጋዮች ወይም ባሮች እንደሚጠብቋቸው ይናገራል:-
----------

🌍ለመጀመር ያህል ለክርስቲያን በሰማይ ጋብቻ የለም:

(“በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም።”
— ማቴዎስ 22፥30)
🌍ጋብቻ ከሌለ ሚስት የለችም።ስለዚህ ጥቅሱን አጣመህ ነው የጠቀስከው ማለት ነው።
🌍"መቶ እጥፍ" ዘይቤያዊ ንግግር ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ የተለያዩ ቦታዎች ላይ ይገኛል።🌍የሚቀጥለው ንባብ ሰው ለክርስቶስ ብሎ በስደት ዘመዶቹን እና ቤቱን ቢተው ..."መቶ እጥፍ"...በዚህ አለም... ያገኛል ሲል ትርጉሙ እነዚህ ነገሮች ከሚሰጡት የውስጥ ደስታ እና ሰላም ብዙ እጥፍ ነው ማለት ነው።🌍በሚቀጥለው አለም ደግሞ የዘላለም ህይወት።

“አሁን በዚህ ዘመን ከስደት ጋር ቤቶችን ወንድሞችንና እኅቶችንም እናቶችንም ልጆችንም እርሻንም መቶ እጥፍ፥ በሚመጣውም ዓለም የዘላለም ሕይወት የማይቀበል ማንም የለም።”
— ማርቆስ 10፥30
🌍ሚስት የተጠቀሰችበት የሚቀጥለው ጥቅስ ላይም ብትወስደው ትርጉሙ የውስጥ ሰላም እና ደስታ ነው:ምክያቱም በሰማይ ጋብቻ የለም።
🌍“ስለ ስሜም ቤቶችን ወይም ወንድሞችን ወይም እኅቶችን ወይም አባትን ወይም እናትን ወይም ሚስትን ወይም ልጆችን ወይም እርሻን የተወ ሁሉ መቶ እጥፍ ይቀበላል የዘላለምንም ሕይወት ይወርሳል።”
— ማቴዎስ 19፥29
---------
🌍ከዚህ ውጪ ግን ብንመለከት መሀመድ በቁርአን የገለጸው ...የሚፈልጋትን ሴት ያለገደብ ማግባትና የማይፈልጋትንም መፍታት...እንደሚችል ነው:-

33:51
"ከእነርሱ የምትሻትን ታቆያለህ፡፡ የምትሻውንም ወደ አንተ ታስጠጋለህ፡፡ (በመፍታት) ከአራቅሃትም የፈለግሃትን (በመመለስ ብታስጠጋ) በአንተ ላይ ኀጢአት የለብህም፡፡ ይህ ዓይኖቻቸው ወደ መርጋት፣ ወደ አለማዘናቸውም፣ ለሁሉም በሰጠሃቸው ነገር ወደ መውደዳቸውም በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም በልቦቻችሁ ውስጥ ያለውን ሁሉ ያውቃል፡፡ አላህም ዐዋቂ ታጋሽ ነው፡፡"

🌍ኢየሱሰ እንደ መሀመድ ያለ ለስጋዊ ፍላጎት ገደብ የለሽ ንግግር አልተናገረም።
🌍በተጨማሪም ይህ ሙስሊሞች "መቶ እጥፍ" እያሉ ጥቅሱን በማጣመም ለማስቀመጥ የሚሞክሩት ጉዳይ በሀዲሳቸው የተቀመጠውን ሙስሊሞችን 72 ደናግላን እና 80,000 ሺህ አገልጋዮች ወይም ባሮች በገነት ይጠብቋቸዋል የሚለውን ንግግር ሊሰርዘው አይችልም:-

"...The least of the people of Paradise in position is the one with eighty thousand servants and seventy-two wives...."

Jami` at-Tirmidhi 2562

Jami` at-Tirmidhi 2562 - Chapters on the description of Paradise - كتاب صفة الجنة عن رسول الله صلى الله عليه وسلم - Sunnah.com - Sayings and Teachings of Prophet Muhammad (صلى الله عليه و سلم) Hadith of the Prophet Muhammad (saws) in English and Arabic

Photos from ክርስቲያኑም አለ: መለሰም's post 10/05/2024

ቁርአን Vs የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖
--------------------
✍️ .....ቁርአን..27:44:-
"ሕንጻውን ግቢ ተባለች፡፡ ባየቺውም ጊዜ ባሕር ነው ብላ ጠረጠረችው፡፡ ከባቶችዋም ገለጠች፡፡ «እርሱ ከመስተዋት የተለሰለሰ ሕንጻ ነው» አላት፡፡ «ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ» አለች፡፡"
✍️የአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ:(Second Targum of Esther...ገጾች 282-283,(https://en.m.wikipedia.org/wiki/Targum_Sheni):
(P.282)
"...When the queen saw the king sitting there, she thought in her heart, and in fact...
(P.283)
said, that he was sitting in water, and she raised her dress to cross the water, when the king noticed that her foot was full of hair. He said to her, "Thy beauty is the beauty of women, and thy hair is the hair of men;.....
====
✍️"ንግስቲቱ ንጉሱን እዚያ ተቀምጦ ባየች ጊዜ በውሃ ውስጥ የተቀመጠ መሰላት:በውሃ ውስጥም እንደተቀመጠ ተናገረች።ውሃ የመሰላትንም ለመሻገር ቀሚሷን ከፍ አደረገች።ንጉሱም እግሯ በጸጉር የተሸፈነ መሆኑን ሲያይ "ቁንጅናሽ የሴቶች ነው:ጸጉርሽ ግን የወንዶች ነው" አላት።.....

✍️ቁርአን 27:44 ላይ የተነገረው ንባብ አስቀድሞ በአይሁድ የትውፊት መጽሐፍ ውስጥ(Second Targum of Esther,
ገጾች 282-283 ላይ) ተቀምጧል።ከሰማይ የወረደ አይደለም።🌍ታርገሙ ኦንላይን የሚገኝበትን ሊንክ(https://en.m.wikipedia.org/wiki/Targum_Sheni)ከኮሜንት አግኝተው ይጫኑት:- Second Targum of Esther...
An Explanatory Commentary on Esther, The Second Targum Translated from Aramaic with notes, Professor Paulus Cassel, Berlin, Germany. Translated to English by Aaron Bernstein, T. & T. Clark, 38 George Street, Edinburgh, Scotland, 1888, p. 282-283.

🌍...https://en.m.wikipedia.org/wiki/Targum_Sheni....
==============================
===========
የአይሁዶቹ ጥንታዊ ታርገም ላይ ያለው ትረካ የቃላት ለውጥ ተደርጎበት በቁርአን የአምላክ ቃል ተብሎ ተተርኳል።
➡️መሀመድ አብዛኛው ቁርአን ውስጥ ያለውን ይዘት ጠላቶች እንደሆኑ ከሚቆጥራቸው አይሁዶች ነው ኮፒ ያደረገው

08/05/2024

🌍ኢየሱስ የተሰቀለው በ3 ሰአት ወይስ በ6 ሰአት?
...ማር 15:25:- ሶስት ሰአት
...ዮሐ.19:14-15:- ስድስት ሰአት
...ሉቃ.23:44:- ስድስት ሰአት
-------------
....ማቴ.27:45-46 :-ከስድስት ሰአት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰአት ድረስ በምድር ላይ ጨለማ ሆነ ይላል እንጂ ኢየሱስ በመጀመሪያ መስቀል ላይ የተቸነከረበትን ሰአት አይጠቅስም።
.....

🌍የወንጌል ጸሀፊያን ወንጌላቱን ከጻፉባቸው ቦታዎች እና ህዝቦች አንጻር በዘመናቸው የነበረን የተለያየ አቆጣጠርን በመጠቀም አስቀምጠውታል።
🌍ዮሐንስ የሮማውያን አቆጣጠርን ሲጠቀም ሌሎቹ ጸሀፊዎች እንደ አይሁዳውያን አቆጣጠር አስቀምጠውታል።

🌍ለዚህ ጉዳይ በጣም ጥሩ ምሳሌ በምንኖርበት አለም በዘመናችን ያለው የተለያየ የሰአት አቆጣጠር ነው።

🌍በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር አሁን ሰአቱ ከቀኑ 10:00 ሰአት ነው።አንድ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለን ፈረንጅ አሁን "What is the time?"ብለን ብንጠይቀው 4:00 p.m (አራት ሰአት ) ብሎ ይመልስልናል።🌍በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር 10:00 ሰአት በፈረንጅ አቆጣጠር 4:00 ሰአት ነው።
🌍ስለዚህ አንድ ሰው 10 ወይስ 4 ብሎ ለመተቸት ቢሞክር የአቆጣጠር ልዩነት አላዋቂነቱን ነው እየተናገረ ያለው።
🌍የአይሁዳውያን የጊዜ አቆጣጠር በጸሀይ መውጣትና መግባት ላይ የተመሠረተ የነበረ ሲሆን የሮማውያን ግን ከእኩለ ሌሊት እስከ እኩለ ቀን ያለውን በመቁጠር ላይ የተመሠረተ ነበር።

04/05/2024

🌸🌸🌸🌸 🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ኢየሱስ አስቀድሞ ስለ ሞቱ እና ትንሳኤው ትንቢት ተናግሮ ነበር:-
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
🌍“መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።”
— ዮሐንስ 10፥14-15
🌍“ነፍሴን ደግሞ አነሣት ዘንድ አኖራለሁና ስለዚህ አብ ይወደኛል።”
— ዮሐንስ 10፥17
🌍ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ኢየሱስም መልሶ፦ ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
²⁰ ስለዚህ አይሁድ፦ ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሠራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት።
²¹ እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።
²² ስለዚህ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ደቀ መዛሙርቱ ይህን እንደ ተናገረ አሰቡና መጽሐፍንና ኢየሱስ የተናገረውን ቃል አመኑ።

07/04/2024

ኢየሱስ ከማርያም ስጋ ተካፍሏል ወይስ አልተካፈለም?
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ተካፍሏል
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸

🌍ኢየሱስ በትክክል የእኛን የሰዎችን ስጋ ከማርያም ተካፍሏል:-

የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ:-

“እንግዲህ ልጆቹ በሥጋና በደም ስለሚካፈሉ፥ እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፥ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፥ በሕይወታቸውም ሁሉ ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ እንዲያወጣ፥ በሥጋና በደም እንዲሁ ተካፈለ።”
— ዕብራውያን 2፥14-15

🌍 ኢየሱስ ከማርያም ስጋ በትክክል ተካፍሏል:ማስረጃዎች:-
1.ባይካፈል ወደ ማርያም ማህጸን መምጣት አያስፈልገውም/ትርጉም አይኖረውም ነበር
2.ኢየሱስ ራሱን.....እንደ ሰው ..."የሰው ልጅ" ብሎ የጠራበት ምክንያት ...=እኔ በትክክል የሰው ስጋ ለብሻለሁ ለማለት ነበር።
3.ኢየሱስ የማርያምን ስጋ አለበሰም ካልን እግዚአብሔር ...አስመሰለ ...እንጂ በትክክል ሐቅ አልሰራም ልንል ነው።ያ ደግሞ የሀሰት ንግግር ነው። እዚህ ጋር ቁርአን የተሰቀለው ተመሰለባቸው እንጂ አልሰቀሉትም:አልገደሉትም:በምትኩ ሌላ ተሰቀለ ...ፈጣሪ አስመሰለ...የሚለው ጉዳይ ትዝ ይለኛል።ያ ከሆነ ፈጣሪ እያስመሰለ/እየዋሸ/ እንጂ ሀቅ እየሰራ አይደለም ማለት ነው።

በተጨማሪም:-

🌍 ኢየሱስ ራሱን የዳዊት ስርና ...ዘር...ብሎ ጠርቷል:-

“እኔ ኢየሱስ በአብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ይህን እንዲመሰክርላችሁ መልአኬን ላክሁ። እኔ የዳዊት ሥርና ዘር ነኝ፥ የሚያበራም የንጋት ኮከብ ነኝ።”
— ራእይ 22፥16

..አንድ ሰው እኔ የእከሌ ዘር ነኝ የሚለው ከዚያ ቤተሰብ ተወላጅ ሲሆን ነው።ኢየሱስ የዳዊትን ቤተሰብ ስጋና ደም ሳይካፈል ዘር ነኝ ይላል ብለን መጠበቅ አንችልም።

🌍ኢየሱስ የአብርሃምን ዘር ነው የያዘው...የመላዕክትን አይደለም ይላል ቃሉ።
.መላዕክቶች መናፍስት እንጂ ስጋ አይሉም።ኢየሱስ ከማርያም/ከሰው /ስጋ አልተካፈለም ካልን....ስጋ/ሰው/ሳይሆን የነበረው ...መንፈስ...ነበር ብለን የኑፋቄ ትምህርት ልንናገር ነው:-

“የአብርሃምን ዘር ይዞአል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም።”
— ዕብራውያን 2፥16

🌍ኢየሱስ ከማርያም ስጋ መካፈል ባያስፈልገው ኖሮ ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ ....ያ ሁሉ ልፋት ...አያስፈልግም ነበር:-
በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ መግባት አያስፈልገውም ነበር።በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ ለመግባት አንድን ዘር በጥንቃቄ ለሺህ አመታት (አብርሃምን መምረጥ : ከ12ቱ ይሁዳን:ከይሁዳም ዳዊነትን:ብዙ ቆይቶ ደግሞ ከዳዊት ማርያምን።)
መርቶ ጠብቆና አቆይቶ ነው..ዕቅዱን ያሳካው......ምክንያቱም እግዚአብሔር በራሱ በመለኮት ሕግ የሚመራ... አምላክ ነው።

እግዚአብሔር በመለኮታዊ ህግጋትና መርሆች የማይመራ ቢሆን ኖሮ በዘፈቀደ ወይም በቅጽበት ኢየሱስ የሆነ ስጋ ለብሶ ቀጥታ ምድር ላይ መገለጥ ይችል ነበር።ግን እንደዚያ አይደለም።

=====================================
=====================================

04/04/2024

🌍አዲስ ፍጡር ከመሆን አንጻር ፈጣሪ አይወለድም ነገር ግን በተወለደ ስጋ ውስጥ መገለጥ ይችላል።🌍
🌍ስለዚህ ከችሎታ አንጻር ፈጣሪ በሴት ማህጸን ውስጥ አልፎ መወለድ ይችላል :ሁሉን ቻይ ነውና።🌍

04/04/2024

🌍🔴🌍🔴🌍🔴🌍🌍🔴🌍🔴🌍🔴🌍🔴🌍
-መሀመድ አያውቅም:
-ኢየሱስ... እንደ አምላክ... ሁሉን ያውቃል
-ኢየሱስ የዘላለምን ህይወት ይሰጣል:ስለዚህ ፈጣሪ ነው።
-በአለም ፍጻሜ ኢየሱስ የሚሽረው የአጋንንትን አለቅነትና ስልጣን ነው።

========

🌍መሀመድ አላውቅም እያለ ነው:-.

46:9:-

«ከመልክተኞች ብጤ የሌለኝ አይደለሁም፡፡ በእኔም በእናንተም ምን እንደሚሥሠራም አላውቅም፡፡ ወደእኔ የሚወረደውን እንጅ ሌላን አልከተልም፡፡ እኔም ግልጽ አስፈራሪ እንጅ ሌላ አይደለሁም» በላቸው፡፡

21:111:-

"እርሱም (ቅጣትን ማቆየት) ምናልባት ለእናንተ ፈተናና እስከ ጊዜው መጠቃቀሚያ እንደሆነም አላውቅም፤ (በላቸው)፡፡"

=====

🌍 ኢየሱስ.... እንደ አምላክ... ሁሉን ያውቃል:-

“ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት።”
— ዮሐንስ 16፥30
=====
🌍 ኢየሱስ በራሱ ለሰዎች ...የዘላለም ህይወትን የመስጠት ሀይል አለው:-

“እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።”
— ዮሐንስ 10፥28
🔴🔴🔴 ከፈጣሪ በቀር ለሰዎች የዘላለም ህይወትን መስጠት የሚችል ማን ነው?..ማንም የለም።ስለዚህ የማመልከው የዘላለም ህይወት የሚሰጠኝ ኢየሱስ ፈጣሪ ነው።
=====
🌍ኢየሱስ በአለም ፍጻሜ የሚሽረው አለቅነት እና ስልጣን የአምላክን ሳይሆን የሰይጣንን ነው።

የሰይጣን መንግስት አሁን ባለው ሁኔታ አለቅነትና ስልጣን አለው:-

“መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”
— ኤፌሶን 6፥12

“በኋላም፥ መንግሥቱን ለእግዚአብሔር ለአባቱ አሳልፎ በሰጠ ጊዜ አለቅነትንም ሁሉና ሥልጣንን ሁሉ ኃይልንም በሻረ ጊዜ፥ ፍጻሜ ይሆናል።”
— 1ኛ ቆሮንቶስ 15፥24
===

Photos from ክርስቲያኑም አለ: መለሰም's post 02/04/2024

ዘዳግም 23:1

ዘዳግም 23:1

"ብልቱ" ✅ ከአዲሱ መደበኛ ትርጉም
"ቁላው" ❎

🌍1954 ላይ ያለው ቃል እንደ ህክምናና ባዮሎጂ አካባቢዎች ብዙ ችግር ባይኖረውም ለአጠቃላይ አንባቢ ግን የአዲሱ መደበኛ ትርጉም ነው ...አመቺ እና ትክክለኛ ቃል።🌍የ1954ቱ ትርጉም ይህን ቃል በተመለከተ ...እንደ ትርጉም...ግድፈት..መወሰድ ይችላል።

02/04/2024

🌍 🌍🌍🌍🌍🌍ዮሐ.17:3,1ኛጢሞ 2:5,ኢሳ9...ወዘተ
ጭማቂ ነጥቦች
=====================================
.. 🌍 ኢየሱስ በምድር በነበረበት ወቅት በዋናነት በሁለት መልኩ ይናገር ነበር:-

1.ከመለኮታዊ ባህሪው እንደ አምላክ (ምሳሌ :- ሀጢአትን ይቅር ብሏል

“ኃጢአትህ ተሰረየችልህ ከማለት ወይስ፦ ተነሣና ሂድ ከማለት ማናቸው ይቀላል?”
— ማቴዎስ 9፥5

2. ከሰብአዊ ባህሪው እንደ ሰው :ምሳሌ:-

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሕይወት ናት።”
— ዮሐንስ 17፥3
=====

🌍በመጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን የተመለከቱ ጥቅሶች አንዳንዶቹ ሰብአዊነቱን:አንዳንዶቹ መለኮታዊነቱን ያሳያሉ።

🌍 1ኛ ጢሞ.2:5 ላይ "..ሰው የሆነ..." ሰብአዊነቱን የሚያመለክት ንባብ ነው።
====
🌍የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች በተለይ በብሉይ ኪዳን በአብዛኛው በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ናቸው:-

የቅርብ እና የሩቅ መልዕክቶች ነበራቸው።በወቅቱ ለነበረው ሰው/ክስተት/ የተነገሩ በተመሳሳይ ሁኔታ በሩቅ ለሚመጣው ሰው/ክስተት

ምሳሌዎች:-

1.ህዝቅኤል 28ን በጥልቀት ስናየው በጊዜው የነበረውን ንጉስ እንዲሁም ሰይጣንን ያመለክታል

2.ኢሳ 7 እና 9 ላይ በወቅቱ የተፈጸመም የሩቅ ክርስቶስን በሩቅ ያሳያል ...ከጊዜ አንጻር።

===
🌍አዲስ ፍጡር ከመሆን አንጻር አምላክ አይወለድም ነገር ግን በተወለደ ስጋ ውስጥ መገለጥ ይችላል።🌍 ከችሎታ አንጻር አምላክ በሴት ማህጸን ውስጥ አልፎ መወለድ ይችላል :ሁሉን ቻይ ነውና።

02/04/2024

"አብ"("አባት") እና "መንፈስ ቅዱስ" የመሳሰሉ ስሞች ጉዳይ
======
የጋራ ወይም (common noun):እና የግል መጠሪያ ስም(Proper noun).....የጥቅል ስም(collective noun)...የነገር/የዕቃ/ ስም(Material noun) እና ወዘተ......የመሳሰሉ የስም አይነቶች አሉ።

🌍"አባት" የጋራ ስም (common noun) ነው። ....የማዕረግ ስም (title) ሆኖም አልፎ አልፎ ያገለግላል።.....
🌍"መንፈስ ቅዱስ" የማዕረግ ስም(Title) ሆኖ ቢያገለግልም የእግዚአብሔር መንፈስን በተመለከተ ግን የግል መጠሪያ ስም(Proper noun) ነው።
🌍አብ ለኢየሱስ አባት ነው ሲባል ....ዘይቤያዊ... ንግግር ነው:-በአብና በወልድ መካከል ያለውን ግንኙነት ለመግለጽ ጥቅም ላይ የዋለ ነው።....መለኮት መለኮታዊ ጽንሰ ሀሳቦችን በሰው ቋንቋ ለመግለጽ የተጠቀመባቸው.....የሰው ቋንቋ ነው።
🌍ኢየሱስ አብ አባቴ ነው ሲል ለእግዚአብሔር የሰው ባህሪ ሰጥቶ ....በዘይቤያዊ ንግግር...እየተናገረ ነው።ያን ዘይቤያዊ ንግግር ነጮች Anthropomorphism ("አካለሰብዕነት") ይሉታል።
🌍"ኢየሱስ"("አዳኝ" የስሙ ትርጉም ): ስም ነው:የግል መጠሪያ ስም (proper noun)።
🌍"ክርስቶስ" ስም ነው: ....ትርጉሙ "የተቀባ" ስለሆነ በብሉይ ኪዳን የማዕረግ ስም (title) ሆኖ ቢያገለግልም የተሰቀለውን ኢየሱስን በተመለከተ ግን የግል መጠሪያ ስም(Proper noun) ነው።

Want your business to be the top-listed Government Service in Addis Ababa?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Category

Website

Address


Churchil Avenue
Addis Ababa
345693