ይህም ግዜ ያልፋል !!!
Negena Nigat / ነገና ንጋት /
09/03/2026
Thanks for all
01/03/2026
ጦርነቱ ከመደረጉ በፊት እ.ኤ.አ በ1880ዎቹ መጀመሪያ ጀርመን አገር በርሊን ከተማ ላይ በተደረገው የአውሮጳ ቅኝ ገዢ (ኮሎኒያሊስት) መንግስታት ሥልጣናትና ልሂቃን የጦር ጄኔራሎችና ሊቃውንት ስብሰባ ላይ ጥቁር ትልቅ ትል ነው ቅንቡርስ ነው እንጂ ነፍስ ያለው ሰው አይደለም ብለው የነበሩ አፈሩ፤ እውነትና ፍትህ ኢትዮጵያና አፍሪቃ ከበሩ፡፡
ሥለጎንደሩ የቤተመንግሥት አናብሥቶች ታሪክ ሲነሳ ዘወትር የንጋትን ብሥራት ሚያስተጋባልኝ የአራዊት ሁሉ አለቃ ( ሰውም አራዊት ነው )የግሣት ድምጽ ነው ። እውነት ግን በኔ ዕድሜ ያላችሁ ሁሉ አልናፈቃችሁም ፣ በነሱ ድምጽና መኖር የደም ስርፀትና ውርሥ ሃይማኖታዊ ጽናት ፣ መንፈሳዊ ጉልበትና አካላዊ ብርታት አይነጥፍብንም ነበር ይህን ለመረዳት ቅንነት አይጠይቅም in Islamic traditions Ali Ibn Abu Talib is called the "Lion of God" (Asadullah) by Shiite Muslims. በክርስትናም representing strength, leadership, and the lineage of Jesus Christ በሌላ አባባል የከተማችን ሞገሥ የአፄ ፋሲል ግምብ ድምቀት ባለጥቁር ጋማው አንበሣ አልናፈቃችሁም ? የአልጣሽ ፓርክ አሟቂ ፣ የጎንደር ነገስታት ዙፋን ጠባቂ የአለማችን ብቸኛ መገኛና መጽኛ ባለጥቁር ጋማው abyssinian lion ከች ይበልልን ልብ እንበል ባለጥቁር ጋማውን
09/10/2025
ይሕ ግንባታ ላይ ያለው የጎንደሯ ሐመረ ብርሐን ደብረ ምጥማቅ ማርያም ሕንፃ ነው ፣ ከተመስረተ ዘመናትን ያስቆጠረው ይህ ደብር በአሁኑ ወቅት እጅግ የተዋጣለት ንድፍ ተሰርቶለት ግንባታው በባለሙያና በቤተክርስቲያን ውድ ልጆች የበረከት ብርታትና ጥረት ካለበት ደርሷል ፣ ብዙም ይቀራል ፣ በመሆኑም ከህንፃው ግዙፍነትና ውበት አንፃር ለማጠናቀቅ የሁላችን የጋራ ርብርብ ስለሚሻ ከመስከረም ፴ እስከ ጥቅምት ፪ በስፍራው በመገኘት የደረሰበትን እየጎበኘን ለቀሪው ስራም እጃችን እንድንዘረጋ ምስለ ፍቅሩ ወልዳ እመብርሃን ጥሪ አድርጋልናለች እና ሁላችንም እዛው እንገናኝ ። ነገ ማልደን እዛው !!!
07/10/2025
እንደኔ አባት አረዳድ አባቶቻችን አሁን ድረስ እንዳይነሱ እና ትውልድ በሂደት እንዲዘነጋቸው ሚፈልጓቸው እውነቶች አሏቸው በአንፃሩ እንኳንስ ለትውልድ ለፍጥረታት እንዳይመክኑ "ወይፈን ካረሰው በሬ ያንደፋረሰው " ብለው ከኮበሌና ከኮረዳ ከሹምኛ እና ከችኩል ሐይማኖተኛ ሚጠነቀቁባቸው ሃቅ አሏቸው ። ለዛም ነው የኢትዮጵያዊያን የሆኑት ሁሉ ያልመከኑት ። እንደ አባቴ አረዳድ አብዛኞቻችን ዝይ ነን ። አባቴ ይህን ሁሉ ሚለኝ ዶር በድሉ ዋቅጅራ ስለ ግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ቀመር ውስጥ መካተት ፣ ስለ አማርኛ ቋንቋ ፊደላት መቀነስ ፣ አማራ ክልል ሊማረው ስለሚገባው ያጎራባች ቋንቋዎች ጥናትና መረጣ የሰነዘራቸውን የጽሁፉ ይዘቶች ካብራራሁለት በኋላ ነው ። አንዳንድ ምሁራን በአፍ ወለምታ ፣ በአንቱታ እና በዶክትሬት ማዕረግ አለልክ በማናአለብኝነት በመወጣጠር ፣ በጭብጨባ ስካር የሰሩትን ስህተት ለማድበስበስ የሚኳትኑበት መድረክን የመሻት ምጥቀት ለሌላ የስህተት ጥልቀት ሲዳርገን አይተናል ። ከሰሞኑ ለጥቅምት 1, 2018 በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የግዕዝ ቋንቋ በትምህርት ስርአት ውስጥ የሚል የውይይት መድረክ በዶር በድሉ ዋቅጅራና በይኩኑአምላክ መዝገቡ መካከል ሙያዊ ውይይት እንደሚደረግ ስሰማ እውን አባትህ አንተን ወለደ ብለው ሲወቅሱኝ ቅቤ የጠጣሁባቸውና ሃገር ማለት ልጀ ብለው በአሽሙር ሲወቅሱኝ የበገንኩባቸው ዶር ምን ፈልገው ወይም ምን አስፈልገው ይህን መድረክ ፈለጉት ወይም አስፈለጉት ? የግንዛቤ አቅምስ ? አላግባብ ዳግም እንዳይገባብንስ ምን ታስቧል? ግዕዝ ገሎ አፈር እንዳለበሰ በቅብረራ ከሚነገር ድምፅና የግእዝ ጉባኤን ደጋሽ መንዙማን ግብሩን አውራሽ ከሆነው ይኩኑ አምላክ መዝገቡ ጋር እንኳንስ መድረክ ማዘጋጀት ሃሳቡን ማንሳት ቢሆን የስህተት በረከት ማብዛት ነው ብየ አመንኩ ።
30/08/2025
እችን እሷን ወደምድር የቀላቀለች እለት በዋዛ ላልፋት አይቻለኝም ፣ እሷ እኮ ፀዳል ናት ፣ ሳሮን ናት፣ ናርዶስ ናት ፣ ሜሎስ ናት ፣ በቃ ብዙ ብዙ ብዙ ብዙ ሁና ሰሎሜ በቃ እፁብ ተብላ ስሟን እንደግብሯ በቅኔ የለወሱላት ፣ አመል ከክህሎት ፣ ዕውቀት ከዕውቅና ተመሰጥሮ የተጋባላት ፣ በሞረሿ አቤት ባይ የበዛላትን እንሥት ሰሎሜ በቃ እፁብ የተወለደችበት ቀን ነውና ባሞጋግስበት ባሞናሙንበት ብየ ተመኘሁና እሷም አትጨበጥ እኔም ባካና ሁኘ በዚሁ እንኳን ተወለድሽልን ልላት ወደድኩ ። እችን ፈጥኖ ደራሽ እናንተም በሉልኝ ። ሰሎሜየ እንኳንም ተወልደሽ እችን ምድር አጣፈጥሽልን እህታለም ፣ ዘመንሽን ፈፅሞ ይባርክልሽ
መጭውን አመት የሰላም የፍቅር የድሎት አመት ያድርግልን
18/08/2024
ይህ በምስሉ ግራ በኩል የምትመለክቱትን የጎንደሩን አስተዳደር ጽ/ቤት ሕንፃና ሌሎችንም ጎንደርና ደሴ ከተማ ውስጥ ጣልያን ከ1928 ጀምሮ የገነባቸውን የሕንፃ ንድፍ ስራውን የሰራው Gherardo Basio የተሰኝ የፍሎሬንስ ተወላጅ የሆነ ጣሊያናዊ ባለሙያ ሲሆን ፣ ይህ ሰው ጣልያን ግዛት ይዛቸው በነበሩ በርካታ ሃገራት ከሰራቸው ንድፎች ውስጥ በተለየ ሁኔታ የሰራው ተወዳጁን የአልባኒያ ቲራና ቤተመንግስት እንደሆነ ይታመናል ። ይህ በ38 አመቱ በጎልማሳ እድሜው በካንሰር በሽታ ዓለምን የተለየው ባለሙያ ታድያ ጎንደር ላይ ይህን ያሁኑን አስተዳደር ጽ/ቤት ሲነድፍ ቁመናውንና ቅርፁን ያባቶቻችን የአፄ ፋሲል ግምብና የራሥ ቢተዎደድን ግምብ (ራስ ግምብን ) አስመስሎታል።ይህም የሆነ ጥበብ ካባቶቻችን እውቀት እንደዘገነ ያመላክታል።በነገራችን ላይ ብዙ ግዜ የዚህ አይነት የንድፍና ግምባታ ስራ የሚሰሩት በተለምዶ rationalist የሚባል ስብእና አላቸው ተብሎ ይታመናል።
02/01/2023
ፋና 90 በማለዳ ፕሮግራሙ ላይ ቱሪዝምና የጎንደርን ጥምቀት በዓል አስመልክቶ ሲያብራሩ ተጠያቂው ጎንደር ላይ ለጥምቀት በሚመጡ እንግዶች ላይ የክፍያ ዋጋ መጨመርን አስመልክቶ ከንቲባችን እስከማናገር ድረስ ብለው የሰጡት ማብራሪያ ሃሳቡ ምንም ቢሆንም ጉዳዩ ግን በፌደራል ደረጃ ከአየር መንገዳችን ጀምሮ ላሊበላ ፣ አክሱም ፣ ቁልቢ ፣አዋሳ ፣ ግሸን ላይም የሚከሰት እንጅ ጎንደር ላይ ብቻ የተከሰተ አድርጎ የማቅረብ አዝማሚያ አይቸ አወይ የኛው እድል ብያለሁ ። የሆነ ሆኖ ከኛ ከከተማችን ማ/ሰብ ሚጠበቀው ፍፁም ሰላማዊ አየር በመፍጠር በደስታና በፍቅር ማስተናገድ ነው። በየቤታችን እንግዳ እንቀበላለን ይህ ደግሞ ያባቶቻችን ነው ። የንግድ ተቋማት ላይ ግን ሃገር አቀፍ ችግር ነው ። እንዴውም ከተማ አስተዳደራችን ለእድምተኞቹ ከሚጨነቀው አንፃር ሲታይ ከተማችን እየተጠቀመ አይደለም ብየ አምናለሁ
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Website
Address
Addis Ababa
147
