11/04/2026
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ:: መልካም በዓል! ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
07/04/2026
መጭው የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት ማዕድ ማጋራት ተደረገ፡፡
(መጋቢት 29 ቀን 2018፣ ማዕድን ሚኒስቴር) ለማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋዮች የትንሳኤ በዓልን በማስመልከት የማዕድ ማጋራት ተደረገ፡፡
የትንሳኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለማዕድን ሚኒስቴር፣ ለኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ኢንስቲትዩት እና ለማዕድን ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ ሠራተኞች የማዕድ ማጋራት መርሐግብር ተካሂዷል፡፡
ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
28/03/2026
የኦፓል ማዕድን የግብይት አፈጻጸም ተገመገመ።
(መጋቢት 19 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር የኦፓል የገበያ ግንባታ አፈጻጸም ያለበትን ደረጃ ከባለድርሻ አካላት ጋር ገመገመ፡፡
ግምገማው በከበሩ ማእድናት ዘርፍ ግብይትን በማዘመን ሀገር ማግኘት ያለባትን የውጪ ምንዛሪ ለማሳደግ እና የአምራቾችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ፡፡ በውይይቱ የጌጣጌጥ ግብይትን ማዘመን አማራጭ የሌለው መሆኑ አጽንኦት ተሰጥቷል።
በግምገማው ላይ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የአማራ ክልል የማእድን ሀብት ልማት ቢሮና የወሎ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ተገኝተዋል፡፡ግብይቱን ለማዘመን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልፀው በሚቀጥሉት ጥቂት ወራት ውስጥ የሚመለከታቸውን ቀሪ ስራዎችን በማጠናቀቅ ግብይቱን ለማስጀመር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል። ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
27/03/2026
ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአዘርባጃን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩሲፋ አብዱላየቭ ጋር ተወያዩ፡፡
(መጋቢት 18 ቀን 2018 ማዕድን ሚኒስቴር) ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ ከአዘርባጃን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዩሲፋ አብዱላየቭ ጋር በማዕድን ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች እና የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ውይይት አድርገዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ.ር) የተመራ ልኡክ ባለፈው በአዘርባጃን ባካሄደው የስራ ጉብኝት ሁለቱ ሃገራት በኢኮኖሚ እና በተለያዩ መስኮች በጋራ ለመስራት መምከራቸው እና አቅጣጫዎች መቀመጣቸው ይታወቃል፡፡
የዛሬው ውይይትም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በማዕድን ዘርፉ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
27/03/2026
ባለፉት 8 ወራት ከማዕድን ዘርፉ ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡
(መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም) የማዕድን ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት ባለፉት 8 ወራት በማዕድን ዘርፍ የተከናወኑ አፈጻጸሞችን በጋራ ገምግመዋል፡፡
ባለፉት 8 ወራት ከወርቅ፣ከጌጣጌጥ ማዕድናት እና ኢንዱስትሪ ማዕድናት ከ3.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል፡፡ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በመጠን 27 በመቶ በገቢ ደግሞ 92 በመቶ ብልጫ ተመዝግቧል፡፡
በበጀት አመቱ የተለያዩ የማዕድን ፕሮጀክቶች ተመርቀው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በወጭ ንግድ እና በተኪ ምርቶች ላይም የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል፡፡በቀጣይ ቀሪ ወራትም በሂደት ላይ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች ወደ ስራ እንዲገቡ አስፈላጊው ድጋፍ የሚደረግ ሲሆን እየተመዘገቡ ያሉትን ውጤቶች ለማስቀጠል በሚቻልባቸው የትኩረት መስኮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ለበለጠ መረጃ ማህበራዊ ድህረ-ገጾቻችን በመከተል ይወዳጁን
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website ፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
25/03/2026
የተቋሙን የተሻለ አሰራር ለማረጋገጥ እየተሰሩ ያሉ የፕሮጀት ስራዎች ተገመገሙ፡፡
(መጋቢት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የማዕድን ሚኒስቴር ተቋሙን የበለጠ ለማዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር እየተሰሩ ያሉ የፕሮጀክት ስራዎችን ገምግሟል፡፡
የማዕድን ሚኒስቴር በዲጂታላይዜሽን፣ በፖሊሲ እና በህግ አገልግሎት ያሉ የተቋሙን አሰራሮች ለማዘመን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር የፕሮጀክት ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ የተጀመሩት የፕሮጀክት ስራዎች ተቋሙን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እና ለማዘምን የሚያስችሉ ናቸው፡፡
ፕሮጀክቶቹን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ በተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ወደተሻለ አሰራር ለማሸጋገር የሚያስችል መሆኑ በግምገማው ተነስቷል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]
24/03/2026
ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡
(መጋቢት 15 ቀን 2018) ኢንጅነር ሃብታሙ ተገኘ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር ተወያዩ፡፡ ውይይቱ በማዕድን ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት እድሎችን እና የትብብር መስኮች ዙሪያ ያተኮረ ነው፡፡ ይህም በማዕድን ዘርፍ የሚገኙ አዳዲስ እድሎችን ለመጠቀም አስፈላጊ መሠረት እንደሚፈጥር ተጠቁሟል።
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]
23/03/2026
የማዕድን ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑ ተገለጸ ፡፡
(መጋቢት 14 ቀን 2018 ዓ.ም ማዕድን ሚኒስቴር) የኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የባይጃ ሴራሚክ ፋብሪካን የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡ የፋብሪካው ግንባታ ሂደት በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱ የስራ ባህልን የቀየረ መሆኑን የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተናግረዋል፡፡
በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ ኢንዱስትሪ እና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት የባይጃ ሴራሚክስ የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡ ፋብሪካው የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ወደ ምርት ለመግባት በሚችልበት ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የፋብሪካው መገንባት ከውጭ ሲገባ የነበረውን ምርት ሙሉ በሙሉ በሃገር ውስጥ ለመተካት ከሚያስችሉ ፕሮጅክቶች አንዱ ነው፡፡ የሃገርን ሃብት ለሃገር ለመጠቀም የሚያስችል ፋብሪካ በመሆኑ አባላቱ ድጋፋቸውን እንደሚያደርጉም ገልጸዋል፡፡
የማዕድን እና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሰቢ የተከበሩ ፍቃዱ መንግስቱ(ዶ.ር) መንግስት ለማዕድን ከፍተኛ ትኩረት የሰጠበት መሆኑን ገልጸው ሚኒስር መስሪያቤቱም በተኪ ምርቶች ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ በድጋፋቸው መመልከታቸውን ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
Twitter፦ https://twitter.com/MinistryofMine_
Website፦ www.mom.gov.et
Facebook፡- https://www.facebook.com/MinesandPetroleum/
Telegram: - https://t.me/+-aNetmkG-WY2YWM8
Email: [email protected]
19/03/2026
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!!