Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ

Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ

Share

የአቀስታ ከተማ አስተዳደር በደቡብ ወሎ ውስጥ ከሚገኙ ከተማ አስተዳደሮች አንዷ ስትሆን ከደሴ 100 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች።

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 18/07/2026

አቀስታ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ለ25ኛ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመደበኛና በማታ መርሀ ግብር ያሰለጠናቸውን 308 ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ አስመረቀ።

ሀምሌ 11/2018 ዓ.ም

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 17/07/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ
የለጋምቦ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት እና የአቀስታ ጤና ጣቢያ ሰራተኞች በአቀስታ ከተማ የጽዳት ዘመቻ አደረጉ::

ሃምሌ 10/2018

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 14/07/2026

የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት 5ኛ አመት የ2018 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት 18ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ።
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ጽ/ቤት 5ኛ አመት የ2018 ዓ.ም 4ኛ ሩብ ዓመት 18ኛ መደበኛ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት እያካሄደ ነዉ።
በጉባኤዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ም/ቤት ፅ/ቤት ዋና አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ ከበዴ ሁሴን ጽ/ቤቶች አሁን ያለበትን ወቅታዊ ሁኔታ በመረዳት እና ወቅቱን ያገናዘበ ሀሳቦችን እና ዉሳኔወችን በመጋራት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ትልቅ ድርሻ አለብን ብለዋል።በመሆኑም በ2018 በ4ኛ ሩብ አመት የሴክተሮች እቅድ አፈፃፀም በትኩረት ይዞ በመገምገም የወከለንን ህዝባችንን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል አለብን ሲሉ ሀሳባቸዉን ገልፀዋል።

የአቀስታ ከተማ አመታዊ የጽ/ቤቶችን የስራ አፈጻጸም፣የፍርድ ቤት ሪፖርት እና የአቀስታ ከተማ አስተዳደር የቋሚ ኮሚቴ ሪፖርት ቀርቦ ምክር ቤቱ ሰፊ ዉይይት አድርጎበታል።

የአስፈፃሚዉን ሪፖርት ያቀረቡት የልማት እቅድ ክትትልና ግምገማ ተወካይ ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ ሀድሴ ናቸዉ።

7/11/2018 ዓ.ም


Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 14/07/2026

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ" መሪ ቃል በአቀስታ ከተማ አስተዳደር የአቀስታ ጤና ጣቢያ የዜጎች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤት ለቤት ግንዛቤ ፈጠራ ህክምና ልየታ እንደቀጠለ ነው።

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 12/07/2026

"በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"

በአቀስታ ከተማ "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ሀሣብ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በከተማው ውስጥ ያሉ በጎ ፈቃደኞች የጽዳት ዘመቻ አካሂደዋል።

11/07/2026

አቀስታ ከተማ

08/07/2026

"የዛሬ 20 እና 30 ዓመት አሁን ያለው መንግሥት፣ አሁን እዚህ ፊትለፊት የምታይዋቸው ሰዎች ከወረዱ በኋላ ተመልሰው መጥተው ኢትዮጵያን እንምራ ካሉ ኢትዮጵያ ሞታለች ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ለዘመኑ፣ ለወቅቱ የሚመጥን መሪ መፍጠር ካልቻለች ሰዎች እየወጡ እየወረዱ የሚመላለሱባት ከሆነ በጥቅሉ ሞታለች ማለት ነው።

ይሄ የሚያኮራ ነገር አይደለም፤ የሚያሳፍር ነገር ነው።

50 ዓመት ፓርቲ መርተህ ፓርቲ የሚተኩ ሰዎች ካልፈጠርክ ሌላ 1000 ዓመት ቢሰጥህም አትፈጥርም ማለት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 08/07/2026

‎በአቀስታ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ተጀመረ።

‎በደቡብ ወሎ ዞን በአቀስታ ከተማ አስተዳደር የዜጎች የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር የከተማው አመራሮች በተገኙበት በአቀስታ ከተማ በይፋ አስጀምረዋል።
በአቀስታ ከተማ የ10 አቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት በአድስ ለመገንባት እንዲሁም 20 ቤቶችን እድሳት ለማድረግ የግንባታ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ተካሂዷል።
በፕሮግራሙም ሶስት (3)ቤት በጥገና 60 ቆርቆሮ እና አንድ(1) ቤት በአድስ 40 ቆርቆሮ ድጋፍ በማድረግ ተጀምሯል

መርሃ ግብሩን በይፋ ያስጀመሩት የአቀስታ ከተማ አስተዳደ ከንቲባ አቶ ብርሀኑ ሺመልስ፣ የዜጎች የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ የበርካታ ዜጎችን ችግር የሚቀርፍ በየአመቱ የሚሰራ መልካም ተግባር መሆኑን ገልፅዋል

‎በከተማው በዘንድሮው የክረምት ወራት በሚከናወነው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በ7ቱም ቀበሌዎች የሚሳተፉና አገልግሎት የሚሰጡ መሆኑን ተናግረው ተግባሩ ውጤታማ እንዲህን በጎፈቃደኞች ፣ባለሀብቶችና መልካም አሳቢዎች በእውቀታቸው፣ በገንዘባቸውና በጉልበታቸው እገዛ እንድያደርጉ አሳስበዋል።

‎የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የህሊና እርካታን የሚፈጥር ብሎም በርካታ ችግሮችን የሚፈታ በመሆኑ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ሁሉም ዜጋ ተሳታፊ ሊሆን ይገባል ሲሉም ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል

Photos from Akesta City Prosperty Party /የአቀስታ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ's post 05/07/2026

የአቀስታ ከተማ አስተዳደር የጠቅላይ ሚንስተሩን የሌማት ትሩፋት ኢንሸቲቭ እውን ለማድረግ ለ147 እናቶች እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በመግዛት መስጠቱ ተገለጸ።
የአቀስታ ከተማ አስተዳደር ለ147 እናቶች ለእያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ዶሮዎችን ማከፋፈል ችሏል። ከተማ አስተዳደሩ በብልጽግና ፓርቲ የጠቅላይ ሚንስተሩን የሌማት ትሩፋት እውን ለማድረግ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ አጠቃላይ ከ800 በላይ ዶሮዎችን ገዝቶ በቀበሌዎች ለተመለመሉ እናቶች ማስረከብ ችሏል።

Want your business to be the top-listed Government Service in Akesta?

Click here to claim your Sponsored Listing.

Location

Address


Akesta