Machakel Woreda Government Communication Affairs Office

Call Directions Website Contact the organization

Machakel Woreda Government  Communication Affairs Office ራዕይ ፦
በመረጀ የበለጸገ ሁለገብ ተሳትፎ የሚያደርግና በጋራ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ መግባባት የፈጠረ ህዝብ መገንባት!!
የማቻክል ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ፌስቡክ ገፅ

 #ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ የመጣነውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።***,******************የምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ፖሊስ...
04/11/2026

#ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባበሰ የመጣነውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል በቅንጅት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።
***,******************
የምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ውድ በሆነውን የሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የትራፊክ አደጋን ለመከላከል ህግ የማስከበር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ።

የከተማ አስተዳድሩ የፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኢንስፔክተር በ ሃይሉ ታከለ ለኮሙንኬሽን በሰጡት መግለጫ ውድ በሆነው የሰው ልጅ ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት የሚያደርሰውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል ህግ- የማስከር ስራ እየተሰራ መሆኑን በመግለጽ በእንደ ከተማ አስተዳድር በባጃጆች ላይ የሚስተዋለውን የትራፊክ ህግ ጥሰት በመከላከል ጤናማ የትራንስፖርት ስርዓት ለመዘርጋት የማህበር አባል ባልሆኑ ፣ከመርሃ ግብር ውጭ በሆኑ እንዲሁም ከታሪፍ በላይ በማስከፈል ማህበረሰቡን በሚያማርሩ ባጃጆች ላይ ህግ የማስከበር ስራ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢንስፔክተር በሃይሉ አያይዘው በከተማ አስተዳድሩ የትራንሰ አገልግሎት የሚሰጡ የባጃጅ አሽከርካሪዎችና ባለ ንብረቶች የማህበር አባል በመሆን፣በተሰጣቸው መርሃ- ግብር መሰረት አገልግሎት ከመስጠት፣ህጋዊ ታልጋ በመለጠፍ እንዲሰጡ ለማድረግ በሚደረገው ህግ - የማስከበር ስራ ማህበረሰቡ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት 5ተኛውን የስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ አካሄደ።********​በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ባህ...
04/11/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት 5ተኛውን የስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ አካሄደ።
********
​በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ባህል ቱሪዝም ስፖርት ጽ/ቤት 5ተኛው የስፖርት ምክር ቤት ጉባኤውን በደመቀ ሁኔታ አካሄዷል።

በመድረኩ ላይ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮች፣ የቀበሌ አስተዳዳሪዎች ፣ባለድርሻ አካላት እና የስፖርት ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን፣ የጉባኤው ዋና ዓላማ የከተማዋን የስፖርት እንቅስቃሴዎች አፈፃፀም መገምገም እና የወደፊት አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

​በጉባኤው መክፈቻ ላይ የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ተወካይ ከንቲባ እና የከተማ አስተዳደሩ የስፖርት ም/ቤት ሰብሳቢ አቶ ይሁን ጥላሁን ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከንቲባው በንግግራቸው ስፖርት ለሰላም፣ ለልማት እና ለቱሪዝም ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን አንስተው፣ በተለይም ማህበራዊ ትስስርንና የእርስ በርስ መስተጋብርን ለማጠናከር ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

​በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዶ የጎሉ ነጥቦች የተለዩ ሲሆን፣ ለቀጣዩ ዓመት የተዘጋጀው የ2019 ዓ/ም ዕቅድ ለተሳታፊዎች ትውውቅ ተደርጓል።

የተከናወኑ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በቀጣይ በከተማዋ ስፖርትን ከማስፋፋት ባሻገር ሰላምና ልማትን ለማፋጠን በተቀናጀ መልኩ ለመስራት አቅጣጫዎች ተሰጥተው መድረኩ ተጠናቋል።

በመጨረሻም ተቋሙን ስደግፉ እና ስያስተባብሩ ለነበሩ የስፖርት ኮሚቲዋችና የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር የመንግስት ተቋማት የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።
መረጃው የአማኑኤል የከተማ አስተዳድር ፖርቲ ነው ።

"የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅዱን ወደ ተጨባጭ ለውጥ ለመቀየር በትብብር  መስራት ይገባል።" -  አቶ አበበ ጓዱ‎****‎ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የ2019  በጀት ዓመት የአሸ...
02/11/2026

"የአሻጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅዱን ወደ ተጨባጭ ለውጥ ለመቀየር በትብብር መስራት ይገባል።" - አቶ አበበ ጓዱ
‎****
‎ የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር የ2019 በጀት ዓመት የአሸጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅድ የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የመንግሥት እና የፓርቲ ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በደብረ ማርቆስ ከተማ እያካሄደ ነው ።
‎
‎በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የምስራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አበበ ጓዱ የአሸጋሪ እድገትና ዘላቂ ልማት እቅዱን ወደ ተጨባጭ ለውጥ ለመቀየር በትብብር እና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

ባለፉት ሦስት ወራት የተፈፀሙ ተግባራትን በቁጥር፣ በጥራትና በጥልቀት በመገምገም፣ የተገኙ ውጤቶችን ለማወቅና ከዕቅድ በታች የሆኑ ተግባራትንና ያጋጠሙ ተግዳሮችን በግልፅ በለመለየትና ለቀጣይ ስራ አቅጣጫ ለመስጠት ዓላማ ተደርጎ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ምክትል አስተዳዳሪው ገልፀዋል።

አቶ አበበ አክለውም በበጀት ዓመቱ የተያዘው ዕቅድ ከተፈጸመው ስራ ጋር ምን ያህል እንደተጣጣመና የተገኙ ውጤቶችም በህዝብ ኑሮ መሻሻል እና በልማት ስራዎች ላይ ያመጣው ለውጥ በጥልቀት ይገመገማል ብለዋል።
‎
‎በሩብ ዓመቱ የታዩ ውጤታማ አሠራሮችን የበለጠ ማስፋት በሚቻልበትና ክፍተት በታየባቸው አፈጻጸሞችን ማሻሻል በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር የሚደረግበት መድረክ መሆኑንም አቶ አበበ ጨምረው ተናግረዋል።
‎
‎ለተግባራት ውጤታማነትም አመራሩና ባለሙያው በመተጋገዝና በመደጋገፍ፣ ችግርን ቀድሞ በመለየት ለቀጣይ ጊዜያት ውጤት ማምጣት ተገቢ መሆኑን አቶ አበበ አንስተዋል።
‎
በውይይት መድረኩ ላይ የስራ ኀላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላትና የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፈውበታል።

የምስራቅ ጎጃም ዞን የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን

 #የመኖ አቅርቦትን ማዘመን ለእንስሳት ምርታማነት ማደግና ለግብርና ዘርፉ ሽግግር ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለዉ የማቻክል ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ገለፀ...
02/11/2026

#የመኖ አቅርቦትን ማዘመን ለእንስሳት ምርታማነት ማደግና ለግብርና ዘርፉ ሽግግር ከፍተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለዉ የማቻክል ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ገለፀ፡፡
*********************
በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት በአማኑኤል ዙርያ ቀበሌ ከእርባታ ዘርፉ ማሻሻል መንገዶች መካከል አንዱ በሆነዉ በመኖ ዝግጅት ዙርያ የገበሬ በዓል አካሂዷል፡፡

የማቻክል ወረዳ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ገደፋዉ አድማሱ የገበሬ በዓሉ ዓላማ ስኬታማ አርሶ አደሮች የእንስሳት አመጋገብ፣ አያያዝና ዝርያ ማሻሻል ላይ ያላቸውን ምርጥ ተሞክሮ ለሌሎች ለማካፈል ያለመ መሆኑን ጠቅሰዉ በመኖ ዝግጅት ዙርያ የሚደረጉ የገበሬ በዓላት ለእንስሳት ምርታማነት ማደግና ለግብርና ዘርፉ ሽግግር ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኖሎጂያዊ ፋይዳ አላቸው ብለዋል፡፡

አቶ ገደፋዉ አያይዘዉም የእንስሳት መኖ ከመኖነት ባለፈ በምግብ ራስን ለመቻልና የተሸሻለ የመኖ እፅዋት ምርትን ለማስፋፋት በእንስሳት ልማት ዘርፍ ውስጥ ወቅቱ የሚጠይቀው ወሳኝ ምዕራፍ ነው ብለዋል፡፡

በበዓሉ ላይ የተገኙት የአማኑኤል ከተማ አስተዳድር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ ሽታዉ የሻነህ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለመጨመር የገበሬ በዓል ያለው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዉ አርሶ አደሮች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችንና ምርጥ ተሞክሮዎችን እንዲቀስሙ በማድረግ የሃገርን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትልቅ ሚና አለዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ሌላዉ በበዓሉ ላይ የተገኙት የማቻክል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አንዷለም እናዉጋዉ የተሸሻለ የመኖ እፅዋት ጥራትን በማስጠበቅ የምግብ ዋስትናንና የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንደሚቻል ገልፀዉ የእንስሳት ሀብት ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የወተትና የሥጋ ምርትን ጥራት ለመጨመር እንዲሁም የአካባቢን የመኖ አቅርቦት ዘላቂ ለማድረግ የተሻሻሉ የመኖ ዝርያዎችን መጠቀም ወሳኝ ሚና አለዉ ብለዋል፡፡

 #ህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል  የህብረተሰቡ ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ********************በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል  ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት በከተ...
01/11/2026

#ህግ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴን ለመከላከል የህብረተሰቡ ድርሻ ወሳኝ መሆኑ ተገለጸ
********************
በምስራቅ ጎጃም ዞን የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት በከተማው ውስጥ በድብቅ ሲዘዋወር የነበረ 202 ሊትር ህገወጥ ቤንዚን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለጸ።

ቤንዚኑ በከተማው ውስጥ በህገወጥ መንገድ ለማዘዋወርና ለመሸጥ በሆቴሎች እና በመኖሪያ ቤቶች በመደበቅ ላይ እንደነበር የተገኘ ሲሆን፣ የፖሊስ ጽህፈት ቤቱ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባደረገው ክትትልና ቁጥጥር 202 ሊትር ቤንዚን መያዝ ችሏል።

አያይዘው የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት ኢኒስፔክተር በሀይሉ ታገለ እንደገለፁት ይህ እርምጃ በከተማው ውስጥ የህገወጥ ንግድን ለመከላከል፣ የነዳጅ ምርት ህጋዊ የስርጭት ሥርዓትን ለመከላከል፣ እንዲሁም ህገወጥ የነዳጅ ዝውውር ሊያስከትል የሚችለውን የደህንነትና የእሳት አደጋ ስጋት ለመቀነስ የሚያግዝ እንደሆነ ገልጸዋል።

የአማኑኤል ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት ህብረተሰቡ ከህገወጥ የነዳጅ ዝውውርና ንግድ ጋር በተያያዘ የሚያውቀውን መረጃ ለሚመለከተው የጸጥታ አካል በማሳወቅ የህግ ማስከበር ሥራውን እንዲደግፍ ጥሪ አቅርቧል።

''ህግን በማስከበር ሰላምንና ደህንነትን እናስጠብቅ'' መረጃውየአማኑኤል ከተማ አስተዳድር

በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ  ከዝበብ ታዳጊ ከተማ ወጣቶች ጋር  በወቅታዊ ሰላምና ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።‎‎ ውይይቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣የትምህርት ጉዳይ እና የመስኖ...
01/11/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ ከዝበብ ታዳጊ ከተማ ወጣቶች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
‎
‎ ውይይቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣የትምህርት ጉዳይ እና የመስኖ ልማት ስራዎችእንዲሁም ህገ- ወጥ የመሬት ወረራ ላይ ያተኮረ ሲሆን በመገዳደል የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን በመገንዘብ መንግስት ችግሩን ከታጣቂዎች ጋር በንግግር እንዲፈታና ታጣቂዎችም ለህዝብ የሚያስቡ ከሆነ ግጭቱን በንግግር ለመፍታት ይስሩ ብለዋል።
‎

በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ ቀረር ቀበሌእና በዝበብ ታዳጊ ከተማ ነዋሪዎች ጋር  በወቅታዊ ሰላምና ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።‎‎ ውይይቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣የትምህርት ጉ...
01/11/2026

በምስራቅ ጎጃም ዞን በማቻክል ወረዳ ቀረር ቀበሌእና በዝበብ ታዳጊ ከተማ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ሰላምና ልማት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።
‎
‎ ውይይቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ፣የትምህርት ጉዳይ እና የመስኖ ልማት ስራዎችእንዲሁም ህገ- ወጥ የመሬት ወረራ ላይ ያተኮረ ሲሆን በመገዳደል የሚመጣ ለውጥ አለመኖሩን በመገንዘብ መንግስት ችግሩን ከታጣቂዎች ጋር በንግግር እንዲፈታና ታጣቂዎችም ለህዝብ የሚያስቡ ከሆነ ግጭቱን በንግግር ለመፍታት ይስሩ ብለዋል።
‎

 #በ2019 በጀት ዓመት ከ72 ሽህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡**********************በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ...
31/10/2026

#በ2019 በጀት ዓመት ከ72 ሽህ በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የፋይዳ መታወቂያ ባለቤት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ፡፡
**********************
በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ መሬት ፅህፈት ቤት እንደ ወረዳ ማህበረሰቡን የፋይዳ መታወቂያ
ባለቤት ከማድረግ አኳያ ያለዉን እንቅስቃሴ በተመለከተ ከሚመለከታቸዉ አጋር አካላት ጋር ዉይይት አካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ የዉይይቱ ሰነድ ያቀረቡት የማቻክል ወረዳ መሬት ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አበባዉ ብንቆይ እንደ ወረዳ በተያዘዉ በጀት ዓመት ከ5 ዓመት እድሜ ጀምሮ 72 ሽህ 9 መቶ 30 የማህበረሰብ ክፍሎችን የፋይዳ መታቂያ ባለቤት ለማድረግ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዉ ባለፉት ወራት 26 ሽህ 5 መቶ 15 የህብረተሰብ ከፍሎች የድጅታል መታወቂያ እንዲያወጡ መደረጉን ተናግረዋል፡፡

በዉይይቱ ላይ የተገኙት የማቻክል ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጅት ዘርፍ ሀላፊ ወይዘሮ ከተማ ይስማዉ ፋይዳ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ግለሰቦች ማንነታቸውን እንዲያረጋግጡ የሚያስችልና ለአገልግሎት አቅራቢዎች ታማኝና ፈጣን የሙሉ ጊዜ ዲጂታል ማረጋገጫ በመሆን የሚያገለግል የመታወቂያ ሥርዓት መሆኑን ገልፀዉ ባላፈዉ ዓመት እንደወረዳ የነበረዉን ክፍተት በማረምና ቅንጅታዊ አሰራርን በማጠናከር ዉጤታማ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ሌላዉ በዉይይቱ ላይ የተገኙት የማቻክል ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለኸኝ መኮነን ድጅታል መታወቂያ አንድ ሰዉ አንድ ነዉ በሚል ንቅናቄ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረ የመንግስት ኢንሸተቭ መሆኑን አንስተዉ ሀገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ብክነትን ለማስቀረትና ህገወጥ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እንደሚረዳ ገልፀዉ ለተፈጻሚነቱ ሁሉም ተቋማት በባለቤትነት ይዘዉ በትኩረት መስራት አለባቸዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የማቻክል ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አንዷለም እናዉጋዉ የፋይዳ መታወቂያ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለዉ አሰራር ለመዘርጋትና ከገጠር መሬት ጋር በተያያዘ የሚፈጠሩ የመልካም አስተዳድር ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን ለማስቀረት ያለዉ ጠቀሜታ የጎላ ስለሆነ እንደ ወረዳ የተያዘዉን እቅድ ለማሳካት መረባረብ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ለሁለንተናዊ ብልጽግና - ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያለው አመራርየኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ቁሳዊና መንፈሳዊ...
31/10/2026

ለሁለንተናዊ ብልጽግና - ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያለው አመራር

የኢትዮጵያን ሥልጣኔ ለመገንባት እንችል ዘንድ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ አለብን፡፡ ሁለንተናዊ ብልጽግና ማለት ቁሳዊና መንፈሳዊ ብልጽግና፣ ባህላዊና ሞራላዊ ብልጽግና የተሸመኑበት ብልጽግና ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ አመራሩ ሁለንተናዊ ዝግጁነት ያስፈልገዋል፡፡ በአካል የዳበረ፣ በሞራል የጠነከረ፣ በዕውቀት የተሳለ፣ በጥበብ የበሰለ እንዲሆን ይጠበቅበታል፡፡ በተለይም በሀገር ፍቅር ስሜትና በሕዝብ ተቆርቋሪነት መንፈስ ግዴታዎቹን እንዲወጣ የሀገር አደራዋ ጥብቅ ነው፡፡

ወታደራዊ ሳይንስ፣ ልምድ እና ሕይወት የሰውን ልጅ ዓላማና ሰብእና በመቅረጽ ረገድ ተወዳዳሪ የለውም፡፡ የሰው ልጅ በአካልም፣ በመንፈስም፣ በሥነ ምግባርም፣ በአፈጻጸምም ዲሲፕሊናዊ እንዲሆን በማስቻል ለዘመናት ትውልድን ሲያዘጋጅ ኖሯል፡፡ ውጫዊና ውስጣዊ ማንነቱ የሠመሩለት ሰብእና በመቅረጽም ታላላቅ መሪዎችን አፍርቷል፡፡ ግዳጅን በብቃት መፈጸም፣ በዐርበኝነት መንፈስ አገልግሎት መስጠት፤ የሥራ ዲሲፕሊንን መቅረጽ፤ የጋራ ግብን በጋራ ማሳካት፤ ወትሮ ዝግጁነት፤ በተዋረድ አመራርን ማፍራት፤ ኃላፊነትና ተጠያቂነት፤ ከላይ እስከ ታች በመናበብ ዓላማን መፈጸም፣ እና የመሳሰሉት ከወታደራዊ ሳይንስና ልምድ ሊወሰዱ የሚችሉ ዕሴቶች ናቸው፡፡

የመደመር መንግሥት አመራሮች በሁርሶ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ሥልጠና በመውሰድ ላይ ናቸው፡፡ የመደመር ሥልጣኔ ታላቁ ስትራቴጂን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ ከወታደራዊ ሳይንስና ሕይወት የምንቀስማቸው ዕውቀቶች፣ ክሂሎቶች እና ልምዶች አሉን፡፡ በተለይም ደግሞ በአንድ ሰዋሰው መግባባት፣ ሥነ ምኅዳርን በሚገባ መጠቀም፤ በተከታታይ ሕዝብን ለዓላማና ለተግባር ማነጽ፤ ለሕዝብ የገባነውን ቃል በሚገባ አከናውኖ መጨረስ፤ ከታች እስከ ላይ ያለውን መዋቅር ለሀገራዊ ዓላማ ማሣለጥ፤ ሀገርን በባለ አደራነት መምራት፤ ለምንምና ለማንም የማትበገር ጽኑ ሀገር መገንባት፤ ተተኪ ትውልድን ማፍራት እና የሀገርን ደኅንነት ምንጊዜም ማረጋገጥ የሚሉትን የስትራቴጂውን ሐሳቦች በተገቢው መንገድ ለመረዳትም ሆነ ለማስፈጸም ወታደራዊ ሥልጠናው የማይናቅ ሚና ይጫወታል፡፡

ወታደሮች ዒላማ፤ ሲቪሎች ደግሞ ዓላማ አላቸው፡፡ የሁለቱም ግብ ድልን ማስመዝገብ ነው፡፡ ሁለቱን ዲሲፕሊኖች በማገናዘብ ዒላማውንም የሚመታ፤ ዓላማውንም የሚያሳካ ትውልድ እንፈጥራለን፡፡

Address

Amanuel, East Gojjam
Amanu'el

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Machakel Woreda Government Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Machakel Woreda Government Communication Affairs Office:

Shortcuts

Share