Tilahun Kebede

Call Directions Website Contact the organization

Tilahun Kebede Addis Ababa city Adminstration with Deputy Mayor Rank, BH for Public service https://t.me/tilahunkebede
(4)

05/10/2026
አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮ እና ቀሬዎች ‘ጮቆርሳ’ (ለምለም ሣር) እና አደይ አበባ ይዘው “መሬ ሆ…!” እያሉ በታላቅ እልልታ እና ምስጋና ያለፈውን ዓመት በሰላም አሳልፈህ፣ ዘንድ...
04/10/2026

አባ ገዳዎች እና ሃደ ሲንቄዎች፣ ቄሮ እና ቀሬዎች ‘ጮቆርሳ’ (ለምለም ሣር) እና አደይ አበባ ይዘው “መሬ ሆ…!” እያሉ በታላቅ እልልታ እና ምስጋና ያለፈውን ዓመት በሰላም አሳልፈህ፣ ዘንድሮ ያደረስከን ፈጣሪ የምያመሰግኑበት የኢሬቻ በዓል በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን !

30/09/2026

ከዚጊቲ ባቆሌ ሻለ እስከ አዲስአበባ በህይወቴ ጉዞ፣ በሞገስና በስኬት ያሻገርከኝ አምላክ ምስጋና ይድረስህ።

ለባለፉት አስርት ዓመታት ከደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል እና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ስኬታማ ጉዞ ሂደት ከጎኔ ለነበራችሁ፣ ስደክም ብርታት፣ ስጠንክር ሚስጢር እና አቅም የሆናችሁ መላዉ የክልላችን ህዝቦች ላቅ ያለ ምስጋና ይድረሳችሁ።

ዛሬ ፓርቲዬ ብልጽግና የበርካታ አለም አገራት የዲፕሎማቶች መቀመጫ፣ የአፍርካ እና የመላዉ ኢትዮጵያውያን መድና የሆነችዉ አዲስአበባ ከተማ አስተዳደር አመራር ፑል ተቀላቅዬ የአመራር አስተዋጽኦዬን እንዳበርከት ዕድል ስላገኘሁና የከተማዉ ምክርቤትም በታሪካዊ ጉባኤ ለሰጠኝ ታላቅ አደራ ምስጋናዬ የላቀ ነዉ።

የሠላም የመቻቻል እና የብልጽግና ተምሳሌቷ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከደረሰችበት ከፍታ ሳትወርድ እንድትቀጥል የሁላችንም ድርሻ የላቀ ነዉና የአመራር መተካካት የዱላ ቅብብሎሽ ዉድድር ዓይነት በመሆኑ ከተከታዩ አመራር ጋር በአብሮነት፣ በመደጋገፍና በመተሳሰብ በቅንነትና በትጋት ወደ ላቀ ከፍታ እንድትጓዙ አደራዬን አስተላልፋለሁ።

መልካም የሥራ ዘመን ለሁላችን!

29/09/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼኽ መሐሙድን ዛሬ ጠዋት በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተቀብለዋል።

Prime Minister Abiy Ahmed welcomes Somali President Sheikh Hassan Mohamud at Bole International Airport this morning.

27/09/2026

በባቦ ደን ጥበቃ ሥርዓት ተንከባክበዉ ባቆዩት አግሮፎረስትሪ እየለማ ያለዉ ባለ ልዩ ጣዕም የአረንጓዴ ወርቅ የይርጋጨፌ ቡና ባለቤት፣ ጥብቅ ደኑን ከሌሎች ቅርሶች ጋር ለአለም ህዝብ ያስታወቀው፣ በቱሪዝም ታይቶ የማይጠገቡ የመስህቦችና የመዳረሻዎች መገኛ፣ በባሌ ባህላዊ አስተዳደር ስርዓት በአባ ገዳ እየተመራ የህዝቡን አንድነት ጠብቀዉ ለሌሎች የመቻቻል ምሳሌ የሆነው ጌደኦ ዞን።

በሀገራችን በደቡብ ምስራቅ ንግድ ቀጠና መስመር የወጪ እና ገቢ ምርቶች መተላለፊያ መንገድና ማዕከል፣ በኮሪደር ልማት የትናንት ገጽታዋን እያደሰች ያለችዉ፤ የተፈጥሮ ኃብት፣ የአገርበቀል ዕዉቀት እና የህዝቡ ባህል ከዘመናዊ ኪነ ህንፃ ጥበብና አመራር የተሰናሰኑ፣ የብልጽግና ተምሳሌቷ ዲላ ከተማ።

ይህንን ተግባር ባለቤት በመሆን የፈፀማችሁና የድርሻችሁን የተወጣችሁ መላዉ ህብረተሰብ፣ ያስተባበራችሁና የመራችሁ አመራሮች፣ ሙያዊ ድጋፋችሁ ያለስስት የለገሳችሁ ባለሙያዎች ሃሳባችሁ ወደ ተግባር ተቀይሮ ዉጤት ማየት መጀመራችንና ለቀጣይ ለበለጠ ስኬት መነቃቃትን ስለፈጠራችሁ ሁሌም ትመሰገናላችሁ።

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰንመስቀል የመሻገር፤ የብሩህ ተስፋና የብርሃን ምልክት ነው፡፡ ብርሃነ መስቀሉ ከጨለማ ወደ ...
26/09/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፤ እንኳን ለደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ! አደረሰን

መስቀል የመሻገር፤ የብሩህ ተስፋና የብርሃን ምልክት ነው፡፡ ብርሃነ መስቀሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገርን፣ ከፈተና ወደ ድል መጓዝን ማብሰሪያ፤ ደመራው ፈታኙን ወቅት በህብረት የመሻገራችን ብስራት፤ የመጪው የብሩህ ተስፋ ስንቅ ምልክት ነው፡፡

በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት እና የመተሳሰብ እንዲሆን ምኞቴን ለመግለጽ እወዳለሁ።

መልካም በዓል!

Address

Hawassa
Arba Minch'
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Tilahun Kebede posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Tilahun Kebede:

Shortcuts

Share