12/10/2026
በጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ምክንያት በማድረግ የውይይት መድረክ ተካሄደ
አርባምንጭ፣ ጥቅምት 2/2019 ዓ.ም (የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ)
"ሰንደቅ ዓላማችን ለብሔራዊ መግባባትና ለአንድነታችን" በሚል መሪ ቃል በሀገራችን ለ19ኛ ጊዜ የሚከበረውን የሰንደቅ ዓላማ ቀን ምክንያት በማድረግ በጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ የሰንደቅ ዓላማን ምንነትና ትርጉም የሚያስረዳ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሄደ።
በመድረኩ ላይ የሰንደቅ ዓላማን ምንነት፣ ታሪካዊ አመጣጥና ትርጉም የሚያብራራውን ሰነድ ያቀረቡት የጋሞ ዞን ቱሪዝም መምሪያ ሀላፊ በሰጡት መግለጫ ሰንደቅ ዓላማ የሀገራችን የሉዓላዊነት፣ የነጻነትና የህዝቦች አንድነት ዋና መገለጫ መሆኑን አብራርተዋል።
አክለውም መሰል ውይይቶች በየደረጃው በሚገኙ ሰራተኞች ዘንድ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ትክክለኛ ግንዛቤን በመፍጠርና ሀገራዊ ፍቅርን በማጎልበት በኩል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ስላላቸው ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ገልጸዋል።
አቶ ሞናዬ ሞሶሌ አያይዘውም እያንዳንዱ አመራርና ባለሙያ በየተሰማራበት የልማት መስክ በሚያስመዘግበው ውጤትና በሚሰጠው ቀልጣፋ አገልግሎት የሰንደቅ ዓላማችንን ክብር ከፍ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።
በመድረኩ የተሳተፉት የመምሪያው ባለሙያዎች በበኩላቸው የቀረበው ሰነድ ስለ ሰንደቅ ዓላማ ያላቸውን ግንዛቤ ያዳበረና ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት ያነሳሳ መሆኑን ገልጸዋል።