03/06/2026
Athlete Tirunesh Dibaba Sport Training Center-Assela
To produce qualified, competent and victorious Athletes in the world championship. Government Organization
03/06/2026
31/05/2026
ከማዕከላችን እስከ ብሔራዊ ኩራት! ሰልጣኞቻችን በብሔራዊ ቡድን ውስጥ እያሳዩት ያለው ድንቅ ብቃት ማዕከላችን ለሀገር ስፖርት እያበረከተው ላለው አስተዋጽኦ ትልቅ ማረጋገጫ ነው።
30/05/2026
ማዕከሉ በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቆ ወደ ቀጣዩ ቶርናመንት አለፈ!
*********
ግንቦት 22/2018 | የማዕከሉ ከ20 ዓመት በታች የ4ኛ ዓመት ሰልጣኞች በኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪሚየር ሊግ ማጠቃለያ ሳምንት አስደናቂ ብቃቱን በማሳየት ሲዳማ ቡናን 3 ለ 2 በሆነ አስደሳች ውጤት አሸንፏል።
በዚህም ማዕከሉ የሊጉን የደረጃ ሰንጠረዥ በ36 ነጥብ በ3ኛነት በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ የቶርናመንት (የአሸናፊዎች አሸናፊ) ውድድር በታላቅ ክብር ማለፉን አረጋግጧል።
በሊጉ 22ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የተደረገው ይህ ወሳኝ ጨዋታ ገና ከመጀመሪያው አጋማሽ በ19ኛው ደቂቃ ላይ ዮሴፍ ሃይሉ የመጀመሪያዋን ጎል፣ በ35ኛው ደቂቃ ፍሬቃል ሃይሉ 2ኛውን ጎል ያስቆጠሩ ሲሆን በ39ኛው ደቂቃ ላይ የሲዳማ ቡናን መነሳሳት የሰበረችውንና የማዕከሉን ድል ያረጋገጠችውን ወሳኝ 3ኛ ጎል አቤኔዘር ድንቁ በድንቅ አጨራረስ አስቆጠረ።
በዚህም ማዕከሉ የ2018 ዓ.ም የሊግ ጉዞውን በደመቀ ድልና በ36 ነጥብ በ3ኛ ደረጃነት አጠናቆ ቀጣይ በሚደረገው የቶርናመንት የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታ ላይ ሀገራዊ እውቅና ለመጨበጥ ዝግጁነቱን አሳይቷል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የማዕከሉ ከ20 ዓመት በታች ወንዶች ዋና አሰልጣኝ ደረጄ ታመነ እንደገለፁት በመጀመሪያ ለዚህ ትልቅ ስኬት የበቁትን ቡድናችንን ከልብ ማመስገን እወዳለሁ። ዛሬ የታየው ወኔና ዲሲፕሊን የዓመቱ ሙሉ ልፋታችን ውጤት ሲሆን ሲዳማ ቡና ጠንካራ ተፎካካሪ ቢሆንም ልጆቻችን ግን ገና ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ ጨዋታውን ለመቆጣጠርና ድል ለማስመዝገብ የነበራቸው ፍላጎት የሚደነቅ ነበር ያሉት አሰልጣኙ አሁን ትኩረታችን በቀጣዩ የቶርናመንት ጨዋታ ላይ ይሆናል። እዚያም የማዕከላችንን ስም የሚያስጠራ የተሻለ ውጤት ይዘን ለመቅረብና የአሸናፊዎች አሸናፊ ለመሆን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል አሰልጣኝ ደረጄ።
በመጨረሻም ማዕከሉ በሊጉ 3ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቅና ወደ ቀጣዩ የቶርናመንት (የአሸናፊዎች አሸናፊ) ውድድር ማለፉ የአሰልጣኙ እና የሰልጣኞቻችንን ጥንካሬ እንዲሁም የማዕከላችንን አመራሮች፣የቴክኒክ ከፍሉ፣ መላው የማዕከላችን ሰራተኞች እና ደጋፊዎቻችን በጋራ በመቆማችን የተገኘ ውጤት መሆኑን ተመልክተናል።
እንኳን ደስ አላችሁ! ወደ ቀጣዩ ፍልሚያ በልበ ሙሉነት!
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: [email protected]
27/05/2026
የ1447ኛው የኢድ አል ዓድሃ በዓል በማዕከሉ በልዩ ድምቀት ተከበረ
************
ግንቦት 19/2018| 1447ኛው የኢድ አል ዓድሃ (አረፋ) በዓል በማዕከሉ ውስጥ የሚገኙ ሰልጣኞች፣ አመራሮች እና ሰራተኞች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት የተከበረ ሲሆን በአከባበር ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት ሰልጣኞችና ሰራተኞች በጋራ በመሆን የበዓሉን መንፈሳዊና ማህበራዊ እሴቶች በሚያንፀባርቅ መልኩ አሳልፈዋል።
የማዕከሉ አመራሮች በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ኢድ አል ዓድሃ የመረዳዳት የመተጋገዝና የመካፈል በዓል መሆኑን ጠቁመው ሰልጣኞች በስልጠና ቆይታቸው ወቅት ይህንን የመረዳዳት እሴት ይዘው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: [email protected]
27/05/2026
እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አል-ዓድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፣ በተለይም በማዕከላችን ለምትገኙ አትሌቶች፣ አሰልጣኞች እና መላው የሥራ ባልደረቦቻችን በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የስኬት እንዲሆንላችሁ ማዕከሉ መልካም ምኞቱን ይገልፃል! ✨
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: [email protected]
25/05/2026
የማዕከሉ ከ20 ዓመት በታች ቡድን ባህር ዳር ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቶርናመንት ማለፉን አረጋገጠ!
*************
ግንቦት 17/2018 | የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች (U-20) ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት ተጠባቂ ጨዋታ በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን የማዕከላችን ተስፈኛ ወጣቶች የባህር ዳር ከተማ አቻቸውን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ታሪክ ሰርተዋል።
ጨዋታው ከመጀመሪያው አጋማሽ ጀምሮ በሁለቱም በኩል ከፍተኛ ፉክክርና ጥንቃቄ የታየበት ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም ጎል መጠናቀቁን ተከትሎ የማዕከሉ ቡድን ሁለተኛውን አጋማሽ በከፍተኛ ማጥቃት እና ተነሳሽነት ጀምሮ
ሁለተኛው አጋማሽ በተጀመረ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በ48ኛው ደቂቃ ላይ የማዕከላችን ድንቅ አጥቂ ዳዊት ፈጠነ የባህር ዳርን የተከላካይ ክፍል በመስበር የተገኘችውን አጋጣሚ በግሩም አጨራረስ ከመረብ አሳርፏታል።
የ2018 የሊጉ ውድድር ሊጠናቀቅ ገና አንድ ጨዋታ እየቀረው ቡድናችን አስደናቂ ብቃቱን በማስመስከር ወደ ቀጣዩ የቶርናመንት (የአሸናፊዎች አሸናፊ) ጨዋታ ማለፉን በይፋ እንዲያረጋግጥ አድርጎታል።
ለዚህ ታላቅ ስኬት በዋና አሰልጣኝነት ቡድኑን እየመሩ ያሉት አሰልጣኝ ደረጄ ታመነ ሚና እጅግ የጎላ ሲሆን አሰልጣኝ ደረጄ በመጀመሪያው አጋማሽ የነበረውን ክፍተት አይተው በሁለተኛው አጋማሽ መጀመሪያ ላይ ቡድኑ ፈጣን ጎል እንዲያስቆጥር ያደረጉት ስልታዊ መስተካከል ሜዳ ላይ የታየው ተነሳሽነት፣ እልህ እና የዲሲፕሊን ጥንካሬ የአሰልጣኙን ጥበብና ልፋት በግልጽ ያሳየ ነበር።
ማዕከሉ ቀጣዩን እና የሊጉን ማጠቃለያ ጨዋታ ግንቦት 21 /2018 ጠዋት 4፡00 ሰዓት ላይ ከሲዳማ ቡና አቻው ጋር ያካሂዳል።
ማዕከላችን የኮከቦች መፍለቂያ መሆኑን በተግባር እያስመሰከረ ይቀጥላል!
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: [email protected]
24/05/2026
🇪🇹 የማዕከላችን ኮከብ ሊዲያ እያሱ በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ደምቃለች! 🇪🇹
*************
ግንቦት 16/2018| በ17 ዓመት በታች የሴቶች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከቡሩንዲ ጋር እያደረገ የሚገኘውን ጨዋታ በበላይነት እየመራ ይገኛል።
የማዕከላችን ኩራት የሆነችው ሰልጣኛችን ሊዲያ እያሱ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት በመጀመሪያው አጋማሽ የብሔራዊ ቡድናችንን መሪነት ያረጋገጡ 2 ግቦችን በደቂቃዎች ልዩነት ከመረብ አሳርፋለች።
የእረፍት ሰዓት ውጤት፦
🇪🇹 ኢትዮጵያ 2 - 0 ቡሩንዲ 🇧🇮
⚽ 27' ሊዲያ እያሱ
⚽ 30' ሊዲያ እያሱ
ለውድ ሰልጣኛችን ሊዲያ እና ለቡድኑ ሁለተኛው አጋማሽም የድል እንዲሆንላቸው እንመኛለን! 💪🔥
ሳይንሳዊ ስልጠና ቀጣይነት ላላው ተተኪ አትሌቶች “
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://atdatc.edu.et
Email: [email protected]
Click here to claim your Sponsored Listing.
Location
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Asella
