10/09/2024
Waajjirri Galiiwwan Godina Arsii Hoggantoota fi Hojjattoota mana Hojii keenyaa sadarkaa sadarkaan jirani fi Ummata Biyya keenyaa maraan baga bara 2017 nagaan ittiin isiin gahee jechaa barri haaraan kan Nagaa, kan Gammachuu, Kan badhaadhinaa fi Milkaa'inaa akka isiiniif ta'u hawwa! Ayyaana Gaarii!
06/10/2023
"Faajjii nageenyaa, tokkummaa fi obbolummaa kan ta'e ayyaana irreechaatiif baga geessan"
*******
Waaqa lafaa fi samii miidhagina goonfachiisee, uumama hundaa sirneessee uume kan itti galateeffannu jala bulti ayyaana Irreechaa irratti argamna. Ayyaana kabajamaa duudhaan obbolummaa, dhiifamaa fi araaraa itti calaqqisu kan Abbootiin Gadaa, Haadholiin Siinqee, Foolleewwanii fi Shamarran Oromoo darbees sabaa fi sablammootni biyyattii biroon uffannaa aadaatiin faayamanii qooda irratti fudhatanu ayyaanni Irreechaa, ayyaana guddaa hawwii fi abdii gaariin eegamu waan ta’eef Oromoota biyya keessaa fi biyyoota alaatti argamtan akkasumas sabaa fi sablammoota biyya keenyaa maraan baga guyyaa kabajamaa kanaan ittiin isin gahe nun gahee.
02/01/2022
ታክስን/ግብርን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት
******
ታክስዎን/ግብርዎን በወቅቱ ሲከፍሉ ከብዙ እንግልት ከመዳንዎ በተጨማሪ አላስፈላጊ ቅጣት ከመቀጣት ይድናሉ፡፡ ግብርን በወቅቱ ከከፈሉ ደግሞ ለሀገርዎ እና ለእርስዎ የሚጠቅመውን በወቅቱ እና በአስፈላጊው ወቅት እንዳደረጉ ይቆጠራል፡፡
ታክስዎን በተለያየ ምክንያት ሳይከፍሉ ካዘገዩ ከሚደርስብዎት ውጣ ውረድ በተጨማሪ ቅጣቶችንም ለማስተናገድ ይገደዳሉ፡፡ ከነኚህ ቅጣቶች ውስጥ ለእርስዎ ለግንዛቤ ይረዳዎት ዘንድ የሚከተሉት ተቀንጭበው ቀርበዋል፡፡
ማንኛውም ታክስ ከፋይ በታክስ መክፈያ ጊዜው ውስጥ ታክስ ሳይከፍል ከቀረ ለዘገየበት ጊዜ፦
1. ለአንድ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ 5% (አምስት በመቶ)፤ እና
2. ከዚያ በኋላ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ከፊል ለሆነው ጊዜ ባልተከፈለው ታክስ ላይ ተጨማሪ 2% (ሁለት በመቶ)፤ ቅጣት ይከፈላል፡፡
I. የሚጣለው የቅጣት መጠን ከዋናው የታክስ ዕዳ መብለጥ የለበትም፡፡
II. መከፈል በማይገባው ታክስ ላይ ሳይከፈል በዘገየበት የተጣለ ቅጣት ለታክስ ከፋዩ ይመለሳል፡፡
III. ታክስን ዘግይቶ መክፈል የሚያስከትለው ቅጣት ከተከፋይ ሂሣብ ላይ ተቀንሶ ከሚከፈል ታክስ ጋር በተገናኘ የሚጣል ቅጣት በሚመለከተው ያልተከፈለ ታክስ ላይ ተፈጻሚ አይሆንም፡፡
ገቢዎችን የተመለከቱ ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
በድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
በፌስቡክ፡- ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በዩትዩብ፦ ministryofrevenuesofethiopia
በቴሌግራም፦ ministryofrevenuesofethiopia/የገቢዎች ሚኒስቴር/
በቴሌቪዥን ፕሮግራሞቻችን ፡- ዋልታ ቴሌቪዥን ሰኞ ማታ ከ 2፡30 ጀምሮ
ፋና ቴሌቪዥን አርብ ማታ ከ3፡00 ጀምሮ
ኢቲዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ
በሬድዮ ፕሮግራሞቻችን፡- ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ
በወርሃዊ ጋዜጣችን፡- ገቢያችን ህልውናችን
እንዲሁም በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡ - 8199 በመደወል መረጃዎችን በመጠየቅ
ስለሚከታተሉን እናመሰግናለን!
18/12/2021
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ወንጀሎች እና ቅጣታቸው
I. ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50ሺ (ሃምሳ ሺ ብር) የገንዘብ መቀጫ እና ከሦስት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
II. በአንድ ግብይት በተሰጡ ተመሳሳይ የደረሰኝ ኮፒዎች ላይ የተለያዩ ዋጋዎችን በመመዝገብ የሽያጭ ዋጋን ያሳነሰ ማንኛውም ሰው ብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እና ከአምስት ዓመት እስከ ሰባት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
III. የሽያጩ ትክክለኛ ዋጋ ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ ከሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (||) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኞቹ ላይ ከተመለከቱት ከፍተኛው የገንዘብ መጠን እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት የሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
IV. ግብይት ሳይፈጸም ደረሰኝ የሰጠ ወይም የተቀበለ ሰው ከብር 100ሺ (አንድ መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሰባት ዓመት እስከ አስር ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
V. በዚህ ተራ ቁጥር (IV) የተመለከተው ደረሰኝ ከብር 200ሺ (ሁለት መቶ ሺ ብር) የሚበልጥ የገንዘብ መጠን የያዘ እንደሆነ በዚህ ተራ ቁጥር (|) መሠረት የሚጣለው ቅጣት በደረሰኙ ከተገለጸው የገንዘብ መጠን ጋር እኩል በሆነ የገንዘብ ቅጣት እና ከአስር ዓመት እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደረስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VI. ባለሥልጣኑ ሳይፈቅድለት የታክስ ደረሰኝ ያተመ ሰው ከብር 300ሺ (ሦስት መቶ ሺ ብር) እስከ ብር 500ሺ (አምስት መቶ ሺ ብር) በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት እና ከሁለት ዓመት እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት ይቀጣል፡፡
VII. በዚህ ተራ ቁጥር (VI) መሠረት ጥፋተኛ የተባለ ሰው ወንጀሉን ለሁለተኛ ጊዜ ፈጽሞ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ የህትመት መሣሪያው እና የማተሚያ ድርጅቱ ይወረሳል፣ የንግድ ፈቃዱም ይሰረዛል፡፡
27/11/2021
Muummee Ministeeraa kiyya waliin Anis nan duula !!
Biyya baraaruuf nutis ni duula !
1. Anis nan duula adda waraana dinagdeetti! !!
Oromiyaas ta'e Itiyoophiyaan sababa hanqina galiitiin harka diinaatti hin kuftu !!
2. Anis nan duula adda waraana dinagdeetti !!
Nuti galii dinagdee biyyaa gahumsaan sassaabuun roorroo fi sodaachisa sababa gargaarsaan biyyoota alaa irraa nutti dhufe qolaachuuf Galii dugignee sassaabnee galchuf ni duula !!
Kun Waadaa dha, Madda galii qabnu hunda sakattaanee adda baasuun galii biyyaa sadarkaa barbaadamu irraan ni geenya !!
Waraana dinagdee madda galii dhoksuu fi nagahee kennu dhisuun shiraa biyya fi Naannoo keenya irratti taasifamu ni fashaleesina !
3. Walabummaa biyya keenyaaf ni hojjenna! Biyyi keenya sababa gargaasaa dhabuun walabummaan ishee akka hin sarbamnee qaamoota galii miliqsan hunda waraana keessoo qaqqabsiisuu danda'an dhabamsiisuun biyya Karaa dinagdees Injifaannoo ni gonfachifina !!
Kun Waada Hojjettoota Waajjira Galiiwwan Godina Arsii Adda Waraana dinagdeettii
27/11/2021
የግብር ከፋይ/ተገልጋዮች መብቶች
ግብር ከፋዮቻችን ወይም ተገልጋዮቻችን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ጋር በሚኖርዎት ግንኙነት የሚከተሉት መብቶች እንዳልዎት ያውቁ ይሆን? ለግንዛቤ እንዲሆንዎ እንደሚከተለው አቅርበንልዎታል፡፡
☞ ተገልጋዮች በሥራ ላይ ስላሉ የግብር ድንጋጌዎች፣ ተቋሙ ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶችና ቅድመ ሁኔታዎች ተገቢውን መረጃ እንደ አግባብነቱ በስልክ እና በአካል በመቅረብ መረጃዎቹን የመጠየቅ፣ ምላሽ የማግኘት እና አገልግሎቶቹን የመጠቀም መብት አላቸው፡፡
☞ ማንኛውም የተቋሙ ተገልጋይ በጾታ፣ በዘርና ቋንቋ፣ በሃይማኖት፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃው መገለል እና አድልዎ ሳይደርስበት በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት የማግኘት መብት አለው፡፡
☞ ማንኛውም ተገልጋይ ክብሩና ስብዕናው ተጠብቆ የመስተናገድ እና ለሚያቀርባቸው አግባብነት ያላቸው የአገልግሎት ጥያቄዎች እንደሁኔታው አዎንታዊ ይሁን አሉታዊ ምላሽ የማግኘት መብት አለው፡፡
☞ ተገልጋዮች ለሚያቀርቡት የአገልግሎት ጥያቄ ወዲያው ምላሽ ለመስጠት የማይቻልበት ሁኔታ ሲኖር እና ቀጠሮ የሚሰጣቸው ከሆነ በሂደት ላይ የሚገኘው ጉዳያቸው ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰ እንዲሁም የትና በየትኛው ክፍል እንደሚገኝ (ጉዳዩ እስኪጠናቀቅ በምስጥር መያዝ የሚገባቸውን ጉዳዮች ካልሆኑ በስተቀር) ጠይቀው የመረዳት መብት አላቸው፡፡
☞ የተቋሙ ተገልጋዮች በተቋሙ አሠራር፣ በሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ሥነ ምግባር እና በአጠቃላይ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታቸውን የማቅረብ፣ ተገቢውን ወቅታዊ ምላሽ የማግኘትና የመደመጥ መብት አላቸው፡፡
☞ በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥና አሠራር ዙሪያ የታዘቡትንና ቢሆን ይሻላል የሚሉትን ተገቢ አስተያየት በማመስገንም ሆነ በመተቸት በነፃነት የመግለጽ መብት አላቸው፡፡
☞ አርአያነት ባለው ሁኔታ የግብር ግዴታቸውን የሚወጡ ግብር ከፋዮች ሽልማት የመቀበል መብት አላቸው፡፡
በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩት መብትዎ መሆኑን ተገንዝበው ይጠቀሙበት፡፡ በሚቀጥለው ክፍል ስለግዴታዎ መረጃ እናቀርብልዎታለን፡፡
24/11/2021
የኤክሳይዝ ታክስን በማስታወቅ እና በመክፈል ሂደት ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ቅጣቶች
ኤክሳይዝ ታክስ በቅንጦት ዕቃዎች፣ የህብረተሰቡን ጤንነት የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግርን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል እንዲሁም ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረም መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ ይጣላል፡፡ ይህንኑ ታክስ በማስታወቅ እና በመክፈል ሒደት ውስጥ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሊያስከትሏቸው ከሚችሏቸው ቅጣቶች ዋና ዋናዎቹን እንጠቁማችሁ፡፡
የወንጀል ቅጣቶች
☞ ፈቃድ ሳይኖረው የሚያመርት እና ከተፈቀደለት ቦታ ውጪ የሚያመርት ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 50ሺ እስከ ብር 100ሺ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡
☞ በፈቃዱ ከተመለከተው ሥፍራ ውጪ የኤክሳይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ዕቃዎች በማምረት ተግባር ላይ የተሠማራ ከ5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሥራት እና ከብር 100ሺ -200ሺ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡
☞ ፈቃድን እስከመታገድ የሚያደርስ ሁኔታ ከተገኘ ከ1 እስከ 3 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 100ሺ ባልበለጠ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡
☞ ታክሱ የሚከፈልባቸውን ዕቃዎች ከቁጥጥር ውጪ ከማምረቻው ፋብሪካ ወጪ ያደረገ፣ ፈቃድ ሳይኖረው በታክሱ ቁጥጥር ሥር ያሉ ዕቃዎች ተከማችተው በሚገኙበት ቦታ የገባ፣ ባልተፈቀደ መንገድ ከተከማቹበት ቦታ ወጪ በማድረግ፣ ባህሪያቸውን በመለወጥ ወይም የቁጥጥሩን ሥራ በማወክ ረገድ የተባበረ ከ5 እስከ 7 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እሥራትና ከብር 100ሺ እስከ 200ሺ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡
☞ ታክሱ ሳይከፈልባቸው ከተመረቱበት ፋብሪካ ወጪ የተደረጉ ዕቃዎችን የገዛ ወይም ሳይፈቀድለት እነዚህን ዕቃዎች የተቀበለ ወይም በይዞታው ሥር ያደረገ ወይም ታክሱ ያልተከፈለባቸውን ዕቃዎች ለሽያጭ በማዋል ተግባር የተሠማራ ከ3 እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና ከብር 100ሺ እስከ 200ሺ በሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይቀጣል፡፡
22/11/2021
የኤክሳይዝ ታክስን ስለማስታወቅ፣ ስለመክፈል እና ግዴታን አለመወጣት የሚያስከተው አስተዳደራዊ ቅጣት
👉 አምራቹ የእያንዳንዱን ወር ሂሳብ የሚቀጥለው ወር 30ኛው ቀን ከማለፉ በፊት ማስታወቅ አለበት፡፡
👉 አስመጪ ወደ ሀገር ውስጥ ባስገባቸው የኤክሳይዝ ታክስ በሚከፈልባቸው ዕቃዎች ላይ ሊከፍል የሚገባውን የኤክሳይዝ ታክስ ዕቃዎቹ ወደ ሀገር በገቡበት ጊዜ ለታክሱ ባለሥልጣን መክፈል አለበት፡፡
አስተዳደራዊ ቅጣቶች
አስተዳደራዊ ቅጣቶች
👉 ፈቃድ ሳይኖረው የኤክሣይዝ ታክስ የሚከፈልባቸውን ዕቃዎች የሚያመርት፣
👉 በፈቃዱ ከተመለከተው ቦታ ውጪ ሲያመርት የተገኘ፣
👉 ከኤክሣይዝ ታክስ ቁጥጥር ውጪ ዕቃ ወጪ አድርጐ የተገኘ፣ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ እጥፍ ይቀጣል፡፡
20/11/2021
ደረሰኝ አለመቀበል እና የወጋ ግሽበት!!!
በሀገራችን ለተከሰተው የኑሮ ውድነት በርካታ ምክንያቶችን መዘርዘር የሚቻል ቢሆንም ችግሩን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያባባሰውና ውስብስብ እንዲሆን ያደረገው የህብረተሰባችን ለገዛው ዕቃ ደረሰኝ የመጠየቅና የመቀበል ባህሉ ዝቅተኛ መሆኑ በዋናነት ተጠቃሽ ነው፡፡ ምክንያቱም ህገወጥ ነጋዴዎች ደረሰኝ የሚቆርጡ ከሆነ ወደ ህጋዊ መስመር ሊገቡና ሲያጠፉም በቀላሉ እርምጃ ለመውሰድ ያስችላል፡፡ በመሆኑም ማህበረሰባችን ለገዛው ዕቃ ደረሰኝ መቀበልን ባህሉ በማድረግ ህገወጦችን ወደ ትክክለኛው መስመር እንዲገቡ ጫና ሊያሳድር ይገባል፡፡