Benishangul Gumuz Education Bureau

Directions Website

Benishangul Gumuz Education Bureau የትምህርት ጥራት ተጠብቆ የተማሪዎቻችን ውጤትና ስነ-ምግባር እንዲሻሻል እንሰራለን !!! Equity

የመማር ማስተማር ስራዎችን ለማሻሻል ለትምህርት ቤቶች የላፕቶፕ ኮምፒውተር ድጋፍ ተደረገ-----------    ------------    -----------------    --------የክልሉ ...
13/11/2026

የመማር ማስተማር ስራዎችን ለማሻሻል ለትምህርት ቤቶች የላፕቶፕ ኮምፒውተር ድጋፍ ተደረገ
----------- ------------ ----------------- --------
የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከUNICEF STEP ፕሮግራምና ከGeneva Global LiTE ፕሮግራም በድጋፍ ያገኛቸውን የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች ለትምህርት ቤቶች እያሰራጨ ይገኛል።

ለትምህርት ቤቶች በድጋፍ የተሰጡት የላፕቶፕ ኮምፒውተሮች የመማር ማስተማር ስራን ለማገዝና የትምህርት መረጃ ስርዓት ለማዘመን አገልግሎት የሚውሉ ናቸው ተብሏል

በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ በቶንጎ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው  የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል  "በብዝሃነት የደመቀች በምክክር  የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ "  በሚል መሪ ...
13/11/2026

በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ በቶንጎ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል "በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ " በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል።

መስፈርቱን የምታሟሉ መምህራን መወዳደር ትችላላችሁ።
13/11/2026

መስፈርቱን የምታሟሉ መምህራን መወዳደር ትችላላችሁ።

በትምህርት ቤቶች የብሄር ብሄረሰቦች በዓል አከባበር እንደቀጠለ ነው…………………………………………………(ህዳር 4/2019 ዓ.ም-አሶሳ) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የዳሬ ሰላም አንደ...
13/11/2026

በትምህርት ቤቶች የብሄር ብሄረሰቦች በዓል አከባበር እንደቀጠለ ነው
…………………………………………………
(ህዳር 4/2019 ዓ.ም-አሶሳ) በአሶሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የዳሬ ሰላም አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዘንድሮ ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀንን በደመቀ ሁኔታ አክብሯል፡፡

በበዓሉ አከባበር ወቅት የትምህርት ቤቱ መምህር መኮንን ይመር ለተማሪዎቹ ህገ መንግስቱን አስመልክቶ ሰፊ ገለፃ አድርገዋል፡፡በትምህርት ቤቱም በዓሉን አስመልክቶ የዕግር ኳስ እና የሩጫ ፕሮግራም የተካሄደ ዚሆን ለአሸናፊዎቹም የተለያዩ የመማሪያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዓሉን በማስመልከትም የተለያዩ ብሄሮችና ብሄረሰቦች ባህላዊ ጭፈራዎች ለበዓሉ ድምቀት ሆነው ውለዋል፡፡

ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ነው

የቤልፉዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ከወዲሁ ለሀገር አቀፍ ፈተና እያዘጋጀ ነው------------   ------------   --------------  --------  ---------...
13/11/2026

የቤልፉዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎቹን ከወዲሁ ለሀገር አቀፍ ፈተና እያዘጋጀ ነው
------------ ------------ -------------- -------- ---------
(ህዳር 4/2019 ዓ.ም ) በቢልዲጊሉ ወረዳ የሚገኘው የቤሊፉዲ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና በኦን-ላይን ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከወዲሁ በኮምፒውተር እንዲለማመዱና ከቴክኖለጂ ጋር እንዲተዋወቁ የሚያርገውን ጥረት ለሌሎች ትምህርት ቤቶችን ተሞክሮ የሚሆን ነው፡፡

የቡለን ወረዳ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ******************(ቡለን ህዳር 4/2019 ዓ/ም ) የቡለን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ የቅድመ ...
13/11/2026

የቡለን ወረዳ የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም
******************
(ቡለን ህዳር 4/2019 ዓ/ም ) የቡለን ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት በወረዳው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ የቅድመ አንደኛ ደረጃ (KG) ተማሪዎች የተዘጋጀውን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም የቡለን ወረዳ ሰ/ግ/ጽ/ቤት ሀላፊ እና የአስተዳዳሪ ተወካይ አቶ እንዳልካቸው ኩልሽ እና የቡ/ወ/ት/ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ሽፈራው በየነ በተገኙበት በይፋ አስጀምሯል።
‎
‎የቡለን ወረዳ ሰላም ግንባታ እና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ እና የቡለን ወረዳ ምክትል የአስተዳዳሪ ተወካይ አቶ እንዳልካቸው ኩልሽ ፕሮግራሙ የተጀመረው በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት በተማሪዎች ላይ የሚከሰተውን የትምህርት መቋረጥና መቅረት ለመቀነስ እንዲሁም ህጻናት በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማስቻል ነው።
‎
‎በማስጀመሪያ መርሐ-ግብሩ ላይ የተገኙት የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ም/ኃላፊ አቶ ሽፈራው በየነ እንደገለፁት የምገባ ፕሮግራሙ ተማሪዎች በትምህርት ገበታቸው ላይ በንቃት እንዲሳተፉ ከማድረግ ባለፈ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል።
‎
‎በቀጣይም ይህ የምገባ ፕሮግራም በዘላቂነት እንዲቀጥልና ሌሎች ተማሪዎችንም ተጠቃሚ እንዲያደርግ የህብረተሰቡ፣ የወላጆች እና የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል። ዘገባው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው፡፡

"በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የጸናች ስልጡን ኢትዮጵያ"21ኛው የኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ ፕሮግራሞች በትምህርት ቤቶች መከበሩን እንደቀጠለ ነው፡፡ በዛሬውም ዕለት ...
13/11/2026

"በብዝሃነት የደመቀች በምክክር የጸናች ስልጡን ኢትዮጵያ"
21ኛው የኢትዮጲያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በተለያዩ ፕሮግራሞች በትምህርት ቤቶች መከበሩን እንደቀጠለ ነው፡፡ በዛሬውም ዕለት በአሶሳ ከተማ በሩሃማ ትምህርት ቤት በዓሉ በስነ-ጹሁፍ ፣ በጥያቄና መልስ ውድድር ፣ በተለያዩ የባህል አልባስትና የባህል ጭፈራዎች እየተከበረ ነው፡፡

ተጠናክሮ የቀጠለው ህብረተሰብ ተኮር የትምህርት ቤት ምገባ !👏በጉባ ወረዳ በአልማሀል 1ኛና መካ/ ደረጃ ትም/ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አስጀምሯል።‎ ‎የምገባ...
12/11/2026

ተጠናክሮ የቀጠለው ህብረተሰብ ተኮር የትምህርት ቤት ምገባ !👏

በጉባ ወረዳ በአልማሀል 1ኛና መካ/ ደረጃ ትም/ቤት የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም አስጀምሯል።
‎

‎የምገባ ፕሮግራሙ የተማሪዎችን መጠነ ማቋረጥ ለመቀነስ ታሳቢ በማድረግ የቀበሌውን ማህበረሰብ በማስተባበር በአልማሀል አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የምገባ ፕሮግራም አስጀምረናል ሲል ትምህርት ቤቱ መረጃውን አድርሶናል።

በማህበረሰብ ውይይት ትምህርት ቤቱ የሚያጋጥሙትን ችግሮች እየፈታ ነው ፤ ርዕሰ መምህር ሲሳይ አበበ-------------     -----------------      ---------------- ...
12/11/2026

በማህበረሰብ ውይይት ትምህርት ቤቱ የሚያጋጥሙትን ችግሮች እየፈታ ነው ፤ ርዕሰ መምህር ሲሳይ አበበ
------------- ----------------- ---------------- ----------
በማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ በሚሚ ያኮቦ 1ኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአንድ ቀን የማህበረሰብ ውይይት ብቻ ህብረተሰቡ 40,000 ብር ድጋፍ ማድረጉን የገለፁት ርዕሰ መምህር ሲሳይ ታደሰ ህብረተሰብ ለትምህርት የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

በቀጣይም ተመሳሳይ ችግሮችን ህብረተሰብ ለመፍታት ቁርጠኛ ነው ፤ የማህበረሰብ ውይይቱ የሴት ልጆችን የትምህርት ተሳትፎ ማሳደግ ፤ ልዩ ፍላጎት የሚሹ ዜጎች ወደ ትምህርት ቤት ማምጣትና ማቆየት ፤ ድጋፍ የሚሹ ተማርዎች ለመደገፍ ፤ የማህበረሰብ ተሳትፎን ማሻሽል ላይ ያተኮረ ነው።

ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን""በብዙሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል አስመልክቶ በኩርሙክ ወረዳ  ሆር-አዛሃብ 1ኛ እና 2ኛ...
12/11/2026

ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን""በብዙሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል አስመልክቶ በኩርሙክ ወረዳ ሆር-አዛሃብ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል።

(ኩርሙክ ህዳር 3/2019 ዓ/ም ለ21ኛ ጊዜ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን""በብዙሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል አስመልክቶ በኩርሙክ ወረዳ ሆር-አዛሃብ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት በተለያዩ ኩነቶች ተከብሯል።

21ኛውን የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ዘንድሮው ''በብዙሃነት የደመቀች በምክክር የፀናች ስልጡን ኢትዮጵያ'' በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የሆር-አዛሃብ 2ኛ ደረጃ ት/ት ቤት ርዕሰ መምህር ብርሃኑ እንቢያለ ገልጿል።

ይህንን ምክንያት በማድረግ በየትምህርት ቤቱ በፓናል ውይይት እንደከበር ከወረዳው ምክር ቤት በደረሰን መረጃ መሰረት በተለያዩ ጥያቄና መልስ ውድድር እና ኩነቶች ማክበራቸውን ተናግረዋል ። ዘገባው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ነው።

Address

Asosa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Benishangul Gumuz Education Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share