Prosperity Party Hawassa City Branch Office

Directions

Prosperity Party Hawassa City Branch Office Building a brighter future for Hawassa through economic growth, social equity, and community development. Join us in creating prosperity for all residents.

10/10/2026

በአንድ ጊዜ የአባልነት መዋጮ ብቻ አመቱን ሙሉ የእርሶን እና የቤተሰቦን የአመት የህክምና ወጪ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ይሸፍኑ

#ሀዋሳብልጽግና
#የጤናብልጽግና
#ሰውተኮር

ግብርን በቴክኖሎጂ በመታገዝ መክፈል አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረትና አገልግሎቱን ለማዘመን ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ​ግብርን በቴሌብር የመክፈል አሰራር አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረትና...
10/10/2026

ግብርን በቴክኖሎጂ በመታገዝ መክፈል አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረትና አገልግሎቱን ለማዘመን ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ

​ግብርን በቴሌብር የመክፈል አሰራር አላስፈላጊ ወጪዎችን ለማስቀረትና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገለጸ።

​ይህ የተገለጸው የሐዋሳ ከተማ ገቢዎች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት በቴሌብር ክፍያ አጠቃቀምና ትግበራ ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በተወያየበት ወቅት ነው። በምክክር መድረኩ የገቢዎች ተቋም ባለሙያዎች፣ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተወካዮችና ባለሙያዎች ተኝተዋል።

​በመድረኩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሐዋሳ ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ፤ በቴሌብር ክፍያ መፈጸሙ የግብር አሰባሰብ ሥርዓቱን ከማዘመኑ ባሻገር ሌብነትንና የግብር ማጭበርበርን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

​አክለውም አሰራሩ ጊዜንና እንግልትን የሚቆጥብ፣ ግብር ከፋዮች ወደ ታክስ ማዕከላት በአካል ሳይሄዱ ባሉበት ቦታ ሆነው ግብራቸውን በወቅቱ እንዲከፍሉ የሚያስችል ዘመናዊ አተገባበር መሆኑን ጠቁመዋል። አሰራሩ በግብር ሰብሳቢው ተቋምና በግብር ከፋዩ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ጤናማ እንደሚያደርገውም ኢንጂነሩ አብራርተዋል።

​የሲዳማ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ኃላፊ አቶ መልኩ ማርቆስ በበኩላቸው፤ በከተማ ደረጃ የሚገኙ የገቢ ተቋማት አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ሥራ በማጠናቀቅ ለግብር ከፋዮች ምቹ ሁኔታ መፍጠራቸውንና ከባለድርሻ አካላት ጋር የተቀናጀ አሰራር መዘርጋታቸውን ገልጸዋል።

​የገቢ አሰባሰብ ሥርዓቱን ከተለምዷዊ አሰራር በማላቀቅ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስደገፍ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ፣ ቀልጣፋ፣ ምቹና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ያሉት አቶ መልኩ፣ ለዚህም የሚረዱ በርካታ ተግባራት መከናወን መጀመራቸውን አስረድተዋል።

​በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች በበኩላቸው አገልግሎቱን በቴሌብር መስጠት መጀመራቸው የታክስ ማጭበርበርን ለመቀነስና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው፤ በትግበራ ወቅት ያጋጠሟቸውን ክፍተቶችና ተፎካካሪ ተ his ችግሮች በስፋት አንስተው ውይይት አድርገውበታል።

በየወቅቱ እየተደረገ ያለው የጽዳት ንቅናቄ የነዋሪውን የጽዳት ባህል እያሳደገ መምጣቱ ተገለፀበሀዋሳ ከተማ በየወቅቱ እየተካሄደ ያለው የጽዳት ንቅናቄ የነዋሪውን የጽዳት ባህል እያሳደገ መምጣቱ...
10/10/2026

በየወቅቱ እየተደረገ ያለው የጽዳት ንቅናቄ የነዋሪውን የጽዳት ባህል እያሳደገ መምጣቱ ተገለፀ

በሀዋሳ ከተማ በየወቅቱ እየተካሄደ ያለው የጽዳት ንቅናቄ የነዋሪውን የጽዳት ባህል እያሳደገ መምጣቱ ተገለፀ። ይህ የተገለፀው የሀዋሳ ከተማ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ የጽዳት ውበትና አረንጓዴ ልማት ዘርፍ አስተባባሪነት በየሳምንቱ ቅዳሜ በሚካሄደው የጽዳት መርሃ ግብር ወቅት ነው።

የሀዋሳ ከተማ ከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የልማታዊ ሴፍትኔት እና አረንጓዴ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሃደራ ሀርቃ እንደገለጹት በየወቅቱ የሚካሄደው የጽዳት ንቅናቄ ማህበረሰቡ ጽዳትን የዕለት ተዕለት ባህሉ እንዲያደርግ ከማገዙም በላይ ለከተማዋ ንጽህናና ውበት መጠበቅ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ነዋሪዎች በተለይም በመኖሪያ አካባቢያቸው ዙሪያ ያለውን ንጽህና በመጠበቅ የከተማዋን አካባቢያዊ ጤናና ውበት ለማስጠበቅ የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

በተጨማሪም እየጨመረ የመጣው የማህበረሰቡ የጽዳት ግንዛቤ ነዋሪዎች በቤታቸው ዙሪያ በ20 ሜትር ራዲየስ ያለውን አካባቢ እንዲያጸዱ እንዲሁም ተቋማት በ50 ሜትር ራዲየስ ውስጥ ያለውን አካባቢ እንዲያጸዱ የተቀመጠውን የጽዳት ደረጃ የመተግበር ልምድ እያዳበረ መምጣቱ ተመላክቷል።

ይህም ነዋሪዎችና ተቋማት ለአካባቢያቸው ንጽህና በተከታታይ ትኩረት እንዲሰጡና የጽዳት ኃላፊነትን እንደ የጋራ ተግባር እንዲወስዱ እያበረታታ ይገኛል።

አቶ ሃደራ ሀርቃ አክለውም የከተማዋን ንጽህናና ውበት በዘላቂነት ለማስጠበቅ የጽዳት ንቅናቄው በተከታታይ መካሄድ እንዳለበትና ሁሉም ነዋሪ እና ተቋም በንቃት መሳተፍ እንዳለበት ጠቁመዋል።

የጽዳት ባህልን ማሳደግ ከከተማዋ ገጽታ ግንባታ ባሻገር ለህብረተሰቡ ጤናማና ምቹ የኑሮ አካባቢ መፍጠር እንደሚያስችልም አመልክተዋል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ስኬታማነት አቅም መፍጠር የሚያስችል ያለፉትን ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂደዋል።የግምገማ መድረኩ ...
09/10/2026

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ስኬታማነት አቅም መፍጠር የሚያስችል ያለፉትን ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ አካሂደዋል።

የግምገማ መድረኩ የፓርቲውን የሥራ አፈጻጸም በጋራ በመገምገም ያለበትን ደረጃ ለመለየት፣ የተገኙ ውጤቶችን ለማጠናከርና የታዩ ክፍተቶችን በማረም የቀጣይ ተግባራትን ስኬታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማራዶና ዘለቀ ባስተላለፉት መልዕክት ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ አቅዳ ከተስፋ ወደሚጨበጥ ውጤት የተሸጋገረችበትና በተለያዩ ዘርፎች እመርታ ያሳየችበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል። በተለይም በስንዴ ምርት፣ በኢኮኖሚ ሪፎርም፣ በከተሞች ዘመናዊነት፣ በዴሞክራሲ ባህል ግንባታና በሰው ተኮር ተግባራት ውጤት ማምጣት መቻሉን አውስተዋል።

በቀጣይም የመደመር መንግሥትን ራዕይ ተረድቶ ለመተግበር የሚችል፣ የአፍሪካ የብልፅግና ተምሳሌት የምትሆን ኢትዮጵያን ለመገንባት የአመራርና የአባላትን አቅም ማጎልበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በተለይም የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በተቀመጡ የፓርቲው የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የመተግበር ዝግጁነትን ማሳደግ፣ ከአደረጃጀት ጀምሮ ጠንካራ የፀረ ሌብነት ትግል ማካሄድና የፓርቲውን ቀይ መስመር በጥብቅ ማስከበር እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።

በተጨማሪም በገቢ አሰባሰብ፣ በማዘጋጃ ቤትና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች የሚሰጡ አገልግሎቶች በጥራትና በግልጽነት እንዲከናወኑ በፓርቲው መሪነት ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ጤናማ የፖለቲካና የነባራዊ ሁኔታ ግምገማን በጥልቀት ማካሄድ፣ በየአደረጃጀቱ የአባላት ሀሳብ በነፃነት የሚንሸራሸርበትን ሁኔታ መፍጠርና የፓርቲውን እሳቤ ከማስረጽ አንጻር ያሉ ሥራዎችን ማጠናከር እንዳለበት አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በልማት፣ በሰላም፣ ህግና ስርዓትን በማስከበር፣ በዴሞክራዊያዊ ስርዓት ግንባታ እና ወሳኝ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባትና የተረጋጋ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት በሚያስችል መልኩ የትብብር ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በመቀጠል የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን አየለ ባስተላለፉት መልዕክት የፓርቲውን አደረጃጀት ይበልጥ ዘመናዊ፣ ጠንካራና ውጤታማ ለማድረግ የአባላትን መረጃ ማዘመን፣ የአባልነት መታወቂያ ሥርዓትን ማጠናከርና የአደረጃጀት አሠራሮችን ማሻሻል ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

የአባላት መረጃ በትክክልና በወቅቱ መያዙ የፓርቲውን የሥራ አፈጻጸም በተገቢው ለመከታተል፣ የአባላትን ተሳትፎ ለማጠናከርና የተቀመጡ ዕቅዶችን በተቀናጀ መንገድ ለመፈጸም እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በተጨማሪም አባላትና አመራሮች የፓርቲውን ዕቅድና የሥራ አቅጣጫዎች በግልጽ እንዲረዱ፣ በአፈጻጸም ሂደት የተግባቡ እንዲሆኑና ለጋራ ዓላማ በትብብር እንዲሠሩ በተከታታይ መሥራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በግምገማው የዝግጅት ምዕራፉ አፈጻጸም፣ የአባላትና የአመራር ዝግጁነት መፍጠር፣ ከአባል እስከ አደረጃጀት የዕቅድ ተደራሽነት፣ በዕቅድ ላይ መግባባትና መረዳት ከመፍጠር አንጻር የተከናወኑ ሥራዎች በዝርዝር ቀርበዋል። በተጨማሪም በመልካም አስተዳደር፣ በሌማት ትሩፋት፣ በከተማ ግብርና፣ በተረጂነት ቅነሳ በካላሞ ኢኒሼቲቭ፣ በፓርቲ ገቢ፣ በትምህርት፣ በአደረጃጀት ማዘመን፣ በጤና መድንና በክረምት በጎ ፈቃድ የተከናወኑ ተግባራት ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የአንድ እቅድ አንድ ሪፖርት ስራ እና ኬፒአይ መሰረት ያደረገ የክትትል ስራ ማጠናከር እንደሚገባ መግባባት ላይ ተደርሷል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመየሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ20...
08/10/2026

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ገመገመ

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ የ2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። በግምገማውም ዘርፉ በዕሩብ ዓመቱ ያከናወናቸው መደበኛና የንቅናቄ ተግባራት፣ የፖለቲካ ጉዳዮችና የአቅም ግንባታ ሥራዎች በዝርዝር ቀርበው አፈጻጸማቸው ተገምግሟል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ባቢሶ ባናታ እንደገለጹት የዕሩብ ዓመቱ የአፈጻጸም ግምገማ የተከናወኑ ሥራዎችን በመፈተሽ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ወሳኝ መድረክ መሆኑ አብራርተዋል። በዕሩብ ዓመቱ የተከናወኑ መደበኛና የንቅናቄ ተግባራትን በዕቅድ መሠረት በመፈጸም የፖለቲካ ውይይቶችንና የአባላት አቅም ግንባታ ሥራዎችን ማጠናከር ቀጣይ የሥራ ትኩረት መሆኑን አቶ ባቢሶ ገልጸዋል።

በግምገማው ወቅት የዘርፉ መደበኛ የፖለቲካ ሥራዎች፣ የንቅናቄ ተግባራት፣ የፖለቲካ ውይይቶችና የአመራርና አባላት አቅም ለማጎልበት የተከናወኑ ሥራዎች በዋናነት ተነስተዋል። ከዕቅድ አንጻር የተገኙ ውጤቶች፣ የታዩ ጥንካሬዎችና በአፈጻጸም ሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችም በመለየት የጋራ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በተጨማሪም የተከናወኑ የዘርፋ ተግባራት በአባላት ዘንድ የፖለቲካ ግንዛቤን ለማጎልበት ያላቸው ሚና፣ የንቅናቄ ሥራዎች ከዕቅድ ጋር ያላቸው ትስስር እና በቀጣይ ሊሰጣቸው የሚገባው ትኩረት ተዳሷል።

በመጨረሻም በግምገማው የተለዩ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠው የ2019 ዓ.ም የቀሪ ወራት የፖለቲካ፣ የንቅናቄና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በተሻለ አፈጻጸም ለማስፈጸም የጋራ መግባባት ተደርሷል።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ አካሄደየሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ አካ...
08/10/2026

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ
የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ አካሄደ

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የመጀመሪያ ዕሩብ ዓመት የአፈጻጸም ግምገማ አካሂዷል። በግምገማው የዕሩብ ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም የአባላት መረጃ ማዘመንና የአባላት መታወቂያ መረጃን በሥርዓት ማደራጀት እንዲሁም የአባላት የብልፅግና ህብረትና የብልፅግና ቤተሰብ የአደረጃጀት አሁናዊ ቁመና በዝርዝር ተዳስሰዋል።

የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊው አቶ መስፍን አየለ በግምገማው ላይ እንደገለጹት ጠንካራ አደረጃጀት ለተቀመጡ የሥራ ዕቅዶች ውጤታማ አፈጻጸም መሠረት በመሆኑ የአባላት መረጃን በወቅቱ ማዘመንና በተደራጀ መልኩ መያዝ ያስፈልጋል። የአባላት የብልፅግና ህብረትና የብልፅግና ቤተሰብ አደረጃጀቶችም በአባላት መካከል የተደራጀ ተሳትፎን ለማሳደግና የአደረጃጀቱን ሥራ በተገቢው ለመከታተል ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባ ጉዳዮች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በግምገማው የብልፅግና ህብረትና የብልፅግና ቤተሰብ አደረጃጀቶች ያላቸው ሚና የአባላት ተሳትፎ የተከናወኑ ሥራዎችና በአፈጻጸም ሂደት የታዩ ክፍተቶች ተመልክተዋል።

በተለይም የአባላትን ተሳትፎ ማጠናከር መረጃዎችን በትክክል ማደራጀትና የአደረጃጀት ሥራዎችን በየደረጃው በተከታታይ መከታተል እንደሚገባ ተገልጿል።

በመጨረሻም በመጀመሪያው ዕሩብ ዓመት የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል ክፍተቶችን በመለየት የማስተካከያ ሥራ ማከናወንና የቀጣይ ዕቅዶችን በተሻለ አፈጻጸም ማሳካት ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው ፀድቋል። በዚሁ መሠረት፡-1. ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ...
08/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የካቢኔያቸውን እጩ አባላት ለምክር ቤቱ አቅርበው ፀድቋል።
በዚሁ መሠረት፡-
1. ተመስገን ጥሩነህ - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) - የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አዲሱ አረጋ (ዶ/ር) - የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) - የገንዘብ ሚኒስትር
5. አቶ መሃመድ እድሪስ - የመከላከያ ሚኒስትር
6. ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) - የትምህርት ሚኒስትር
7. ወ/ሮ ሃና አርአያሥላሴ - የፍትሕ ሚኒስትር
8. ወ/ሮ ያስሚን ወሃብረቢ - የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር) - የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) - የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. መቅደስ ዳባ (ዶ/ር) - የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ- የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ - የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍስሃጽዮን - የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ሰላማዊት ካሳ- የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወ/ሮ ዓለምጸሃይ ጳውሎስ - የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ - የሎጂስቲክስ ሚኒስትር
18. ወ/ሮ ሻዊት ሻንካ - የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም - የሰላም ሚኒስትር
20. ወ/ሮ ፍሬሕይወት ታምሩ - የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. መሃመድ አብዱራሃማን (ኢ/ር) - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ሱልጣን ወሊ (ዶ/ር) - የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር) - የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር ሆነው በእጩነት ቀርበዋል፡፡ See less

የሐዋሳ ከተማን ማዘጋጃ ቤታዊ መዋቅር በአዲስ መልክ ለማደራጀት ሲካሄድ የቆየውን ጥናት ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄደ።​የከተማዋን የህዝብ ቁጥ...
07/10/2026

የሐዋሳ ከተማን ማዘጋጃ ቤታዊ መዋቅር በአዲስ መልክ ለማደራጀት ሲካሄድ የቆየውን ጥናት ወደ ትግበራ ለማስገባት የሚያስችል የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ ተካሄደ።

​የከተማዋን የህዝብ ቁጥር እድገት፣ የልማት ፍላጎትና የአገልግሎት ጥያቄ የሚመጥን የማዘጋጃ ቤታዊ መዋቅር ለመገንባት ጥናቱ ሲካሄድ መቆየቱ በመድረኩ ተጠቁሟል።

​ለአንድ ዓመት ያህል ሲካሄድ የቆየው ይህ ጥናት ለክልሉ ካቢኔ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበት መፅደቁም ተመላክቷል።

​የዛሬው ውይይት ዋና ዓላማም ጥናቱ የፐብሊክ ሰርቪስ ቅርጽ እንዲይዝ፣ በቢፒአር ትግበራ ውስጥ እንዲገባና የተጠኑ መዋቅሮች ወደ ተግባር እንዲገቡ ለማስቻል ያለመ ነው።

​በመድረኩ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት የከተማዋን ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገትና ተያይዞ የሚመጣውን የልማትና የአገልግሎት ጥያቄ የሚመጥን መዋቅር መገንባት ያስፈልጋል።

​መዋቅሩም የስራ ክፍፍልን፣ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን በማስፈን የከተማዋን ህዝብ ጥያቄ በተሻለ ደረጃ መመለስ የሚያስችል መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።

​ከንቲባው አክለውም አዲሱ መዋቅር የከተማዋን ፈጣን እድገት፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን በተገቢው ለመመለስ የሚያስችል፣ የስራ ውጤታማነትን የሚያሳድግና የተቋማትን አቅምና ቅልጥፍና በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ተወዳዳሪ ከተማ የመገንባት ስራውን የሚያጎለብት እንደሆነ አስገንዝበዋል።

​የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መንግስቱ ማቴዎስ በበኩላቸው፣ የመዋቅር ጥናቱ ከክልሉ ካቢኔ በተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት በክልልና በከተማ ባለሙያዎች በጋራ መካሄዱን ገልጸዋል።

​በጥናቱ መነሻ አዋጆችን እና ደንቦችን ማገናዘብና ከሚመለከታቸው ቢሮዎችና ተቋማት ጋር የጋራ በማድረግ ወደ ትግበራ ለማስገባት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

​አቶ መንግስቱ አክለውም የመዋቅር ጥናቱ ዋና ትኩረት በማዘጋጃ ቤት ስር ተጠርንፈው የቆዩ ስፋት ያላቸው የስራ ዘርፎች ብቁ እና በቂ በሆነ የሰው ኃይል የራሳቸውን ግልጽ የስራ መስመር እንዲይዙና አገልግሎቶች በተሻለ አደረጃጀት እንዲሰጡ ማስቻል መሆኑን አስረድተዋል።

​በጥናቱ መሰረት ከነባር መዋቅሮች ተስበው እንደአዲስ ከተደራጁት መካከል የመንገድ መብራት አስተዳደር ራሱን የቻለ መዋቅር እንዲሆን፣ የከተማ ፕላን ራሱን ችሎ ተጠሪነቱ ለማዘጋጃ ቤት እንዲሆንና በጽ/ቤት ደረጃ እንዲደራጅ፣ ሰፊ የሆኑት የህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች በጽ/ቤት ደረጃ ተደራጅተው ተጠሪነታቸው ለከንቲባ እንዲሆን እና የኮንስትራክሽን ዘርፍ ባለስልጣን ሆኖ በከንቲባ ጽ/ቤት ስር እንዲደራጅ ተደርጓል።

​በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በከተማዋ መዋቅር ውስጥ ያልነበሩ የስማርት ከተማ ግንባታ ጽ/ቤትና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት አዲስ ተፈጥረው በከንቲባ ጽ/ቤት ስር ራሳቸውን ችለው እንዲደራጁ ተደርጓል።

​በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ ኢንጂነር ቸርነት ፍላቴ በበኩላቸው፣ የተደረገው የመዋቅር ጥናት የከተማዋን የስራ ክብደት፣ የህዝብ ቁጥር እድገትና የአገልግሎት ጥያቄ ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑን ገልጸዋል።

​ኢንጂነር ቸርነት አክለውም፣ ጥናቱ በክልል ምክር ቤት መፅደቁን ተከትሎ የቢፒአር ጥናቱን ወደ ተግባር በማስገባት የመደቦችን ደረጃ ማውጣት፣ የሰው ኃይል ብዛት መወሰን፣ እንዲሁም በተፈጠሩት መደቦች ላይ አመራርና ባለሙያ መመደብ ቀጣይ ተግባራት መሆናቸውን ጠቁመዋል።

​አዲሱ መዋቅር የሐዋሳ ከተማን የማዘጋጃ ቤታዊ አሰራር በማዘመን፣የስራ ክፍፍልንና ተጠያቂነትን በማጠናከር እና የከተማዋን የህዝብ ጥያቄ በተሻለ ደረጃ መመለስ በሚያስችል አግባብ የማዘጋጃ ቤታዊ አደረጃጀትን ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ከንቲባ ጥራቱ በየነ ከፖሊስ ማኔጅመንት አካላት ጋር በወቅታዊና በከተማዋ ፀጥታ ዙሪያ ውይይትና የምክክር መድረክ አካሄዱ​በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ የሀዋሳን ተፈጥሯዊ ተወዳጅነትና የታወቀው...
07/10/2026

ከንቲባ ጥራቱ በየነ ከፖሊስ ማኔጅመንት አካላት ጋር በወቅታዊና በከተማዋ ፀጥታ ዙሪያ ውይይትና የምክክር መድረክ አካሄዱ

​በመድረኩ ላይ እንደተገለጸው፣ የሀዋሳን ተፈጥሯዊ ተወዳጅነትና የታወቀውን የእንግዳ ተቀባይነት ባህል ለአለም ለማስተዋወቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ የከተማዋን በጎ ገጽታ፣ የህዝቡን ደህንነትና የእንግዶችን ሰላማዊ ቆይታ ማረጋገጥ ቀዳሚ ትኩረት ተሰጥቶታል።

​ከንቲባ ጥራቱ በየነ እንደገለጹት፣ አስተዳደሩ ህገወጥነትንና ህገወጥ አሰራርን የመከላከል ስራውን አጠናክሮ ይቀጥላል። አክለውም አልፎ አልፎ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በአስተማማኝ ሁኔታ ለመቅረፍ የከተማ አስተዳደሩ በሙሉ ቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋልለዚህም ስኬት ህብረተሰቡን ያሳተፈ የተቀናጀ አሰራር ስራ ላይ እንደሚውል ተመላክቷል ።

ዘመናዊና ስልጡን ከተማን ለመገንባትም ህግን የተከተለና እንከን የለሽ አሰራርን የመተግበር ስራ ከምንጊዜውም በላይ በትኩረት ይከናወናል ብለዋል።

​ህግን በማስከበርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሀዋሳን መልካም ገጽታ እና የህዝቦችን ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ እየተገነባ ባለው ዘመናዊ ከተማ ላይ ዘመኑን የሚመጥን የፖሊስ ተቋም ለመገንባት መስራት እንደሚገባም ከንቲባው ተናግረዋል።

​በተጨማሪም የማሕበራው ሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም የመንግስት መዋቅርና በህዝብ ዘንድ ጥርጣሬ ውስጥ እንዲወድቅ የሚያደርጉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡና የሲዳማ ክልል ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያስተላለፈውን ጥሪ፣ የከተማው አስተዳደር ለማስፈጸም ቁርጠኛ መሆኑ ተገልፃል።

​የውይይቱ ተሳታፊ የሆኑት የፖሊስ ማኔጅመንት አካላት በበኩላቸው፣ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማስጠበቅ፣ ወንጀልን ለመከላከልና የህዝቡን አደራ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንና በትጋት እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

የአባላት መረጃ ማዘመን ለዘመናዊ የፓርቲ አደረጃጀት ግንባታ በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ። የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የከተማ ማዕከል የብልፅግና ህብረት አመራሮችን በማ...
07/10/2026

የአባላት መረጃ ማዘመን ለዘመናዊ የፓርቲ አደረጃጀት ግንባታ በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ የከተማ ማዕከል የብልፅግና ህብረት አመራሮችን በማሳተፍ “የአባላት መረጃ ማዘመን ለዘመናዊ የፓርቲ አደረጃጀት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ውይይት አካሂዷል።

ውይይቱ የፓርቲ አባላት መረጃን በወቅቱ ማዘመን፣ የአባላት ዳታ ቤዝን ወቅታዊና ትክክለኛ ማድረግ እንዲሁም መደበኛ የፓርቲ አደረጃጀት ሥራዎችን በተጠናከረ አሠራር ማከናወን በሚቻልበት ላይ ያተኮረ ነበር።

የሀዋሳ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፍን አየለ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፣ የአባላት መረጃን በወቅቱና በትክክል ማዘመን የፓርቲውን የአደረጃጀት ሥራ በመረጃ ላይ በተመሠረተ መልኩ ለመምራት ወሳኝ ነው። የአባላት ዳታ ቤዝ በየጊዜው በመመርመርና በማዘመን የአባላትን ትክክለኛ መረጃ ማስጠበቅ የሚቻል ሲሆን፣ ይህም የአደረጃጀት አቅምን ለማጠናከርና የፓርቲ ሥራዎችን በመደበኛነት ለማስኬድ የሚያግዝ መሆኑን ጠቁመዋል።

አቶ መስፍን አየለ አክለውም፣ የአባላት መረጃ ማዘመን አንድ ጊዜ ተከናውኖ የሚቆም ሥራ ሳይሆን ቀጣይነትና መደበኛነት የሚፈልግ የአደረጃጀት ሥራ መሆኑን አስገንዝበዋል። በመሆኑም የከተማ ማዕከል የብልፅግና ህብረት አመራሮች የአባላት መረጃ በየጊዜው እንዲታደስና የዳታ ቤዝ አያያዝ ሥርዓቱ እንዲጠናከር በትኩረት እንዲሠሩ አሳስበዋል።

በውይይቱ የአባላት መረጃ ማዘመንና የዳታ ቤዝ አያያዝ ሥራዎች በመደበኛነት እንዲከናወኑ፣ የአባላት መረጃ ትክክለኛነትና ወቅታዊነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም የፓርቲ አደረጃጀት ሥራዎች በተቀናጀ አሠራር እንዲመሩ በሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር ተደርጓል።

Address

Awassa
0000

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Prosperity Party Hawassa City Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share