ANRS Occupational Competence Assessment and Certification Authority

Call Directions Website Contact the organization

ANRS Occupational Competence Assessment and Certification Authority Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ANRS Occupational Competence Assessment and Certification Authority, Government Organization, Ethiopia, Bahir Dar.

ተልዕኮ፡-
በመደበኛ፣ መደበኛ ባልሆኑ የሥልጠና ፕሮግራሞች እና በኢ-መደበኛ መንገድ በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ ሙያው የሚጠይቀውን ዕውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ላካበቱ ባለሙያዎች በአገር አቀፍ የሙያ ደረጃዎች ላይ የተመሠረተ የሙያ ብቃት ምዘና እና ብቁ ለሆኑት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በመስጠት ብቃቱ የተረጋገጠ ባለሙያ ለገበያው እንዲቀርብ በማድረግ የኢንዱስትሪውን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣

ራዕይ፡-

በ2022 ብቃቱ የተረጋገጠና በገበያ ተወዳዳሪ የሆነ ባለሙያ በኢንዱስትሪው ተገንብቶ ማየት፣

እሴቶች፡-

· ቅንነት፣

· ታማኝነት፣

· በቡድን የመስራት ባህል፣

· አዳዲስ እውቀቶችንና ክህሎቶችን መማር፣

· ኪራይ ሰብሳቢነትን መታገል፣

· ጥራትና ተወዳዳሪነት፣

· በሥነምግባር መረሆዎች መመራት፣

· በብቃት ማመን፣

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሥራ ላይ ያሉ የሆቴል ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ የኩባንያ ውስጥ ሥልጠና ሊሰጥ ነው።ደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በሥራ ላይ ...
26/10/2026

የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሥራ ላይ ያሉ የሆቴል ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ የኩባንያ ውስጥ ሥልጠና ሊሰጥ ነው።

ደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ በሥራ ላይ ለሚገኙ ባለሙያዎች የኩባንያ ውስጥ ሥልጠና (In-Company Training) ለመስጠት ከሀይሌ ሆቴልና ከደብረ ብርሃን ከተማ ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ተወካዮች ጋር በጋራ ውይይት አካሄደ።

ውይይቱ በሀይሌ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን፣ በመድረኩም የሆቴሉ የምግብና መጠጥ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ፣ የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን፣ የኮሌጁ የሆቴልና ቱሪዝም ዲፓርትመንት ኃላፊ እና የከተማው ባህልና ቱሪዝም ዘርፍ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በውይይቱም በሆቴል ዘርፍ በሥራ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች ያላቸውን የሙያ ክፍተት በመለየት፣ የአቅም ግንባታ ሥልጠና በመስጠት የአገልግሎት ጥራትንና የሙያ ብቃትን ለማሳደግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የኩባንያ ውስጥ ሥልጠና (In-Company Training) ልዩ ባህሪው ባለሙያዎች ከሥራ ቦታቸው ሳይለዩ፣ በተለመዱት የሥራ ሂደቶች ውስጥ ተግባራዊ ሥልጠና እንዲያገኙ ማስቻሉ ነው። ሥልጠናውም በዘርፉ የሚታዩ የክህሎት ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ዘመናዊ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማስፋፋትና ባለሙያዎች በሥራቸው የበለጠ ብቃት እንዲያሳዩ ለማገዝ ያለመ ነው።

በቀጣይም በተመረጡ 10 ከፍተኛ የሆቴል ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ሥልጠናውን ለመተግበር የዝግጅት ሥራዎችን ለማከናወን በውይይቱ ተነስቷል። ሥልጠናውም በኮሌጁ ባለሙያዎች የሚሰጥ ሲሆን፣ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የሚገኙ የሥራ ላይ ባለሙያዎችን ብቃት ለማሳደግ ይጠበቃል።

የኩባንያ ውስጥ ሥልጠናው በሆቴል ዘርፍ የተጀመረ ሲሆን፣ በቀጣይ በሌሎች የኢንዱስትሪ ዘርፎችም በማስፋፋት በሥራ ላይ ያሉ ባለሙያዎች ከዘመኑ የሙያ ፍላጎትና የኢንዱስትሪ ደረጃ ጋር የሚጣጣም ክህሎት እንዲያጎለብቱ ለማስቻል ታቅዷል።

መረጃው የደብረ ብርሃን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ህዝብ ግንኙነት ነው።

የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።የፌዴራል እና የክልል እንዲሁም የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደጀን ከተማ እየተገነባ የሚገኘው...
26/10/2026

የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካን በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው።

የፌዴራል እና የክልል እንዲሁም የምሥራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በደጀን ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካን የግንባታ ሂደትን ጎብኝተዋል፡፡፡
‎
‎የዓባይ ሲሚንቶ ፋብሪካ የግንባታ ሂደት 65 በመቶ ላይ ደርሷል መድረሱ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል።
‎
‎በክልሉ ብሎም በሀገር አቀፍ ደረጃ ለግንባታው ዘርፍ ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል ተብሎ የሚጠበቀው ይህን ግዙፍ ፕሮጀክት በ2019 ዓ.ም መጨረሻ ላይ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡

በጉብኝት መርሐ ግብሩ ላይ የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማኅበር የቦርድ ሠብሣቢ መላኩ አለበል፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ዋለ አባተን ጨምሮ የዓባይ ሲሚንቶ ፕሮጀክት ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር አስራት ኪዳኔ እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

26/10/2026
“የሠራተኞችን መብት ማከበርና ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ የኢኮኖሚ ሉዐላዊነትን ለማረጋገጥ መሠረት ነው” — ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ​የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ...
26/10/2026

“የሠራተኞችን መብት ማከበርና ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ የኢኮኖሚ ሉዐላዊነትን ለማረጋገጥ መሠረት ነው” — ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ
​
የአብክመ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ እና ከኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ጋር በመተባበር በአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ አሠሪዎች፣ የሠራተኞች ተወካዮች እና የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚዎች የተሳተፉበት አጠቃላይ የጋራ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ ላይ በተደረጉ ውይይቶች የኢንዱስትሪ ሰላም ከተራ የዕለት ተዕለት ግንኙነት ባሻገር ለአንድ አገር ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትና ማኅበራዊ መረጋጋት ዋና መሠረት መሆኑ በሰፊው ተመልክቷል።

የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር፣ የሠራተኞችን መብትና ጤንነት ማስጠበቅ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ዋነኛ ተግባርና ኃላፊነት መሆኑን ጠቁመዋል።

አክለውም በሥራ ቦታዎች ላይ አስተማማኝ የኢንዱስትሪ ሰላምን በማረጋገጥ አገራዊ ምርታማነትን ማሳደግ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልጸው፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 92 መሠረት ሠራተኞች የሙያ ደኅንነታቸውና ጤንነታቸው ተጠበቆ እንዲሠሩ የሕግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ መገባቱን አብራርተዋል።
​
በአንዳንድ ድርጅቶችና አሠሪዎች በኩል የሚታዩ የሥራ ላይ ደኅንነት መሣሪያዎችን በአግባቡ አለማቅረብ ክፍተቶች በአስቸኳይ ሊታረሙ እንደሚገባ የቢሮ ኃላፊው አሳስበው የሠራተኞችን መብት ማከበርና ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ ለኢኮኖሚ ሉዐላዊነትን ለማረጋገጥ መሠረት ነው እንደሆነ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

ሠራተኞች የደኅንነት መጠበቂያዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል የግንዛቤ ፈጠራ ሥራ መስራት እንዳለባቸው እና በዚህም በሥራ ላይ የሚደርሱ አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ኢንዱስትሪ ማለት የአሠሪ እና የሠራተኛ የተቀናጀ ውጤት መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ስቡህ፣ በመካከላቸው ያለው መልካም ግንኙነት የምርት መጠንና ጥራትን ለመጨመር፣ የሠራተኞችን ተነሳሽነት ለማሳደግና በትጋት በመሥራት ለጋራ ውጤታማነት የሚያበቃ መስተጋብር መሆኑን ገልጸዋል።

አምራች ኢንዱስትሪው ተኪ ምርቶችን በሰፊው እንዲያመርት የሠራተኞችን ክህሎት ማላቅና አሠራሩን በቴክኖሎጂ መምራት እንደሚገባ በመጠቆም፣ የተሳለጠ የኢንዱስትሪ ግንኙነት መፍጠር አገራዊ ምርትን ለማሳደግ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና በውጭ ንግድ አማራጮች የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል።

በሌላ በኩል የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሀመድአሚን የሱፍ በከተማዋ በሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሳለጠ ግንኙነት መፍጠር ለከተማዋም ሆነ ለአገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ቀጣይነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፣ ከተማ አስተዳደሩ ለዚህ ስኬት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ አቶ ይትባረክ ጌታሁን በበኩላቸው የሠራተኞችን ክህሎት ማላቅና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር መተግበር ተኪ ምርቶችን ለማምረት ቁልፍ መሆኑን በመጠቆም፣ በ2019 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ከ6 ሺህ 170 በላይ ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደሚገኙ ገልጸዋል።
​
በምክክር መድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአሠሪዎች እና የሠራተኞች ተወካዮች የሠራተኞች የሥራ ላይ ደኅንነት መጠበቅ ለድርጅቶች ምርታማነት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

"የሠራተኞችን መብት ማከበርና የሥራ ላይ ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ የተሻለ ምርታማነትን ከመፍጠሩም በላይ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለዘላቂ ብልፅግና ጠንካራ መሠረት ነው"የአማራ ክልል ሥራና ...
26/10/2026

"የሠራተኞችን መብት ማከበርና የሥራ ላይ ደኅንነታቸውን ማረጋገጥ የተሻለ ምርታማነትን ከመፍጠሩም በላይ ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት እና ለዘላቂ ብልፅግና ጠንካራ መሠረት ነው"

የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር)

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት መምሪያ ከኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ጋር በመተባበር በአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች፣ አሠሪዎች፣ ሠራተኞች ተወካዮች እና የመንግሥት ሥራ አስፈጻሚዎች ጋር የጋራ የምክክር መድረክ አካሂደዋል።

የኢንዱስትሪ ሰላም ከተራ ግንኙነት በላይ በመሆኑ ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ እድገት መሠረት መሆኑን በመድረኩ ላይ ተመልክቷል።

የአማራ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) እንደገለፁት የሠራተኞችን መብትና ጤንነት ማስጠበቅ የመንግሥት የመሥሪያ ቤቶች ዋነኛ ተግባር መሆኑን በመጠቆም፣ የኢንዱስትሪ ሰላምን በማረጋገጥ ምርታማነትን ማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን ገልፀዋል።

በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ ቁጥር 1156/2011 አንቀጽ 92 ሠራተኞች የሙያ ደህንነታቸውና ጤንነታቸው ተጠበቆ እንዲሠሩ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቶለት ወደ ስራ መገባቱን አብራርተዋል።

​በአንዳንድ ድርጅቶች እና አሠሪዎች በኩል የሚታዩ የሰራተኞች የሥራ ላይ የደህንነት መሣሪያዎችን በአግባቡ አለማቅረብ ክፍተቶችን ማረም ይገባል ብለዋል። አያይዘውም የሥራ ላይ ደህነት መሳሪያዎቹን አጠቃቀም ሠራተኞች በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ በሥራ ላይ አደጋ እንዳይገጥም የግንዛቤ ፈጠራ ስራ መስራት እንደሚገባ አብራርተዋል።

ኢንዱስትሪ የድርጅቱ የአሠሪ እና የሠራተኛ ቅንጅት ሲሆን፣ በመካከላቸው ያለው መልካም ግንኙነት ​የምርት መጠን እና ጥራትን ለመጨመር ፣ የሠራተኞች ተነሳሽነት ለማሳደግ ፣ሠረተኝች በትጋትና በትኩረት በመስራት ለጋራ ውጤታማነት የሚደረግ መልካም መስተጋብር ነው ብለዋል።

ኢንዱስትሪው ተኪ ምርቶችን በሰፊው እንዲያመርቱ የሠራተኞችን ክህሎት ማላቅና በቴክኖሎጂ መር አሠራር መመራት እንዳለበት የገለፁት ቢሮ ኃላፊው የተሳለጠ የኢንዱስትሪ ግንኙነት መፍጠር የሀገር ውስጥ ምርት ለማሳደግ ፣ ሰፊ የሥራ ዕድል ለመፍጠር እና የውጭ ንግድ አማራጮች በመፈለግ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል ።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሙሀመድአሚን የሱፍ በበኩላቸው በከተማዋ በሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሳለጠ ግንኙነት መፍጠር ለከተማዋም ሆነ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ቀጣይነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተማ አስተዳደሩ የተሳለጠ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እንዲኖር አስፈላጊውን ድጋፍ ይደርጋል ብለዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ሥራና ክህሎት መምሪያ ኃላፊ​አቶ ይትባረክ ጌታሁን በሰጡት አስተያየት የሠራተኞችን ክህሎት ማላቅ፣ የሥራ ቦታ ደህንነትን ማረጋገጥና በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርን መተግበር ተኪ ምርቶችን ለማምረትና ድርጅቶችን ለማሳደግ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በ2019 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ ቁጥጥር የሚደረግባቸው ከ6ሸህ 170 በላይ ከፍተኛ፣ መካከለኛ እና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች/ድርጅቶች እንደሚገኙ አብራርተዋል።

በምክክር መድረኩ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት የአሠሪዎች እና የሠራተኞች ተወካዮች በበኩላቸው፣ የሠረተኞች የሥራ ላይ ደህንነት መጠበቅ ለድርጅቶች ምርታማነት መረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል። ድርጅቶች ምርታማ ከሆኑ የሰራተኛውን መብት ለማክበር አስፈላጊ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ግምገማ አካሄደ የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና ...
24/10/2026

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ዕቅድ ግምገማ አካሄደ

የጎንደር ሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ከኮሌጅ ዲኖችና ከኢንዱስትሪና ኢንተርፕራይዝ ምዘና ማዕከላት ኃላፊዎች ጋር ገምግሟል።

በመድረኩ የሙያ ብቃት ምዘና ጥራትንና ፍትሐዊነትን ለማረጋገጥ እየተጋጠሙ ባሉ ተግዳሮቶች፣ የምዘና ማዕከላትን በማቋቋምና ወደ ተግባር በማስገባት ረገድ ባሉ ውስንነቶች እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት ሊሰጣቸው በሚገቡ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ተካሂዶ የጋራ መግባባት ተደርሷል።

በተጨማሪም የዶሜስቲክ ወርክ ሥልጠናና ምዘና አፈጻጸም ለውይይትና ለግምገማ የትኩረት ነጥብ ተደርጎ ተነስቷል።

የክላስተር ማዕከሉ ኃላፊ ወ/ሮ ፀሐይ አምሳሉ፣ ማዕከሉ ለመድረኩ ያስቀመጠውን ዓላማ ማሳካት መቻሉን ገልጸዋል።

በውይይቱ ለተነሱት ጉዳዮች ማብራሪያ በመስጠትና የቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎችን በማመላከት፣ የኮሌጅ ዲኖችና የምዘና ማዕከላት ኃላፊዎች በመድረኩ የተነሱ ጉዳዮችን ወደ ተግባር በመቀየር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል ሲል የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

"አማራ ክልል እንዲህ አይነት ጉባኤ በማዘጋጀቱ ኩራት ይሰማዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ12ኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ ጸጥታ ፎረም "የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እ...
24/10/2026

"አማራ ክልል እንዲህ አይነት ጉባኤ በማዘጋጀቱ ኩራት ይሰማዋል" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

12ኛው የጣና ከፍተኛ የአፍሪካ ጸጥታ ፎረም "የሰላም መንገዶች በአፍሪካ፦ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካ ሽግግር" በሚል መሪ መልዕክት በባሕር ዳር እየተካሄደ ነው።

በፎረሙ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ተገኝተዋል።

በፎረሙ መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ወደ ባሕርዳር ስለመጣችሁ ደስ ብሎኛል ነው ያሉት።

ጣና ፎረም የአፍሪካ መሪዎችን በአንድ አሠባሥቦ ስለ አፍሪካ የሚመከርበት መድረክ መኾኑን ገልጸዋል። ጣና ፎረም ሲመሠረት መሠብሠቢያ ባሕር ዳርን መምረጡን አስታውሰዋል።

ፎረሙ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎች ለመስጠት የሚደረግ መኾኑንም ገልጸዋል።

ሰላም የሚሰፍነው በአዋጅ አይደለም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ሰላም የሚሰፍነው ተግባራዊ ርምጃዎች ሲኖሩ መኾኑን አመላክተዋል። ሰላም እና ልማት የማይነጣጠሉ መኾናቸውን እንገነዘባለን ነው ያሉት።

የአማራ ክልል ብሎም የኢትዮጵያን አስተማማኝ ሰላም ለማረጋገጥ እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል። ፎረሙ ለሰላም እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ እናደንቃለንም ነው ያሉት።

ባሕር ዳር ለውይይት የተመቸች፣ ጥልቅ የኾነ ታሪክ እና ተፈጥሮ ያለባት ከተማ ናት፤ ባሕር ዳር የጥንታዊ ገዳማት እና በርካታ ቅርሶች መገኛ መኾኗንም ተናግረዋል። ባሕር ዳር የምትታወቀው በትምህርት ከተማነቷ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ባሕርዳር የሥብሠባ እና የጉብኝት ማዕከል እንድትኾንም እየሠሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።

የአማራ ክልል እንዲህ አይነት ጉባኤ በማዘጋጀቱ ኩራት ይሰማናል፤ ወደፊት መስተንግዶው እየላቀ፣ መድረኩም የበለጠ እያደገ እንደሚሄድ ተስፋ እናደርጋለን ነው ያሉት።

ወደ ባሕር ዳር መምጣታችሁ ትርጉም ያለው ትስስር ለመፍጠር ያስችላልም ነው ያሉት። እንግዶች በባሕር ዳር እና አካባቢው ያለውን ሀብት እንዲጎበኙ፣ የክልሉን ባሕል እና እሴት እንዲያዩም ጥሪ አቅርበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል።

አፍሪካውያን መሪዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ከተማዋ ባሕር ዳር ተገናኝተው እየመከሩ ነው።12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ...
24/10/2026

አፍሪካውያን መሪዎች በጣና ሐይቅ ዳርቻ ከተማዋ ባሕር ዳር ተገናኝተው እየመከሩ ነው።

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ተጽዕኖ ፈጣሪ ምሁራን በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

12ኛው የአፍሪካ ደህንነት ጉባኤ ጣና ፎረም “የሰላም መንገዶች በአፍሪካ - የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት እና የጂኦፖለቲካዊ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል ነው የሚካሄደው።

በጉባኤው ወቅት ተሳታፊዎቹ በአህጉሪቱ ዘላቂ ሰላምና ደህንነትን ማስፈን፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፈጣን ለውጥና ሽግግር በማሳየት ላይ ባለው ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት ውስጥ አፍሪካ ሊኖራት ስለሚገባው ስትራቴጂካዊ ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች በሰፊው ይመክራሉ።


!
!🇪🇹

የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ማጠናከር ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና ትኩረት ተሰጥቶታል።የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደ...
24/10/2026

የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትን ማጠናከር ለዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያለው ሚና ትኩረት ተሰጥቶታል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል በመግባባትና በመተማመን ላይ የተመሠረተ ጤናማ ግንኙነት መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ኃላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) በበኩላቸው፣ የሠራተኞችን መብት፣ ጤናና ደኅንነት ማስጠበቅ የምርት ጥራትንና ውጤታማነትን ከማሳደግ ባለፈ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማፋጠን ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

ቢሮውም ከኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በመተባበር የሥራ ሰላምን ለማስፈንና የኢንዱስትሪ ምርታማነትን ለማሳደግ እየሠራ መሆኑን አመልክተዋል።

በመድረኩ የክልልና የከተማ አመራሮች፣ የፋብሪካ ባለቤቶችና ተወካዮች እንዲሁም የሠራተኛ ማኅበራት አመራሮች ተሳትፈዋል ሲል አማራ ኮሙኒኬሽን ዘግቧል።

23/10/2026

Address

Ethiopia
Bahir Dar
6000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ANRS Occupational Competence Assessment and Certification Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to ANRS Occupational Competence Assessment and Certification Authority:

Shortcuts

Share