Mershu z great

Call Directions Contact the organization

Mershu z great ወቅታዊና ትክክለኛ መረጃን እናደርሳለን

26/09/2026

ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ!
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሠላም አደረሳችሁ!!!

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል ጋር የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ሰጠየኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ...
25/09/2026

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል ጋር የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ሰጠ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ የጋራ ግብረ ኃይል (CJTF-HOA) ጋር በመተባበር ያዘጋጀውን 7ኛ ዙር የጋራ የልምድ ልውውጥ ሥልጠና ሰጥቷል።

ከተለያዩ የሠራዊቱ ክፍሎች ለተውጣጡ አመራሮችና አባላት የተሰጠው ይህ ሥልጠና፤ በዘመናዊ የመገናኛና የመረጃ ቴክኖሎጂ ሥርዓቶች፣ የመከላከያ ተቋሙን የመገናኛ አውታረ መረብ ብቃት በማሳደግ፣ የመረጃ ፍሰትን በማፋጠን እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን በማጠናከር ላይ ያተኮረ መሆኑ ተገልጿል።

በሥልጠናው ማጠቃለያ መርሃ ግብር ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ የመከላከያ ወታደራዊ አታሼ ኮሎኔል ማቲው ኮፕ፤ ሥልጠናው በተሳታፊ ሀገራት መካከል የእውቀትና የልምድ ልውውጥን በማጠናከር የጋራ አቅምና ወታደራዊ ትብብርን ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ገልጸዋል።

ባለሙያዎች በበኩላቸው መሰል ሥልጠናዎች የመከላከያ ተቋሙን የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና ተግባራዊ ብቃት በማጠናከር ለሀገራዊ ደህንነት ያለውን አስተዋጽኦ እንደሚያጎለብቱ አብራርተዋል።

https://t.me/addisreporter2

25/09/2026
የአማራ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር  የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አደረገ=========//========​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ልማት ክላስተር...
14/09/2026

የአማራ ክልል የገጠር ልማት ክላስተር የ2018 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2019 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አደረገ
=========//========
​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ልማት ክላስተር የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የ2019 ዓ.ም እቅድ ረንቴሽን

ኦንቴሽን በባህር ዳር ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ​በመድረኩ የተገኙ ከፍተኛ አመራሮች፦
​ዶ/ር ድረስ ሳህሉ – በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ፣ ​አቶ ደረጀ ማንደፍሮ – የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ እና ​ሌሎች የገጠር ልማት ክላስተር ተቋማት የቢሮ ኃላፊዎችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። በመድረኩ የ2018 ዓ.ም የገጠር ክላስተር ልማት አፈጻጸም በሰፊው የተገመገመ ሲሆን፣ የ2019 ዓ.ም ዝርዝር እቅድና የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ለተሳታፊዎች "ሰፊ ኦሬንቴሽን እየተሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ በሴክተሮች ለስራ ፍሰት ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን፣ የሀብትና የግብዓት እጥረቶችና የእርስ በእርስ የግንኙነት ክፍተቶችን በጋራ ለመፍታትና ግልጽ የሆነ የአሰራር ስርዓት መግባባት ላይ የተደረሰ ሲሆን
ወደፊት ትኩረት ተደርጎ መሠራት ያለባቸው ነጥቦች
✍️​መልካም አጋጣሚዎችንና እድሎችን በሙሉ አቅም አቅዶ መፈጸም
✍️የቅንጅትና የትብብር ተብለን ብሎም የጋራ ኃላፊነት እና ቅንጅታዊ አሰራር መከተል የግድ እንደሚል
✍️በጎ እድሎችን፣ የቴክኖሎጂ አማራጮችንና አጋር አካላትን አስተባብሮና መምራትን በመገንዘብ የሴክተሮች ቅንጅት ለጠቅላላው ተቋማዊ ስኬት ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ መምራት እንደሚገባ ሲጠቃለል ​ተቋማት የተጣለባቸውን ህዝባዊ አደራና ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት ተቋማት አሰራራቸውን ከፍትሃዊ አገልግሎት አሰጣጥና ተጠቃሚነት አኳያ አገናዝቦ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተመላክቷል።
ዘመናዊ ግብርና ለሁለንተናዊ ብልጽግና !!
​ዘገባው የግብርና ቢሮ ነው!

11/09/2026
11/09/2026

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!!

አዲስ ዓመት የበለጠ ተስፋ የምንሰንቅንበት፣ ቂምና ጥላቻን በይቅርታ ሽረን በአብሮነት የምንሻገርበት ጊዜ ይሁንልን።

አዲሱ ዓመት ለመጪው ትውልድ አሻራ የምናስቀምጥበት፤ ያለንን ዕምቅ የመልማት ፀጋ ከሕዝባችን አቅም ጋር አቀናጅተን በመጠቀም ልማታችን የምናፋጥንበት ዓመት ይሆናል።

ዘላቂ ሰላማችን አፅንተን፤ አብሮነታችንና ትብብራችንን ካጠናከርን ከፊት ለፊታችን አዲስ ድልና ስኬት ይጠብቀናል። ለዚህም ቃላችን ጠብቀን የተሻለ ዘመን ለመፍጠር አልቀን እንሰራለን።

ስለሆነም ያአጋጠሙንን ሳንካዎች ተሻግረን፤ ጉድለቶቻችንን አርመን፤ ስኬቶቻችንን የሞራል ስንቅ አድርገን በ2019 የላቀ ውጤት ለማምጣት በቁጭት እንተጋለን።

አዲሱ ዓመት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ትብብራችን እና አብሮነታችን የበለጠ የሚጠናከርበት፤ የእድገትና የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ።

መልካም አዲስ ዓመት!

"የደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን ማረፊያ ፋይዳው ብዙ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው...
12/07/2026

"የደብረ ማርቆስ የአውሮፕላን ማረፊያ ፋይዳው ብዙ ነው" ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የደብረ ማርቆስ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አውሮፕላን ማረፊያን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

በማስጀመሪያ ሥነ ሥርዓቱ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በተጨማሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ደብረ ማርቆስ ከተማ የጎጃም ክፍለ ሀገር መቀመጫ ኾና ለረጅም ጊዜ ያገለገለች ፣ ማዕከላዊ መንግሥቱን ከሰሜን ምዕራብ ጋር ስታገናኝ የኖረች ናት ብለዋል።

በውስጧ ታሪካዊ እና መንፈሳዊ ሃብቶችን ያቀፈች መኾኗንም ገልጸዋል። ከዓመታት በፊት የአየር መንገድ ተጠቃሚ የነበረች ቢኾንም በመካከል ተቋርጦ የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ መኖሩን አንስተዋል።

ደብረ ማርቆስ የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት እንደኾነች ያነሱት ርእሰ መሥተዳድሩ የደብረ ማርቆስ ከተማ ሕዝብ የአውሮፕላን ማረፊያ ጥያቄን ለዓመታት ሲጠይቅ ቆይቷል፤ ነገር ግን አይኾንም የሚል ተስፋ አስቆራጭ መልስ ይሰጠው እንደነበር አንስተዋል።

አሁን ግን ያ ተስፋ ጥያቄ መልስ አግኝቶ የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ ተገንብቶ ለአገልግሎት መብቃቱን ገልጸዋል።

ከዓመታት በፊት አይኾንም የተባለው ተስፋ አስቆራጭ ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ላደረጉት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ምሥጋና ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ዛሬ የተመረቀው የአውሮፕላን ማረፊያ ፋይዳው ብዙ ነውም ብለዋል። የተጋመደች ኢትዮጵያን የበለጠ ለማስተሳሰር፣ ማኅበራዊ ትስስርን ለማጠናከር እና ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግም አንስተዋል።

አሁን የሕዝብ ጥያቄ ተመልሷል፤ ሌሎች ጥያቄዎችም ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ ተስፋ አለኝ፤ ነገር ግን የልማት ሥራዎችን ለማረጋገጥ ሰላምን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት። በአማራ ክልል በሕዝብ ስም የሚንቀሳቀሱ አሜካላዎች አሉ፤ ሕዝባችን በስቃይ ውስጥ እንዲኖር የሚያደርጉ ናቸው፤ እነዚህን መታገል እና ሰላምን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ነው ያሉት። ሕዝቡ አሜካላዎችን እንዲታገላቸው እና ሰላሙን እንዲያረጋግጥም አሳስበዋል።

የአውሮፕላን ማረፊያው ምርት እና ምርታማነትን እንድናሳድግ የሚያስገድድ ነው ብለዋል። ምርት እና ምርታማነትን ማሳደግ ከሁሉም የሚጠበቅ መኾኑንም አንስተዋል። የደብረ ማርቆስ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲጠናቀቅ ላደረጉ ሁሉ ምሥጋና አቅርበዋል።

#ንጉሥተክለሃይማኖትአውሮፕላንማረፊያ

#ባሕር ዳር:ሐምሌ 05/2018 ዓ.ም

Address

Bahir Dar

Telephone

+251911974850

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Mershu z great posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Mershu z great:

Shortcuts

Share