Guagusa Shikudad Prosperity

Call Directions Website Contact the organization

Guagusa Shikudad Prosperity Political Party
(1)

ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ዐቢይ አሕመድን (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ሠርተዋል።

ሀገር በቀል የመደመር የፖለቲካ እሳቤ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲኾን አስችለዋል።

የጥል ግድግዳ እናፍርስ፤ የፍቅር ድልድይ እንገንባ በሚለው መርሐቸው ለዓመታት ተራርቀው የነበሩ ፖለቲከኞችን አገናኝተዋል። በሥልጣን ዘመናቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በሀገሪቱ ሥልጣን እንዲይዙ እና ሀገር እንዲያገለግሉ አድርገዋል።

በከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበረውን የሕዳሴ ግድብ ከችግር በማውጣት እንዲጠናቀቅ አመራር ሰጥተዋል። ከሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ማግስት ታላላቅ ፕሮጄክቶችን አስጀምረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ አጽፈዋል። ኢትዮጵያን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ኢኮኖሚ በማሸጋገር አስደናቂ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖራት አድርገዋል። በከተማ እና በገጠር ኮሪደር ልማቶች የኢትዮጵያን ገጽታ በከፍተኛ ሁኔታ ቀይረዋል። የኢትዮጵያን ከተሞች ከተጎሳቆሉበት አውጥተው ወደ ውብ እና ሳቢ ገጽታ መልሰዋል።

ኢትዮጵያ የስንዴን ምርት ከውጭ መቀበል አቁማ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር ያደረጓት በእርሳቸው የሥልጣን ዘመን ነው። በሌማት ቱሩፋት መርኃ ግብርም በእንስሳት ሃብት ሀገሪቱ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን እድገት እና ለውጥ አምጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸው ታላላቅ ሀገራዊ ሥራዎችን ያሳኩ ዘንድ በድጋሜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ተሹመዋል።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹

መረጃ ሹመትበአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት  ወ/ሮ የሻሽወርቅ መላኩ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥተዋል። ...
05/10/2026

መረጃ ሹመት

በአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወ/ሮ የሻሽወርቅ መላኩ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥተዋል።

•••
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•••

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!አቶ  በእውቀት ገዛኸኝ  የአዊ ብሄ/አስ ምክትል አስተዳዳሪ ኾነው ተሾሙ። አቶ በእውቀት ገዛኸኝ  የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ እና ንግድና ገበያ ...
05/10/2026

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

አቶ በእውቀት ገዛኸኝ የአዊ ብሄ/አስ ምክትል አስተዳዳሪ ኾነው ተሾሙ።

አቶ በእውቀት ገዛኸኝ የአዊ ብሄ/አስ ዋና አስተዳዳሪ እና ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ ኾነው ተሹመዋል።

የአዊ ብሄረሰብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ የመንግስት ምስረታ ጉባኤ አካሂዷል።

ምክር ቤቱ አቶ በእውቀት ገዛኸኝ እሽቴን የአዊ ብሄ/አስ ም/አስተዳዳሪና ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሀላፊ አድርጎ ሹሟል።

አቶ በእውቀት ገዛኸኝ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የኢንስፔክሽንና ሥነ-ምግባር ኮሚሽን ሀላፊ ሁነው ያገለገሉ ናቸው።

ለጤና ተቋማት የሚደረገው የሶላር ሃይል ድጋፍ በማንኛውም ሰዓት ተገቢ የሆነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ፡፡  አቶ በቃሉ የኔአለም የጉሻ ጤና ጣቢያ ዳይሬክተርበአዊ ብሔረሰብ...
03/10/2026

ለጤና ተቋማት የሚደረገው የሶላር ሃይል ድጋፍ በማንኛውም ሰዓት ተገቢ የሆነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነው ፡፡ አቶ በቃሉ የኔአለም

የጉሻ ጤና ጣቢያ ዳይሬክተር

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ዩኒሴፍ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሰናይ ድርጅት ለጉሻ ጤና ጣቢያ የሶላር ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ፡፡

ትልቅ የመልካም አስተዳደር ችግር የነበረዉን የመብራት መቆራረጥ የሚፈታ 24 የሶላር ምጣድ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን በገንዘብ ሲተመንም ከ13 ሚሊየን ብር በላይ ይሆናል ብለዋል ዳይሬክተሩ። አሁን ላይ የዝርጋታ ስራዉም ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩንም ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለዉም የተደረገልን የሶላር ድጋፍ በሁሉም ክፍሎች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሀቅም ያለው ሶላር በመሆኑ በማንኛውም ሰዓት ተገቢ የሆነ የህክምና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ነዉ ብለዋል።ጤና ጣቢያ ይህን ሶላር ተጠቅሞ ከ24ሺህ 151 በላይ የሚሆን የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

በመጨረሻም የጤና ጣቢያዉ ዳይሬክተር ይህን ድጋፍ ላደረገዉ ለዩኒሴፍ ድርጅት በተቋሙ ስም ከልብ የመነጨ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡

‎

መረጃ ሹመትበአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋሁን ተሰማ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥ...
03/10/2026

መረጃ ሹመት

በአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋሁን ተሰማ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥተዋል።

•••
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•••

 #በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ "በፅምዶ ስም ጦርነት ያወጁብንን ታሪካዊ ጠላቶቻችን በጋራ ክንዳችን በመመከትና በመደምሰስ አንፀባራቂ ድል እናስመዘግባለን" በሚል  መሪ ሃ...
01/10/2026

#በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ "በፅምዶ ስም ጦርነት ያወጁብንን ታሪካዊ ጠላቶቻችን በጋራ ክንዳችን በመመከትና በመደምሰስ አንፀባራቂ ድል እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ሃሳብ ከንግድ ማህብረሰብ ጋር ውይይት ተካሄደ።

መድረኩን የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው አለሙ የመሩት ሲሆን የንግዱ ማህበረሰብ ለህገ ወጦች መጠቀሚያ ከመሆን እራሱን ሊያቅብ እንዲገባና ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የወገነን ጠላት በጋራ መታገል እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት አፀደቀርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት ተሿሚዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። ምክር ቤቱም ...
01/10/2026

የአማራ ክልል ምክር ቤት የክልሉን የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት ሹመት አፀደቀ

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመሥተዳድር ምክር ቤት አባላት ተሿሚዎችን ለምክር ቤቱ አቅርበዋል። ምክር ቤቱም የቀረበውን ሹመት ተቀብሎ አጽድቋል።

በዚህም መሰረት፡-

1. የአብክመ ግብርና ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር መስፍን አበጀ ተፈራ
2. የአብክመ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ኢብራሂም መሀመድ እንድሪስ
3. የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ= አቶ እንድሪስ አብዱ አህመድ
4 የአብክመ መሬት ቢሮ ኀላፊ = አቶ ሲሳይ ዳምጤ አበባዬ
5 የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ = ዶ/ር ሞላ መልካሙ ከበደ
6. የአብክመ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ዳኝነት ፈንታ መኮነን
7. የአብክመ ማዕድን ቢሮ ኀላፊ = አቶ ሃይሌ አበበ ብዙዓየሁ
8. የአብክመ መንገድ፣ ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ቢሮ ኀላፊ = ዶ/ር ጋሻው አወቀ ትኩየ
9. የአብክመ ስራና ክህሎት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ስቡህ ገበያው ታረቀ
10. የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኀላፊ = አቶ አታላይ ጥላሁን ጫኔ
11. የአብክመ ገቢዎች ቢሮ = አቶ ጥላሁን ፈንታው ተሾመ
12 የአብክመ ትምህርት ቢሮ ኀላፊ = አቶ ጥላሁን ወርቅነህ ተክሌ
13. የአብክመ ጤና ቢሮ ኀላፊ = አቶ አብዱከሪም መንግስቱ ይማም
14. የአብክመ ፍትህ ቢሮ ኀላፊ = አቶ ብርሃኑ ጎሽም አዘረፍ
15. የአብክመ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ = ዶ/ር እሸቱ የሱፍ አየለ
16. የአብክመ ሴቶች፣ ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኀላፊ = ወ/ሮ ብርቱካን ሲሳይ እንየው
17. የአብክመ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ኀላፊ= አቶ አባይ መንግስቴ ሰላምሰው
18. የአብክመ ሲቪል ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኀላፊ= ወ/ሮ ባንቻምላክ ገ/ማርያም በላይ
19. የአብክመ ፕላንና ልማት ቢሮ ኀላፊ =ዶ/ር ደመቀ ቦሩ ባህሩ
20. የአብክመ ባህል፣ ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ = አቶ መልካሙ ጸጋየ ገላው
21. የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ቢሮ ኀላፊ= ዶ/ር ጋሻው ሙጭ አለምነው
22.የአብክመ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኀላፊ=ዶ/ር የሻለም ገዛኸኝ ዳምጠው
23. የአብክመ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን = አቶ ተስፋሁን አለምነህ ይስማው በመሆን ተሹመዋል፡፡


‎ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ያልተገባ ጋብቻ መፈፀም ለዘመናት ህይወቱን የገበረበትን ፣ደሙን ያፈሰሰበትን፣ አጥንቱን የከሰከሰበትን የአማራን ህዝብ ክብር፣እሴትና ማንነት መካድ እንደሆነ ተገለፀ።...
01/10/2026

‎ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ያልተገባ ጋብቻ መፈፀም ለዘመናት ህይወቱን የገበረበትን ፣ደሙን ያፈሰሰበትን፣ አጥንቱን የከሰከሰበትን የአማራን ህዝብ ክብር፣እሴትና ማንነት መካድ እንደሆነ ተገለፀ።
‎
‎በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ "በፅምዶ ጦርነት ያወጁብንን ታሪካዊ ጠላቶቻችን በጋራ ክንዳችን በመመከትና በመደምሰስ አንፀባራቂ ድል እናስመዘግባለን" በሚል መሪ ቃል ከጠቅላላ የወረዳው ሙህራን የመንግስት ሰራተኞች ጋር በሁለት ክላስተር በመክፈል የውይይት መድረክ አካሄደ።
‎
‎በመድረኩ የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያና ወሌን ጨምሮ የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደረጀ ወልደገሪማና ጠቅላላ የወረዳ አመራሩና ሁሉም የመንግስት ሰራተኞች ተገኝተዋል።
‎
‎በመድረኩ እንደ ሀገር በአሁኑ ሰዓት ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ያልተቀደሰና ያልተገባ ጋብቻ በመፈፀም የአማራ ህዝብ ለዘመናት ህይወቱን በመገበር ፣ደሙን በማፍሰስ፣አጥንቱን በመከስከስ የታገለለትን የወሰንና የማንነት ማስከበር ትግልና ተጋድሎ ዋሻ ውስጥ በመጣል የአማራ ህዝብን ለዳግም እልቂትና ስቃይ ለመዳረግ የሚላላክ ቡድን እንደሆነ ተገልጿል።
‎
‎ በመሆኑም ይህንንን ሀገር አፍራሽ ቡድን የሚያስተላልፋቸውን የተዛቡ መረጃዎችና የሀሰት ትርክቶች እንዲሁም የማደናገሪያ ሀሳቦች ለማህበረሰቡ በመረዳትና በማስረዳት የመንግስት ሰራተኛው ቀዳሚውን ድርሻ ሊወስድ ይገባል ተብሏል።
‎
‎የጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደረጀ ወልደገሪማ የፅምዶ ጥምረት ሆን ተብሎ በኢትዮጵያ ጠላቶች የተደራጀ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ በመቆለፍ የወደብ ባለቤት እንዳትሆን የሚሰራ ልዩ ተልዕኮና የባንዳነት ተግባር የሚፈፀም ነው ሲሉ ለመድረኩ ተሳታፊዎች አስገንዝበዋል።
‎
‎ይህ ሀገር አፍራሽና የኢትዮጵያን ዘላቂ ጥቅም ለማስቀረት የሚያደረገውን መሯሯጥና መፈራገጥ ከእንጭጩ በተባበረ ክንዳችን በመመከት ልንደመስሰው ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
‎
‎በመጨረሻም ከመድረኩ ለተነሱ ጥያቄዎችና ሀሳቦች መልስ የሰጡት የጓጉሳ ሽኩዳድ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ አያና ወሌ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጥምረት ሀገር ለማፍረስ ባልተገባ መልኩ አንድነትና ጋብቻ በመፈፀም ኢትዮጵያን ከዚህ በፊት በየተናጠል ሞክረው ያልተሳካላቸው ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማፈራረስና የተመሰረተውን ጠንካራ የለውጥ መንግስት ለመጣል እያሰቡ ስለሚገኝ ይህንን ከንቱ የሆነ ቀቢጠ ተስፋ ሙከራ በተባበረ ክንዳችን በመመከት ከስር መሰረቱ ልናስወግደው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

 #ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሾሙ። የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን  መሥራች ...
01/10/2026

#ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ!

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ኾነው ተሾሙ።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባዔውን ማካሄዱን ጀምሯል።

ምክር ቤቱ አቶ አረጋ ከበደን የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አድርጎ በድጋሜ ሾሟል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፈታኝ የጸጥታ ችግር በገጠመው ወቅት ኀላፊነት ወስደው ክልሉ እንዲረጋጋ ያደረጉ ብርቱ መሪ መኾናቸው ተገልጿል።

በእርሳቸው የመሪነት ዘመን ክልሉን ከፈታኝ የጸጥታ ችግር አውጥተው ወደ ተረጋጋ ሰላም እንዲመለስ፣ በርካታ የልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ያደረጉ መሪ ናቸው።

ክልሉ በፈተና ውስጥ ኾኖ የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ በማቀድ ከግጭት አዙሪት እና ከድህነት እንዲወጣ የሚያስችሉ ሥራዎችን ሠርተዋል።

ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተሾሙ። ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ  ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተሹመዋል።የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር...
01/10/2026

ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተሾሙ።

ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባኤ ኾነው ተሹመዋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልል ምክር ቤት ሰባተኛ ዙር አንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን መሥራች ጉባዔውን እያካሄደ ነው።

ምክር ቤቱ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬን በድጋሜ የክልሉ ምክር ቤት አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟል። ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ ባለፉት ዓመታት የአማራ ክልልን ምክር ቤት በዋና አፈጉባኤነት መርተዋል።

አፈጉባኤዋ ባለፉት ዓመታት ውጤታማ ሥራዎችን መሥራታቸው ተገልጿል። በዚህ ውጤታማነታቸው እንዲቀጥሉ በድጋሜ የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አድርጎ ሾሟቸዋል።

Address

Bahir Dar_Addis Ababa
Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Guagusa Shikudad Prosperity posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Guagusa Shikudad Prosperity:

Shortcuts

Share