09/10/2026
በደዌ ሀረዋ ወረዳ በዝናብ እጥረት ሳቢያ ሊከሰት የሚችልን የአደጋ ስጋት ለመግታት የሚያስችል ጥናት ተካሄደ
በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በደዌ ሀረዋ ወረዳ የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን የአደጋ ስጋት አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል አስቸኳይ የዳሰሳ ጥናት ተካሂዷል።
የዞኑ አደጋ ስጋት አይበገሬነት ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በወረዳው የተከሰተው የዝናብ እጥረት በኅብረተሰቡ፣ በሰብልና በእንስሳት ሀብት ላይ ያሳደረውን ተፅዕኖ በቦታው ተገኝተው የዳሰሱ ሲሆን፣ ከመስክ ምልከታው መልስም ከደዌ ሀረዋ ወረዳ ስቲሪንግ እና ቴክኒክ ኮሚቴ አባላት ጋር ጥልቀት ያለው የምክክር ውይይት አካሂደዋል።
በመድረኩ ላይ ከመስክ ዳሰሳ ጥናቱ የተገኙ መረጃዎችና የምልከታ ውጤቶች በዝርዝር የቀረቡ ሲሆን፣ ሁለቱ ወገኖች በጋራ በመምከር በቀጣይ ሊወሰዱ በሚገባቸው የአደጋ ስጋት ቅነሳ እና የመከላከል እርምጃዎች ላይ ሙሉ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
ይህ ቅንጅታዊ የመስክ ምልከታና የተደረገው የጋራ ውይይት በወረዳው የዝናብ እጥረቱ የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ፈጣን የቅድመ ማስ his warning (የቅድመ ማስጠንቀቂያ) እና የቁስ ድጋፍ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የማህበረሰቡን አይበገሬነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተገልጻል።
Harawa