Amhara Region Police

Call Directions Website Contact the organization

Amhara Region Police law enforcement organization

በጎንደር ከተማ ሕገወጥ የቁማር ቤቶችና ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት ላይ እርምጃ ተወሰደበጎንደር ከተማ በሕግ የተከለከሉ የቁማር ቤቶችን፣ ቤቲንግ ቤቶችን፣ የጫትና ሽሻ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ሕገወጥ...
07/10/2026

በጎንደር ከተማ ሕገወጥ የቁማር ቤቶችና ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት ላይ እርምጃ ተወሰደ

በጎንደር ከተማ በሕግ የተከለከሉ የቁማር ቤቶችን፣ ቤቲንግ ቤቶችን፣ የጫትና ሽሻ ቤቶችን ጨምሮ ሌሎች ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቦታዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስጥሪ እንደገለጹት በከተማዋ ሰላምና ፀጥታን ለማስጠበቅና በሕግ የተከለከሉ ተግባራትን ለመቆጣጠር በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተጠናከረ ቁጥጥር ተካሂዷል ብለዋል።

በዚህም በ84 የቁማር ቤቶች፣ 13 የሽሻ እና ጫት ቤቶችን ጨምሮ በድምሩ 109 ሕገወጥ ተግባራት በሚፈጸሙባቸው ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የጎንደር ከተማ ፖሊስ አዛዥ ገልጸዋል።

እርምጃው የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቅ ባለፈ ሕገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር ሕግና ሥርዓትን ለማስከበር በከተማ ደረጃ ከተጀመረው የተጠናከረ የቁጥጥር ሥራ አካል መሆኑንም አዛዡ አብራርተዋል።

ለህብረተሰቡ ጉዳት የሚያደርሱ ሕገወጥ የቁማር፣ የቤቲንግ፣ የጫትና የሽሻ ንግድን ጨምሮ በመሰል ሕገወጥ ተግባራት የሚሳተፉ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኮማንደር አንተነህ አስገንዝበዋል።

ህብረተሰቡ ሕገወጥ ተግባራትን በመከላከልና ሰላምና ፀጥታን በማስጠበቅ ረገድ ለፀጥታ አካላት የሚያደርገውን የተለመደ ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር አንተነህ ቴዎድሮስጥሪ አቅርበዋል።

17 የህገወጥ ታጣቂ ቡድን አባላት በታች አርማጭሆ ወረዳ እጅ ሰጡ።በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በወርቅ ምድር እና በኩርቢ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ቡድ...
05/10/2026

17 የህገወጥ ታጣቂ ቡድን አባላት በታች አርማጭሆ ወረዳ እጅ ሰጡ።

በአማራ ክልል ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በወርቅ ምድር እና በኩርቢ ቀበሌዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የታጠቁ ቡድን አባላት በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን ሰጡ።

በአካባቢው ሲንቀሳቀስ የነበረውን ስብስብ በመምራት ላይ የነበረው ሙሉ አቸነፍን ጨምሮ 17 የቡድኑ አባላት የቀረበላቸውን የሰላም ጥሪ በመቀበል በምህረት እጃቸውን መስጠታቸውን የወረዳው ፖሊስ አስታውቋል።

እጃቸውን የሰጡት የቡድኑ አባላት 1 ኤም-14 ጠመንጃ፣ 8 የክላሽ ንኮቭ መሣሪያዎች፣ 2 የቃታ መሣሪያዎች እና ልዩ ልዩ ጥይቶችን ይዘው ገብተዋል።

የወረዳው ፖሊስ እንደገለጹት የተቀሩት የህገወጥ ታጣቂ ቡድን አባላትም የሰላሙን አማራጭ ተቀብለው እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን በአካባቢው ሙሉ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክለው አስታውቀዋል።

የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት  የወንጀል መከላከልንና የሰላም ማስጠበቅን እያጠናከረ መሆኑ ተገለጸ።በደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ስር የሚገኙት የ2ኛ እና 3ኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ...
03/10/2026

የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት የወንጀል መከላከልንና የሰላም ማስጠበቅን እያጠናከረ መሆኑ ተገለጸ።

በደሴ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ስር የሚገኙት የ2ኛ እና 3ኛ ፖሊስ ጣቢያዎች ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት ባከናወኗቸው የሰላምና የፀጥታ ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስመዘገቡ እንደሚገኙ ተገለጸ።

የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ከህዝቡ ጋር ያለውን ትብብር በማጠናከር ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል ረገድ የላቀ ውጤት ማምጣት እንደሚቻል ማሳያ ሆነዋል።

ህብረተሰቡ የፀጥታ ተግባራትን ሙሉ በሙሉ በባለቤትነት በመመራት በቀንም ሆነ በሌሊት አካባቢውን ተደራጅቶ በመጠበቅ ሰላሙን በጽናት እያስጠበቀ ይገኛል።

በተለይም ከታላቁ የግሼን ማርያም በዓል የተመለሱ እንግዶችን በአግባቡ በመቀበል፣ በማስተናገድና ደህንነታቸውን በመጠበቅ ረገድ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ይገኛል።

አካባቢውን ከማረጋጋት ባሻገር፣ ህብረተሰቡና የፀጥታ ኃይሉ በመቀናጀት አጠራጣሪ አካላትን (ጸጉረ-ልውጦችን) በንቃት በመከታተልና በመቆጣጠር ሰላም እና ፀጥታን አስተማማኝ ማድረግ ተችሏል።

የፀጥታ ኃይሉና የህዝብ ጥበቃው ዛሬም በከፍተኛ ንቃትና ቁርጠኝነት የዕለት ተዕለት የጥበቃ ሥራውን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ይህ ተግባር ማህበረሰቡ ሰላምን የሚሻና ለኑሮው መረጋጋት ቀዳሚውን ቦታ የሚሰጥ መሆኑን በግልጽ ያሳያል።

የህዝብና የፀጥታ አካላት አብሮነት የትኛውንም ፈተና ሰብሮ ማለፍ የሚያስችል አቅም የሚሰጥ በመሆኑ፣ መሰል መልካም ተሞክሮ፣ በሌሎች አካባቢዎችም ተጠናክሮ ሊቀጥልና ሊተገበር ይገባል።

በታች አርማጭሆ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች እጃቸውን ለሠራዊቱ ሰጡ።በታች አርማጭሆ ወረዳ በተሳሳተ መንገድ ነፍጥ አንስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 19 የፅንፈኛው ቡድን ታ...
01/10/2026

በታች አርማጭሆ ወረዳ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች እጃቸውን ለሠራዊቱ ሰጡ።

በታች አርማጭሆ ወረዳ በተሳሳተ መንገድ ነፍጥ አንስተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 19 የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ለሰሜን ምዕራብ ዕዝ ክፍለጦር እጅ መስጠታቸውን የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል በንድር በደድ ተናግረዋል።

እነዚሁ ታጣቂዎች በሃይማኖት አባቶች እና በሀገር ሽማግሌዎች የተደረገላቸውን ምክር በመቀበል እጅ መስጠታቸውንም አዛዡ ገልፀዋል።

የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶቹ ከተሳሰተ መንገድ ተመልሰው ህዝባቸውንና አገራቸውን ማገልገል እንደሚጠበቅባቸውና የበደሉትን ህዝብም መካስ እንዳለባቸው በአቀባበል ስነስርዓቱ ላይ የተገኙ የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶቹ መናገራቸውን ዘገባው የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነው።

በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በሙሉ ሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል በባህር ዳር አለምዓቀፍ ስታዲየም...
29/09/2026

በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በሙሉ ሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

በኢትዮጵያ እና በሴኔጋል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል በባህር ዳር አለምዓቀፍ ስታዲየም የተካሄደው የእግር ኳስ ጨዋታ በሙሉ ሰላምና በጥሩ ስፖርታዊ ጨዋነት መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል አበበ ውቤ ገለጹ።

ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል አበበ ውቤ እንዳስታወቁት ጨዋታው በሰላም እና በስኬት ይጠናቀቅ ዘንድ ከተዘጋጀው አጠቃላይ የፀጥታ ማስከበር ዕቅድ ጀምሮ በቅንጅት ሲሰሩ የነበሩ ሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ እና ብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም የክልሉ የፀጥታ ኃይል ባደረጉት የተቀናጀና ውጤታማ ሥራ ጨዋታው ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ አስችሏል ብለዋል።

በተጨማሪም የባህር ዳር ከተማ እና የአካባቢው ወጣቶችና መላው ማህበረሰብ ያሳዩት ከፍተኛ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል፣ የስፖርት ፍቅር እና የፀጥታ አካላትን በመተባበር ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፤ ላሳዩት መልካም ትብብርና የሰለጠነ ስፖርታዊ ጨዋነት የላቀ ምስጋና አቅርበዋል።

የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።በመላው የአማራ ክልል የተከበረው የ2019 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ሳይገጥመው በሰላም መጠናቀቁን ...
27/09/2026

የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም መጠናቀቁ ተገለጸ።

በመላው የአማራ ክልል የተከበረው የ2019 ዓ.ም የደመራ እና የመስቀል በዓል ምንም ዓይነት የፀጥታ ችግር ሳይገጥመው በሰላም መጠናቀቁን የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቋል።

በዓሉ በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ ኃይሉ ባደረገው ከፍተኛ ቁርጠኝነት፣ ቀን ከሌት በመትጋትና በቅንጅት በመስራቱ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን ዋና ጠቅላይ መምሪያው ለፀጥታ አካላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

በተጨማሪም መላው የክልሉ ህዝብ ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም፣ አስፈላጊውን ትብብርና ጥንቃቄ በማድረግ በዓሉ በሰላም እንዲያልፍ ላሳየው አጋርነትና ከፍተኛ ትብብር የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ምስጋናውን አስተላልፏል።

በደብረ ማርቆስ ከተማ በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደከፍተኛ የክልል እና የዞን የፀጥታ አመራሮች በጎጃም ቀጠና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በቅንጅት ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ዙሪ...
27/09/2026

በደብረ ማርቆስ ከተማ በወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

ከፍተኛ የክልል እና የዞን የፀጥታ አመራሮች በጎጃም ቀጠና ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ እና በቅንጅት ሊከናወኑ በሚገቡ ተግባራት ዙሪያ በደብረ ማርቆስ ከተማ ውይይት አደረጉ።

በመድረኩ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአስተዳደር ክላስተር አስተባባሪ ዶ/ር አማኑኤል ፈረደ፣ የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ፣ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራሎች፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ፣ የምስራቅ ጎጃም ዞንና የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ተቋማት ኃላፊዎች እንዲሁም የአማራ ክልል ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አመራሮች ተገኝተዋል።

ውይይቱ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታዎች ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በቀጣናው የሚሰሩ የፀጥታ ማስከበር ስራዎችን በቅንጅትና በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል።

"ሰላምና ፍቅር የነገሠበት የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን!" ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴበአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ...
25/09/2026

"ሰላምና ፍቅር የነገሠበት የደመራና የመስቀል በዓል ይሁንልን!" ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ

በአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለፌደራል ፖሊስ፣ ለክልሉ መደበኛና አድማ መከላከል ፖሊስ፣ ለሚሊሻ፣ ለሰላም ማስከበር አባላት እንዲሁም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ እንኳን ለ2019 ዓ.ም የደመራና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ በመልዕክታቸው የሀገራችን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር፣ የሕዝብን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ በጽናትና በቆራጥነት በማገልገል ላይ ለሚገኙ የፀጥታ አካላት እንዲሁም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በዓሉ የፍቅር፣ የደስታና የመደጋገፍ እንዲሆን መልካም የበዓል ምኞታቸውን ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም የመስቀል በዓል የፍቅር፣ የይቅርታና የእርቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ እሴታችን መሆኑን ጠቅሰው፤ የፀጥታ አካላት የሚያደርጉት የተቀናጀ ጥረት ለሀገራችንና ለሕዝባችን ዘላቂ ሰላምን፣ እውነተኛ ወንድማማችነትንና እድገትን እንደሚያበስር ሙሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል።

በየግንባሩና በየአካባቢው ሌት ከቀን ሳያቋርጡ ለሀገር ሉዓላዊነትና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ የፀጥታ አባላቱ የሚከፍሉት ውድ መስዋዕትነትና የሚያሳዩት ጽናት በታሪክ ማህደር ወርቃማ ስፍራ የሚሰጠውና የሚዘከር መሆኑንም ኃላፊው ገልጸዋል።

በመጨረሻም በዓሉ ሲከበር እርስ በእርስ በመደጋገፍ፣ ህብረታችንን በማጠናከርና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት በማስጠበቅ ሊሆን እንደሚገባ ረዳት ኮሚሽነር ክንዱ ወንዴ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ጥሪ አቅርበዋል።

ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚያሥቀድመው ህወሃት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተጣምሮ መስከረም 12 ቀን 20...
24/09/2026

ሠላም ጠል የሆነው ህገ-ወጡ ህወሃት በለኮሰው እሳት መለብለቡን የዕዙ አዛዥ ገለፁ።

ከሰላም ይልቅ ጦርነትን የሚያሥቀድመው ህወሃት ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተጣምሮ መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከሌሊቱ 9 ሰዓት ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ ዕዝ የግዳጅ ቀጣና በከፈተው ማጥቃት በዕዙ ሠራዊት ጠንካራ ክንድ የተመከተ ሲሆን ታጣቂዎቹን ጨምሮ የተለያዬ ዓይነት መሳሪያና ተተኳሽ በቁጥጥር ስር ውሏል።

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል ህወሃት እና መሰል ተጣማሪ ቡድኖች በቀጣናው ሰብሮ በመግባት ህዝብን የመዝረፍ እና የመበተን ዓላማቸው መክሸፉን ገልፀው የዕዙ ሠራዊት በወሰደው ፈጣን የፀረ-ማጥቃት ምላሽ በህገ ወጡ ህወሃት ቡድን ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ማድረስ መቻሉን አሥረድተዋል።

ህወሃት እና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ኢትዮጵያን የማፍረስ አላማ አሸክመው ያጣመሩት ቡድኑ በሰሜን ወሎ ዞን ተኩለሽ፣ ድልድይ፣ ቀይ አፈር፣ በረሃ ማርያም፣ ባይብዋ፣ በጭሮ እና ኩቤ ቀረንሳ በሚባሉ አካባቢዎች ያለ የሌለ ኃይሉን አሰልፎ ሾልኮ ለመግባት የሞከረ ሲሆን በደረሰበት ጠንካራ ምት ንብረት እና የሰው ኃይሉን እያንጠባጠበ ወደ መጣበት ለመመለስ መገደዱን አዛዡ ተናግረዋል።

ሠላም ጠል የሆነው ቡድን በጀመረው እና ሠራዊታችን ባካሄደው መልሶ ማጥቃት በርካታ የቡድን እና የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያዎችም ተማርከዋል።

በዚህም መሰረት 04 ዲሽቃ፣ 22 መትረየስ፣ 08 ስናይፐር፣ 50 ክላሽንኮፍ ጠብመንጃ፣ 03 አርፒጂ7፣ 1ዐ አይኮም የመገናኛ ሬድዮ፣ 01 አይነት 77 የመገናኛ ሬድዮ፣ 03 የድሸቃ ወሳ እግር፣ 11 የአይኮም መገናኛ ባትሪ እና 12 አይኮም ቻርጀር ይገኙበታል። በተጨማሪም በርካታ የጠላት ኃይል ሲማረክ 272 ተደምስሷል፣ 260 የጠላት ኃይል ቆስሏል።

አሁን ላይ ሠራዊቱ የጠላትን ሁኔታ እያነበበ ከያዛቸው ቁልፍ ወታደራዊ መሬቶች እየተወረወረ የተጠኑ ፀረ-ማጥቃቶችን በመፈፀም የግዳጅ ቀጣናውን ከጠላት የማፅዳት ወሳኝ ግዳጆችን በመፈፀም ላይ ይገኛል።

ዕድሜ ልኩን ከስህተቱ የማይማረው ህገ-ወጡ ህወሃት ካሰባሰባቸው ጀሌዎቹ ጋር ግንባር በመፍጠር የሞከረው የሽብር ተግባር በእንጭጩ እንዲቀጭ እና ዕዙ ድል እንዲቀዳጅ የአካባቢው ማህበረሰብ ላበረከተው ድጋፍና ሚና የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አዛዥ ምስጋና ማቅረባቸውን የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

በወሎ ቀጣና ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በተገኙበት በወሎ ቀጣና ...
24/09/2026

በወሎ ቀጣና ከሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ጥጋቡ ይልማ በተገኙበት በወሎ ቀጣና የሚገኙ የፀጥታ ተቋማት አመራሮች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ የፀጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ የጋራ ውይይት መድረክ በኮምቦልቻ ከተማ ተካሂዷል።

በዚህ የጸጥታ መድረክ ላይ ምክትል ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ ረዳት ኮሚሽነር አያልነህ ተስፋዬ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል እና የአስተዳደርና ልማት ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ፣ ረዳት ኮሚሽነር ዘለቀ አለባቸው ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል እና ኦፕሬሽናል አዛዥ ተገኝተዋል።

Address

Police Commission
Bahir Dar
244

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Region Police posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara Region Police:

Shortcuts

Share