Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch

Call Directions Website Contact the organization

Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch በሕግ የተደነገጉ የዜጎች መብቶችና ጥቅሞች በአስፈጻሚው አካ? አዋጅ ቁጥር 1142/2011 የኢትዮጵያ ህዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን እንደገና ለማቋቋም የወጣ አዋጅ፡፡

25/01/2019
05/10/2026

25/01/2019

ትምህርት ቤቶችና  አካታችነት ...........25/01/2019..........እንደሚታወቀው ማካተት (Inclusion) በዘመናዊው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ማዕከላዊ ቦታ የሚሰጠው እና የሰብ...
05/10/2026

ትምህርት ቤቶችና አካታችነት ...........25/01/2019..........

እንደሚታወቀው ማካተት (Inclusion) በዘመናዊው የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ማዕከላዊ ቦታ የሚሰጠው እና የሰብአዊ መብት ጉዳይ ተደርጎ ይወሰዳል። ትምህርት ቤቶች ለሁሉም ተማሪዎች — ልዩ ትኩረት ለሚሹ (አካል ጉዳተኞች፣ ከቀድሞ ማህበራዊ ኑሮ ውጪ የሆኑ፣ ወይም ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ) ተማሪዎችን ጨምሮ — ከሌሎች ተማሪዎች እኩል ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ዕድል ማመቻቸት ተገቢ ነው። ይህ ትውልድን በእኩልነት ለማነጽ፣ ፍትሃዊ ማህበረሰብ ለመገንባት እና የሁሉንም አቅም ሙሉ በሙሉ ለመጠቀም ቁልፍ የሆነ ሚና እንዳለው መረዳት ያስፈልጋል፡፡።

ትምህርት ቤቶችን ልዩ ትኩረት ለሚሹ ተማሪዎች እኩል
ተደራሽ የማድረግ አስፈላጊነት

ልዩ ትኩረት የሚሹ ተማሪዎች መሰረታዊ የትምህርት መብታቸውን በማንኛውም መልኩ ከሌሎች እኩል ማግኘት ይገባቸዋል። በትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚደረግ እኩል ተደራሽነት የሚከተሉትን ጥቅሞች ያስገኛል፦

• ማህበራዊ መቀላቀልን ማሳደግ፡ ተማሪዎች በለጋ እድሜያቸው አብረው ሲማሩ አንዱ የሌላውን ልዩነት እና አቅም በመረዳት መቻቻልን እና አብሮነትን ይለማመዳሉ።
• ራስን የመቻል አቅምን ማዳበር፡ ተስማሚ የመማሪያ አካባቢ፣ ግብዓቶች እና የትምህርት አሰጣጥ ዘዴዎች ሲኖሩ ልዩ ትኩረት የሚሹ ተማሪዎች በራሳቸው በመተማመን ውጤታማ መሆን ይችላሉ።
• የድህነት ዑደትን መስበር፡ ጥራት ያለው እና ተደራሽ ትምህርት ማግኘት ለወደፊት ህይወታቸው የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ዋስትና እንዲኖራቸው መሠረት ይጥላል።

ዓለም አቀፍ ህጎችና ድንጋጌዎች ስለ ተደራሽነትና እኩል ተጠቃሚነት

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የትምህርት ተደራሽነትን እንደ መሠረታዊ የሰብአዊ መብት በመገንዘብ በርካታ ስምምነቶችን አጽድቋል፦
• የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፍ አዋጅ (Universal Declaration of Human Rights - 1948): አንቀጽ 26 ሁሉም ሰው የትምህርት መብት እንዳለው ይደነግጋል። ትምህርት ነጻ መሆን አለበት፤ ቢያንስ የመጀመሪያ እና መሰረታዊ ደረጃዎች ግዴታ ሊሆኑ ይገባል ይላል።
• የዩኔስኮ የትምህርት ውስጥ አግላይነትን አለመቀበል ስምምነት (UNESCO Convention against Discrimination in Education - 1960): በማንኛውም መልኩ በዘር፣ በቀለም፣ በጾታ፣ በቋንቋ፣ በሃይማኖት ወይም በአካል ጉዳት ምክንያት በምርት ወይም በትምህርት ተደራሽነት ላይ ልዩነት መፈጠርን ይቃወማል።
• የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት (UNCRPD - 2006): አንቀጽ 24 አባል ሀገራት ለአካል ጉዳተኞች አካታች የሆነ የትምህርት ሥርዓት (Inclusive Education System) በሁሉም የትምህርት ደረጃዎች ማረጋገጥ እንዳለባቸው በግልጽ ያዛል። ይህም አካል ጉዳተኞች ከሌሎች ጋር እኩል ማህበረሰቡን እንዲቀላቀሉ እና የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ያስችላል።
• ቀጣይ ልማት ግቦች (SDGs - ግብ 4): እስከ 2030 ድረስ ሁሉን አቀፍ እና እኩልነት ያለው ጥራት ያለው ትምህርት ማረጋገጥ እና ለሁሉም የዕድሜ ልክ የትምህርት ዕድሎችን ማስተዋወቅ የሚል ዓላማ አስቀምጧል።

05/10/2026

የአካል ጉዳተኞች በእኩልነት መረጃ የማግኘት መብት................25/01/2019.............

አባል ሀገራት አካል ጉዳተኞች በመረጧቸው የመገናኛ ዘዴ ዐይነቶች ሁሉ መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ሐሳብን በነጻነት የመያዝ እና የመግለጽ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ ተገቢውን ሁሉ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል
ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 21((ሀ)(ሐ)(መ))
አባል ሀገራት አካል ጉዳተኞች በመረጧቸው የመገናኛ ዘዴ ዐይነቶች ሁሉ መረጃን የመፈለግ፣ የመቀበል እና የማሰራጨት ነጻነትን ጨምሮ ከሌሎች ጋር በእኩልነት ሐሳብን በነጻነት የመያዝ እና የመግለጽ መብቶቻቸውን መጠቀም እንዲችሉ ተገቢውን ሁሉ እርምጃ ሊወስዱ ይገባል። ይህም:-
• ለተለያዩ የአካል ጉዳት ዐይነቶች አግባብነት ባላቸው ተደራሽ አቀራረቦች እና ቴክኖሎጂዎች ለጠቅላለው ሕዝብ የታሰበ መረጃን ለአካል ጉዳተኞች በወቅቱ እና ያለተጨማሪ ወጪ መስጠት፤
• በይነመረብን ጨምሮ ለጠቅላለው ሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ የግል ተቋም እና አካላት መረጃ እና አገልግሎትን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እና ጥቅም ላይ በሚውሉ ቅርጾች እንዲያቀርቡ ማሳሰብ፤
• በበይነመረብ በኩል መረጃ አቅራቢዎችን ጨምሮ የመገናኛ ብዙኃን አገልግሎቶቻቸውን ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ እንዲያደርጉ ማበረታታትን ያካትታል፡፡

ሴቶችና መልካም አስተዳደር ..........25/01/2019 ዓመተ ምህረት.........መልካም አስተዳደር ስንል ህግ በማውጣትና እና አገልግሎት በመስጠት ብቻ የሚያበቃ ጉዳይ ተደርጎ መወሰድ ...
05/10/2026

ሴቶችና መልካም አስተዳደር
..........25/01/2019 ዓመተ ምህረት.........

መልካም አስተዳደር ስንል ህግ በማውጣትና እና አገልግሎት በመስጠት ብቻ የሚያበቃ ጉዳይ ተደርጎ መወሰድ የለበትም፡፡ ከዚህም በላይ ዜጎች በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች መሳተፍ፣ ተጠያቂነት፣ ግልጽነት፣ ፍትሃዊነትና ማኅበራዊ አካታችነት የመልካም አስተዳደር መሠረቶች ናቸው ተብሎ ይመናል። በዚህ ሂደት የሴቶች ድምፅ ከሌለ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ አካታች ሊሆን ይችላልን? ብሎ መጠየቅ የሁላችን ኃላፊነት ነው፡፡

ለሴቶች መልካም አስተዳደር ምንድነው?

ለሴቶች መልካም አስተዳደር ማለት ሴቶች እንደ ዜጋ መብታቸው በእኩልነት እንዲከበር፣ የሚመለከታቸው ውሳኔዎች ሲወሰኑ ድምፃቸው እንዲሰማ፣ ለሕግና ለፍትሕ እኩል ተደራሽነት እንዲኖራቸው፣ የሕዝብ አገልግሎቶች የሴቶችን ልዩ ፍላጎት እንዲያስቡ እና በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ውሳኔ ሰጪ ቦታዎች እንዲሳተፉ ዕድል መፍጠር ማለት እንደሆነ ጥናቶች ይጠቁማሉ። ይህ ማለት ግን ለሴቶች ልዩ መብት መስጠት ሳይሆን፣ በተግባር ያሉትን እንቅፋቶች በመቀነስ እኩል ዕድል መፍጠር ማለት እንደሆነ መገንዘብ ያስፈልጋል።

ፋይዳውስ ምንድነው?

ሴቶች በውሳኔ ሰጪነት ቦታዎ ች ሲሳተፉ የሴቶችን ጉዳይ ብቻ ለማንሳት ሳይሆን የመላውን ማኅበረሰብ ውሳኔ የበለጠ አካታች ለማድረግ ይረዳል ተብሎ ነው የሚታመነው። የጤና፣ የትምህርት፣ የውሃ፣ የሥራ፣ የሕፃናት እንክብካቤና የደኅንነት ጉዳዮች በውሳኔ ሰጪ ሴቶች የተሻለ ትኩረት ሊያገኙ ይችላሉ በሚለው ሀሳብ ብዙዎች ይስማማሉ፡፡ እናንተስ?

03/10/2026
የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ
02/10/2026

የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ

20/01/2019
30/09/2026

20/01/2019

16/01/2019 ዓ/ም
26/09/2026

16/01/2019 ዓ/ም

26/09/2026

ሕዝብን ማገልገል ክብር ነው!
እውነተኛ የአገልጋይነት መንፈስ ያለው ሠራተኛ /አመራር/፤
☞ የሕዝብ አገልጋይ መሆኑን ያምናል፤
☞ ለሚያገለግለው ሕዝብ ክብር ይሰጣል፤
☞ ጉዳዩን በፍጥነትና በፍትሃዊነት ለመፈጸም ይጥራል፤
☞ ሕግን ያከብራል፣
☞ ጉቦን ይጸየፋል፣
☞ ሙስናን ይቃወማል፣
☞ የሕዝብን ንብረትና ሀብት እንደራሱ ይጠብቃል።
☞ የተሰጠው ሥልጣን ለግል ጥቅም፣ ለወዳጅነት ወይም ለዘመድ ጥቅም ሳይሆን ለሕዝብና ለሀገር ጥቅም ያውላል።

Address

0947111122
Bahir Dar
1957

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Ombudsman Bahirdar Branch:

Shortcuts

Share