Visit Amhara

Call Directions Website Contact the organization

Visit Amhara This page is dedicated to promote the diverse natural, historical & cultural heritages of Amhara region.
(1)

We constantly publish new articles, photos and other helpful information on this page to get you traveling to the Land of Amhara, Ethiopia. Visit Amhara is the official page of Amhara culture & tourism bureau, dedicated to promote the diverse natural, historical & cultural heritages of Amhara region.

06/10/2026

አርቲስት ፀደንያ ገብረ ማርቆስ ስለ አስደናቂዎቹ የቅዱስ ላሊበላ እና አካባቢ የመስህብ ቦታዎች ይሄን ብላለች።

እናመሰግናለን🙏

Lalibela

የግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓልን ለማክበር በግሸን አምባ የሰነበቱ እንግዶች የመልስ ጉዞ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ በግሸን ቆይታ ያደረጋችሁ እንግዶቻችን በመንገዳችሁ የሚገኙ ሌሎች የድንቅ ምድር ...
02/10/2026

የግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓልን ለማክበር በግሸን አምባ የሰነበቱ እንግዶች የመልስ ጉዞ ማድረግ ጀምረዋል፡፡

በግሸን ቆይታ ያደረጋችሁ እንግዶቻችን በመንገዳችሁ የሚገኙ ሌሎች የድንቅ ምድር መዳረሻዎችን እንድትጎበኙ እየጋበዝን በሰላም ወደ ቤታችሁ እንድትደርሱ እንመኛለን፡፡

የብዙኅን ማርያም በዓል እና ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል ግሸን አምባ የገባበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ የሚከበረው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት ተከብ...
01/10/2026

የብዙኅን ማርያም በዓል እና ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ግማደ መስቀል ግሸን አምባ የገባበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ የሚከበረው የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ የንግሥ በዓል በድምቀት ተከብሯል።

መስከረም አጋማሽ በጀመረው የግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሀይማኖታዊ ተጓዦች ከኢትዮጵያ ሁሉም አቅጣጫ ተሰባስበው ታድመውበታል።

01/10/2026

የግሸን ደብረ ከርቤ ዓመታዊ ክብረ በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል የሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ እና ከሚሴ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የምዕራብ ካናዳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ፣ የደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት መምህር ቆሞስ አባ ለይኩን ወንድይፍራው እንዲሁም ሌሎች የሀይማኖት አባቶች እና ከመላው ኢትዮጵያ የተሰባሰቡ ምዕመናን በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡

01/10/2026

ግሸን ደብረ ከርቤ✝️

እንኳን ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል አደረሳችሁ።
01/10/2026

እንኳን ለግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል አደረሳችሁ።

የግሸን ደብረ ከርቤ አንድ ጠባብ በር ብቻ ባለው አምባ ላይ የምትገኝ ድንቅ ሀይማኖታዊ መዳረሻ ናት፡፡ ከደሴ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 82 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የግሸን አምባ ለመጀመ...
30/09/2026

የግሸን ደብረ ከርቤ አንድ ጠባብ በር ብቻ ባለው አምባ ላይ የምትገኝ ድንቅ ሀይማኖታዊ መዳረሻ ናት፡፡ ከደሴ ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 82 ኪ/ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው የግሸን አምባ ለመጀመሪያ ጊዜ ቤተ ክርስቲያን የተሰራበት በአፄ ካሌብ ዘመነ መንግስት አባ ፈቃደ ክርስቶስ በተባሉ አባት በ517 ዓ.ም ነበር፡፡

ግሸን አሁን የምትጠራበትን ግሸን ደብረ ከርቤ የሚለውን ስያሜ ያገኘችው በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግስት ነው፡፡ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀል ከሲናር ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት በዚህ አምባ ሲያሳርፉ አምባው የመስቀሉ መገኛ ነው በማለት ደብረ ከርቤ ብለው ሰይመውታል፡፡

መስከረም 21 በግሸን ልዩ የክብረ በዓል ቀን ነው፡፡ የብዙኃን ማርያም ክብረ በዓል እና የኢየሱስ ክርስቶስ ግማደ መስቀል ግሸን አምባ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን የገባበትን ቀን ታሳቢ በማድረግ በሚከበረው በዚህ ታላቅ ዓመታዊ ክብረ በዓል ለመሳተፍ በርካታ ምዕመናን በቦታው ተገኝተዋል።

የግሸን ክብረ በዓል ከአጼ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምሮ ለረጅም ዓመታት በመከበሩ፣ በርካታ ምዕመናን በማሳተፉ እና በድምቀቱ በኢትዮጵያ ከሚከናወኑ ቀዳሚ ሀይማኖታዊ በዓላት አንዱ ለመሆን ችሏል።

መልካም በዓል!

30/09/2026

ነገ የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በግሸን አምባ በድምቀት ይከበራል።

ክብረ በዓሉን ለመታደም በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን ሁሉንም የጉዞ አማራጮች በመጠቀም ግሸን ደርሰዋል።

እንኳን አደረሳችሁ!

መልካም በዓል!

ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም📷 Amanuel Bekele
30/09/2026

ግሸን ደብረ ከርቤ ማርያም

📷 Amanuel Bekele

29/09/2026

በልዩ መንበሯ
ሀገሯ ግሸን ማማሯ!

መስከረም 21 ቀን የግሸን ደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል ይከቀራል።

Address

Bahir Dar

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Visit Amhara posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Visit Amhara:

Shortcuts

Share