08/10/2026
ለተሻለ ህብረተሰብ ግንባታ፤ ተቋማት ከሙስናና ብልሹ አሰራር ሊፀዱ ይገባል!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ተቋማት የሀገር አንቀሳቃሽ ሞተሮችና የህብረተሰብ መስተጋብር ማዕከላት ናቸው። ይሁን እንጂ ተቋማት ከሙስና እና ከብልሹ አሰራር ራሳቸውን ነጻ ሳያወጡ፣ በህብረተሰቡ ዘንድ ጤናማ እና መልካም ሥነ ምግባር ያለው ትውልድ መገንባት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው። ሙስና የህግ የበላይነትን የሚሸረሽር፣ ፍትህን የሚያዛባ እና የህብረተሰቡን እሴቶች የሚበክል አደገኛ መርዝ ነው።
ህብረተሰቡ ሰዎችን የሚያየውና የሚለካው ከሚመራባቸው ተቋማት ባህሪ አንጻር ነው። ተቋማት በግልጽነት፣ በፍትሃዊነት እና በኃላፊነት ስሜት ሲመሩ ውስጥ የሞራል እሴቶች ይስፋፋሉ።
ተቋማት ውስጥ ብልሹ አሰራርና ሙስና ሲሰለጥን፣ ህብረተሰቡ በሕግና በሥርዓት ላይ ያለው እምነት ይጠፋል። "በሥነ ምግባር መታነጽ ዋጋ አለው" የሚለው እምነት እየተዳከመ ሲመጣም ራስ ወዳድነትና ህገ-ወጥነት ይሰለጥናሉ።
ጤናማ ማህበረሰብ ለመፍጠር መጀመሪያ የሀገርን አምድ የያዙ ተቋማትን ከስር እስከ ላይ በብቃት፣ በግልጽነት እና በሥነ-ምግባር መርሆዎች ማጽዳት ቅድሚያ የሚሰጠው ብሔራዊ ጉዳይ ነው።
በአጠቃላይ መልካም ሥነ ምግባር ያለው ማህበረሰብ ለመፍጠር የሚደረግ ጥረት መጀመር ያለበት ከራሳቸው ከተቋማት የማጽዳት ስራ ነው።
ተቋማት ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና የሞቀ የስራ ከባቢን ሲፈጥሩ ብቻ ነው ለህብረተሰቡ አርአያ መሆን የሚችሉት።
ስለዚህ የሙስና እና የብልሹ አሰራርን ሰንሰለት በመበጠስ ጠንካራ፣ ታማኝ እና በሥነ ምግባሩ የተጠበቀ ተቋማትን መገንባት የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ሊሆን ይገባል።