Janamora Communications

Call Directions

Janamora  Communications የጃናሞራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የወረዳውን ህብረተሰብ የመረጃ ተጠቃሚ ማድረግ ነው።

‎የየጃናሞራ ወረዳ ንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን አስወገደ።‎‎መስከረም 26/2019 ዓ.ም‎‎ጽ/ቤቱ በመካነ ብርሃን ከተማ በንግ...
06/10/2026

‎የየጃናሞራ ወረዳ ንግድና ገቢያ ልማት ጽ/ቤት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸውን የተለያዩ የኢንዱስትሪ ምርቶችን አስወገደ።
‎
‎መስከረም 26/2019 ዓ.ም
‎
‎ጽ/ቤቱ በመካነ ብርሃን ከተማ በንግድ ድርጅቶች የምግብ ደህንነትን ለማረጋጥ ባደረገው የበር ከበር ጉብኝት የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው በርካታ የኢንዱስትሪ ምርቶችን ሰብስቧል።
‎
‎የተለያዬ መጠን ያላቸው የታሸጉ ጁሶች ፣ከረሚላዎች እና የጸጉር ቅባቶች የሚገኙበት ሲሆን ማህበረሰቡ እንደነዚህ አይነት የታሸጉ ምርቶችን ሲገዛ የመጠቀሚያ ጊዜያቸውን አረጋግጦ እንዲጠቀም የገለጹት የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ሰለሞን ጌታቸው ቀጣይ ከአስወጋጅ ኮሚቴው በተገኘበት የማስወገድ ስራ የሚሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

‎የጥንታዊው የእርሰ ገዳማት ፈጠቆች ቅ/ጊወርጊስ ወ አውስግንዮስ አንድነት ገዳም የተፈጥሮ ደን ጥበቃና የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝት ተደረገ።‎‎መስከረም 25/2019 ዓ.ም‎‎በሰሜን ጎንደር ዞን...
05/10/2026

‎የጥንታዊው የእርሰ ገዳማት ፈጠቆች ቅ/ጊወርጊስ ወ አውስግንዮስ አንድነት ገዳም የተፈጥሮ ደን ጥበቃና የልማት እንቅስቃሴ ጎብኝት ተደረገ።
‎
‎መስከረም 25/2019 ዓ.ም
‎
‎በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ የሚገኘው የፈጠቆች ጊርጊስ አንድነት ገዳም ከግብፅ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ተሰደው ከመጡ 9999 ቅዱሳን መካከል በፃድቁ በአቡነ አውስግንዮስ በ10ኛው ክፍለ ዘመን እንደተመሰረት ታሪክ ያስረዳል።
‎
‎የበርካታ ገድላትና ታምራት ባለቤት የሆነው ገዳሙ እስከ 1970 ዓመተ ምህረት ድረስ ገዳማውያን በፆም በፀሎት ተወስነው እንደኖሩበት የሚነገር ሲሆን በ2017 ዓ.ም የመንግስት አካላት ፣የወረዳው ቤተ ክህነት ተወካዮች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ እና የጸጥታ አካላት በተገኙበት በአካባቢው ያለው የተፈጥሮ ደን ወደ ገዳሙ እንዲከለል ተወሰነ።
‎
‎የገዳሙ አስተዳዳሪ አባ ወ/ዮሀንስ ወ/ጊወርጊስ በቦታው ያለው ትልቅ የተፈጥሮ ጸጋ በማልማት የየሻለ ገቢ እንዲያስገኝ ትልቅ ሃሳብ ይዘው ጎዟቸውን ጀምረዋል።
‎
‎በአካባቢው ያለው የተፈጥሮ ደን ለንብ ማነብ ምቹ መሆኑን የተረዱት እኒህ አባት ከተወሰኑ መነኮሳት ጋር በመሆን ባለፈው አመት የጀመሩት የንብ ማነብ ስራ ዛሬ ላይ ከ40 በላይ ቀፎዎች የደረሱ ሲሆን ያለውን ፀጋ በመጠቀም እስከ 150 የሚደርስ ቀፎ በማዘጋጀት እና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር በየሁለት ሳምንቱ የማር ምርት በማግኘት በአመት በሚሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ሃብት ለማግኘት እና የአካባቢው ማህበረሰብ ትምህርት እንዲሆን እቅድ አቅደው እየሰሩ ይገኛሉ።
‎
‎በሌላ በኩል በዘመናዊ ሸመና ፣የልብስ ስፌት ፣ የአትክልትና ፋራፍፍሬ ልማት እየተሰራ ሲሆን በቀጣይ የደሮ እርባታ የአሳ እርባታ ስራ ለመስራት አቅደዋል።
‎
‎ትልቅ ራዕይ ይዘው የተነሱት አባት በገዳሙ ዙሪያ ያሉ የተፈጥሮ ፀጋዎችን እና የመልክአ ምድር ገጽታ የመለየት ስራ ከሰሩ በኋላ በሰፊው የሚበቅለውን የእሬት ተክል ማቀነባበሪያ ፍብሪካ መክፈት ለሀገራቸውም ለዓለምም የሚተርፍ ምርት ማምረት ፣የድንጋይ ወፍጮና የቱሪስት መዳረሻ በመሆን የሚያገለግሉና ገቢ የሚያስገኙ ሆቴሎች ይገነባሉ።
‎
‎ገዳማት ይሰጣሉ እንጂ ለምነው አያውቁም የሚሉት አባ ወ/ዮሀንስ የተጀመረውን ትልቅ ፕሮጀክት በማሳካት የሰሜኑን ክፍል ይበልጥ የቱሪስት መስህብነት የበለጠ ከፍ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን መንግስት የአካባቢው ማህበረሰብ በውል በመረዳት ሁሉም የቻለውን እገዛ እንዲያደርግ በገዳሙ ስም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
‎
‎ገዳሙን በገንዘብ ለማገዝ ለምትፈልጉ ወገኖች፤
‎
‎በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ፣
‎
‎1000 77 6016 504 መደገፍ ይችላሉ
‎
‎

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ ******************በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን...
05/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ቃለ መሃላ ፈጸሙ
******************

በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመስረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በመሰየም ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

በዳባት ወረደ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።መስከረም 25/2019 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በጃንበለው ቀበሌ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የ...
05/10/2026

በዳባት ወረደ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀበሉ።

መስከረም 25/2019 ዓ.ም

በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ በጃንበለው ቀበሌ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የየዳባት ወረዳ የሥራ ኃላፊዎች እና የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሰላም አማራጭን ከተቀበሉ ታጣቂዎች መካከል ባዘዘው ትዛዙ እና ጌትነት ሙቀቴ የሰላም አማራጭን መቀበላቸው ለቀጣይ ሕይወታቸው አዲስ ተስፋ እንደሚፈጥርላቸው ገልጸዋል።

ከባለፈው ስህተታቸው በመፀፀት አሁን ላይ ለወረዳው ብሎም ለዞኑ ዘላቂ ሰላም የበኩላቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ መኾናቸውን ተናግረዋል። ሌሎች በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ኅብረተሰቡ እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርበዋል።

ቀደም ሲል ሕዝቡን ሲጨቁኑ ከነበሩ ሀገር-ጠል ኀይሎች ጋር ጥምረት መፈጠሩ እንዳሳዘናቸው አንስተዋል፡፡ እየተፈጠረ ያለው ሂደት ሕዝቡን ለከፋ ጉስቁልና ከመዳረጉ ባሻገር በርካቶችን ላላስፈላጊ መስዋዕትነት መዳረጉን ታጣቂዎች ጠቁመዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች ወደ ሰላማዊ ኑሮ እንዲቀላቀሉ የሚያግዙ ሥራዎች እንደሚከናወኑ የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ መርሻ ወረታ አስረድተዋል ፡፡

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከአምስት መቶ በላይ የታጠቁ ኃይሎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው የገቡ መሆኑን ያነሱት አስተዳዳሪው ስልጠና ወስደው በመንግስት የፀጥታ መዋቅር፣ በግል ማህበራዊ መሰረታቸው እና በሲቪል ሰርቪስና በትምህርት ተቋም የተመደቡ መሆኑን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ስዓት መንግስት የሰላም አማራጩን በማስፋት ከነትጥቃቸው ገብተው ከመንግስት በሚሰጣቸው አቅጣጫ የአካባቢያቸውን ሰላም እንዲያስከብሩ ጥሪ ስለቀረበላቸው የታጠቁ ኃይሎችም አማራጩን ተቀብለው እየገቡ መሆናቸውን አክለዋል፡፡

ከሰላም የሚጠቀም እንጂ የሚጎዳ ነገር እንደሌለ የጠቆሙት የ70ኛ ክፍለ ጦር መገናኛና ኢንፎርሜሽን ኃላፊ ሻለቃ ሙሉብርሃን ጋሻው በበረሀ ያሉ ታጣቂዎች እድሉን ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በየአቅጣጫው የሚገኙ የታጠቁ ኃይሎች በሰላም ወደ መንግስት እንዲገቡ ለማስቻል ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን የዳባት ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደስታው ጌታቸው አስታውቀዋል፡፡

ሂደቱን ውጤታማ ለማድረግና የሰላምን አማራጭ ለማስፋት የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ሰፊ ስራ እያከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

የማህበረሰቡ ዘላቂ ሰላም እንዲረጋጋጥ የፀጥታ መዋቅሩን በስልጠናና በሎጅስቲክስ የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑን ተመላክቷል፡፡

ዘገባው፦ የዳባት ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ*********************7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥ...
05/10/2026

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ
*********************

7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ነው።

በዚህም ወ/ሮ አየለች እሸቴን የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

! ! !

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ  !  !  !
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲሆኑ በእጩነት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረቡ

! ! !

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙየኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀ...
05/10/2026

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የፌዴሬሸን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተሰየሙ

የኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የ7ኛው የፓርላማ ዘመን 1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ 1ኛ መደበኛ ጉባዔውን በዛሬው ዕለት ማካሄድ ጀምሯል።

በዚህም ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልን የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አድርጎ ሰይሟል።

የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። መ/ብርሀን መስከረም 25/01/2019    ለመካነ ብርሀን 2 ኛ ደረጃ ተ/ቤት ተማሪዎች  የመማሪያ ቁሳቁስ መግዛት...
05/10/2026

የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
መ/ብርሀን መስከረም 25/01/2019

ለመካነ ብርሀን 2 ኛ ደረጃ ተ/ቤት ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ መግዛት ለማይችሉ የደብተርና እስክቢርቶ ድጋፍ የተደረገላቸው ሲሆን የኢትዮጲያ ቀይ መስቀል ማህበር 62 ደርዘን ደብተርና 10 ባኮ እስክቢርቶ በዛሬው እለት ድጋፍ አድርጎል።
የት/ቤቱ ር/ መምህር የሆኑት አቶ አምባቸው አወቀ ቀይ መስቀል ኢትዮጲያ ለትምህርት ቤታቸው አያደረገ የሚገኝውን ድጋፍ አመስግነው በባለፈው አመት ለሴት ተማሪዎች የንፅህና መጠበቂያ እና ዘመናዊ ሞንታርቦ ድጋፍ ያደረገልን ሲሆን በዘንድሮው አመት ደግሞ በደብተር እና እስክቢርቶ እጥረት ምክንያት ለመማር የተቸገሩ ተማሪዎች ስላደረገገልን ድጋፍ ከልብ ልናመሰግነውና ድርጅቱ በምነንችለው አቅማችን መደገፍና ማበረታት እንደሚገባም ሀሳባቸውን አጋርተዋል።

 የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከመስከረም 21/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ዞኖች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም 👉 አቶ ደጀን ግርማው አለሙ ➙የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳ...
01/10/2026



የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከመስከረም 21/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ ዞኖች ሹመት ሰጥተዋል። በዚህም

👉 አቶ ደጀን ግርማው አለሙ ➙የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

👉 ወ/ሮ መዝናናት ጣዕመ ➙የሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር የአደረጃጀት ዘርፍ አማካሪ ሁነው ተሹመዋል።

መልካም የስራ ዘመን!!

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ በድጋሜ እንዲመሩ ለአቶ አባይ መንግስቴን ሹመት ሰጥተዋል።መልካም የስራ ዘመን!
01/10/2026

አቶ አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ሆነዉ በድጋሜ እንዲመሩ ለአቶ አባይ መንግስቴን ሹመት ሰጥተዋል።

መልካም የስራ ዘመን!

Address

Writer
Debark'

Telephone

+251927564796

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Janamora Communications posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share