Amhara Agricultural Research Institute-ARARI

Call Directions Website

Amhara Agricultural Research Institute-ARARI The Amhara Agricultural Research Institute (ARARI) was established in 1999/2000 by the ANRS council proclamation no 48/1992 as an autonomous apex body.

The Research Institute is working on technology innovation, adaptation & dissemination.

08/10/2026

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል 2018/19 የምርት ዘመን ምልካም የተባለች የማሽላ ዘር የመነሻ የዘር ብዜት በ43ሄክታር ማሳ መሸፈኑን እና 1364 ኩንታል ምርት እንደሚጠበቅ አሳወቀ
ቀረፃእና ቅንብር፡- ታደሰ ምስጋናው

07/10/2026

የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል በምዕራብ ጎንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ በአርሶ አደር ማሳ በተሻሻለ አሰራር (በመካናይዜሽን) እየተገበረው ያለውን የሰብል የዘር ብዜት ሥራዎችን ለባለ ድርሻ አካላት አሰጎብኝቷል።
ዘገባው የአሚኮ ነው
ምንጭ :-የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ከተፈጥሮአዊ ውህዶች ጋር በማቀነባበር ጥራቱን የጠበቀ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለማዘጋጀት የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ድህረ-...
06/10/2026

ከተፈጥሮአዊ ውህዶች ጋር በማቀነባበር ጥራቱን የጠበቀ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለማዘጋጀት የሚያስችል የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የምግብ ሳይንስና ድህረ-ምርት አያያዝ ምርምር ክፍል በምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም /FSRP/ የበጀት ድጋፍ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂን ከተፈጥሮአዊ ውህዶች ጋር በማቀነባበር ጥራቱን የጠበቀ ጭማቂ ለማዘጋጀት የሚያግዝ የምርምር ቴክኖሎጅን ምዕ/ ጎጃም ዞን ፍኖተ ሰላም ከተማ በፍራፍሬ ጭማቂ የንግድ ስራ/ጁስ ንግድ/ ለተሰማሩ እና ለአጋር አካላት ፍኖተ ሰላም ከተማ ዳሞት ሆቴል አዳራሽ መስከረም 25/2019 ዓም የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

ስልጠናውን የሰጡት በኢንስቲትዩቱ የምግብ ሳይንስና ድህረ-ምርት አያያዝ ምርምር ክፍል ተመራማሪ አቶ ክበር ተመስጌን ሸንኮር አገዳ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ሚና ካላቸው ሰብሎች መካከል አንዱ ቢሆንም ምርቱን ጥራቱን በጠበቀ መንገድ አቀነባብሮ ወደ ገበያ የማቅረብ ሂደት ላይ ክፍተት እንዳለ ገልፀዋል፡፡

አቶ ክበር እየተስተዋለ ያለውን ክፍተት ለመሙላትም የሸንኮር አገዳ ሰብልን በጥንቃቄ መሰብሰብ ከተሰበሰበ በኋላም በ24 ሰዓታት ውስጥ ወደ ማቀነባበሪያ ሂደት ማስገባት እንደሚጠበቅ ለተሳታፊዎች ስልጠና ሰጥተዋል፤
አቶ ክበር አክለውም ምርቱን ለጤና ተስማሚ በሚሆን መንገድ ማዘጋጀት የግድ መሆኑንም ያስረዳሉ ትኩስ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ በአጭር ጊዜ ውስጥ የመበላሸት ባህሪ ስላለው መወሰድ ስለሚገባው ጥንቃቄም አብራርተዋል። በተለይም በቂ የንጽህና አጠባበቅ ባልተከተለ አያያዝና በሽያጭ ወቅት በረቂቅ ተህዋስያን ሊከሰት የሚችል ብክለት፣ እንዲሁም በኢንዛይም ምላሾች ምክንያት ጭማቂው በፍጥነት ስለሚበላሽ ሊወሰዱ የሚገባቸውን ጥንቃቄዎች አስረድተዋል፡፡

አቶ ክበር የሸንኮራ አገዳ ጭማቂን ጥራቱን እንደጠበቀ ለረጅም ጊዜ አቆይቶ ለመጠቀም የሚያግዝ የምርምር ቶክኖሎጅን በዘርፉ ለተሰማሩ የንግድ ማህበረሰብና አጋር አካላት የንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለማዘጋጀት የምንጠቀማቸው የተፈጥሮ ግብዓቶች ሎሚ፣ ዝንጅብል እና ጨው ሲሆኑ አዘገጃጀቱም በ100 ሚሊ የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ላይ 3.0 ሚሊ ሎሚ፤ 0.8 ሚሊ ዝንጅብል እና 1.5 ግራም ጨው ጨምሮ አዘጋጅቶ በመጠቀም የተሸለ ጣዕም እንዲኖረው ከማድረጉም በተጨማሪ ለረጅሚ ጊዜ ሳይበላሻ ለማቆየት እንደሚቻል በመግለፅ አዘገጃጀቱን በተግባር የተደገፈ ስልጠና በተመራማሪው ተሰጥቷል፡፡

በስልጠና መድረኩ ላይ በመገኘት የተሳታፊዎችን አስተያየት በመቀበል ቀጣይ አቅጣጫ የሰጡት በኢንስቲትዩቱ የምግብ ሳይንስና ድህረ-ምርት አያያዝ ምርምር ክፍል አስተባባሪ ተመራማሪ አያሌው ደምስ የሸንኮራ አገዳ ጭማቅን ለምግብነት ለማዋል የታየውን ሰፊ ፍላጎት በማድነቅ በውስንነት የተጠቀሱ የመጭመቂያ ማሽን አቅርቦት እጥረት እና ጭማቂውን ለተጠቃሚው ማህበረሰብ በማስተዋወቅ ላይ የታየውን ክፍተት ለመሙላት ኢንስቲትዩቱ ከባለድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪ አያሌው በጭማቂ ንግድ ስራ የተሰማራችሁ አካላት የወሰዳችሁትን ስልጠና ለሸንኮር አገዳ አምራች አርሶ አደሮችም በመስጠት የተሸለ ግንዛቤ በመፍጠር በዘርፉ ላይ ተገቢውን ውጤት ለማምጣት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ የጭማቂውን ቀለም በተመለከተ ለተነሳው ጥያቄም በተፈለገው የጥራትና የአዘገጃጀት መስፈርት መሠረት ማዘጋጀት እንደሚቻል አብራርተዋል። ተመራማሪው በመጨረሻም በስልጠናው የተሳተፉ አካላት የተማሩትን ቴክኖሎጂ በየአካባቢያቸው ለሚገኘው ማህበረሰብ በማስተማርና ልምዳቸውን በማካፈል የቴክኖሎጂው ተጠቃሚነት እንዲሰፋ የሚጠበቅባቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል።

በስልጠናው የተሳተፉ የጭማቂ ቤት ባለቤቶችም በአስተያየታቸ ቴክኖሎጅውን ለመጠቀም የሸንኮራ አገዳ ጭማቂ ለማዘጋጀት የሚያግዘው የመጭመቂያ ማሽን የገበያ ተደራሽነት ላይ መስራት እንደሚገባ ገልፀው ጭማቂውን ከመጠቀም አንፃር በህብረተሰቡ ዘንድ የሚታየውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት በምርምሩ በኩል የተጀመረው ማስተዋወቅ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ ደሳለኝ አሳየ
ፎቶ ታደሰ ምስጋናው

06/10/2026
የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ ማዕከል ውጤታማ የምርምር እና ብዜት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተጠቀሰበአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምር ...
06/10/2026

የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምርና ስልጠና ንዑስ ማዕከል ውጤታማ የምርምር እና ብዜት ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ ተጠቀሰ

በአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የወራሚት አትክልትና ፍራፍሬ ምርምር እና ስልጠና ንዑስ ማዕከል በን/ማዕከሉ ግቢ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች የኢንስቲትዩቱ የስራ ኃላፊዎች፣ ተመራማሪዎችና ተጋባዥ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተጎብኝተዋል።

የንዑስ ማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ምንየለት ጀምበሬ በፍራፍሬ፣ በአትክልትና በሰብል ጥበቃ ዘርፎች በርካታ የምርምር፣ ብዜትና ማስተዋወቅ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው በFAO በጀት ድጋፍ ከ2.6 ሚሊዮን በላይ የብርቱካናማ ስኳር ድንች ቁርጥራጭ ከ4ሺህ በላይ ለሚሆኑ አርሶ አደሮች መሰራጨቱን እና አሁን ላይም ከ2.8 ሚሊዮን በላይ ቁርጥራጭ መባዛቱን ተናግረዋል። በዚንክ እና ብረት የበለፀጉ የቦሎቄ ዝርያዎችም እየተባዙ መሆናቸውን አቶ ምንየለት ገልጸዋል።

በቡና ምርምር ዘርፍ ምርታማ የቡና ዝርያዎችን የማላመድ፣ የማባዛትና የማስተዋወቅ እንዲሁም ውጤታማ የቡና ተክል አያያዝ ስልቶችን ለአርሶ አደሮች የማስተዋወቅ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው የንዕስ ማዕከሉ ዳይሬክተር ተናግረዋል።

በአቮካዱ፣ ማንጎ፣ ፓፓያ፣ ቀይ ሽንኩርት እና በርበሬ ሰብሎች ላይ የምርምር እና የብዜት ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንና የተሻለ የንጥረ ምግብ ይዘትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአትክልት አይነቶችን የማላመድ፣ የማባዛትና የማስተዋወቅ ስራዎችም እየተከናወኑ ስለመሆናቸው አቶ ምንየለት አስረድተዋል።

የንዕስ ማዕከሉ ተመራማሪዎችም በየዘርፉ እየተሰሩ ስለሚገኙ የምርምር ስራዎች ለጎብኝዎች ገለፃ አድርገዋል።

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስማረ ደጀን በንዑስ ማዕከሉ በምርምር እና መሰረተ-ልማት ግንባታ ዘርፎች አበረታች ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተመልክተናል ብለዋል። በቀጣይም ንዑስ ማዕከሉ ራሱን ችሎ ወደ ማዕከል ደረጃ ሲያድግ ከዚህ የተሻሉ ሰፋፊ የምርምር ስራዎችን ማከናወን የሚችል አቅም ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ንዑስ ማዕከሉ እንዲጠናከርና የሚጠበቅበትን ውጤት እንዲያስመዘግብ ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

የግዙፉ ቀርቀሃ ዛፍን የማባዛትና የማስተዋወቅ ስራዎች በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ተገለጸበአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በባህርዳር ከተማ ቤዛዊት አካባቢ...
05/10/2026

የግዙፉ ቀርቀሃ ዛፍን የማባዛትና የማስተዋወቅ ስራዎች በትኩረት መሰራት እንዳለባቸው ተገለጸ

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በባህርዳር ከተማ ቤዛዊት አካባቢ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለውን ግዙፉ ቀርቀሃ ዛፍን(giant bamboo) የማላመድና የማባዛት ስራዎችን እየሰራ ሲሆን ተግባሩን የኢንስቲትዩቱ የማኔጅመንት አባላት፣ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ጎብኝተውታል።

በምርምር ማዕከሉ የደን ምርምር ክፍል አስተባባሪ አቶ ጌታቸው ካሳ ማዕከሉ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የዛፍ አይነቶችን የማላመድ፣ የማባዛትና የማስተዋወቅ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ገልፀው ግዙፉን ቀርቀሃን ጨምሮ ለጣውላ እና እንጨት ምርት የሚያገለግሉ ሀገር በቀል የቀርቀሃ እና ሌሎች የዛፍ አይነቶች ዝርያዎች ላይ የምርምር ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ግዙፉ ቀርቀሃን ከውጭ ሀገር በማስመጣት ያለው የመላመድ ችሎታ ተፈትሾ በሚማማው ስነ ምህዳር በሚፈለገው ልክ ማደግ እንደሚችል የገለፁት ተመራማሪው የመባዛት ተፈጥሮአዊ ባህሪው ልዩ ትኩረትን የሚጠይቅ በመሆኑ በተሰራ ተከታታይ የመባዛት ስልቶች ሙከራ በቲሹ ካልቸር እና ግንጣዩን ኬሚካል በመጠቀም ማባዛት ውጤታማ ስልት ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል። በመሆኑም የችግኝ ማባዛት ስራው በቤዛዊት ጣቢያ እየተሰራ መሆኑን አቶ ጌታቸው አስረድተዋል።

በኢንስቲትዩቱ የደን ምርምር ዳይሬክተር ዶ/ር ምናለ ወንዴ በበኩላቸው ግዙፉ ቀርቀሃ ከሀገር በቀል ዝርያዎች በተሻለ በፍጥነት በማደግ ከ5-6 አመት ጊዜ ውስጥ የሚፈገውን ቁመት፣ ስፋትና ጥንካሬ መስጠት የሚችል መሆኑን ገልጸው ዛፉ ከፍተኛ ጥንካሬ ያለው በመሆኑ በተለያዩ ሀገራት ለግንባታ እና ለቤት እቃዎች መስሪያነት፣ ለጨርቃጨርቅና ለወረቀት ኢንዱስትሪ፣ ከአካባቢ ጥበቃና ውሃ ማቆር፣ ለምግብነትና ለእንስሳት መኖነት እና ለሀይል ምንጭነት የሚያገለግል በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ የማባዛት ስራውን እያከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። ዛፉን በቀጣይ በስፋት ለማባዛትና ለማስተዋወቅ የተለያዩ አጋርና ባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ይጠይቃልም ብለዋል።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስማረ ደጀን የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ግዙፉ ቀርቀሃን ለማላመድና ለማባዛት ያደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልፀው በቀጣይ በስፋት ተባዝቶ ጥቅም ላይ እንዲውል የማባዛት ስራው ላይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መስራትና የሚፈለገው ውጤት ላይ ማድረስ ይገባል ብለው ለዚህ ደግሞ ኢንስቲትዩቱ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የተሳተፉ አካላትም በምርምር እና ዘር ብዜት ስራው ዙሪያ በርካታ አስተያየቶችንና ጥያቄዎችን አንስተው ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በቀጣይ የብዜትና የማስተዋወቅ ስራው ላይ በጋራ በመስራት የማዕከሉን ጥረት ለተሻለ ውጤት ማብቃት እንደሚገባም አንስተዋል።

የምርምር እና ዘር ብዜት ስራዎችን በታቀደላቸው አግባብ እየፈፀመ መሆኑን የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀበአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018/...
04/10/2026

የምርምር እና ዘር ብዜት ስራዎችን በታቀደላቸው አግባብ እየፈፀመ መሆኑን የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018/2019 የመኸር ወቅት በምርምር ጣቢያ ደረጃ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎችን ለኢንስቲትዩቱ የማኔጅመት አባላት፣ ከፍተኛ ተመራማሪዎችና ጥሪ ለተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት አስጎብኝቷል።

በመስክ ጉብኝቱ የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ፈረደ ምርምር ማዕከሉ በሁሉም የምርምር ዘርፎች ውጤታማ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን አስረድተዋል። ማዕከሉ በመኸር ወቅት 122 ሙከራዎችን በመስራት 23 ቴክኖሎጅዎችንና ምክረሀሳቦችን ለማውጣት እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው 18 ቴክኖሎጅዎችን ደግሞ ለተጠቃሚዎች የማስተዋወቅ ስራ እየሰራን ነው ብለዋል።

ማዕከሉ በራሱ አቅዶ ከሚሰራቸው የምርምር ስራዎች በተጨማሪ ክልላዊ እና ብሔራዊ ሙከራዎችንም ከሌሎች የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑን ማዕከል ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።

በመነሻ ዘር ብዜት በኩልም በብዕርና አገዳ እና በጥራጥሬ ሰብሎች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀው 3.2 ሄ/አራቢ ዘር፣ 37.6 ቅድመ መስራች እና 84ሄ/ር መሬት በማህበረሰብ አቀፍ የዘር ብዜት ስርአት እየተባዛ መሆኑን አብራርተዋል።

ስርአተ-ምግብን ለማሻሻል ከFAO በተገኘ በጀት ድጋፍ 2.6 ሚሊዮን የብርቱካናማ ስኳር ድንች ቁርጥራጭ መባዛቱን የገለፁት አቶ ምስጋናው ማዕከሉ በብሔራዊ ደረጃ በሚያስተባብረው የድንች ምርምር ለቤት ውስጥ ፍጆታ እና ለመስኖ የሚሆኑ ዝርያዎች መውጣታቸውና ከበሽታ ነፃ የሆነ 450ሺህ ኮረት ድንች መመረቱን ተናግረዋል። በደን እና ጥምር ጠቀሜታ ባላቸው ችግኞች ብዜት በኩልም 50ሺህ ልዩ ልዩ ችግኞች መባዛታቸውን ገልፀዋል።

ማዕከሉ በአጠቃላይ በሰብል፣ በአፈርና ውሃ፣ በደን፣ በዘር እና በማህበራዊ ምጣኔ ሀብት የምርምር ዘርፎች ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ችግሮችን ተቋቁሞ የተሻሉ ስራዎችን እየፈፀመ መሆኑ ተገልጿል።

በመስክ ጉብኝቱ በየዘርፉ የሚመለከታቸው ተመራማሪዎች የተሰሩ ስራዎችን በዝርዝር ለጎብኝዎች አስረድተዋል።

በቀጣይ ይለቀቃሉ ተብለው ለታሰቡ የሰብል ዝርያዎች የማረጋገጫ ሙከራ ስራዎች እየተሰሩ ስለመሆናቸው፣ በማዕከሉ የወጡ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ተለቀው በዘር አባዦች አና አርሶ አርሶ አደሮች ዘንድ ተፈላጊ የሆኑ የሰብል ዝርያዎችን የአራቢ እና የቅድመ መስራች የዘር ደረጃዎች በጥንቃቄ የማባዛት ስራ እየተሰራ መሆኑን እና የቴክኖሎጅ ማስተዋወቅ ስራዎችም አርሶ አደሩን ባሳተፈ መልኩ በአርሶ አደር ማሳ ላይ እየተሰሩ መሆናቸውን ተመራማሪዎች አስረድተዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የተሳተፉ አካላትም ማዕከሉ ፈተናዎችን ተቋቁሞ እያከናወናቸው የሚገኙ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ገልጸዋል።

አረጋውያንን በምርምር ስርአቱ ውስጥ ማካታትና ለአረጋውያን ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸየአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 35ኛው  የአረጋውያን  ቀንን በፓናል ...
01/10/2026

አረጋውያንን በምርምር ስርአቱ ውስጥ ማካታትና ለአረጋውያን ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 35ኛው የአረጋውያን ቀንን በፓናል ውይይት አክብሯል።

በፓናል ውይይቱ የኢንስቲትዩቱ የማህበራዊ ምጣኔ ሀብትና ምርምር ስርፀት ክፍል ተመራማሪ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ የአረጋውያን ቀንን አስመልክቶ የውይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን አረጋውያን ለሀገር ያበረከቱትን አስተዋፅኦ የሚመጥን ድጋፍና እንክብካቤ ማድረግ፣ ያላቸውን የካበተ ዕውቀትና ክህሎት እንዲያካፍሉ እድሉን ማመቻቸት እና አሉታዊ ተፅዕኖ በሚያሳድሩባቸው ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ አለም አቀፍ እና ሀገራዊ የህግ ድጋፎችንና ድንጋጌዎችን በማጣቀስ አብራርተዋል።

በውይይቱ የተሳተፉ የኢንስትዩቱ ሰራተኞችም ኢንስቲትዩቱ አረጋውያንን በምርምር ስርአቱ ውስጥ በማሳተፍ ልምድና ችሎታቸውን እንዲያካፍሉ፣ በአረጋውያን ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ እና እንደ ኢንስቲትዩት አጋውያንን በመደገፍ ማህበራዊ ሀላፊነታችንን መወጣት ይገባናል የሚሉ ሀሳቦችን አንስተዋል።

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰማኝ አስረዴ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ በቀጣይ መከናወን በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አተኩረው አቅጣጫ ሰጥተዋል። በዚህም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በማዕከላት ደረጃም እንዲጠናከሩ፣ በምርምር ስርአቱ ውስጥ አረጋውያንን ያሳተፈ ስራ እንዲሰራ፣ በጦሮታ ከተቋሙ የወጡ አረጋውያንን ማገዝና እውቅና መስጠት የሚቻልበት መንገድ እንደሚፈጠርና አጋዥ የሌላቸው አረጋውያንን በተለያየ አግባብ በቀጣይ ኢንስትቲዩቱ እና ሰራተኞች ማገዝ የሚችሉበት መንገድ እንደሚመቻች በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል  የማህበረሰብ አቀፍ የሽንብራ ዘር ብዜት አመራረት ስልጠና ሰጠየአዴት ግብርና ምርምረ ማዕከል በንጥረ- ነገር ይዘታቸው የበለፀጉ ሰብሎችን በመያዝ የምግብ ስርዓ...
30/09/2026

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል የማህበረሰብ አቀፍ የሽንብራ ዘር ብዜት አመራረት ስልጠና ሰጠ

የአዴት ግብርና ምርምረ ማዕከል በንጥረ- ነገር ይዘታቸው የበለፀጉ ሰብሎችን በመያዝ የምግብ ስርዓትን የሚያሻሽል ስልጠና በሰሜን ጎጃም ዞን በሶስት ወረዳዎች ለተመረጡ አርሶ አደሮች ስልጠና አካሄደ።

በአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል ከአለም አቀፍ የምግብ እና እርሻ ድርጅት (FAO ) የበጀት ድጋፍ ማህበረሰብ አቀፍ የሽንብራ የዘር ብዜት አመራረት ቴክኖሎጂዎች ላይ ስልጠና ተሰጧል። የሽንብራ ሰብል ከፍተኛ የፕሮቲን ይዘት ያለው በመሆኑ በተለይም የአፈር ለምነትን ከማሻሻሉ በተጨማሪ በሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ ተፈላጊ በመሆኑ ትኩረት እንደተሰጠው ተገልጿል፡፡

የአማራ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አስማረ ደጀን(ዶ/ር) በመክፈቻ ንግግራቸው እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ የማህበረሰብ የአመጋገብ ስርዓት ችግርን ለመቅረፍ ከተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር እየሰራ ይገኛል ከእነዚህም ውስጥ አንዱ የአለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (FAO) አንዱ ነው ብለዋል። ስለዚህ የህዝብ ቁጥራች በየጊዜው ከመጨመሩ እንፃር ምርት እና ምርታማነትን የሚጨምሩ አዳድስ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ፤በጥራት እና በመጠን በአነስተኛ ቦታዎች ማምረት ካልቻልን የአመጋገብ ስርዓታችን ሆነ የተሻለ ትውልድ መገንባት አንችልም ብለዋል።

የአዴት ግብርና ምርምር ማዕከል በ2018 ዓ.ም ጀምሮ በፕሮጀክቱ ድጋፍ በቦሎቄ እና በብርቱኳናማ ስኳር ድንች ሰብሎች ላይ ሲሰራ መቆየቱን አስታውሰው አሁን ደግም የሽንብራ ሰብልን በማካተት የዘር ብዜት ስራ እየሰራ መሆኑን የማዕከሉ ዳይሬክተር አቶ ምስጋናው ፈረደ ገልፀዋል፤ስለዚህም ይህ ስልጠና በንጥረ ነገር ይዘታቸው የበለፀጉ ሰብሎችን ለተጠቃሚ ማህበረሰብ ለማድረስ እና ስርዓተ-ምግብን ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው ብለዋል።

በኢንስቲትዩት የዘር ቴክኖሎጂ እና የዘር ምርምር ዳይሬክተር እንዲሁም የአለም የምግብ እና እርሻ ድርጅት(FAO) አስተባባሪ ዶ/ር አእምሮ በዛብህ እንደገለፁት ፕሮጀክቱ በ2019 ዓ.ም በሰሜን ጎጃም ዞን በሶስት ወረዳዎች ማለትም በይልማና ዴንሳ፣ በሰሜን ሜጫና በባህር ዳር ዙርያ ለ66 አርሶ አደሮች 33 ኩንታል የሽንብራ ዘር ፣ለ102 አርሶ አደሮች 40 ኩንታል ቦለቄ እንዲሁም ለ2430 አርሶ አደሮች 2.6 ሚሊየን የብርቱካናማ ስኳር ድንች ቁርጥራጭ መስጠቱን ገልፀው የፕሮጀክቱ አላማ ጥራት ያለው እና ለቀጣይ የሚሆን ዘር ማምረት እንጅ ለምግብነት የሚውል ዘር ማምረት እንዳልሆነ ጠቁመዋል።
ለዚህም የዛሬ ሰልጣኝ አርሶ አደሮች ከማዕከሉ የሚሰጣቸውን ጥራት ያለው ዘር እና ስልጠና በአግባቡ በመጠቀም ከራሳችው አልፈው ለሌላው ማህበረሰብ የዘር ምንጭ መሆን እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

በስልጠናው አርሶአደሮች ፣የወረዳ ግብርና ባለሙያዎች፣ የወረዳ ማህበራት ባለሙያዎች ፣የአማራ ምርጥ ዘር ባለሙያ እና የግብርና ጥራት እና ቁጥጥር ባለስልጣን ባህር ዳር ቅርንጫፍ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
(በታደሰ ምስጋናው

Address

Debra Markos
527,BAHIRDAR

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara Agricultural Research Institute-ARARI posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share