Basocommunication

Call Directions Contact the organization

Basocommunication ባሶና ወራና ወረዳ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ውስጥ ከሚገኙት 22 የገጠር ወረዳዎች አንዱ ግዙፍ ወረዳ ነው። ባሶና ወራና ወረዳ በሰሜን ሸዋ ዞን ከሚገኙት 24 የገጠር ወረዳዎች አንዷ ስትሆን በውስጧ 21 የገጠር ቀበሌዎችን ይዛለች

ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1...
05/10/2026

ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሾሙ።

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ ዐቢይ አሕመድን (ዶ.ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በ2010 ዓ.ም ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ በርካታ ስኬታማ ተግባራትን ሠርተዋል።

ሀገር በቀል የመደመር የፖለቲካ እሳቤ አዲስ የፖለቲካ ባሕል እንዲኾን አስችለዋል።

የጥል ግድግዳ እናፍርስ፤ የፍቅር ድልድይ እንገንባ በሚለው መርሐቸው ለዓመታት ተራርቀው የነበሩ ፖለቲከኞችን አገናኝተዋል። በሥልጣን ዘመናቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በሀገሪቱ ሥልጣን እንዲይዙ እና ሀገር እንዲያገለግሉ አድርገዋል።

በከፍተኛ ችግር ውስጥ የነበረውን የሕዳሴ ግድብ ከችግር በማውጣት እንዲጠናቀቅ አመራር ሰጥተዋል። ከሕዳሴው ግድብ መጠናቀቅ ማግስት ታላላቅ ፕሮጄክቶችን አስጀምረዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በዓለም ላይ አዲስ ታሪክ አጽፈዋል። ኢትዮጵያን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ኢኮኖሚ በማሸጋገር አስደናቂ የኢኮኖሚ እድገት እንዲኖራት አድርገዋል። በከተማ እና በገጠር ኮሪደር ልማቶች የኢትዮጵያን ገጽታ በከፍተኛ ሁኔታ ቀይረዋል። የኢትዮጵያን ከተሞች ከተጎሳቆሉበት አውጥተው ወደ ውብ እና ሳቢ ገጽታ መልሰዋል።

ኢትዮጵያ የስንዴን ምርት ከውጭ መቀበል አቁማ ለውጭ ገበያ የምታቀርብ ሀገር ያደረጓት በእርሳቸው የሥልጣን ዘመን ነው። በሌማት ቱሩፋት መርኃ ግብርም በእንስሳት ሃብት ሀገሪቱ በታሪኳ አይታው የማታውቀውን እድገት እና ለውጥ አምጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸው ታላላቅ ሀገራዊ ሥራዎችን ያሳኩ ዘንድ በድጋሜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ኢትዮጵያን እንዲመሩ ተሹመዋል።

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ 🇪🇹

•••
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊
•••

"የጎርጎራ ቃልኪዳናችን፤ ለዘላቂ ሰላም እና ለሁለንተናዊ ብልጽግናችን"
•••
ለወቅታዊ ፣ ትክክለኛና አዳዲስ መረጃዎች የፓርቲያችንን የማህበራዊ ገፆች ይወዳጁ።
ትዊተር :- twitter.com/AppAmhara?s=09
ዩቲዩብ :- youtube.com/channel/UCxQ5MOnm-YH514Qdta0Kysg
ቴሌግራም:- t.me/amharaapp
ቲክቶክ፡- tiktok.com/

05/10/2026

አዲስ መንግሥት፣ አዲስ አቅጣጫ፣ አዲስ ተስፋ፦ የኢትዮጵያ የታደሰ የከፍታና የዕድገት ምዕራፍ
******************
አዲስ መንግሥት፣ አዲስ አቅጣጫ፣ አዲስ ተስፋ በሚል መሪ ጽንሰ-ሀሳብ የሚገለጸው ይህ ታሪካዊ ምዕራፍ፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ ወደ ላቀ የስልጣኔ ማማ፣ ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለመሸጋገር የያዘችውን ፅኑ ሀገራዊ ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

ከታሪካዊው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አዳራሽ የሚመነጨው ይህ አዲስ አቅጣጫ፣ የሕዝባችንን የነገ ብሩህ ተስፋ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባትና የሀገር በቀል ልማት ስትራቴጂዎቻችንን በላቀ የውጤታማነት ደረጃ ለማስቀጠል የተቀረፀ ታላቅ ራዕይ ነው።
ይህ የታደሰ ጉዞ በሁሉም የልማት መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን ይበልጥ በማጠናከር፣ ተቋማዊ አቅምን በማጎልበት እና የዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ወደ ተጨባጭ ተግባር ይቀየራል።

የሕዝባችንን አንድነትና ጥንካሬ አስተባብሮ በመያዝ፣ በጋራ ጥረትና በማይበገር ቁርጠኝነት ወደፊት መራመድ የነገዋን የበለፀገችና የታፈረች ኢትዮጵያን እውን የማድረጊያ ዋነኛ ቁልፍ ነው።

በአዲስ ተስፋና በጠራ አቅጣጫ ኢትዮጵያን እንገነባለን!

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርየውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ...
05/10/2026

ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ እና በቀይ ባሕር ዙሪያ ያላትን መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በማንኛውም ኃይል ሊቀየሩ አይችሉም - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው፤ ኢትዮጵያ የዓባይ ወንዝ መነሻ ስትሆን፣ ከሞላ ጎደል አብዛኛው የዓባይ ውሃ የሚመነጨው ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ቦታዎች ነው፡፡

ወንዙ ለናይል ወንዝ አጠቃላይ የውኃ መጠን 85 በመቶውን አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡ በመሆኑም በዓባይ ወንዝ አጠቃቀም እና አስተዳደር ዙሪያ የሚደረጉ ማናቸውም ውይይቶች እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ያገናዘቡ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡

በተመሳሳይ ቀይ ባሕር ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ ትስስር ያላት የውኃ አካል መሆኑን የጠቀሰው መግለጫው፤ በጊዜ ሂደት የፖለቲካ ድንበሮች ቢቀያየሩም ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላት የጠበቀ ቁርኝት ዛሬም እንደቀጠለ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

የኢትዮጵያ ቅርብ የተባለው ድንበር ከባሕር ዳርቻው 48 ኪ.ሜ ብቻ ርቀት ላይ እንደሚገኝም አብራርቷል፡፡

በመሆኑም በቀጣናዊ የባሕር ላይ ጉዳዮች እና የደኅንነት መዋቅር ላይ የሚደረግ ማንኛውም ውይይት የኢትዮጵያን ሕጋዊ ጥቅሞች እና ከቀይ ባሕር ጋር ያላትን ዘላቂ ትስስር ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት ሲል አሳስቧል፡፡

እነዚህ መልክዓ ምድራዊ እና ታሪካዊ እውነታዎች በፖለቲካዊ ዲስኩር፣ በማስገደድ እርምጃዎች ወይም ሀገርን በማተራመስ ድርጊቶች ሊቀየሩ እንደማይችሉ የገለጸው ሚኒስቴሩ፤ በተላላኪዎች አማካይነት የሚወሰዱ እርምጃዎች ወይም የጥቃት ድርጊቶች መሬት ላይ ያለውን እውነታ እንደማይቀይሩት ሁሉ፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሕጋዊ ጥቅም፣ ሚና እና ኃላፊነት ሊያሳንሱት አይችሉም ሲል አስምሮበታል፡፡

ኢትዮጵያ ሰላማዊ ግንኙነትን፣ የጋራ መከባበርን እና ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር እንደምትቀጥል ያረጋገጠው ሚኒስቴሩ፤ ሉዓላዊነቷን፣ የግዛት አንድነቷን እና ዋነኛ ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለመጠበቅ ምንጊዜም ዝግጁ መሆኗን አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም ሁሉም የቀጣናው ተዋናዮች የጋራ ፈተናዎችን ከግጭት እና አንዱ ተጠቃሚ ሌላው ተጎጂ ከሚሆንበት (ዜሮ-ድምር) አካሄድ ይልቅ፣ ገንቢ በሆነ ውይይት፣ በአጋርነት እና በመልካም ጉርብትና መርሆች ላይ ተመሥርተው እንዲፈቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫው ጥሪ አቅርቧል፡፡

05/10/2026

በሰሜን ሸዋ ዞን በባሶና ወራና ወረዳ እየለማ የሚገኝ የስንዴ፣ የገብስ እና የባቄላ ስብል አሁናዊ ገጽታ በከፊል የምስል ማሳያ

05/10/2026
የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል።/መሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን : መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም/የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ  ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል። በግ...
05/10/2026

የአዲሱ መንግሥት ምስረታ ዛሬ ይካሄዳል።

/መሐል ሜዳ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን : መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም/

የአዲሱ መንግሥት ምሥረታ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በግንቦት ወር 2018 ዓ.ም በተካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ያለው ሆኖ መጠናቀቁ የሚታወስ ነው።

በዚሁ ምርጫ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10,438 እጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች ተሳትፈዋል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲሆን ተጠሪነቱም ለሀገሪቱ ሕዝብ መሆኑ ተደንግጓል።

በተጨማሪም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀመር በተደነገገው መሠረት፣ የመንግሥት ምስረታ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ይከናወናል።

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መንበር ያገኘው የፖለቲካ ፓርቲ የፌደራሉን ሕግ አስፈጻሚ አካል የሚያደራጅ ሲሆን፣ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ ሕግ አስፈጻሚ አካል በዕለቱ በይፋ ኃላፊነት ይረከባል።

ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።

ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች አስቀድመው የመንግስት ምስረታ አካሂደዋል።

ብቃት እንጂ ኮታ አይደለም - ለአዲሱ የመንግሥት ምስረታ የቀረበ ጥሪአዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪ...
04/10/2026

ብቃት እንጂ ኮታ አይደለም - ለአዲሱ የመንግሥት ምስረታ የቀረበ ጥሪ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 24፣ 2019 (ኤፍ ኤም ሲ) በነገው ዕለት የሚካሄደው የመንግሥት ምስረታ ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚ ከተደቀኑባት ዘመን ተሻጋሪ ፈተናዎችና እድሎች አንፃር ሲታይ እጅግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።

የሚመሰረተው አዲስ መንግሥት ሀገርን የሚያሻግር፣ ፍትህን የሚያረጋግጥ፣ ሀገር የሁሉም መሆኗን በተግባር የሚያሳይና በጋራ ጠንካራ ሀገር የመመስረት ሂደቱን ይበልጥ የሚያፋጥን እንዲሆን የሕዝብ ተስፋ ከፍተኛ ነው።

ሆኖም ይህ ተስፋ እውን ሊሆን የሚችለው የመንግሥት ስልጣን ክፍፍል በብቃት፣ በአርቆ አሳቢነትና በሀገር አራማጅነት ላይ ሲመሰረት፤ በብሄር ወይም በቡድን "ኮታ" ስብስብ ላይ ሳይወድቅ ሲቀር ብቻ ነው።

የስልጣን ክፍፍልን በኮታ ማደላደል ለጊዜያዊ የፖለቲካ ማረጋጊያ ይጠቅም ከሆነ እንጂ፤ በረጅም ጊዜ ውጤቱ የተቋማት መዳከምን፣ የሙስና መስፋፋትንና የአመራር ውድቀትን እንደሚያስከትል የታሪክ ተሞክሯችን ያሳያል።

ሀገርን ወደተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚቻለው ይዘውት የሚመጡት የብሄር ወይም የቡድን ማንነት ብቻ ሳይሆን፤ ያላቸው እውቀት፣ ክህሎት፣ ስነምግባር እንዲሁም አርቆ አሳቢነት በሚመዝናቸው አዳዲስ መሪዎችና ባለሙያዎች ስብስብ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመር መንግሥት በተሰኘው መፅሐፋቸው ላይ እንደገለጹት፤ የአንዲት ሀገር ጥንካሬ በምትገነባቸው ጠንካራ ተቋማትና በተቋማቱ ውስጥ በሚመደቡ ብቁ ስብዕናዎች ይወሰናል፡፡

ስልጣን ኮታ ሲሆን ተቋማት የቡድን ጥቅም ማስጠበቂያ ይሆናሉ፤ ብቃት ሲሆን ግን ተቋማት ለሕዝብ እኩል አገልግሎት የሚሰጡ የአገልግሎት ማዕከል እንደሚሆኑም ይኸው መጽሐፋቸው ያትታል፡፡

ቀጣይ ሀገር ለመምራት በሚመሰረተው መንግሥት ውስጥ የሚካተቱ አመራሮች የዕለት ተዕለት የፖለቲካ ትኩሳትን ብቻ የሚመለከቱ ሳይሆን፤ የሀገሪቱን የቀጣይ ዓመታት ህልም የሚቀርፁ አርቆ አሳቢዎችና ለውጡን ከመሬት የሚያገናኙ ሀገር አራማጆች ሊሆኑ ይገባል።

«የመደመር መንገድ» መፅሐፍ ውስጥ እንደተወሳው፤ ሀገራዊ ትረካችንን ከግጭትና ከከፋፋይነት ወደ ልማትና ህብረት ለመቀየር የላቀ የሀሳብ ልህቀት ያላቸው መሪዎች ያስፈልጉናል።

ብቃት ያለው አመራር የህግ የበላይነትንና ፍትሃዊነትን ያረጋግጣል፤ የሁሉም ዜጋ መብት እኩል የሚከበረውና ሀገር የሁሉም መሆኗ የሚረጋገጠው የመንግሥት አመራሮች ለሁሉም ዜጋ እኩል የሚቆሙ የሙያ ብቃት ሲኖራቸው ብቻ ነው።

አሁን ያለንበት ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ ሁኔታ በስሜት ሳይሆን በዕውቀትና በስትራቴጂ የሚመራ አመራርን ይፈልጋሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተለያዩ ጊዜያት ደጋግመው እንደገለጹት፤ ሀገር የምትገነባው በጋራ ስራና በችሎታ እንጂ በዘርና በፖለቲካ ቅርጫ አይደለም፡፡

ሀገር የሁሉም የምትሆነው ሁሉም ዜጋ በችሎታውና በስራው የሚመዘንበት ስርዓት ሲዘረጋ ነው፤ ይህ እውነት በነገው ዕለት ለሚመሰረተው መንግሥትም ዋና መርህ ሊሆን ይገባል።

በታሪኩ ለገሰ

#ኢትዮጵያ #ትልቅሀገር #ትልቅሕዝብ #ታላቅርዕይ

Address

Debre Berhan
251

Telephone

251116813902

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Basocommunication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Basocommunication:

Shortcuts

Share