Amhara North Shewa Zone Communication

Call Directions Website Contact the organization

Amhara North Shewa Zone  Communication ሰሜን ሸዋ ዞን በግምት 8 degree 38’ --- 10 degree 42’ ሰሜን ላቲቲዩድ 38 degree 40’ – 40 degree 43’ ሎጊትዩድ

ደብረብርሃን የተቆረቆረችውና የተሰየመችው ከ5ዐዐ ዓመት በፊት በ1446 ገደማ በአፄ ዘርዓያዕቆብ /1426 – 146ዐ/ ነበር፡፡
ከተማዋ ቀድሞ ደብረ ኢባ በመባል የምትታወቅ ሲሆን የንጉሱ የግራ በአልቲሐት ርስት ነበረች፡፡
በ144ዐ ዎቹ መጀመሪያ ንጉሱ ጐበኟትና ደስ ስለተሰኙባት የድንኳን ከተማቸውን ከተሙባት፡፡ አሁንም የስላሴ ቤ/ክርስቲያን በሚገኝበት ቦታ ላይ ሶስት አብያተ ክርስቲያናት ነበሩ፡፡
ከተማዋ ስያሜዋን ያገኘችው ለስዕልና ለመስቀል አንሰግድም የሚሉ የእስጢፋኖስ ተከታዮች በ1446 ከንጉሱና ከካህናቱ ጋር በጉባኤ ክርክር ላይ አቋማቸውን አንለውጥም በማለታቸው ምላሣቸው ተቆርጦ እንዲገደሉ ተፈረደባቸው ፍርዱ በተፈፀመ በ38ኛው ቀን በስላሴ ቤ/ክርስቲያን “ ብርሃን “ ታዬ ይባላል፡፡ ንጉሱም በመዋዕለ ዜናቸው ይህንኑ ማየታቸውን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ እስጢፋኖሳውያኑ ላይ ለተፈረደው ቅጣት ለትክክለኛነቱ የታየው ብርሃን አምላካዊ ማረጋገጫ ነው በማለት ንጉሱ ከተማዋን ደብረብርሃን ብለው መሠየም ለ14 ዓመት በከተማዋ ኖረውባታል፡፡

በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማት የልምድ ልውውጥ ተካሄደበሙዝ ክላስተር ልማት የተገኙ ተሞክሮዎችን ለማካፈልና የጋራ ልማትን ለማፋጠን ያለመ የልምድ ልውውጥ በደዋ ጨፋ ወረዳ ተካሄደ።በጥ...
27/10/2026

በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማት የልምድ ልውውጥ ተካሄደ

በሙዝ ክላስተር ልማት የተገኙ ተሞክሮዎችን ለማካፈልና የጋራ ልማትን ለማፋጠን ያለመ የልምድ ልውውጥ በደዋ ጨፋ ወረዳ ተካሄደ።

በጥቅምት 16/2019 ዓ.ም የሰሜን ሸዋ ዞንና የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር አመራሮች፣ ባለሙያዎችና የህብረተሰብ ተወካዮች በወረዳው እየተካሄደ ያለውን የሙዝ ክላስተር ልማት በመጎብኘት የመስክ ምልከታና የልምድ ልውውጥ ውይይት አካሂደዋል።

በጉብኝቱ የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ፣ የሰሜን ሸዋ ዞን የብልፅግና ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ኢሊያስ አበበ እንዲሁም ከሰሜን ሸዋ ዞን በስድስት ወረዳዎች የተውጣጡ ባለሙያዎችና የህብረተሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በመስክ ምልከታው የሙዝ ክላስተር ልማቱ ለአርሶ አደሩ ተጨማሪ የገቢ ምንጭ በመፍጠር፣ የኑሮ ደረጃን በማሻሻልና የኢኮኖሚ አቅምን በማጠናከር ረገድ ያለው አስተዋጽኦ ተገምግሟል። ተሞክሮውም ሌሎች አካባቢዎች በመተግበር ሊጠቀሙበት የሚችሉት አበረታች የልማት ልምድ መሆኑ ተጠቁሟል።

ተሳታፊዎቹ የጋራ ጉብኝቱ በአጎራባች ህዝቦች መካከል ያለውን የአብሮነት፣ የትብብርና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ከማጠናከሩም በላይ የጋራ ልማትን ለማፋጠንና ለጋራ ብልጽግና ለመድረስ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋ።

"የበደልነዉን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን" የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በጫካ  ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል። የ...
26/10/2026

"የበደልነዉን ሕዝብ ለመካስ ዝግጁ ነን" የመንግስትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጠገዴ ወረዳ በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን ተቀብለዋል።

የሰላም አማራጭን የተቀበሉት ታጣቂዎች እርስ በእርስ መጠፋፋት ምንም ዓይነት ፋይዳ እንደሌለው ገልጸዋል።

የሰው ሕይወትን ከሚቀጥፈው ግጭት ወጥቶ ሰላማዊ ሕይወትን መምረጥ እንደሚገባ በመገንዘብ የሰላም ጥሪውን መቀበላቸውን ተናግረዋል።

የውጭ ኃይሎች እና የውስጥ ተላላኪዎች የፍላጎት ማስፈጸሚያ መኾን እንደማይፈልጉ አመላክተዋል። ላደረሱት ጉዳት ይቅርታ በመጠየቅ ሕዝብን ለመካስ እንደሚሠሩ ተናግረዋል።

የሰላም አማራጭ የተቀበሉትን ታጣቂዎች የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ እንደሚያመላክተው በጫካ ውስጥ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎች የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ ቀርቧል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።ሞጃ ኮሙኒኬሽን (ጥቅምት 2019 ዓ.ም) በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ከኢፌደሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት 52...
26/10/2026

በሰላምና ጸጥታ ዙሪያ ከመንግስት ሰራተኞች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።
ሞጃ ኮሙኒኬሽን (ጥቅምት 2019 ዓ.ም)
በሰሜን ሸዋ ዞን በሞጃና ወደራ ወረዳ ከኢፌደሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት 52ኛ ክፍለጦር ዋና አዛዥ ኮለኔል አብርሃ ታደሰ በተገኙበት በወቅታዊ የሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከጠቅላላ የወረዳው የመንግሥት ሠራተኞች ጋር ዉይይት ተካሂዷል።
የ52ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል አብርሃ ታደሰ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ "ኢትዮጵያ ጡት ነካሽ ታሪካዊ ጠላቶቿ ባሰቡባት እኩይ ሴራ ልክ ሳይሆን፣ ሁልጊዜም በጀግኖች ልጆቿ ጽናት አሸናፊ በመሆን ከነክብሯ ትቀጥላለች" ብለዋል።
አዛዡ አክለውም የአካባቢያችን ሰላም በዘላቂነት እንዲረጋገጥ ከተፈለገ እያንዳንዱ ዜጋ ስለ ሰላም መሥራትና ማኅበራዊ አንድነትን ማጠናከር እንዳለበት ጠቅሰው፤ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ያለምንም መስተጓጎል ለማስቀጠል የመንግሥት ሠራተኛው በግንባር ቀደምትነት የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ምሁራን ሀገር ያስቀመጠቻቸውን ታላላቅ የብልፅግና ግቦች ለማሳካት መሪና ቀዳሚ ፈጻሚ መሆን እንዳለባቸው ገልጸው፤ በተለይም ኢትዮጵያ በታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶቿ (ቀይ ባሕርና አሰብን ጨምሮ) የመጠቀም መብት ጥያቄዋ ዳር እንዲደርስ በሙሉ አቅም መደገፍና ደጀን መሆን እንደሚገባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋ በበኩላቸው፤ የገጠመንን የጸጥታ ቀውስ በጋራ ክንድ ቀልብሰን፣ የወረዳችንን ሰላም በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ ሕዝባችን በሰላም ወጥቶ በሰላም እንዲገባ ለማስቻል መረባረብ ይገባል ብለዋል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም "በሕዝባችን ላይ እየደረሰ ያለው መከራ፣ ሞት፣ እንግልትና ዝርፊያ ሙሉ በሙሉ ሊያበቃ ይገባል፤ ይህንን የጥፋት ተግባር ሁላችንም በአንድ ድምፅ ማውገዝ አለብን" ሲሉ ተናግረዋል።
አሁን ያለው ጠላት ሀገርን የማፍረስ አጀንዳን አንግቦ 'ፅምዶ' በሚል እኩይ ስያሜ ኅብረት ፈጥሮ እየሠራ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ነው ካሉ በኋላ፤ ይህንን የጥፋት ቡድን በዘላቂነት ለመደምሰስ የመንግሥት ሠራተኛው ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር ያለውን ትስስር ማጥበቅ፣ እርስ በእርስ አንድነቱን ማጠናከርና ከመንግሥት ጎን በጽናት መሰለፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በመጨረሻም የመንግሥት ሠራተኞች ያጋጠሙትን የጸጥታ ተግዳሮቶች በንቃት ለመመከት፣ ለጸጥታ ኃይሉ አስተማማኝ የመረጃና የሎጅስቲክስ ምንጭ መሆን እንዳለባቸዉ ዋና አስተዳዳሪዉ ገልፀዋል ።
መድረኩን የሀገር መከላከያ ሠራዊት የ52ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል አብርሃ ታደሰ እና የሞጃና ወደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ የማነብርሃን ተስፋ በጋራ መርተውታል።
ሞጃና ወደራ ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን

ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለ1ሺህ 500 ሰዎች ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ፤ደብረ ብርሃን፤ጥቅም 16/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):- ...
26/10/2026

ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ለ1ሺህ 500 ሰዎች ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ፤

ደብረ ብርሃን፤ጥቅም 16/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):- የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከኪውር ብላይንድነስ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር ለመስጠት ባቀደው ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ።

የደብረ ብርሃን አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ስፔሻሊስት ዶክተር ሲሳይ ፀጋይ የዓይን ሞራ ግርዶሽ በዓለም፣በሀገራችን፣ በአማራ ክልልና በሰሜን ሸዋ ዞን እያስከተለ ያለውን ጉዳት በአሀዝ አስደግፈው ሰነድ አቅርበዋል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ንጉሴ ተፈራ እንደገለጹት፣ሆስፒታሉ ኪዩር ብላይንድነስ ከሚባል ግብረ ሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር በመጪው ኅዳር ወር ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እንደሚሰጥ ገልጸዋል።

ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ከአጋር ድርጅቱ ጋር በመቀናጀት ለበርካታ የችግሩ ተጠቂዎች ነፃ የዓይን ምራ ግርዶሽ ህክምና ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰዋል።

በዚህ ዙርም በመጪው ኅዳር ወር ለ1 ሺህ 500 ሰዎች ነፃነት የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን በመጥቀስ፣በደብረ ብርሃን፣በሰሜን ሸዋ፣በኦሮሚያ ክልል አጎራባች ወረዳዎች ያሉ በዓይን ሞራ ግርዶሽ የሚቸገሩ ሁሉ በነፃ የዕድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ በቀለ ገብሬ በውይይቱ ማጠቃለያ እንዳሉት፣ሆስፒታሉ ከኪዩር ብላይንድነስ ጋር በመተባበር ለበርካታ ሰዎች የዓይናቸው ብርሃን እንዲመለስላቸው ማድረጉን አስታውሰዋል።

አክለውም በዚህ የኅዳር ወር አጋማሽ 1ሺህ 500 ለሚሆኑ ወገኖች ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና ለመስጠት ዝግጅት ማድረጉ የሚያስመሰግን መልካም ስራ ነው ብለዋል።

ስራው ሰፊና የብዙ አካላት ትብብር የሚጠይቅ ነው ያሉት አቶ በቀለ፣ዕቅዱ እንዲሳካ እንደተለመደው በየደረጃው የሚመለከታቸው አካላት ተናበውና ተቀናጅተው በመንቀሳቀስ የየድርሻቸውን ኃላፊነት ሊወጡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች በሚወጣው የልየታ መርሐ ግብር መሠረት በአቅራቢያቸው ወደ ሚገኘው የጤና ተቋማት እየሄዱ በመመዝገብ የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

በውይይቱ የሆስፒታሉ፣የደብረ ብርሃን ከተማና የሰሜን ሸዋ ዞን የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚዲያ ሙያተኞች ተገኝተዋል።

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የ« #ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ተጠናክሮ ቀጥሏል​በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በብሔራዊ ደረጃ የሚሰጠውን የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ የመመዝገብና የመስጠ...
26/10/2026

በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የ« #ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ንቅናቄ ተጠናክሮ ቀጥሏል
​በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በብሔራዊ ደረጃ የሚሰጠውን የ«ፋይዳ» ዲጂታል መታወቂያ የመመዝገብና የመስጠት ህዝባዊ ንቅናቄ በተጠናከረ መልኩ እየተካሄደ ይገኛል።

​ዛሬን ጨምሮ በተለያዩ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በየማህበረሰብ ማዕከላት የተዘረጉ የላቀ ቴክኖሎጂ የታጠቁ የፋይዳ ምዝገባ መስጫዎች የህብረተሰቡን ክፍሎችና ተማሪዎችን በስፋት በማስተናገድ ላይ ናቸው።

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያገለግል፣ የላቀ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የፊት ገጽታን፣ የአይን ብሌንና የጣት አሻራን ከግል መረጃ ጋር በማቀናጀት የሚዘጋጅ ህጋዊና መሠረታዊ የነዋሪዎች መለያ ነው።

ይህ መታወቂያ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚኖሩ ማናቸውም ነዋሪዎች ያለምንም ልዩነትና መከልከል የሚሰጥ አስተማማኝ መለያ ነው።

ፋይዳ እንደ ስሙ ፋይዳው በርካታና ዘመነኛ ነው፤ ​አሰራርን በማዘመን ቀልጣፋ የባንክ፣ የጤና እና የሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ ​የሰዎችን ማንነት በማረጋገጥ ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠትና ማጭበርበርን ለመከላከል፣ ​የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።

​በመሆኑም የወረዳው ነዋሪዎች ተማሪዎችና የህብረተሰብ ክፍሎች በሚቀርቧቸው የትምህርት ቤቶችና የተመደቡ የምዝገባ ጣቢያዎች በመገኘት ይህን ዘመናዊ መታወቂያ እንድታወጡ ጥሪ ቀርቧል።
​«ፋይዳ መታወቂያ በማውጣት የዲጂታል ኢትዮጵያን ራዕይ እውን እናድርግ!»
Menz mama werda communication office

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማት ጉብኝት ተካሔደበአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ  ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ...
26/10/2026

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማት ጉብኝት ተካሔደ

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ ወረዳ በገርቢ ቀበሌ የሚገኘውን የሙዝ ክላስተር ልማት ጎብኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ፣ እንዳሉት በአካባቢው የተገኘው ሰላምና የሕዝቦች አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፣ ለሰላም መረጋገጥ የጸጥታ አካላት፣ የሃይማኖትና የባህል አባቶች እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም አንጾኪያ እና አካባቢው ትልቅ የልማት አቅም እንዳለው የተገለፁ ሲሆን፣ ክልሉና ዞኑ በጀመሩት አዲስ የዕይታ ጉዞ እና የ25 ዓመት የልማት እቅድ መሰረት ሰላምን በማስፈን የተሻለ ውጤት ለማምጣት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

​በመጨረሻም አቶ አህመድ አሊ ይህ አካባቢ ትልቅ እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ፣ በጋራ በመቆም ሰላማችንን ጠብቀን ወደ የተሻለ ልማት መሸጋገር እንችላለን ብለዋል

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ በበኩላቸው፣ ሰላምን ለማስፈን ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ጠቁመው፣ ሰላም ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የተገኘውን ሰላም ወደ ዘመናዊ ግብርናና ዘላቂ ልማት በመቀየር የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል።

አቶ መካሽ አካባቢው ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ማንጎና ሌሎች ፍራፍሬዎችን በስፋት ለማምረት ምቹ የተፈጥሮ ሀብትና የውሃ አቅም እንዳለው በመጥቀስ፣ የክላስተር ልማትን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ገቢ ማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ከድህነት የሚያላቅቁ የልማት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

በጉብኝቱ ላይ ከአንጾኪያ ገምዛ፣ ከኤፍራታና ግድም፣ ከቀወት፣ ከጣርማ በርና ከሸዋ ሮቢት ከተማ የመጡ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

በእነዋሪ ከተማ የልማትና የሰላም ሥራዎችን በጋራ ለማስቀጠል ጥሪ ቀረበ!!በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠልና ሰላምን ለማስጠበቅ የሕዝብና የመንግሥት ቅንጅት ማጠናከር...
26/10/2026

በእነዋሪ ከተማ የልማትና የሰላም ሥራዎችን በጋራ ለማስቀጠል ጥሪ ቀረበ!!

በሰሜን ሸዋ ዞን እነዋሪ ከተማ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠልና ሰላምን ለማስጠበቅ የሕዝብና የመንግሥት ቅንጅት ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።

የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊና አካባቢያዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባካሄደው ውይይት፦

የልማት ጥረቶችን ማስቀጠልና የሰላም ሥራዎችን ማጠናከር ላይ ትኩረት ተደርጓል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች የከተማው የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን አድንቀው፦

የልማት ሥራዎች እንዲቀጥሉና ሰላም እንዲጠበቅ ከከተማው አስተዳደር ጋር በትብብር ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ በሚችሉት መንገድ በመደገፍ ሀገራዊ ፍቅራቸውን በተግባር ማሳየት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የእነዋሪ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ አቶ አጥላባቸው አጣለ፣ ልማት ከችግሮች መውጫ ቁልፍ በመሆኑ ለልማት ሥራዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

ሕዝቡም ከመንግሥት ጋር በመተባበር በልማትና በሰላም ሥራዎች ላይ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

የዲጂታል በብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በእንሳሮ  ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በወቀሎ አንፆኪያ ቀበሌ ምዝገባ እየተከሄደ ይገኛል።በመሆኑም  በየቀበሌዎች  ክትትል እየ...
26/10/2026

የዲጂታል በብሔራዊ ፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በእንሳሮ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በወቀሎ አንፆኪያ ቀበሌ ምዝገባ እየተከሄደ ይገኛል።

በመሆኑም በየቀበሌዎች ክትትል እየተደረገ ሲሆን የእንሳሮ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ዝናቧ መስፍንና የእንሳሮ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊው አቶ ብዙአየሁ ፀጋው እንዲሁም የቀበሌው ደጋፊ የወረዳ አመራሮች በወቀሎ አንፆኪያ ቀበሌ ተገኝተው አስተባብረዋል ።

በመጨረሻም የፋይዳ መታወቂያ እንደ ስሙ ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች ስላሉት ሁሉም የወረዳችን ነዋሪዎች ጊዜ ባለመስጠት እንድት መዘገቡ በማለት ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።
Ensaro Wereda Government Communication affairs office

የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮች በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማትን ጎበኙ!በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተ...
26/10/2026

የሰሜን ሸዋ ዞን አመራሮች በደዋ ጨፋ ወረዳ የሙዝ ክላስተር ልማትን ጎበኙ!

በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ የተመራ የልዑካን ቡድን፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ደዋ ጨፋ ወረዳ በገርቢ ቀበሌ የሚገኘውን የሙዝ ክላስተር ልማት ጎብኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ አሊ አባፍሮ እንዳሉት፣ በአካባቢው የተገኘው ሰላምና የሕዝቦች አብሮነት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸው፣ ለሰላም መረጋገጥ የጸጥታ አካላት፣ የሃይማኖትና የባህል አባቶች እንዲሁም መላው ማኅበረሰብ ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

አክለውም አንጾኪያ እና አካባቢው ትልቅ የልማት አቅም እንዳለው ገልጸው ክልሉና ዞኑ በጀመሩት አዲስ የዕይታ ጉዞ እና የ25 ዓመት የልማት እቅድ መሰረት ሰላምን በማስፈን የተሻለ ውጤት ለማምጣት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

​በመጨረሻም አቶ አህመድ አሊ ይህ አካባቢ ትልቅ እምቅ አቅም ያለው በመሆኑ፣ በጋራ በመቆም ሰላማችንን ጠብቀን ወደ የተሻለ ልማት መሸጋገር እንችላለን ብለዋል

የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መካሽ አለማየሁ በበኩላቸው፣ ሰላምን ለማስፈን ባለፉት አራት ዓመታት ከፍተኛ ጥረት መደረጉን ጠቁመው፣ ሰላም ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የተገኘውን ሰላም ወደ ዘመናዊ ግብርናና ዘላቂ ልማት በመቀየር የማኅበረሰቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል እንደሚገባ አሳስበዋል።

አካባቢው ሙዝ፣ ፓፓያ፣ ማንጎና ሌሎች ፍራፍሬዎችን በስፋት ለማምረት ምቹ የተፈጥሮ ሀብትና የውሃ አቅም እንዳለው በመጥቀስ፣ የክላስተር ልማትን በማስፋፋት የአርሶ አደሩን ገቢ ማሳደግ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና ከድህነት የሚያላቅቁ የልማት ሥራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።

አማራ ኮሙኒኬሽን

የክልልና የዞን የትምህርት አመራሮች በባህርዳር ከተማ የተለያዩ የትምህርት ተቋማትን ተዘዋውረው ጎበኙ።=====ጥቅምት 16/1019 ዓ.ም(ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እያካሄደ ...
26/10/2026

የክልልና የዞን የትምህርት አመራሮች በባህርዳር ከተማ የተለያዩ የትምህርት ተቋማትን ተዘዋውረው ጎበኙ።
=====
ጥቅምት 16/1019 ዓ.ም(ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እያካሄደ የሚገኘው የሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካል የሆነው የተሞክሮ ልውውጥ መርሃ ግብር ዛሬ በጠዋቱ ተካሂዷል።

በጉብኝት ፕሮግራሙ የኮስኮስ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የኑቢያ አካዳሚ፣ የአፄ ሰርፀ ድንግል መለክ ሰገድ ልዩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና የአሜን ፋውንዴሽን የልዩ ፍላጎት ትምህርት ማእከል የጉብኝቱ አካል ሆነዋል።

የባህርዳር ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ሙሉዓለም አቤ (ዶክተር) ለጎብኝዎች ተናግረዋል።

ከማህበረሰቡንና ከአጋር አካላት ጋር ተቀናጅተን በመስራታችን በየአመቱ አዳዲስ ሞዴል ትምህርት ቤት እየገነባን ነውም ብለዋል።

የትምህርት አመራሮች በትምህርት ቤቶች ያለውን ምቹ የትምህርት ቤት አካባቢ፣ የቅድመ አንደኛ ደረጃ እና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች የመማር ማስተማር ሂደት ተዘዋውረው ተመልክተዋል።

በጉብኝቱ የተሳተፉት የትምህርት አመራሮች የከተማውን የትምህርት ስራ እንቅስቃሴ አድንቀዋል።

አመራሮቹ ከከተማ አስተዳደሩ በርካታ ተሞክሮ የሚሆኑ ስራዎችን ወደዞናቸው ወስደው እንደሚተገብሩ ተናግረዋል።

ተመሳሳይ የተሞክሮ ልውውጦች በቀጣይም ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተሳታፊዎች አክለው ገልፀዋል።
AmharaEducation
#ትምህርትለትውልድ

Address

Debre Birehan
Debre Birhan
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Amhara North Shewa Zone Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Amhara North Shewa Zone Communication:

Shortcuts

Share