Debre Birhan city Communication Affairs Office

Call Website Contact the organization

Debre Birhan city Communication Affairs Office ይህ ገጽ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ነው

በደብረ ብርሃን ከተማ ዙሪያ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹ ለመከላከል የተሰጠ የአቋም መግለጫበዘንድሮው የመኸር የእርሻ ወቅት አርሶ አደሩ በከፍ...
13/11/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ ዙሪያ በሚገኙ የገጠር ቀበሌዎች የደረሱ ሰብሎች ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እንዳይበላሹ ለመከላከል የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በዘንድሮው የመኸር የእርሻ ወቅት አርሶ አደሩ በከፍተኛ ትጋት፣ በላብ እና በጥረት ያለማቸው ሰብሎች አሁን ለፍሬ እና ለአጨዳ ደርሰዋል። ይህ የተደመበትን የዓመቱ ምርት የሚሰበሰብበት ወሳኝ ወቅት ቢሆንም፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን የማበላሸት፣ የጥራት ደረጃቸውን የመቀነስ እና ምርትን ለብክነት የመዳረግ ስጋት ፈጥሯል።
ስለሆነም የአርሶ አደሩ ድካም መና እንዳይቀር እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት እንዳይደናቀፍ፣ ከተማ አስተዳደሩ የሚከተሉትን የቅድመ ጥንቃቄ እርምጃዎች በአስቸኳይ ተግባራዊ እንዲደረጉ ጥሪውን ያቀርባል፦
የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት መሰብሰብ፦ አርሶ አደሮች ለአጨዳ የደረሱ እንደ ገብስ፣ ስንዴ፣ ጤፍ እና የጥራጥሬ ሰብሎችን «ነገ» ሳትሉ በተቻለ ፍጥነት ማጨድ እና መሰብሰብ ይኖርባችኋል።
​በደቦ እና በቅንጅት መስራት፦ የሰው ኃይል እጥረት እንዳያጋጥም እና አጨዳውን ለማፋጠን ባህላዊ የመረዳዳት እሴቶቻችንን (ደቦ እና ወንፈል) በማጠናከር፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ በጋራ በመሆን የደረሱ ሰብሎችን በዘመቻ እንድትሰበስቡ እናሳስባለን።
የተሰበሰቡ ሰብሎችን በአግባቡ መከመር እና መሸፈን፦ የታጨዱ ሰብሎችን ውኃ በማይተኛበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ በጥንቃቄ መከመር፣ ከስር የእርጥበት መከላከያ ማንጠፍ እንዲሁም ከላይ ዝናብ እንዳያስገባ በሸራ፣ በፕላስቲክ ወይም በተዘጋጁ መሸፈኛዎች በአግባቡ መሸፈን ያስፈልጋል።
የውቂያ እና የጎተራ ዝግጅት ማድረግ፦ የአየር ሁኔታው ምቹ በሆነባቸው ሰዓታት የታጨደውን ሰብል በንጹሕ እና በደረቅ አውድማ ላይ በፍጥነት በመውቃት፣ ምርቱን እርጥበት ወደማይገባበት እና አየር ወደሚዘዋወርበት ደረቅ ጎተራ ማስገባት ይገባል።
የባለሙያ ምክር እና የአየር ሁኔታ መረጃን መከታተል፦ በየቀበሌው የሚገኙ የግብርና ልማት ጣቢያ ባለሙያዎች የሚሰጡትን ሙያዊ ምክር እና ወቅታዊ የአየር ሁኔታ መረጃዎችን በንቃት በመከታተል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባችኋል።

ደብረ ብርሃንን እንደስሟ ፁዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፤​ደብረ ብርሃን፤ኅዳር 3/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ...
12/11/2026

ደብረ ብርሃንን እንደስሟ ፁዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ በትኩረት እንደሚሰራ ተገለጸ፤

​ደብረ ብርሃን፤ኅዳር 3/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ጽዳትና ውበት አረንጓዴ ልማት ጽህፈት ቤት የአራት ወር የሥራ አፈፃጸም ገምግሞ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀመጠ።

​በመድረኩ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንዳሉት፣ደብረ ብርሃን ትላልቅ ፋብሪካዎች የሚገነቡባት፣ ከፍተኛ የሰው ፍሰት ያለባትና በመንግሥትም ግዙፍ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑባት በፍጥነት በማደግ ላይ የምትገኝ ከተማ መሆኗን አስረድተዋል።

ነገር ግን በከተማዋ እየታየ ያለውን ፈጣን የኢንቨስትመንትና የልማት ዕድገት የሚመጥን የጽዳትና የውበት ሥራ በማከናወን በኩል ክፍተቶች መስተዋላቸውን ተጠቁመው፣ውስንነቶችን ፈጥኖ በማረም ከተማዋን እንደስሟ ፁዱና ለነዋሪዎቿ ምቹ ከተማ ለማድረግ በትኩረት መስራት አማራጭ የሌለው ግዴታ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለዚህም የከተማውን ጽዳትና ውበት አረንጓዴ ልማት ተግባራት አፈፃጸም ገምግሞ የቀሪ ጊዜያት ተልዕኮ መከፋፈል አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከተማ አስተዳደሩ የከተማውን ጽዳት ለማስጠበቅ ከነዋሪዎች ከውሃ ቢል ጋር ገንዘብ እንዲሰበሰብ በማድረግ ሥራ ላይ እንዲውል ቢያደርግም ማኅበረሰቡ በአገልግሎቱ እንዳልረካ ቅሬታ እያቀረበ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

በመሆኑም በመድረኩ በጽዳት ማህበራትም ሆነ በአጋር አካላት በኩል ያለውን ችግር ነቅሶ በማውጣት በቀጣይ ለመፍትሄው በጋራ መስራትና የከተማዋን ጽዳት ማስጠበቅ የሁሉም ኃላፊነት ስለመሆኑ በማሳሰብ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ጽዳትና ውበት አረንጓዴ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ወይንሸት ጀማነህ በበኩላቸው፣የከተማውን ጽዳትና ውበት በማስጠበቅ ለመኖሪያና ለሥራ ምቹ ለማድረግ እንዲቻል የግምገማ መድረኩ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

በዚሁ መሠረት የባለፉት አራት ወራት የሥራ አፈፃጸም ምን ይመስል እንደነበር እና በሂደቱ የጽዳት ባለቤቶች እነማን እንደሆኑ በጥልቀት መገምገሙንና በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ መደረሱን አመልክተዋል።

​ከተቀመጠው አቅጣጫ ውስጥ ከተማውን ጽዱ፣ውብና ማራኪ ለማድረግ የሁሉም ርብርብ ወሳኙ መሆኑን ጠቁመው፣ሥራው ውጤታማ እንዲሆንም ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር በቅንጅት በመምራትና ማህበረሰቡን የጽዳቱ ባለቤት ማድረግ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንደሚፈጸም አስታውቀዋል።

በመድረኩ ከተቋሙ ቡድን መሪዎች ጀምሮ ጠቅላላ ሠራተኞች፣ የክፍለ ከተማ ኃላፊዎች እና የቀበሌ ማህበረሰብ ኮሚቴዎች የተውጣጡ አካላት ተገኝተዋል።

በክልሉ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል። በአማራ ክልል ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል "ነጭ ወርቅ" በመባል የሚታወቀው የሰሊጥ ምርት አንዱ ነው። ምርቱ ከፍተኛ የውጭ ...
12/11/2026

በክልሉ ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የሰሊጥ ምርት ይጠበቃል።

በአማራ ክልል ከሚመረቱ ሰብሎች መካከል "ነጭ ወርቅ" በመባል የሚታወቀው የሰሊጥ ምርት አንዱ ነው። ምርቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ከሚያስገኙ ምርቶች መካከልም የሚጠቀስ ነው።

የክልሉ ግብርና ቢሮ የሰብል ልማት እና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ.ር)፣ በበጀት ዓመቱ ከ519 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በሰሊጥ ሰብል መሸፈኑን ተናግረዋል። ከ4 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የምርት መሠብሠብ ሥራ በስፋት እየተከናወነ ነው። እስካሁን ከ315 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት መሠብሠቡን አንስተዋል።

ሰሊጥ በክልሉ በብዛት በቆላማ አካባቢዎች የሚመረት እና ዋና ከሚባሉ የቅባትና የውጭ ምንዛሬ ማስገኛ ሰብሎች አንዱ በመኾኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል ነው ያሉት። ሰብሉ በወቅቱ እንዲሠበሠብ ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል። የተሻለ ምርት ይጠበቃል ነው ያሉት።

የሰሊጥ ምርቱ በቀላሉ ለብክነት የሚዳረግ በመኾኑ በጥንቃቄ እንዲሠበሠብ እና እንዲከማች ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን የማስፋፋት ሥራ መከናወኑን ነው የገለጹት። በተለይም ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ እና በሌሎችም ጉዳት እንዳይደርስበት በጥራት ለመሠብሠብ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዘርፉ ለተሰማሩ አርሶ አደሮች እና ባለሀብቶች የሀብት ምንጭ በመኾን የሀገርን ኢኮኖሚ ለመገንባት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ ለመላክ እየተሠራ እንደኾነ ነው የተናገሩት። በሀገር ውስጥ ሰሊጥን እንደ ግብዓት የሚጠቀሙ ፋብሪካዎች እየተገነቡ መኾናቸውንም አብራርተዋል ሲል የዘገበው አሚኮ ነው።

አማራ ኮሙኒኬሽን

አመራሩ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸየደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም ግ...
12/11/2026

አመራሩ ወቅታዊና መደበኛ ተግባራትን አቀናጅቶ በመምራት ውጤታማነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ

የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ወቅታዊ የፀጥታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም ግምገማ ላይ ያተኮረ የውይይትና የቀጣይ አቅጣጫ መድረክ አካሂዷል።

መድረኩ እስካሁን የተከናወኑ የልማትና የፖለቲካ ሥራዎችን ጥንካሬና ድክመት በመለየት፣ በቀጣይ የሚጠበቁ ሀገራዊና ክልላዊ ተልዕኮዎችን በብቃት ለመወጣትና የሕዝብን ፍላጎት በተሻለ ሁኔታ ለመመለስ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

በግምገማው መድረኩ የከተማው ሰላምና ፀጥታ ም/መምሪያ ኃላፊ አቶ ብቅአለ አሰፋ በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ተግባራት የተከናወኑ ሥራዎችን በዝርዝር አቅርበዋል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዳንኤል እሸቴ በበኩላቸው፣ ሰላም የሁሉም የልማት ሥራዎች ቀዳሚ መሠረት በመሆኑ ወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ሥራዎችን ከሌሎች ተግባራት ጋር በማስተሳሰር በልዩ ትኩረት መሥራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

የከተማውን ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማስጠበቅ የፖለቲካ አመራሩ፣ የፀጥታ መዋቅሮችና የሕብረተሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።
አመራሩ የነባራዊ ሁኔታ ትንተናን መሠረት በማድረግ በአንድነት፣ በኃላፊነትና በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበት የገለጹት አቶ ዳንኤል፣ አደረጃጀቶችን በአግባቡ መጠቀም፣ ከተለምዷዊ አሠራር በፍጥነት ወጥቶ ወቅቱ በሚጠይቀው ልክ ተግባራትን አቀናጅቶ መምራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

ተልዕኮዎች «ጊዜ የለኝም» በሚል መንፈስ በጥብቅ ዲስፕሊንና በተቋማዊ አሠራር ተመርተው በውጤት ሊታጀቡ፣ የፓርቲና የመንግሥት ተልዕኮም ከግብ ሊደርስ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

የተጠናከረ የፀጥታ ተቋም በመገንባት ረገድ በባለቤትነት መፈጸም፣ በዕቅድ በመመራትና ተልዕኮዎችን ወደ መሬት በማውረድም ከወትሮ በተለየ መልኩ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የከተማው ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ በሰጡት ማጠቃለያ፣ ተግባራትን በተቀመጠላቸው ጊዜ አጠናቆ በሁሉም ዘርፍ ማኅበረሰቡን የሚመጥን ሥራ መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል።

በተግባራት ሂደት የሚታዩ የተዛቡ አመለካከቶችን በመቅረፍ ተልዕኮን መፈጸም እንደሚገባ ጠቁመው፣ የአመራር ስምሪት ሁሉንም ተግባራት በእኩል አቅም ለመፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል።

በተቋማትና በወቅታዊ ሥራዎች ላይ ያለውን የአፈጻጸም ልዩነት ማጥበብ እንደሚገባ ጠቅሰው፣ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ አመራሩ በቅንጅትና በርብርብ ተግባራዊ በማድረግ ለተሻለ ውጤት መሥራት እንዳለበት አስገንዝበዋል፤ ለዚህም የአመራሩና የባለድርሻ አካላት ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው ብለዋል። የታዩ ጉድለቶችን አርሞ በቀጣይ ቀናት ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ ውጤት ማስመዝገብ፣ ተግባራትም በሁሉም አካባቢዎች በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ሳይጓደሉ በሙሉ አቅም መከናወን እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በመጨረሻም በተልዕኮ አፈጻጸም የታዩ ውስንነቶችን በቅርቡ ለማረም የሚያስችል የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጦ መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ በየደረጃው የሚገኙ የፖለቲካ አመራርና የፀጥታ ሚኒ ካቢኔ አመራሮችና አባላት ተገኝተዋል።

በደብረ ብርሃን ከተማ የዓለም የቱሪዝም ቀን በድምቀት ተከበረ፤​ደብረብርሃን፤ ኅዳር 3/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ  "የቱሪዝም ዘርፍን እ...
12/11/2026

በደብረ ብርሃን ከተማ የዓለም የቱሪዝም ቀን በድምቀት ተከበረ፤
​
ደብረብርሃን፤ ኅዳር 3/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ "የቱሪዝም ዘርፍን እንደገና ለመቅረፅ የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሚና" በሚል መሪ ቃል የዓለም የቱሪዝም ቀን በድምቀት አከበረ።
​
በበዓሉ ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንደተናገሩት፣ደብረ ብርሃን ከተማ በ14ኛው ክፍለ ዘመን የተመሰረተች በርካታ ታሪካዊ፣ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ የቱሪስት መስህብ ሀብት ያላት ከተማ መሆኗን አብራርተዋል።

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ፈጣን፣ዘላቂቃና ዘርፈ ብዙ የልማት ቱሩፋቶቸ የተመዘገቡቧት ሰላማዊና የኢንዱስትሪ ማዕከል በመሆን ተመራጭ እና ተወዳጅ ከተማ ሆናለች ብለዋል።

ይሁን እንጂ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት በሚገባ በማልማትና በመጠቀም ረገድ ክፍተቶች እንዳሉ ጠቁመው፣ምክንያቱ ለቱሪዝም ዕድገት ወሳኝ የሆነው የሆቴል ኢንደስትሪው ልማት በሚፈለገው ልክ ተጣጥሞ ባለማደጉ መሆኑን አመልክተዋል።

ከተማው ለነዋሪዎችና ለቱሪስቶች ምቹ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ የኮሪደር ልማት እና ሌሎች ትልልቅ የልማት ፕሮጀክቶችን እያስመረቀና እያስፋፋ እንደሚገኝ ዘርዝረዋል።

የቱሪዝም ልማቱ ተጣጥሞ እንዲያድግ በከተማው የሚገኙ የሆቴል ባለቤቶችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመስራት ቱሪስቶች ቆይታቸውን እንዲያራዝሙ አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ አስደግፈው ጥራት ያለው መስተንግዶ ማቅረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ለዚህም አርቴፊሻል ኢንቲሊጀንስና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በማዘመን ቱሪስቶች ባሉበት ሆነው ስለ ቱሪስት መስህቦች እና የሆቴል አገልግሎት ሰጪዎች ትክክለኛ እና ጥራት ያለው መረጃ ማቀበል እንደሚገባ በማሳሰብ የቀጣይ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ አይናለም አሰፋ በበኩላቸው እንደተናገሩት፣የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ፀጋ ባለቤት የሆነችው ደብረብርሃን በየዓመቱ በርካታ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ቱሪስቶችን እያስተናገደች እንደምትገኝ አንስተዋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት ምክንያት አዳዲስ መዳረሻዎችን እያለማ፣ ነባሮቹን እያስተዋወቀና አዳዲስ ሀይማኖታዊ የቱሪስት መዳረሻዎች እየተስፋፋ ስለመሆኑ ተናግረዋልደ

የዘንድሮው የዓለም ቱሪዝም ቀን "የቱሪዝም ዘርፍን እንደገና ለመቅረፅ የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሚና" በሚል መሪ ቃል እየተከበረ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

በዓሉ በዓለም ለ47ኛ፣ በኢትዮጵያ ለ39ኛ እንዲሁም በአማራ ክልል ለ34ኛ ጊዜ የሚከበር ሲሆን፣ ቴክኖሎጂ በዘርፉ ላይ እያመጣ ያለውን አብዮታዊ ለውጥ በከተማዋ የቱሪዝም ልማት ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ያለመ ስለመሆኑ አስገንዝበዋል።

በዚህ በዓል ላይ የተሳተፉ አካላትም ለቱሪዝም ልማትና እድገት ከተቋሙ ጋር ተባብረው በመስራት አጋርነታቸውን እንዲያረጋግጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የደብረ ብርሃን ከተማ ባህል ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ የቅርስ ጥበቃ ቱሪዝም ልማት ቡድን መሪ አቶ አክሊል ጌታቸው የዓለም የቱሪዝም ቀን አስመልክቶ ሰነድ አቅርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በበዓሉ ላይ የሚመለከታቸው አካላት፣የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ የተሳካ COP32 ለማካሄድ  ቁርጠኝነት እና  ዝግጁነት አላት።  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ. ር) በUNFCCC ስር የአረብ ቡድን...
12/11/2026

ኢትዮጵያ የተሳካ COP32 ለማካሄድ ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት አላት።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ. ር) በUNFCCC ስር የአረብ ቡድን አባል ሀገራት የልዑካን መሪዎች ስብሰባ ላይ ተጋብዘው ንግግር አድርገዋል።

በስብሰባው ወቅት አባላቱ በኢትዮጵያ አመራር እና በCOP32 ሂደት ላይ የተመራጭ ፕሬዝዳንቱ በሚያሳዩት መሪነት ላይ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል። በኢትዮጵያ እና በአረብ ቡድን አባል ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ እና ጠንካራ ግንኙነት ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ. ር) ኢትዮጵያ ከሁሉም ተዋዋይ አካላት ጋር በቅርበት በመሥራት የተሳካ COP32 ለማካሄድ ያላትን ቁርጠኝነት እና ዝግጁነት ለቡድኑ አረጋግጠዋል።

‎ ከአማራ ኮሙኒኬሽን

አማራ ባንክ በደብረ ብርሃንና አካባቢው ካሉ መስራች ባለአክስዮኖች ጋር ውይይት አካሄደ​አማራ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማና አካባቢው ከሚገኙ መስራች ባለአክስዮኖቹ ጋር ወቅታዊ የባንኩን ቁመና...
11/11/2026

አማራ ባንክ በደብረ ብርሃንና አካባቢው ካሉ መስራች ባለአክስዮኖች ጋር ውይይት አካሄደ

​አማራ ባንክ በደብረ ብርሃን ከተማና አካባቢው ከሚገኙ መስራች ባለአክስዮኖቹ ጋር ወቅታዊ የባንኩን ቁመናና የወደፊት ዕቅዶች አስመልክቶ የውይይት መድረክ አካሄዷል።

የአማራ ባንክ ደብረ ብርሃን ድስትሪክት ዳይሬክተር አቶ አይርሳው አብዬ እንደገለጹት ባንኩ በቀጣይ 5 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ከሚገኙ ታላላቅ 4 ባንኮች አንዱ፣ በቀጣይ 15 ዓመታት ደግሞ በአፍሪካ ከሚገኙ 40 ታላላቅ ባንኮች ውስጥ አንዱ ለመሆን በቁርጠኝነት እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጿል።

አክለውም የባንኩ 5ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ጃንሜዳ የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክስዮኖች በባለቤትነት ስሜት በቅርንጫፎች በመገኘት ህጋዊ ውክልና እንዲሰጡ ወይም በዕለቱ በቦታው ተገኝተው እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል።

ባለአክስዮኖችም በደብረ ብርሃን ከተማ የዲስትሪክት ጽ/ቤት መከፈቱና የህንፃ ግንባታ እንቅስቃሴ መጀመሩ ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል።

በተለይም ለአርሶ አደሮች፣ ለወጣቶችና ለደብረ ብርሃንና ለሰሜን ሸዋ ማህበረሰብ የሚደረግ የብድር አቅርቦት እንዲጠናከር ጨምረው ገልፀዋል።

የባንኩ የሥራ ሃላፊዎች ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን፤ ዲስትሪክቱ ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ ለበርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች ብድር ማመቻቸቱን አስታውሰዋል።

ባንኩ በቴክኖሎጅ ታግዞ ለማህበረሰቡ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሰራ አስታውቀው ​ባለአክስዮኖች ከባንኩ ጎን በመቆም ለተቋሙ ዕድገትና ራዕይ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ በማሳሰብ መድረኩ ተጠናቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ፤ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር ...
11/11/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያዩ፤

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር ተወያይተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከኢራቁ ፕሬዝዳንት ኒዛር አሚዲ ጋር መክረናል ብለዋል።
‎
‎የሁለቱን ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ለማጠናከር እና በልማት ትብብር ረገድ የጋራ አቅም ያላቸውን ዘርፎች ወደ ውጤት የመቀየር ሥራዎች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ነው ያሉት።
‎
‎በኢትዮጵያ የልማት ውጥኖች እና በጋራ ፍላጎት ላይ በተመሰረቱ ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ መለዋወጣቸውን ገልጸዋል። በተግባር ላይ ለተመሰረተ ትብብር ጠንካራ ትስስር መገንባት ያለውን አስፈላጊነት በትኩረት ተመልክተናልም ብለዋል።

ከአማራ ኮሙኒኬሽን

በድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን 219 የሺሻ ዕቃዎች እንዲወገዱ ማድረጉን የምኒልክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለጸ፤ደብረ ብርሃን፤ኅዳር 2/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-በደብረ ...
11/11/2026

በድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን 219 የሺሻ ዕቃዎች እንዲወገዱ ማድረጉን የምኒልክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ገለጸ፤

ደብረ ብርሃን፤ኅዳር 2/2019 ዓ.ም (ደብመኮ):-በደብረ ብርሃን ከተማ የምኒልክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት በተጠና መንገድ በ11 የሺሻ ቤቶች ላይ ባካሄደው ድንገተኛ ፍተሻ 219 የሺሻ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ እንዲወገዱ ማድረጉን አስታውቋል።

የምኒልክ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኮማንደር ፍቅረ ሳህሉ እንደገለጹት፣የወንጀል መከላከል ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ ማህበረሰቡን ያሳተፈ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

ለዚህም አራት የወንጀል መከላከል ስልቶችን እንደሚጠቀሙ የጠቀሱት ኮንደር ፍቅረ፣ችገሮችን መለየት፣ መተንተን፣ ምላሽ መስጠት እና የተወሰደውን የመፍትሄ እርምጃ ገምግሞ አቅጣጫ ማስቀመጥ ስለመሆኑ ዘርዝረዋል።

በዚሁ መሠረት በጥናት ላይ ተመስርተው በክፍለ ከተማው ስር በሚገኙ በተመረጡ 11 የሺሻ ቤቶች ላይ ባካሄዱት ድንገተኛ ፍተሻ 219 የሺሻ ዕቃዎችን በቁጥጥር ስር አውለው የማኅበረሰብ ተወካዮች በተገኙበት እንዲወገዱ ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

አስጠቃሚዎች ከዚህ ትውልድንና ሀገርን ከሚጎዳ ህገወጥ ድርጊት እንዲታቀቡ በተደጋጋሚ ፖሊስ ትምህርት ቢሰጣቸውም ከድርጊታቸው ባለመታቀባቸው በማህበራዊ ፍርድ ቤት አማካኝነት 107 ሺህ ብር ተቀጥተው ገንዘቡ ለመንግስት ገቢ መደረጉን አስረድተዋል።

አክለውም ሺሻና መሰል አደንዛዥ እጾች ወጣቱንና አምራች ሃይሉን በሱስ አደንዝዞ ለከፋ ማኅበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ከመዳረጉም ባሻገር ለወንጀል መንስኤ መሆኑን አብራርተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሱስ ተጠቂ የሆነ ሰው ሰርቶ ሀገርና ሕዝብ ከማገልገል ይልቅ ተመልሶ ሸክም ይሆናል ያሉት ኃላፊው፣መፍትሄው ቤተሰብና ማኅበረሰቡ ልጆችን በማስተማር፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ቅድመ መከላከል ላይ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመጨረሻም የከተማው ሰላምና ፀጥታ በዘላቂነት ለማስከበር እንደተለመደው ነዋሪዎች ከፖሊስና ከፀጥታ አካላት ጋር ተባብረው መስራታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ኮማንደር ፍቅረ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከተለያዩ አካባቢዎች የተሰበሰቡ የሺሻ እቃዎች ሲያቃጥሉ ያገኘናቸው ተወካዮች እንደተናገሩት፣ሺሻ ጎጂ በመሆኑን ኅብረተሰቡ ሊያወግዘው እንደሚገባ አስምሮበታል።

አክለውም ትውልዱን ለማዳን መንግስት ለአስጠቃሚዎች ሌላ የስራ መስክ እንዲያመቻችላቸው፣ወላጆችና ማኅበረሰቡ ግንዛቤ እንዲፈጥሩና ክትትል እንዲያደርጉ አስተያየት በመስጠት፣በስራው የድርሻቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ የዓለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች!በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አስደናቂ አፈ...
10/11/2026

ኢትዮጵያ በዳካር የወጣቶች ኦሎምፒክ በአትሌቲክስ የዓለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች!

በሴኔጋል ዳካር እየተካሄደ በሚገኘው የወጣቶች ኦሎምፒክ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አስደናቂ አፈጻጸም በማሳየት የሜዳሊያ ሰንጠረዡን ከዓለም አንደኛ ሆኖ ማጠናቀቁ ተገለጸ።

በውድድር መርሃ ግብሩ መሰረት የአትሌቲክስ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ መጠናቀቃቸው የተነገረ ሲሆን፣ የውድድሩ ማጠቃለያ እና የመዝጊያ ስነ-ሰርዓት አርብ ዕለት ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አባላት የመዝጊያ ስነ-ሰርዓቱን አጠናቀው ቅዳሜ ዕለት ወደ አዲስ አበባ እንደሚመለሱ ታውቋል።

ለሀገራቸው ታላቅ ክብርን ላጎናጸፉት አትሌቶቻችን እና መላው የኢትዮጵያ ስፖርት ቤተሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!

የአትሌቲክስ የሜዳሊያ ደረጃ ሰንጠረዥ (Athletics Medal Table)

1ኛ. ኢትዮጵያ (ETH) – 5 ወርቅ, 3 ብር, 0 ነሐስ (ድምር 8)

2ኛ. ኬንያ (KEN) – 3 ወርቅ, 2 ብር, 0 ነሐስ (ድምር፡ 5)

3ኛ. ናይጄሪያ (NGR) – 3 ወርቅ, 0 ብር, 0 ነሐስ (ድምር፡ 3)

4ኛ. ጃማይካ (JAM) – 2 ወርቅ, 2 ብር, 0 ነሐስ (ድምር፡ 4)

5ኛ. ደቡብ አፍሪካ (RSA) – 2 ወርቅ, 1 ብር, 2 ነሐስ (ድምር፡ 5)

6ኛ. ቻይና (CHN) – 1 ወርቅ, 3 ብር, 1 ነሐስ
(ድምር፡ 5)

7ኛ. ፈረንሳይ (FRA) – 1 ወርቅ, 1 ብር, 1 ነሐስ
(ድምር፡ 3)

8ኛ. ጃፓን (JPN) – 1 ወርቅ, 1 ብር, 1 ነሐስ
(ድምር፡ 3)

9ኛ. የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች (UAE) – 1 ወርቅ, 1 ብር, 1 ነሐስ (ድምር፡ 3)

10ኛ. ሀንጋሪ (HUN) – 1 ወርቅ, 1 ብር, 0 ነሐስ
(ድምር፡ 2)

መላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ደስ አለን፤
እንኳን ደስ አላችሁ!

Address

Amhara
Debre Birhan
251

Telephone

2516813085

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Birhan city Communication Affairs Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Debre Birhan city Communication Affairs Office:

Shortcuts

Share