Debre Markos city communication

Call Directions

Debre Markos city  communication ዓላማው ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃን ለህዝብ ማድረስ ነው።

የመሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ህብረት 1ኛ ሩብ ዓመት የመንግስት ሰራተኛ አባላት ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቀርንጫፍ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመሰ...
09/10/2026

የመሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ህብረት 1ኛ ሩብ ዓመት የመንግስት ሰራተኛ አባላት ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ቀርንጫፍ ጽ/ቤት የ2019 በጀት ዓመት የመሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ህብረት 1ኛ ሩብ ዓመት የመንግስት ሰራተኛ አባላት ኮንፈረንስ ተካሄደ፡፡

በመድረኩ የመሰረተ ልማትና ኢኮኖሚ ህብረት የመንግስት ሰራተኛ የተቋማት የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

"የህዝብ አደራን በተጨባጭ የተግባር ውጤት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል" ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር )የመንግሥት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚያከናውኑትን እያንዳንዱን ተግባር ከህዝብ ጥቅም አንጻር በመገምገም...
09/10/2026

"የህዝብ አደራን በተጨባጭ የተግባር ውጤት ማረጋገጥ ይጠበቅባችኋል" ጋሻው ሙጨ (ዶ/ር )
የመንግሥት አመራሮችና ባለሙያዎች የሚያከናውኑትን እያንዳንዱን ተግባር ከህዝብ ጥቅም አንጻር በመገምገም፣ “ለቀበሌውና ለወረዳው ማህበረሰብ ምን ሠራን?” በሚል ጥያቄ ራሳቸውን በየዕለቱ መገምገም እንዳለባቸው የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ አሳሰቡ።
የሥራ አፈጻጸምን በህሊናና በተግባር መፈተሽ የሚጀምረው የቀበሌዎችን አደረጃጀት ከመገምገም እንዲሁም የቀበሌ ግብርና ባለሙያዎችንና አርሶ አደሩን በግልጽ ዕቅድ፣ ራዕይና አቅጣጫ በመምራት መሆን እንዳለበት ገልጸዋል።
ዘላቂና ተስፋ ሰጪ የልማት ውጤት ለማስመዝገብ አሰራርን በዕቅድና በሥርዓት መምራት ወሳኝ መሆኑን ያመለከቱት ዶ/ር ጋሻው፣ ተግባራት በዕለታዊ፣ በሳምንታዊና በወርሃዊ ዕቅዶች የተመሩ፣ በቼክሊስት የሚከታተሉና በወቅታዊ ግብረ መልስ የሚሻሻሉ መሆን እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
በድጋፍና ክትትል ሂደትም ስህተትን ከመፈለግ ይልቅ ችግርን የሚፈታ፣ የአፈጻጸም አቅምን የሚገነባና የሥራ ውጤታማነትን የሚያሳድግ ድጋፍ መስጠት እንዲሁም ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
በሀገርና በክልል ደረጃ የሚነደፉ ታላላቅ የልማት ኢኒሼቲቮች የህዝብን ሕይወት መለወጥ የሚችሉት በየቀበሌው ወርደው በተጨባጭ ሥራ ሲተረጎሙ ብቻ መሆኑንም ጠቁመዋል። በየአካባቢው የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችም የተበታተኑ ተግባራት ሳይሆኑ፣ የስትራቴጂካዊ ኢኒሼቲቮቹን ዓላማ የሚያሳኩና የልማት ሂደቱን የሚያፋጥኑ መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል።
የልማት ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ የአገልግሎት አሰጣጡ ከቢሮክራሲና ከሙስና የጸዳ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችንም በቆራጥነት የሚፈታ መሆን እንዳለበት ዶ/ር ጋሻው አስገንዝበዋል።
በተመሳሳይ፣ የህዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሥራዎች በቢሮ ውስጥ መግለጫ ከማዘጋጀት ባለፈ፣ የአካባቢውን ጸጋዎች የሚያስተዋውቁ፣ ማህበረሰቡን የሚያስተምሩና ለልማት የሚያነሳሱ መሆን እንዳለባቸው ጠቁመዋል።
ለዚህም ምቹ የሥራ ሁኔታ መፍጠር፣ ውጤታማ ፈጻሚዎችን የሚያበረታታና የአፈጻጸም ክፍተቶችን በሥርዓት የሚያርም የተጠያቂነት ሥርዓት መዘርጋት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።
በመጨረሻም፣ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮችና ባለሙያዎች በቅንጅትና በቁርጠኝነት በመሥራት የህዝብን አደራ በተጨባጭ የልማት ውጤት እንዲመልሱና የማህበረሰቡን ተስፋ እውን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
AmharaCommunications

‎"የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣትን ለማሻሻል እየተሰራ  ነው።" የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ‎‎የጤና ተቋማትን በማዘመን፣  ምቹና ጽዱ በማድረግ የተገልጋዮች እርካታን ለማሳ...
09/10/2026

‎"የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣትን ለማሻሻል እየተሰራ ነው።" የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ
‎
‎የጤና ተቋማትን በማዘመን፣ ምቹና ጽዱ በማድረግ የተገልጋዮች እርካታን ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል።
‎
‎​በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ህዳሴ ጤና ጣቢያ ያነጋገርናቸው ተገልጋዮች፣ በጤና ተቋሙ ተገቢውን የህክምና አገልግሎት እያገኙ መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎​በጤና ጣቢያው የእናቶች ህክምና ባለሙያ ዶክተር ሀብተማሪያም ኃይሉ ለታካሚዎች አስፈላጊውን የህክምና አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል።
‎
‎​ጤና ጣቢያው አሁን ከሚሰጠው አገልግሎት በተሻለ ተደራሽ ለማድረግ ያለበትን የሰው ኃይል እና የህክምና ክፍል እጥረት ሊቀረፍ እንደሚገባም ገልጸዋል።
‎
‎​የህዳሴ ጤና ጣቢያ ኀላፊ ይከበር ይዘንጋው፣ በጤና ጣቢያው አገልግሎቱን ለማሻሻል የላብራቶሪ አገልግሎትና በመድኃኒት አቅርቦት ላይ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መኾኑን ገልጸዋል።
‎
‎ተቋሙን ለተገልጋዮች ምቹ ለማድረግም የግቢውን ጽዳትና ውበት ከመጠበቅ ባለፈ የህክምና መሳሪያዎችን ለማሟላት ከማኅበረሰቡ ጋር በመተባበር እየተሰራ ነው ብለዋል።
‎
‎​የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ ሀብቴ ወርቁ ፣የህክምና ግብዓት በማሟላትና የባለሙያዎችን ተደራሽነት በመጨመር የጤና ተቋማት አገልግሎት አሰጣትን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል።
‎
‎​በከተማ አሥተዳደሩ ለሚገኙ ጤና ተቋማት የህክምና መሳሪያዎች በማሟላት፣ የጤና ጣቢያዎችን የምርመራ ዓቅም በማሳደግ በሆስፒታሎች ላይ ያለውን ጫና ለመቀነስ ትኩረት መሰጠቱን አንስተዋል።
‎
‎አሚኮ እንደዘገበው በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በሚገኙ የጤና ተቋማት ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ባለፈ ተቋማቱን ጽዱና ምቹ ለማድረግ እየተሰራ ስለመኾኑም ተገልጿል።

ትክክለኛ መረጃ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ከሚዲያ አካላት ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ተባለ።​ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ያልተረጋገጡና ሀሰተኛ መረጃዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ እንዳያዛቡ ለማ...
09/10/2026

ትክክለኛ መረጃ ለህብረተሰቡ ለማድረስ ከሚዲያ አካላት ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ተባለ።

​ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሰራጩ ያልተረጋገጡና ሀሰተኛ መረጃዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ እንዳያዛቡ ለማድረግ፣ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት እውነተኛና የተረጋገጠ መረጃ በወቅቱ ለህዝብ ማድረስ እንደሚገባቸው ተገለጸ።

​የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ ክልልአቀፍ እና አገርአቀፍ የሚዲያ አመራሮች ጋር የተግባራት አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ የሚዲያ አጀንዳዎች አቅጣጫ ላይ ያተኮረ የምክክር ፎረም አካሂዷል።

​በመድረኩ ላይ እንደተመላከተው፣ በአሁኑ ወቅት በማህበራዊ ሚዲያዎች በስፋት የሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች የህብረተሰቡን ግንዛቤ እያደናገሩ ይገኛሉ።

ይህንን ተጽእኖ መመከት የሚቻለው ደግሞ ሚዲያዎችና የኮሙኒኬሽን መዋቅሮች ተናበው በመስራት ወቅታዊና የተረጋገጠ የመሬት ላይ እውነታን በተከታታይነት ለህዝቡ ማቅረብ ሲችሉ ብቻ እንደሆነ ተብራርቷል።

​የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አባይ መንግስቴ እንደገለጹት፤ በየደረጃው ያሉ የጋራ ፎረሞች ስራዎችን ተቀናጅቶ ለመስራትና ያልተገባ ግንዛቤ እንዳይፈጠር ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አላቸው።

አክለውም ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃዎችን የመመከት፣ ዘላቂ ሰላምን የመገንባት እንዲሁም የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በትኩረትና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ የመዘገብ ታላቅ ሀገራዊና ሙያዊ ኃላፊነት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

​የትክክለኛ መረጃ ተደራሽነት ለሰላም መስፈን፣ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር መረጋገጥ መሰረታዊ መሳሪያ መሆኑን የጠቀሱት ቢሮ ኃላፊው፤ ያልተረጋገጡ ወሬዎች ስጋት እንዳይፈጥሩ ሚዲያዎች ቀድመው የተረጋገጡ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።

​የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ በበኩላቸው፤ የዘርፉ ዋነኛ ሚና የህብረተሰቡን አመለካከት በበጎ መንገድ መቅረጽና የአገርን ገጽታ መገንባት መሆኑን ጠቁመዋል። ተበታተኖ ከመስራት ይልቅ በጋራ መድረኮች በመታገዝ የተናበበ የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የህግ የበላይነትና ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን እውነታውን ተከትሎ ለመዘገብ ያስችላል ብለዋል።

​በተጨማሪም ባለፈው የመስከረም ወር የተከናወኑ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት፣ የጳጉሜ ቀናት ሁነቶች፣ የትምህርት አጀማመር በባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም የተካሄደው የኢትዮጵያና ሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን የእግር ኳስ ጨዋታ የህዝቡን እንግዳ ተቀባይነት በሚያጎላ መልኩ በሚዲያዎች መሸፈናቸው በበጎ ተወስዷል።

በመድረኩ ማጠቃለም በቀጣይ ጉድለቶችን በማረም የተናበበ አሰራርን መከተል እንደሚገባ የተገለጸ ሲሆን፣ በሰላም፣ በልማትና የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ በእውነት ላይ የተመሰረተ መረጃ ለህዝብ ለማድረስ በየደረጃው የሚገኙ የሚዲያ አካላትና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ቁርጠኝነታቸውን አረጋግጠዋል።

መረጃው የአማራ ኮሙኒኬሽን ቢሮ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።በ​2019 በጀት ...
08/10/2026

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተካሄደ።

በ​2019 በጀት ዓመት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፕላንና ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ማማሩ በሪፖርታቸው ባለፉት ሦስት ወራት የታቀዱ ዋና ዋና ዕቅዶች በኢንቨስትመንት፣ በምግብ ዋስትና፣በግብርና፣ የከተማ የመሰረተ ልማት ፣ በእሰሳትና ሀብት ልማት የስራ አድል ፈጠራ የተሰሩ ስራዎች ጥሩ ውጤት ታይቶባቸዋል ሲሉ በሪፖርታቸው አቅርበዋል።

ኃላፊው አክለውም ሩብ ዓመቱ የታቀዱ ግቦች የተከናወኑበት ቢሆንም የታዩ ክፍተቶችን በዝርዝር በመገምገም በቀጣይ ሩብ ዓመታት በላቀ ደረጃ ለመፈጸም የቅንጅትና የክትትል ሥርዓታችንን ማጠናከር ይጠይቃል ብለዋል።

ውጤት ለማምጣት ፈጻሚ አካላትን ማዘጋጀት ጸጋን ለይቶ እቅድ ማቀድ፣አቅምን አሟጦ ተግባራትን ለመፈጸም የሚደረግ ጥረት የተሻለ ነው ያሉት የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ መልካሙ ሽባባው መታረም አለባቸው ያሉትን አገልግሎት አሰጣጥ እና የገቢ አሰባሰብ ስርአትን ማሻሻል ይገባል ብለዋል።

የከተማችንን ህዝብ ፍላጎት መሠረት ያደረጉ የልማት ሥራዎችን ማፋጠን፣ በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ባለሙያ ህዝቡ የሚነሳቸውን የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች በቅንነትና በፍጥነት የገባል ሲሉ ከንቲባው ተናግረዋል።

በዚህ ሩብ ዓመት የታዩ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋፋትና ማነቆ የሆኑ አሰራሮችን በማስወገድ የቀጣይ ዕቅዶቻችንን በስኬት ማጠናቀቅ ይኖርብናል ሲሉ ከንቲባው አስገንዝበዋል።

ከንቲባው አክለውም የከተማዋን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የመልካም አስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የሚታቀዱ ዕቅዶችን በተገቢው መንገድ መፈጸም መቻል ለቀጣይ ተግባራት መሳለጥና ለወደፊት የሥራ አቅጣጫን ለማስቀመጥ ወሳኝ ነው ያሉት የርዕሰ መስተዳደር ፅ/ቤት የኢኮኖሚ አማካሪ አቶ አስናቀ ይርጉ በቀጣይ የሥራ ዘመን የከተማዋን ፕላን በመጠበቅ የልማት ሥራዎችን በጥራት ማስፈጸምና ከሚመለከተው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ይገባል ብለዋል።

ለሕዝብ የሚታይ ውጤት ማምጣትና ለከተማዋ የሚመጥን የልማትና የመልካም አስተዳደር የጠራ ዕቅድ በመያዝ ተግባራትን ማከናወን ይገባል ሲሉ አቶ አስናቀ ተናግረዋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገጠር መንገድ ኤጀንሲ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አስራቴ አለኸኝ በበኩላቸው የመምሪያው አመራርና የሚመለከተው ባለድርሻ አካላት በተሰጣቸው ኃላፊነት ላይ በትጋት እንዲሠሩና የሕዝብን ጥያቄ በፍጥነት እንዲመልሱ እንዲሁም የሥራ ግልጽነት ተጠያቂነት በቀጣይ ሩብ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

የልማት ሥራዎች የነዋሪዎችን ፍላጎት በሚመልስ መልኩ መፈጸም እና የተጀመሩ ሥራዎችን በወቅቱ ማጠናቀቅ ይገባል ብለዋል።

የከተማዋን የተቀናጀ ልማት ለማረጋገጥ የከተማ ፕላንና የልማት ሥራዎች በዕቅድ መመራት፣ የመሬት አጠቃቀምን በሕግና በስርዓት መምራት፣ ለሼድ ቦታዎች ማመቻቸት ቢቻል፣ ከ5አመት በላይ የተያዙ ሼዶችን በህግ መጠየቅና ማስመለስ ቢቻል፣ የታቀዱ ዕቅዶችን በጥራትና በጊዜ ማከናወን ለመስራት ዝግጁዎች ነን ሲሉ የመምርያና የክፍለ ከተማ አመራሮች ተናግረዋል።

መድረኩም የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣የመምርያ ሀላፊዎች፣ የቀበሌና ክፍለ ከተማ አመራሮች ተገኝተዋል።

በዕለቱም ለደጋፊ የክልል አመራሮች የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

መስከረም 28/2019 ዓ.ም
ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን

"አረጋውያንን ስንከባከብ ግዴታችን አድርገን ሳይሆን ኃላፊነታችን እንደሆነ በመረዳት ነው።" ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻየአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሠራተኞች "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት...
08/10/2026

"አረጋውያንን ስንከባከብ ግዴታችን አድርገን ሳይሆን ኃላፊነታችን እንደሆነ በመረዳት ነው።" ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሠራተኞች "እንክብካቤና ዘላቂ ደህንነት ለአረጋውያን፣ መልካም ሕይወት!" በሚል መሪ ሐሳብ ዓለም አቀፍ የአረጋውያን ቀንን በፓናል ውይይት አክብረዋል።

በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ትብለጥ መንገሻ፤ የአረጋውያን ቀን ወደዚህ ምድር ለመምጣትና በነፃነት ለመኖር መሠረት የሆኑትን፣ ጊዜያቸውን፣ ገንዘባቸውን እና ጉልበታቸውን የሰጡንን እናቶችና አባቶች የምንዘክርበት፣ የምናከብርበትና እውቅና የምንሰጥበት ታላቅ በዓል በመሆኑ ከሌሎች በዓላትና ሁነቶች ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።

ይህን ቀን ስናከብር በአረጋውያን በኩል በአውራምባ የሚገኘውን መልካም ተሞክሮ ማስፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል። አረጋውያንን ስንከባከብም ግዴታችን አድርገን ሳይሆን ኃላፊነታችን እንደሆነ በመረዳት ሊሆን እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ዘበነ በበኩላቸው፤ አረጋውያን ለሀገርና ለማኅበረሰብ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ከማክበርና ከመዘከር ባለፈ፣ በሀገራዊና ማኅበራዊ ውሳኔዎች ላይ እንዲሳተፉ ዕድል መስጠት ከሁሉም የሚጠበቅ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

በፓናል ውይይቱ በቀረበ የመነሻ ሰነድ የአረጋውያን ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ36ኛ ጊዜ፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ35ኛ ጊዜ እንደሚከበር ተገልጿል። የዕለቱ ዓላማም አረጋውያን ለሀገርና ለሕዝብ ያበረከቱትን አስተዋፅኦ ለመዘከርና እውቅና ለመስጠት መሆኑ በሰነዱ ተመላክቷል።

ሀገርን ከክብሯና ከሙሉ ነፃነቷ፣ እንዲሁም ከድንቅ ወግና ልማዷ ጋር ያቆዩ በርካታ ኢትዮጵያውያን አረጋውያን በውስብስብ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ችግሮች ተተብትበው እንደሚገኙም በሰነዱ ተጠቁሟል።

የአረጋውያን ቀን መከበር በሕፃናት፣ በወጣቶች፣ በጎልማሶችና በአረጋውያን መካከል የመደጋገፍ ባህልን ከማጠናከር ባለፈ፣ በትውልዶች መካከል የልምድና የዕውቀት ልውውጥ ሂደት ውጤታማ እንዲሆን እንደሚያግዝ ተመላክቷል።

አረጋውያን ከሚገጥሟቸው ዋና ዋና ችግሮች መካከልም በቂና የተመጣጠነ ምግብ፣ ምቹ መጠለያ፣ ጥራቱንና ወቅቱን የጠበቀ የሕክምና አገልግሎት እንዲሁም የማኅበራዊ ዋስትና እጦት ተጠቃሽ መሆናቸው ተገልጿል።

በውይይቱ የተሳተፉ አካላት በበኩላቸው፤ በክልሉ የሚገኙ አረጋውያን በዓላቸውን ከማክበር ባለፈ ዘላቂ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።

ማኅበረሰቡም አረጋውያንን ተረጂዎች ብቻ ከማድረግ ባለፈ፣ በአቅማቸውና በልምዳቸው ማኅበረሰቡን እንዲያገለግሉና የተሻለ ሕይወት እንዲኖሩ ምቹ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የአረጋውያንን ችግር ለመቅረፍም 'የእኔ አስተዋፅኦ ምንድነው?' በሚል መንፈስ ሁሉም የራሱን ድርሻ መወጣት እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

ጠንካራ ሀገርን ለመገንባት የአረጋውያንን ልምድ፣ ዕውቀትና ጥበብ በአግባቡ መጠቀም ይገባል ሲሉም ተሳታፊዎቹ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

መረጃው የአማራ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።

በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀ የቡና ዝግጅት ከፊል ምስል፦
08/10/2026

በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ለ2019 በጀት ዓመት የተዘጋጀ የቡና ዝግጅት ከፊል ምስል፦

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 22 የካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ~~~~~የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ ...
08/10/2026

የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት 22 የካቢኔ አባላትን ሹመት አፀደቀ
~~~~~
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ7ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የቀረቡ 22 የካቢኔ አባላትን ሹመት መርምሮ አጽድቋል።

በዚህ መሠረት፦

1. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) የገንዘብ ሚኒስትር፣

2. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የትምህርት ሚኒስትር ፣

3. አቶ አዲሱ አረጋ የግብርና ሚኒስትር፣

4. አቶ መሐመድ እድሪስ የመከላከያ ሚኒስትር፣

5. ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣

6. ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር፣

7. ወ/ሮ ሃና አርአያ ሥላሴ የፍትሕ ሚኒስቴር፣

8. ፍስሐ ይታገሱ (ዶ/ር) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር፣

9. ወ/ሮ ያስሚን ወሀቢረቢ የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር፣

10. አቶ አወሉ አብዲ የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር፣

11. ወ/ሮ ሸዊት ሻንካ የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣

12. አቶ ሙሳ አደም የሰላም ሚኒስትር፣

13. ፍሬሕይወት ታምሩ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር፣

14. ዓለምፀሐይ ጳውሎስ የማዕድን ሚኒስትር፣

15. ኢንጂነር ሙሐመድ አብዱራህማን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር፣

16. አቶ ሳዳት ነሻ የሎጂስቲክስ ሚኒስትር፣

17. አቶ በረከት ፍስሐፅዮን የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር፣

18. ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሤ የገቢዎች ሚኒስትር፣

19. ዶ/ር መቅደስ ዳባ የጤና ሚኒስቴር፣

20. ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር፣

21. ሱልጣን ወሌ (ዶ/ር ኢንጂነር) የመስኖ እና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስትር፣

22. (ዶ/ር) አክሊሉ ታደሰ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ሆነው ተሹመዋል።

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የኢፌ...
08/10/2026

አቶ ተመስገን ጥሩነህ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ።

ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ሥብሠባውን እያካሄደ ነው። ምክር ቤቱ አቶ ተመስገን ጥሩነህን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ ሾሟል። አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባለፉት ዓመታት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር በመኾን ሀገር አገልግለዋል። አሁንም በድጋሜ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኾነው ተሹመዋል።

!🇪🇹

የሰቆጣ ቃልኪዳን  ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን የመቀንጨር መጠን በዓመት ከ3% በላይ መቀነስ የሚያስችል አሰራር  በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር  በየቦ አር...
08/10/2026

የሰቆጣ ቃልኪዳን ከ2 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን የመቀንጨር መጠን በዓመት ከ3% በላይ መቀነስ የሚያስችል አሰራር በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በየቦ አርጀና ቀበሌ እየለማ ያለው የጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም አዝርቶች ልምድ ልውውጥ በፎቶ፤

Address

Debre Mark'os
381

Telephone

+251587714141

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Debre Markos city communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share