06/06/2026
በደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳደር የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የመንግስትና የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የጋራ የምክክር መድረክ ተካሄደ።
የፋርጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ጌትነት በመክፈቻ ንግግራቸዉ እንደገለፁት እንደመንግስት በወረዳችን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች እየሰሩት ያለዉ እንቅስቃሴ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ እያደረገ ያለ ነዉ።
በመሆኑም ከመንግስት ጎን በመሆን የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች የራሳቸዉን ታርጌት በመጠቀም አስቸጋሪዉን ጊዜ በመቋቋም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረጋቸሁ ታሪክ የማይረሳዉ ነዉ ። ስለዚህ ዛሬ የምናካሂደዉ የምክክር መድረክ በመንግስት ስር ያሉ ድርጅቶች አፈፃፀማቸዉ አንፃራዊ በሆነ መንገድ የሲቪል ማህበራቶች በወረዳችን ተግባሮቶችን ሲያከናዉኑ የድርጅት አስተባባሪዎች እና በስሩ ያሉ ሠራተኞች ተግባሮቹ አንፃራዊ በሆነ መልኩ የሚታይበት ሁኔታ ነዉ ብለዋል።
የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የፎካል ባለሙያ የሆኑት አቶ አብዩ ዋለልኝ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የወረዳችን አጠቃላይ አፈፃፀም በጥንካሬና በድክመት በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
የፋርጣ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማድነዉ ብርሃን በወረዳዉ ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች በዝርዝር አቅርበዋል።
የፋርጣ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አጥናፉ አለምየ እንደገለፁት ፕሮጀክቶቹ በሁሉም ዘርፍ ለሚያደርጉት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ አመስግነው ለተግባሩ ስኬታማነት ሁሉም የሚመለከተው አካል መተጋገዝ እንደሚገባ ተናግረዋል ።
የፋርጣ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አማረ ይሁኔ እንደገለፁት የሲቪል ማህበራት ኘሮጀክቱ በዓመቱ የተሰሩት ተግባራት የወረዳውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ ማድረጋቸውን አመስግነዉ በዓመቱ ያልተከናወኑ ተግባራትን በቀጣይ ዓመት መሰራት እንዳለባቸውና ክፍተቶችን በመሙላት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል መስራት አለባችሁ ብለዋል፡፡
የፋርጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይርጋ ጌትነት በማጠቃለያዉ እንደገለፁት ኘሮጀክቱ በወረዳው እየሰራ ያለው ተግባር ውጤታማ መሆኑን ገልፀው ለቀጣይ ህበረተሰቡን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ ለኘሮጀክቶች ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ሀላፊነታችሁን መወጣት አለባችሁ ብለዋል፡፡
ተሳታፊዎችም በበኩላቸዉ በሰጡት አስተያየት ፕሮጀክቱ እየሰራ ያለዉ ጥሩነዉ ወደፊትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ኃላፊነታችን መወጣት አለብን ብለዋል።
በውይይቱም ጥሪ የተደረገላቸው አመራሮች፣ ባለሙያዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅትና ሙያተኞች ፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካልት ተገኝተዋል፡፡