Loma Bossa Woreda Prosperity Party

Directions

Loma Bossa Woreda Prosperity Party Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Loma Bossa Woreda Prosperity Party, Political Party, Dawuro Loma, Debre Zeyit.

28/09/2026
26/09/2026

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2019 የደመራ እና የመስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ፦ አቶ አስፋው ጮራሞ

የሎማ ቦሳ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አስፋው ጮራሞ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2019 የደመራ እና መስቀል በዓል በሰላም አደረሳችሁ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የመስቀል በዓል በታላቅ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ከሚከበሩ የአደባባይ በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በዓለም አቀፍ የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም /UNESCO/ የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ልዩ በዓል ነው ።

በዓሉ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተላለፈ የመጣ የኢትዮጵያን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የሚያሳይ እንዲሁም ውብ ባህላችን የሚገለፅበት ድንቅ በዓል ነው ።

የደመራና መስቀል በዓል መንግስት ትልቅ ትኩረት ለሰጠው የቱሪዝም ዕድገትም ከፍተኛ ድርሻ የሚያበረክት በዓል ነው ።

የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓል የምናከብረው የ7ኛውን ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ በስኬት በማጠናቀቅ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር በጀመርነው ማግስት መሆኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ።

እንደ ወትሮው ሁሉ በዓሉን ስናከብር እንደ ደመራው በአብሮነት ተደምረን፣ በትብብር፣ በመተሳሰብ እና በፍቅር ከምንም በላይ ለሰላማችን ዘብ በመቆም እንድናከብር መልካም ምኞቴን እገልጻለሁም።

በዓሉ የሰላም የፍቅር የአንድነት እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን እየገለፅኩ በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን ።

መስከረም 16/2019 ዓ.ም

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

21/09/2026

አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩና አማኑኤል መኩሪያ የተባሉት በተደራጀ መንገድ ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 2: 00 ሰአት አከባቢ በሎማ ቦሳ ወረዳ ሚዳ ዘሎ ቀበሌ ልዩ ስፍራው ሰኞ ተብሎ በሚጠራው ቦታ የ15 አመት ሕጻንን አስገድዶ በመድፈር በእስራት መቀጣታቸውን የወረዳው ፍርድ ቤት አስታውቋል፡፡

ግለሰቦቹ ጥፋተኛ የተባሉት በኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 620 (2) ሀ እና መ፤ አንቀጽ 37(1,4) ሥር የተደነገገውን ህግ በመተላለፍ መሆኑን ችሎቱ አስታውቋል።

ተከሳሾቹ በተደራጀ መንገድ ሕፃኗን ከምትኖርበት ቤት ጨለማን ተገን በማድረግ 1ኛው ዋና የወንጀል አድራጊ ወደ ጓሮ እንሰት ሥር በማስገባት ኃይል በመጠቀም የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀሙን፤ 2ኛው ተከሳሽ የኢፌዴሪ ወንጀል ህግ አንቀጽ 37(1,4) ሥር አባሪ ተባባሪ በመሆን ለ1ኛው ተከሳሽ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንዲፈፅም ያመቻቹ በመሆኑ ነው ከቀረበው የዐቃቤ ህግ ማስረጃዎች ለማረጋገጥ የተቻለው።

በዚህ መሠረትም የወረዳው ፍ/ቤት መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ማረከኝ ድንበሩ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ አማኑኤል መኩሪያ በ5 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ገልጿል።

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾቹ ላይ ያስተላለፈው የቅጣት ውሳኔ መሰል የወንጀል ድርጊቶች እንዳይከሰቱ የሚያስተምርና የሚያስጠነቅቅ መሆኑም ተገልጿል።

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉን 👇
Follows us via👇
page https://www.facebook.com/profile.php?id=100064822177806
Telegram channel https://t.me/lomabosaworedgovtcomnctnaffairs/email [email protected]//
https://www.youtube.com/
http://twitter.com/

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!

Address

Dawuro Loma
Debre Zeyit
SWEP

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Loma Bossa Woreda Prosperity Party posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share