Dessie Zuriya Woreda Livestock Resource Development Office

Directions

Dessie Zuriya Woreda Livestock Resource Development Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Dessie Zuriya Woreda Livestock Resource Development Office, Government Organization, Dessie.

👉 ተልእኮ
ጥራቱን የጠበቀ ግብዓትና ቴክኖሎጂ በስፋት በማቅረብ፣የእንስሳት መኖ አቅርቦትን፣ አጠቃቀምን እና የእንስሳት ዝርያን በማሻሻል እና የእንስሳት በሽታን ቀድሞ በመከላከልና በመቆጣጠር፣ ስነ ምህዳርንና ክላሰተርን መሰረት ያደረገ በገበያ የሚመራ የኤክስቴንሽን አገልግሎት ለተጠቃሚዉ በመሰጠት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የወረዳውን ሕብረተሰብ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ ማድረግ።

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የለማ የተሻሻለ መኖ ዝርያዎች በከፊል፡
23/10/2026

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የለማ የተሻሻለ መኖ ዝርያዎች በከፊል፡

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1376/2018 (Proclamation No. 1376/2025) ምን ይላል?​ሰላም የዚህ ገጽ ተከታታዮች! እንስሳት ከሚያበረክቱት ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽ...
23/10/2026

የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ቁጥር 1376/2018 (Proclamation No. 1376/2025) ምን ይላል?

​ሰላም የዚህ ገጽ ተከታታዮች! እንስሳት ከሚያበረክቱት ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦ በላይ እንደሰው ስሜት ያላቸውና መሰረታዊ ፍላጎት እንዲሟላላቸው የሚሹ ፍጡራን በመሆናቸው፣ የእነሱን ጤና እና ደህንነት መጠበቅ የሁላችንም የሞራል እና የህግ ግዴታ ነው።

​በሀገራችን የወጣው የእንስሳት ጤና እና ደህንነት አዋጅ ቁጥር1376/2018 (1376/2025) ስለዚህ ወሳኝ ጉዳይ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች ያስቀምጣል፡-

​📋 የእንስሳት ባለቤቶች እና ጠባቂዎች ኃላፊነት (አንቀጽ 24)
​ማንኛውም እንስሳ የሚይዝ ወይም የሚንከባከብ ሰው ለእንስሳው የሚከተሉትን የማሟላት ኃላፊነት አለበት፡
✔️ ​በቂ የእንስሳት መኖ የማቅረብ፤
✔️ ​በቂ እና ንጹህ ውሃ የማቅረብ፤
✔️ ​ከእንስሳው ባህርይ እና ከአየር ጠባዩ ጋር የሚስማማ ምቹ መጠለያ የማቅረብ፤
✔️​ የተሟላ የእንስሳት ሕክምና እና ክትባት እንዲያገኙ የማድረግ፤
✔️ ​አግባብነት ያለው አያያዝ እና ጥበቃ እንዲያገኙ የማድረግ፤
✔️ ​ተገቢውን ደረጃ በሚያሟላ ማጓጓዣ የማጓጓዝ፤
​በእርጅና እና በበሽታ ወይም በሌላ አስገዳጅ ምክንያት መወገድ ካለበት ለሚመለከተው አካል የማሳወቅ።

​🚫 በእንስሳት ላይ የሚደረግ ጭካኔ የተከለከለ ነው! (አንቀጽ 25)
​አዋጁ በእንስሳት ላይ የሚፈጸሙ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶችን አጥብቆ ይከለክላል፡
​እንስሳትን በጭካኔ ማሰቃየት፣ መደብደብ፣ መጉዳት ወይም አካላቸውን ማቁሰል ወይም መቁረጥ፤
​እንስሳት ከአቅማቸው በላይ መጫን ወይም ማሠራት፤
​እንስሳትን ሆን ብሎ ወይም በቸልተኝነት አላግባብ መያዝ ወይም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ጉዳት ማድረስ፤
​በእንስሳት ላይ ህመምን ወይም ስቃይን የሚያስከትል ወይም ምቾትን የሚነሳ የእንስሳት እርባታ ዘዴ ማካሄድ የተከለከለ ነው።

​🎯 አዋጁን ማክበር ለምን ይጠቅማል?
✔️ ​የሰዎችን ጤና ለመጠበቅ: ከእንስሳት ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ በሽታዎችን (Zoonosis) በመከላከል የሕብረተሰቡን ጤና ይጠብቃል።
✔️ ​የእንስሳትን ደህንነት ለማረጋገጥ: እንስሳት ከስቃይ፣ ከህመም፣ ከፍርሃትና ከጭንቀት ተጠብቀው የተፈጥሮ ባህርያቸውን መግለጽ እንዲችሉ ያስችላል።
✔️ ​የገበያ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ: የእንስሳት ውጤቶች ጥራትና ደህንነት ዓለም አቀፍ ደረጃን እንዲያሟሉ በማድረግ አዳዲስ ገበያዎች ውስጥ ለመዘልቅ ይረዳል።

​እንስሳትን በአግባቡ በመንከባከብና ሕጎቹን በማክበር ኃላፊነታችንን እንወጣ!

​ #የእንስሳትጤናናደህንነት #ግንዛቤ #ሕግ

02/09/2026

የደቡብ ወሎ ዞን እንስሳት እና አሳ ሀብት መምሪያ በክልሉ ካሉ ዞኖች በ2018 በጀት አመት ካሉት ዞኖች በስራ #1ኛ በመውጣት የሞተር ሳይክል ፣ ዲስክ ቶፕ እና የምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነ። ከዞን እስከ ቀበሌ ያላችሁ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንኳን ደስ አላችሁ!!

30/07/2026
11/07/2026

የአብክመ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ
# ዶኩመንተሪ

06/07/2026
የደሴ ዙሪያ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በወረዳችን ባሉ   የበጎችና_ፍየሎች_የውጭ_ጥገኛ(Mange)_ቁጥጥር_ህክምና_ዘመቻ በስፋት በንቅናቄ እየተከናወነ ይገኛል።
10/06/2026

የደሴ ዙሪያ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በወረዳችን ባሉ
የበጎችና_ፍየሎች_የውጭ_ጥገኛ(Mange)_ቁጥጥር_ህክምና_ዘመቻ በስፋት በንቅናቄ እየተከናወነ ይገኛል።

የደሴ ዙሪያ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት   የዘመቻ  ኦሬንቴሽን ለቀበሌና የወረዳ እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ተሰጥቷል።   ስራው በሁለት ዙር በወረዳው ባሉ 33 ቀበሌዎች ላይ የ...
05/06/2026

የደሴ ዙሪያ ወረዳ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የዘመቻ ኦሬንቴሽን ለቀበሌና የወረዳ እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ተሰጥቷል።

ስራው በሁለት ዙር በወረዳው ባሉ 33 ቀበሌዎች ላይ የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር #ከሰኔ 1-5/10/2018 ዓ.ም ከ15 ቀናት በኋላ የሚሰጥ መሆኑን ተገልጿል። የሜንጅ ቁጥጥር ቅድመ መከላከል ህክምና ለሁሉም በጎችና ፍየሎች ይሰጣል።

በመድረኩ የቀበሌዎች የ8 ወራት ጥቅል የስራ አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን በዋናነት የክትባት አፈጻጸም፣የቅድመ መከላከል ህክምና፣ የምርመራ አገልግሎት ገቢ አፈጻጸምና አገልግሎት አሰጣጥ ያለበትን ሁኔታ በጥልቀት በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የ015 ቀበሌ አባሶቆቱ የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ በለማ   ላይ  በግብርና ልማት ቡድኖች የተካሄዴ የገበሬ በዓል (Farmers demonistration)፦
08/05/2026

የ015 ቀበሌ አባሶቆቱ የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከል ውስጥ በለማ ላይ በግብርና ልማት ቡድኖች የተካሄዴ የገበሬ በዓል (Farmers demonistration)፦

Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie Zuriya Woreda Livestock Resource Development Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share


Other Government Organizations in Dessie

Show All