Dessie PP Youth Wing

Directions

Dessie PP Youth Wing የደሴ ከተማ ብልፅግና ፖርቲ ወጣቶች ክንፍ የወጣቶች ፓለቲካዊ:ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንሰራለን!

የደሴ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 14ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ገባዔ አቶ ዱባለ አብራሬ ስጦቴን የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ም/ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።
05/10/2026

የደሴ ከተማ ምክር ቤት ባካሄደው 4ኛ ዙር 14ኛ ዓመት 47ኛ መደበኛ ገባዔ አቶ ዱባለ አብራሬ ስጦቴን የደሴ ከተማ ተቀዳሚ ም/ ከንቲባ አድርጎ ሾሟል።

መረጃ ሹመትበአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋሁን ተሰማ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥ...
03/10/2026

መረጃ ሹመት

በአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የወጣቶች ክንፍ ኃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋሁን ተሰማ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ ሆነው እንዲያገለግሉ ሹመት ተሰጥተዋል።

01/10/2026

ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ራዕይ

የአማራ ክልል ምክር ቤት አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰየመ

የአማራ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር 1ኛ ዓመት መስራችና 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ባለበት ወቅት አቶ አረጋ ከበደን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ ሰይሟል።

ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልል ፈታኝ የጸጥታ ችግር በገጠመው ወቅት ኀላፊነት ወስደው ክልሉ እንዲረጋጋ ያደረጉ ብርቱ መሪ መሆናቸው ተገልጿል።

በእርሳቸው የመሪነት ዘመን ክልሉን ከፈታኝ የጸጥታ ችግር አውጥተው ወደ ተረጋጋ ሰላም እንዲመለስ፣ በርካታ የልማት ሥራዎች እንዲሠሩ ያደረጉ መሪ ናቸው።

ክልሉ በፈተና ውስጥ ኾኖ የ25 ዓመታት የአሻጋሪ እድገት እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ በማቀድ ከግጭት አዙሪት እና ከድህነት እንዲወጣ የሚያስችሉ ሥራዎችን ሠርተዋል።
Amhara Prosperity Party /APP/

በደሴ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከወጣቶች ጋር ተካሂዷል።በመድረኩ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ፣ የሰላምና የልማት እንቅስቃሴዎችን...
28/09/2026

በደሴ ከተማ አስተዳደር በወቅታዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ከወጣቶች ጋር ተካሂዷል።

በመድረኩ የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ፣ የሰላምና የልማት እንቅስቃሴዎችን በማጠናከር ወጣቶች በሰላም ግንባታ ውስጥ ያላቸውን ሚና እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ ነው።

የአብክመ ከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሱለይማን እሸቱ በበኩላቸው በክልሉ የገጠመውን የሰላም እጦት ለመቅረፍ ወጣቶች ችግሩን በመረዳት ከመንግስት፣ ከጸጥታ አካላትና ከማህበረሰቡ ጋር በመቀናጀት መታገልና ሰላምን ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት በነበረው የሰላም እጦት ወቅት ከማህበረሰቡ ጋር ተቀናጅቶ መስራትና የመጣውን ሰላም ማስቀጠል፣ ሀገርን መጠበቅና የተጀመሩ ልማቶችን ውጤታማ ማድረግ ከወጣቶች የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አቶ ሱለይመን እሸቱ ጠቁመዋል።

የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዓለማየሁ ወጣቶች ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ድሎችን በማስቀጠል የገጠሙ ችግሮችን በመገምገም የሚጠበቅባቸውን ተልዕኮ ለመወጣት መረባረብ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

በዚህም ወጣቱ ለሀገሩ ልማትና ዕድገት የሚጠበቅበትን ድርሻ በመወጣት፣ በክልሉ የሚገጥሙ ችግሮችንም ለመፍታት የድርሻውን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አቶ አሸናፊ አለማየሁ አስገንዝበዋል።

በደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በወ/ሮ አዝመራ ማስረሻ የመወያያ ሰነድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

የአብክመ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ም/ቢሮ ኀላፊ አቶ ተፈሪ ታረቀኝ በከተማዋ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የልማት ሥራዎችን ለማደናቀፍ በሚሰሩ አካላት ላይ የሕግ የበላይነትን ማስከበርና የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ከወጣቱ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን አሳስበዋል።

ወጣቶች በሀገርና በክልል ደረጃ የሚገጥሙ ችግሮችን በጋራ በመረዳት መፍትሄ ላይ እንዲሳተፉ፣ ሰላምን እንዲያስጠብቁና ለልማትና ዕድገት የሚጠበቅባቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው በትብብር ስም ሀገር ለማፍረስ እየተንቀሳቀሰ ያለውን ኃይል አስተሳሰብ በማምከን ለሰላምና ለልማት የድርሻቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል።

02/09/2026
ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን! »​በደሴ ከተማ በሁሉም ቀበሌዎች «ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋ...
02/09/2026

ውጫዊ የወረራ ስጋት እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን! »

​በደሴ ከተማ በሁሉም ቀበሌዎች «ውጫዊ የወረራ ስጋትን እና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን!» በሚል መሪ ቃል ከወጣቶችና ከሴቶች ጋር የውይይት መድረክ ተካሂዷል።

​ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት በማጠናከር የውጭና የውስጥ ወራሪዎችን እንዲሁም የፅንፈኛ ቡድኖችን እኩይ አላማና እንቅስቅሴ በፅናት ለመታገል የወጣቶችና የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።

የደሴ ከተማንና የክልሉን ዘላቂ ሰላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል አስፈላጊ መሆኑም በመድረኮቹ ተገልጿል።

ተሳታፊ ወጣቶችና ሴቶች በበኩላቸው የከተማዋንና የሀገራቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ የፅንፈኝነት አደጋዎችን ለማክሸፍና የህዝቡን አንድነት ለማጠናከር የበኩላቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

31/08/2026
በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል የደሴ ከተማ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቀደኛ ወጣቶች በሀይቅ ከተማ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት አከናውነዋል።​በመርሀ ግብሩ ከተከናወኑ...
20/08/2026

በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ!» በሚል መሪ ቃል የደሴ ከተማ ወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቀደኛ ወጣቶች በሀይቅ ከተማ በመገኘት ዘርፈ ብዙ የበጎ አድራጎት ተግባራት አከናውነዋል።

​በመርሀ ግብሩ ከተከናወኑት አበይት ተግባራት መካከል ​የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር፣ የጽዳት ዘመቻና ​ የአዲሱን የትምህርት ዘመን ምክንያት በማድረግ አቅም ደካማ ለሆኑ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶችን በማስረከብ ለነገ ሀገር ተረካቢዎችን ወገንተኝነት አሳይተዋል።

​ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በወሰን ወይም በአካባቢ የማይወሰን የጋራ እሴታችን መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ተግባር በወጣቶች መካከል የመረዳዳት፣ የትብብር እና የእህትማማችነት/ወንድማማችነት ባህልን በፅኑ የሚያጎለብት መሆኑም ተመላክቷል።

​ይህ የደሴ ከተማ ወጣቶች በጎ አድራጎት ከአንድ ከተማ አልፎ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች ሁሉ ፍቅርንና አንድነትን መዝራት እንደሚቻል ማሳያ ሲሆን፣ የመደጋገፍና አብሮ የመስራት አገራዊ እሴትን በተግባር ያሳየ ሞዴል ተግባር እንደሆነ ተገልጿል።

የደሴ ከተማ ሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ የሀይቅ ከተማ አስተዳደር ላደረገለት ደማቅ አቀባበል ምስጋና አቅርቧል

በደሴ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ዕቅድ እስከአሁን  ውጤታማ ሥራ መከናወኑን የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገል...
07/08/2026

በደሴ ከተማ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተያዘው ዕቅድ እስከአሁን ውጤታማ ሥራ መከናወኑን የክልሉ ሱፐርቪዥን ቡድን ገለጸ

​በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሱፐርቪዥን ቡድን በደሴ ከተማ አስተዳደር ያደረገውን የመስክ ምልከታ በማጠናቀቅ ከከተማው አስተባባሪ ስቲሪንግ ኮሚቴ ጋር የማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል።

​ቡድኑ እስከ ሃምሌ 29/2018 ዓ.ም ድረስ የተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አፈጻጸም በዝርዝር የገመገመ ሲሆን፣ በበጀት ዓመቱ በተለዩት 17ቱም የክረምት የተግባር መስኮች ከተጠበቀው በላይ የተሻለና አበረታች ሥራ መከናወኑን አረጋግጧል።

​በዘንድሮው የክረምት ወራት የዜጎች የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች ማሳተፍ ተችሏል።

ይህም የበጎ ፈቃድ ባህልን በማህበረሰቡ ዘንድ የበለጠ ለማስረጽና የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።

​የሱፐርቪዥን ቡድኑ በምልከታው ያረጋገጣቸውን ዋና ዋና ስኬቶችና የትኩረት አቅጣጫዎች ​የ17ቱ ተግባራት አፈጻጸም፡ ከአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ እስከ አቅመ-ደካሞች ቤት እድሳት፣ የደም ልገሳ፣ ማህበራዊ ድጋፍና የትምህርት ቁሳቁስ ማሰባሰብ ባሉት ሙሉ 17ቱ የተግባር መስኮች የተቀናጀና ውጤታማ እንቅስቃሴ ተደርጓል።

​የህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነት ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በእውቀቱ ያደረገው ንቁ ተሳትፎ ለስራው ስኬታማነት ዋና ምክንያት መሆኑ ተጠቅሷል።

​በየደረጃው ያሉ የአመራር አካላትና የስትሪንግ ኮሚቴው ያደረጉት ቅርብ ክትትልና ድጋፍ በስራው ላይ ግልጽ ለውጥ ማምጣቱ ተመላክቷል።

​በመድረኩ ማጠቃለያ የደሴ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሸናፊ ዓለማየሁ እንደገለፁት ያሉት ጥንካሬዎችን በማስቀጠል ከተሰጡት ግብረ-መልሶች በመነሳት የቀሩትን የክረምት ወራት ተግባራት በተመሳሳይ ትጋትና ጥራት በማጠናቀቅ የታቀዱትን ግቦች ሙሉ በሙሉ ለማሳካት ከተማ አስተዳደሩ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል።

ተስፋን እንትከል !🌴በደሴ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ መልዕክት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መርሀ ግብር በመንበረ ፀሐይ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተ...
03/08/2026

ተስፋን እንትከል !🌴

በደሴ ከተማ አስተዳደር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ መልዕክት የአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ የንቅናቄ መርሀ ግብር በመንበረ ፀሐይ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ተጀምሯል።

በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላው በከተማው ባሉ ቀበሌዎች በሙሉ በ92 ሄክታር መሬት ላይ 359 ሺህ ችግኞች ይተከላል ተብሏል።


Address

Dessie

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dessie PP Youth Wing posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share