Dire Dawa Administration City Manager

Directions

Dire Dawa Administration City Manager ይህ ገጽ የከተማዋን መሰረተ ልማትና ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶ የሚያሳይ ነው�

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደም ከህዝብ ጋር በተወያዩበት ወቅት የተነሱ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ጀመሩበመንገዶች ባለስልጣን በራስ አቅም መገንባት...
10/10/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደም ከህዝብ ጋር በተወያዩበት ወቅት የተነሱ የመንገድ መሰረተ ልማት ጥያቄዎች ምላሽ ማግኘት ጀመሩ

በመንገዶች ባለስልጣን በራስ አቅም መገንባት የጀመረው ከወዳጆ ገንደ አዳ የመንገድ ስራ በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የማኔጅመንት አባላት የተጎበኘ ሲሆን አመራሩ ከህዝብ ለሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በተገባው ቃል መሰረት ነው።
የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ እንዳስታወቁት አዲሱ አመራር ከነዋሪዎች ጋር ባደረጓቸው ውይይቶች በርካታ የልማት ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ችግሮችን በየደረጃው ለመፍታት በእቅድ እንደሚሰራ በህዝባዊ መድረኮቹ የተገለጸ ሲሆን ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት ጥያቄዎች ፈጣንና ምላሽ እንዲሰጣቸው በክቡር ከንቲባው በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመንገድ ስራው እንደተጀመረ ገልጸዋል።

በሕዝብ መድረክ ለቀረቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ የመንገድ ግንባታዎች መጀመራቸውን አቶ ፋሚ ሙሜ ገለጹ መስከረም 30 ፥ 2019 ዓ.ም | ድሬዳዋበሕዝብ የውይይት መድረኮች ሲነሱ ለነበሩ...
10/10/2026

በሕዝብ መድረክ ለቀረቡ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡ የመንገድ ግንባታዎች መጀመራቸውን አቶ ፋሚ ሙሜ ገለጹ

መስከረም 30 ፥ 2019 ዓ.ም | ድሬዳዋ

በሕዝብ የውይይት መድረኮች ሲነሱ ለነበሩት የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችሉ፣ ገጠርንና ከተማውን የሚያገናኙና የመንገድ ትስስርን የሚያጠናክሩ ሥራዎች መጀመራቸውን የድሬዳዋ አስተዳደር ከተማ ሥራ አስኪያጅ ኃላፊ አቶ ፋሚ ሙሜ ገለጹ።

ይህ የመንገድ መሠረተ ልማት ግንባታ ወደ ሥራ ሊገባ የቻለው የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን በዚህ ሳምንት ከነዋሪዎች ጋር ሰፊ ውይይት ካካሄዱ በኋላ፤ አዲሱ ካቢኔ ለሕዝብ ጥያቄዎች ቅድሚያ በመስጠት ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲገባ ባስቀመጡት አቅጣጫ መሠረት መሆኑን ኃላፊው አስረድተዋል።

በመሠረተ ልማት ቅንጅት በአዲስ መልክ መገንባት የጀመረውና 13 ነጥብ 3 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ይኸው የመንገድ ፕሮጀክት በዚህ ወር ውስጥ ወደ ተግባር መግባቱ ታውቋል።

አቶ ፋሚ ሙሜ፤ አሁን እየተገነባ ያለው የመንገድ ትስስር ሥራ በተለይ ምርታማ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን በቀጥታ ወደ ዋናው አስፋልት መንገድ የሚያስወጣ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አርሶና አርብቶ አደሩ ምርታቸውን በቀላሉ ወደ ገበያ እንዲያቀርቡና ከልማቱ እኩል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል እጅግ ወሳኝ የልማት መሠረት መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል።

አስተዳደሩ የሕዝብ ቅሬታና ጥያቄ የሆኑ የመሠረተ ልማት ክፍተቶችን በጥናት በመለየት ፈጣንና ዘላቂ ምላሽ የመስጠት ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አመልክተዋል።

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የ2019 አንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።መድረኩ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን ለአዳዲሶቹ አመ...
09/10/2026

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የ2019 አንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን ለአዳዲሶቹ አመራሮች ከሰራተኞች ጋር ወቅቱን የጠበቀ የትውውቅ አጋጣሚ የፈጠረና አብሮነትን የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ ከተማዋን የተረከበው አዲሱ አመራር የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ርካታ እና የህዝብ ተአማኒነት ላይ ለመስራት ቁርጠኝነቱን አስታውቀው ከተማችንን የሚመጥንና የሚለውጥ ተቋም ለመገንባት እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጅና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሮብሌ ዑመር የተቋሙ ለነዋሪዎች የሚሰጠው የከተማ አገልግሎቶችን ለማዘመንና ለውጥ ለማምጣት ሰራተኛው ከአመራሩ ጎን በመሆን ድጋፍ እንዲያደርጉና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በመጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ተገምግመዋል።

09/10/2026

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ተጠሪ ተቋማት የ2019 አንደኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ እየተካሄደ ነው።

መድረኩ በኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር የተጀመረ ሲሆን ለአዳዲሶቹ አመራሮች ከሰራተኞች ጋር ወቅቱን የጠበቀ የትውውቅ አጋጣሚ የፈጠረና አብሮነትን የሚያጎለብት መሆኑ ተገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ ከተማዋን የተረከበው አዲሱ አመራር የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ርካታ እና የህዝብ ተአማኒነት ላይ ለመስራት ቁርጠኝነቱን አስታውቀው ከተማችንን የሚመጥንና የሚለውጥ ተቋም ለመገንባት እንደሚሰሩ አብራርተዋል።

ምክትል ስራ አስኪያጅና የደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሮብሌ ዑመር የተቋሙ ለነዋሪዎች የሚሰጠው የከተማ አገልግሎቶችን ለማዘመንና ለውጥ ለማምጣት ሰራተኛው ከአመራሩ ጎን በመሆን ድጋፍ እንዲያደርጉና ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል።

በመጀመሪያው ሩብ አመት ሪፖርት የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት ተገምግመዋል።

08/10/2026

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 3.5 ቢሊየን ብር በላይ ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው።
የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ እና ም/ስራ አስኪያጅ እና የደንብ ማስከበር ጽ/አቤት ሀላፊው አቶ ሮብሌን ጨምሮ የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት በገቢ አመንጪና ተሰብሳቢ ተቋማት ላይ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 3.5 ቢሊየን ብር በላይ ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ  ታቅዶ እየተሰራ ነው።  የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ እና ም/ስራ አስኪያጅ እና የደንብ ማስከ...
08/10/2026

በከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት 3.5 ቢሊየን ብር በላይ ማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ ነው።

የከተማዋ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋህሚ ሙሜ እና ም/ስራ አስኪያጅ እና የደንብ ማስከበር ጽ/አቤት ሀላፊው አቶ ሮብሌን ጨምሮ የተቋሙ የማኔጅመንት አባላት በገቢ አመንጪና ተሰብሳቢ ተቋማት ላይ የስራ ጉብኝት አድርገዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የልማት ግስጋሴን ለማፋጠንና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ መስከረም  28/2019የድሬዳዋ አስተዳደር  ከንቲባ ...
08/10/2026

የድሬዳዋ አስተዳደር የልማት ግስጋሴን ለማፋጠንና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተገለጸ

መስከረም 28/2019

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደም በተገኙበት፣ የሴክተር ተቋማትና ወረዳዎች እያከናወኗቸው የሚገኙ ስራዎችን ለመገምገም፣ ለመመልከትና ለማጠናከር ያለመ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዛሬው ዕለትም የአስተዳደሩ የከተማ ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤትና ተጠሪ ተቋማት፣ የስራ አፈጻጸም እንዲሁም በአስተዳደሩ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ያሉበት ደረጃ በዝርዝር ተገምግሟል።

በዚሁ የምክክር መድረክ ላይ የ2018 ዓ.ም የስራ አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ዋና ዋና ተግዳሮቶች እና የ2019 ዓ.ም ዕቅዶች ላይ ትኩረት ያደረገ ውጤታማ ውይይት ተካሂዷል።

በተለይም የአገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በማዘመንና ዲጂታላይዝ በማድረግ የተገልጋዩን ማህበረሰብ እርካታ ማሳደግ እንደሚገባ ከንቲባው ገልጸዋል።

አክለውም፣ የመዘጋጃቤታዊ ገቢን በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ በቁርጠኝነት መስራትና ለስራ ስኬት እንቅፋት የሚሆኑ ተግዳሮቶችን በፍጥነት መፍታት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በአጠቃላይም ከንቲባ አብዱላሂ የድሬዳዋ አስተዳደር የልማት ግስጋሴን ለማፋጠንና የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ስራዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።

ይህ የግምገማና የውይይት መድረክ የድሬዳዋን ሁለንተናዊ የብልፅግና ጉዞ ይበልጥ የሚያፋጥንና የተቋማትን የአፈጻጸም አቅም ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑ ተገልጿል።

የቄራ አገልግሎት ድርጅት አዲሱን ታሪፍ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እያደረገ በመሆኑ በመጀሪያው ሩብ አመት እስከ መስከረም አጋማሽ ብቻ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የድርጅቱ ስራ አስኪያ...
07/10/2026

የቄራ አገልግሎት ድርጅት አዲሱን ታሪፍ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ እያደረገ በመሆኑ በመጀሪያው ሩብ አመት እስከ መስከረም አጋማሽ ብቻ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ አቶ አዩብ ኢብራሂም ገለጹ።

በከተማ ልማት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ሸሪፍ የተመራ የከፍተኛ ባለሙያዎች ቡድን በገቢ አመንጪ እና ገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ላይ የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ማከናወን ጀምሯል።
በውይይቱ የገቢ አሰባሰብ ስርአቱ አለመዘመኑ፣ የአገልግሎት አሰጣጥና የጥራት ችግር፣ ተቋማቱ ተናቦና ተቀናጅተው አለመስራት፣ የበጀት እጥረት፣ የአደረጃጀት፣ የሰውሀይል የግብአት እና የሎጀስቲክስ እጥረት ተግዳሮት ቢሆንበትም በውጤታማነት መቀጠሉን ስራ አስኪያጁ ገልጸዋል።
ተደራሽነትን ከማስፋት አንጻር ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች አነስተኛ አገልግሎት መስጫ ማእከላት በአማራጭነት ቢዘጋጁ፣ ህገወጥ እርድ ቁጥጥር፣ የተረፈምርት ማቀነባበሪያውን ወደስራ ማስገባት፣ የውሀ አቅርቦት ችግሮች እንዲፈቱና ተቋሙ በሙሉ አቅሙ ወደስራ እንዲገባ ድጋፍ እንዲደረግ ጠይቀዋል ።
አቶ ሸሪፍ በበኩላቸው የተነሱ ጥያቄዎች በሪፎርም የሚፈቱ ቢሆንም የሪፖርት ስርአት እና የመረጃ አያያዝ፣ የአሰራር ስርአቶችን መዘርጋት፣ ትልቁን የውሀ ችግር በአስተዳደር ደረጃ ለመፍታት ጥረት እንደሚያደርጉና አዲሱ አመራር የህዝብ አገልግሎቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ ስለሚሰራ ችግሮችን አብሮ ለመፍታት እንደሚሰሩ አስታውቀዉ ተቋሙ በዚህ ሁሉ ችግር ውስጥ ሆኖ ውጤት ማምጣት መቻሉንም አድንቀዋል።

ድሬዳዋ አሰተዳደር ክቡር ከንቲባ አብዱላሂ አደን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ።መስከረም 7 2019የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደን ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮ...
07/10/2026

ድሬዳዋ አሰተዳደር ክቡር ከንቲባ አብዱላሂ አደን የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያን ጎበኙ።

መስከረም 7 2019

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ክቡር አቶ አብዱላሂ አደን ከአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን በድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የተከናወኑና በመከናወን ላይ ያሉ የልማት፣ የዘመናዊ አሰራርና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ጎበኙ።

በጉብኝቱ ወቅት የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር አለሙ መግራ ተቋሙ በቅርብ ጊዜያት ያስመዘገባቸውን የአሰራር ለውጦች፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምና የልማት ፕሮጀክቶች ለከንቲባውና ለልዑካን ቡድኑ አስጎብኝተዋል።

የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያው የድሬዳዋን ከተማ ሰላምና ፀጥታ በተሻለ አቅም ለማስጠበቅ በቴክኖሎጂ፣ በአሰራር፣ በኮሙኒኬሽንና በሎጂስቲክስ ዘርፎች ላይ የሚታዩ ለውጦችን ማስመዝገቡ ተገልጿል።

በተቋሙ ከተዘረጉት ዘመናዊ አሰራሮች መካከልም የዲጂታል ሶፍትዌሮች አጠቃቀም፣ የCCTV ካሜራ ዳታቤዝ፣ የአርቴፊሻል ሳር ሜዳ፣ የዋና ገንዳ፣ የጦር መሣሪያ ጥገና ክፍልና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙበታል። አንዳንዶቹ ተጠናቀው ለአገልግሎት ዝግጁ ሲሆኑ፣ ሌሎች ደግሞ በሂደት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

ክቡር ከንቲባ አቶ አብዱላሂ አደን ድሬዳዋ የፍቅርና የመቻቻል ከተማ መሆኗን ጠቁመው፣ የከተማዋን ይህን እሴት በመገንዘብ ሰላምና ደህንነቷን ለማስጠበቅ የድሬዳዋ ፖሊስ እያከናወነ ያለው ሥራ አስደናቂ መሆኑን ገልጸዋል።

ክቡር ከንቲባው በተለይ በኮሚሽነር አለሙ መግራ መሪነት በፖሊስ ጠቅላይ መምሪያው የተከናወኑ ሥራዎች ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆኑ መሆናቸውን አድንቀዋል።

በሌላ በኩል፣ ከሌሊት ታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር በተሰራው የጋራ ሥራ ረገድ አሽከርካሪዎቹ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ከንቲባው አድንቀዋል። ይህንንም ውጤታማ የጋራ ሥራ በቀጣይ የበለጠ በማጠናከር ለመቀጠል እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በጉብኝቱ ላይ የከንቲባው ጽሕፈት ቤትና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ምክትል ኮሚሽነሮችና የፖሊስ አባላት እንዲሁም የሌሊት ታክሲ አሽከርካሪዎች ማህበር አባላት ተገኝተዋል።
📸Dire Dawa Police

ተቋማት ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በርብርብ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ መስከረም 26/2019የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱ...
06/10/2026

ተቋማት ላይ እየተከናወኑ የሚገኙ አበረታች ሥራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በርብርብ መሥራት እንደሚገባ ተገለጸ

መስከረም 26/2019

የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አብዱላሂ አደም የድሬዳዋ አስተዳደር የሥራና ክህሎት ቢሮ፣ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ፣ የገቢዎች ባለሥልጣን እንዲሁም የግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የ2018 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እና የ2019 ዓ.ም ዕቅዶች ተገምግመዋል።

በዚህም ከንቲባ አብዱላሂ በግምገማው ወቅት እንደገለጹት፤ መድረኩ የቢሮዎቹን አሁናዊ የሥራ ሁኔታ በመገምገም ጠንካራ አፈጻጸሞችን ለማስቀጠልና ክፍተቶች ባሉባቸው መስኮች ላይ ደግሞ በቅንጅትና በርብርብ ለመሥራት ያለመ ነው።

በግምገማ መድረኩ ላይ በየዘርፎቹ በርካታ ዋና ዋና ነጥቦችና ተግዳሮቶች የተነሱ ሲሆን፣ በግብርናው ዘርፍ ማህበረሰቡን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የተከናወኑ ተግባራት፣ በአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ በአረንጓዴ አሻራ እንዲሁም በሌማት ቱሩፋት የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶች ተጠናክረውና ሰፍተው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ተመልክቷል።

በሌላ በኩል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ አሰራሮችን ዲጂታላይዝ በማድረግ ቀልጣፋና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት፣ የማህበረሰቡን እርካታ ማሳደግ እና የ‘መሶብ’ አገልግሎትን አጠናክሮ ማስቀጠል የ2019 ዓ.ም የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን አብራርቷል።

የሥራና ክህሎት ቢሮን ዕቅድና አፈጻጸም በተመለከተም፣ በከተማም ሆነ በገጠር ክህሎትን መሠረት ያደረገ የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በከፍተኛ ሁኔታ መረባረብ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን፣ በአስተዳደሩ ያሉ ወጣቶች በብቃት የስራ ላይ ልምምድ በመመዝገብ የተሻለ ገቢ እና ኑሮ እንዲያገኙ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባው ተጠቁሟል።

የገቢዎች ባለሥልጣንም በበኩሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና ቅንጅታዊ አሰራርን በመጠቀም የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ፣ አዳዲስ ደንቦችን ወደ ሥራ ማስገባት እንዲሁም የማዘጋጃ ቤታዊ ገቢን ማሳደግ እንደሚገባው አቅጣጫ ተቀምጧል።

ከንቲባ አብዱላሂ አደም በየዘርፉ ለቀረቡ ዕቅዶች ስኬታማነት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅትና በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ከንቲባ አብዱላሂ አደም አሳስበዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይም በቀረቡት ዕቅዶችና ተግዳሮቶች ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ የተቋማቱን አፈጻጸም በማሻሻል የ2019 ዓ.ም ዕቅዶችን በተገቢው ሁኔታ ለማስፈጸም የሚያስችሉ መመሪያዎች ተሰጥተዋል።

Address

Dire Dawa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dire Dawa Administration City Manager posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share