የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን

  • Home
  • Ethiopia
  • Durame
  • የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን
Call Directions Website

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የትምህርትና ሥልጠና  ጥራት ቁጥጥር  ባለሥልጣን Official page of Central Ethiopia Regional State Education and Training Quality Regulation Authority(CERS ETQRA)

13/11/2026
12/11/2026
‎"የመስኖ ልማት ሥራ ውሃን ወደ ምርት በመቀየር የሕዝቡን ገቢ በማሳደግ የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል መሆኑ ተመላከተ‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ከዞኖች እና ልዩ...
12/11/2026

‎"የመስኖ ልማት ሥራ ውሃን ወደ ምርት በመቀየር የሕዝቡን ገቢ በማሳደግ የዜጎችን ኑሮ ማሻሻል መሆኑ ተመላከተ
‎
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ከዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች የዘርፉ አመራሮች ጋር የ2019 በጀት ዓመት የሴክተሩን የእስካሁን ሥራ አፈፃፀም ለመገምገምና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያዘጋጀው የምክክር መድረክ በዱራሜ ከተማ እየተካሔደ ነው።

‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ መድረኩን ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የመስኖ ልማት ሥራ ውሃን ወደ ማሳ በማድረስ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ውሃን ወደ ምርት በመቀየር የዜጎችን ገቢ ትርጉም ባለው መልኩ በማሳደግ የሕዝቡን ኑሮ ማሻሻልን ግብ ያደረገ ተግባር መሆኑን ገልፀዋል።
‎
‎የዞኖችና ልዩ ወረዳዎች የዘርፉ አመራሮች ስለተቋሙ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው እንዲመሩ ለማድረግ የዘርፉን ተልዕኮ ለማስተዋወቅ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ መድረኩ መዘጋጀቱን የቢሮ ኃላፊው አቶ ሰላሙ አማዶ አብራርተዋል።
‎
‎የከምባታ ዞን መስኖና ቆላማ አካባቢዎች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በፍቅር ታምራት በበኩላቸው የመደመር መንግሥት ለሰው ልጆች ኑሮ መሻሻል በሰጠው ትኩረት ዘርፉ በአዲስ መልክ እንዲደራጅ መደረጉን ገልፀው በተቋሙ የሚከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ድርቅን ለመቋቋም እና ኢኮኖሚያዊ ገቢን ለማሳደግ ላቅ ያለ አበርክቶ እንዳላቸው አስረድተዋል።
‎
‎የዘርፉን የእስካሁን አፈፃፀም የተመለከተ ሰነድ እየቀረበ ሲሆን በተሳታፊዎች ውይይት እንደሚደረግበትም ተመላክቷል።

Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau
‎

‎

12/11/2026

"ኮፕ ኢትዮጵያ ሲዘጋጅ 65 ቢሊየን ችግኝ መትከል የቻለች ሀገር የሚል ዜና ለመላው ዓለም የምናበስርበት ጊዜ ይሆናል"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ11ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ ውድድር 2ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸላሚ ሆነበትምህርት ሚኒስቴርና በተባባሪ አካላት አዘጋጅነት በተካሄደው 11ኛው ሀገር አቀፍ የሳ...
11/11/2026

ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በ11ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ ውድድር 2ኛ ደረጃን በመያዝ ተሸላሚ ሆነ

በትምህርት ሚኒስቴርና በተባባሪ አካላት አዘጋጅነት በተካሄደው 11ኛው ሀገር አቀፍ የሳይንስና ፈጠራ ውድድር፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ከሀገሪቱ ክልሎች የ2ኛ ደረጃ አሸናፊ በመሆን ተሸላሚ ሆነዋል።

''በሳይንስ የሚገኝ የጋራ ዲፕሎማሲ'' በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ሀገር አቀፍ ውድድር ላይ ክልሉን ወክለው የተሳተፉ ተማሪዎችና መምህራን በየፈርጃቸው ድንቅ ፈጠራዎቻቸውን በማቅረብ አሸናፊ ሆነዋል።

በተማሪዎች ምድብ ከ7ኛ - 8ኛ ክፍል ፈርጅ የክልሉ ተወዳዳሪዎች 2ኛ እና 3ኛ ደረጃዎችን በመያዝ የዘመናዊ ስማርት ስልክ ተሸላሚ ሆነዋል።

በተማሪዎች ምድብ ከ11ኛ - 12ኛ ክፍል ፈርጅ የክልሉ ተወዳዳሪ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ስማርት ስልክ ተሸልሟል።

በመምህራን ምድብ በመካከለኛ ደረጃ ፈርጅ የክልሉ መምህራን 2ኛ ደረጃን በማስመዝገብ ታብሌት ተሸላሚ ለመሆን ችለዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ የተመዘገበው ድል የትምህርት ቤቶችን፣ የመምህራንን እና የተማሪዎችን የፈጠራና የቴክኖሎጂ አቅም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያስመሰከረ ታላቅ ምዕራፍ መሆኑን ገልጿል።

ቢሮው ለዚህ ታላቅ አገራዊ ስኬትና ድል አስተዋጽኦ ላደረጉ የትምህርት ባለሙያዎች፣ አመራሮች፣ ተማሪዎችን ላሰለጠኑ አሰልጣኝ መምህራን እንዲሁም ለተሸላሚ ተማሪዎች በሙሉ እንኳን ደስላችሁ በማለት የላቀ ምስጋናውን አቅርቧል።

Central Ethiopia Region Bureau of Education-ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ

Address

Central Ethiopia Region
Durame

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የትምህርትና ሥልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለሥልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share