Dawit Fantaye Kocha

Call Directions Website

Dawit Fantaye Kocha የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ, Gofa Zone chief Administrator

14/10/2026

ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ጋር በሁለትዮሽ፣ በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የጋራ ትኩረትን በሚሹ ጉዳዮች ላይ እጅግ ፍሬያማ የሆነ የስልክ ውይይት አድርጌያለሁ።

ያካሄድነው ውይይት በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን እድሜ ጠገብ ወዳጅነት ወደ ላቀ ስትራቴጂካዊና ተግባራዊ አጋርነት ለማሳደግ በሁለቱም አገራት በኩል ያለውን ቁርጠኝነት ማረጋገጫ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በተመለከተ የሰጠችውን ማረጋገጫ እያደነቅኩ የሁለትዮሽ ትብብራችንን ለማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊና ባለብዙ ወገን መድረኮች ቅድሚያ በምንሰጣቸው የጋራ ጉዳዮች ላይ አብረን ለመሥራት ያለንን ቁርጠኝነት አረጋግጣለሁ።

Ministira Dhimma Alaa Ameerikaa, Maarkoo Ruubiyoo waliin dhimmoota garlamee, naannawaafi dhimmoota gar-daneessa xiyyeeffannoo waloo barbaadan irratti bilbilaan marii firii-qabeessa gooneerra.

Mariin keenya michummaa umurii dheeraa Itiyoophiyaafi Ameerikaa giddu jiru gara michummaa olaanaafi tarsiimowaatti guddisuuf kutannoo biyyoota lamaan gidduu jiru kan mirkaneessudha.

Deeggarsa ittifufiinsa qabu Ameerikaan Itoophiyaaf gootu ilaalchisee wabii kennan dinqisiifachaa walta'insa keenya garlamee cimsuuf akkasumas waltajjiiwwan nannawaafi gar-daneessa ta'an irratti dhimmoota waloo dursa kenninuuf irratti waliin hojjechuuf kutannoo qabnun mirkaneessaa.

I held a very fruitful telephone conversation with U.S. Secretary of State Marco Rubio on key bilateral, regional and multilateral issues of mutual interest.

Our discussion is proof to the commitment of both countries in translating the enduring relationship between Ethiopia and the United States into a more strategic and practical partnership.

I welcome the assurance of continued U.S. support for Ethiopia and our shared commitment to advancing bilateral cooperation and addressing regional and multilateral priorities.

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር ተገቢና ወቅታዊ መልዕክት ነው
14/10/2026

ክቡር ርዕሰ መስተዳድር ተገቢና ወቅታዊ መልዕክት ነው

12/10/2026
12/10/2026

ሰንደቅ ዓላማችን፤ የነፃነታችን፣ የሉዓላዊነታችንና የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን የማይደበዝዝ ዓርማ!

ሰንደቅ ዓላማችን ከቀለማት ቅንብርና ከብሔራዊ መለያነት የላቀ ጥልቅ ታሪካዊ፣ ሀገራዊና ሥነ-ልቦናዊ ትርጉም ያለው የጋራ ማንነታችን ነው። የአባቶቻችንንና የእናቶቻችንን የጀግንነት ታሪክ፣ ለነፃነት የተከፈለውን ውድ መስዋዕትነት፣ የሉዓላዊነታችንን ክብርና የአብሮነታችንን ጽናት የሚያንጸባርቅ ሕያው የታሪክ ምስክር ነው። በትውልዶች መካከል የማይቋረጥ የሀገር ፍቅር ድልድይ፣ ያለፈውን ከዛሬ፣ ዛሬንም ከነገው የኢትዮጵያ ተስፋ ጋር የሚያስተሳስር የጋራ ኩራታችን መገለጫ ነው።

ሰንደቅ ዓላማችን የትናንት የድል ታሪካችን ማስታወሻ ብቻ ሳይሆን፣ የዛሬ ኃላፊነታችንንና የነገ የጋራ ዕጣ ፈንታችንን የሚያስታውሰን ታላቅ ሀገራዊ አደራ ነው። ለዚህ የማይደበዝዝ ሀገራዊ ክብር መጠበቅ፣ ከጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ጀምሮ ለሀገራችን ሰላም፣ ለሕዝባችን ደኅንነትና ለሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓታችን ጥበቃ በቁርጠኝነት እየተጉ ያሉ የፀጥታና የደኅንነት አካላት የላቀ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። ለሀገር የሚከፈለው መስዋዕትነት ትርጉም የሚኖረውም የሕዝባችንን ሰላም፣ ክብርና ደኅንነት በማረጋገጥ፣ የሕግ የበላይነትን በማጽናትና ለትውልድ የተሻለች ሀገር በማስረከብ ነው።

ኢትዮጵያ የብዝኃነት ውበት፣ የአብሮነት ጥንካሬና የጋራ ዕጣ ፈንታ መገለጫ ናት። ሰንደቅ ዓላማችንም ይህንን ብዝኃነት ወደ የጋራ ጥንካሬ፣ ልዩነቶቻችንን ወደ መግባባት፣ የጋራ ተስፋችንንም ወደ ተግባራዊ ብልጽግና የመለወጥ ታላቅ ሀገራዊ ጥሪ ነው። የኅብረ-ብሔራዊ አንድነታችን መሠረት እርስ በርስ መከባበር፣ መተማመን፣ መደማመጥና ለጋራ ዓላማ በአንድነት መቆም ነው።

ስለሆነም የሰንደቅ ዓላማ ቀንን ስናከብር፣ ለታሪካችን ክብር በመስጠት ብቻ ሳንወሰን፣ ለወረስነው ሀገራዊ አደራ ቃላችንን የምናድስበት፣ የጋራ መግባባታችንን የምናጠናክርበት፣ ወንድማማችነታችንንና እህትማማችነታችንን የምናጸናበት፣ ለዘላቂ ሰላም፣ ለሀገራዊ አንድነትና ለጋራ ብልጽግና በተግባር የምንተጋበት ዕለት ሊሆን ይገባል።

09/10/2026
09/10/2026
እግዚአብሔር ፍሬያማ የአመራርነት አገልግሎት ዘመን ያድርግልህ !!
08/10/2026

እግዚአብሔር ፍሬያማ የአመራርነት አገልግሎት ዘመን ያድርግልህ !!

07/10/2026

Address

Felege Niway

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Dawit Fantaye Kocha posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share