West Gojjam Zone Finance

Call Directions

West Gojjam Zone Finance Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from West Gojjam Zone Finance, Government Organization, Finote Selam.

01/09/2026
የምዕ/ጎጃም ዞን ለግዥን ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በአዲሱ የግዥ ና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ:: ስልጠናው የተሻለ አሰራር በተቋ...
01/09/2026

የምዕ/ጎጃም ዞን ለግዥን ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች በአዲሱ የግዥ ና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ዙሪያ ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና አጠናቀቀ:: ስልጠናው የተሻለ አሰራር በተቋሙ እንዲኖር እውቀት የተገኘበት ሲሆን ሰልጣኞች ለአሰልጣኞች የማበረታቻ ሽልማትና እውቅና ሰጠዋል በእለቱም የመምሪያው ተወካይ አቶ ይባቤ ካሴ ቀጣይ ብዙ ሀላፊነቶች እንደሚጠበቁብን አሳስበዋል

የምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ ስር ላሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪዎችና የግዥ ባለሙያዎች ከ20/12/2018 ዓ/ም ጀምሮ በአዲሱ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ዙሪያ ስልጠና ...
26/08/2026

የምዕራብ ጎጃም ዞን ገንዘብ መምሪያ በዞኑ ስር ላሉ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪዎችና የግዥ ባለሙያዎች ከ20/12/2018 ዓ/ም ጀምሮ በአዲሱ የግዥ አፈጻጸም መመሪያ ዙሪያ ስልጠና መሥጠት ጀመረ።

 #ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 እቅድን  ገመገመ ****************************************የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ ከዳይሬክ...
13/08/2026

#ቢሮው የ2018 በጀት ዓመት አፈፃፀም እና የ2019 እቅድን ገመገመ
****************************************
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ ከዳይሬክቶሬቶች ጋር የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም እና የ2019 እቅድ ዝግጅትን በተናጠል በጥልቀት በመገምገም የማስተካከያ ሀሳብ እና አቅጣጫ አስቀምጦል፡፡

የአብክመ ገንዘብ ቢሮ ኃላፊ አቶ አታላይ ጥላሁን ቢሮው በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት በእቅድ ይዞ ሲፈጽም የቆየውን በጥንካሬና በድክመት በመለየት እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት አቅርቦ ማስገምገሙ ለቀጣይ አፈፃፀማችን ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልፀው በያዝነው 2019 በጀት ዓመት የሚተገበሩ ተግባራት ከክልሉ የአሻጋሪ እድገትና ዘለቂ ልማት እቅድ በመነሳት በቢሮ ደረጃ የታቀደውን በማውረድ እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት የራሱን ተግባራትን በአግባቡ ለይቶ በመያዝ እና የመፈፀሚያ ጊዜ አስቀምጦ በማቀድ የሚጨበጥ ውጤት ለማምጣት እንደተቋም አስበን እንድንሠራ ያግዘናል ብለዋል፡፡

እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት የ2018 በጀት አፈፃፀሙን በተናጠል በዳይሬክቶሬት ደረጃ አቅርቦ በማስገምገም አቅጣጫ የተሰጠበት ሲሆን በተመሳሳይ የ2019 በጀት ዓመት እቅድ ከተቋሙ እቅድ ከመካተቱ በፊት እያንዳንዱ ዳይሬክቶሬት አቅርቦ በማስገምገሙ የማስተካከያና የወደፊት የስራ አቅጣጫ ጭምር ተሰጥቷል፡፡

በቀጣይም በተቋም ደረጃ የተዘጋጀው የተጠቃለለ እቅድ አፈፃፀም እና ተቋማዊ እቅድ በቢሮው ሰራተኞች እና እንዲሁም በዞን እና ሪጂዮፖሊታን ከተሞች ገንዘብ መምሪያዎች ቀርቦ በቅርቡ የሚገመገም ይሆናል፡፡

ከአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን ሊንኮች ይጠቀሙ
ፌስቡክ https://www.facebook.com/share/191YyDU2YK/
ዩቲዩብ http://www.youtube.com/
ቴሌግራም https://t.me/AmharaBureauofFinance
ዋትስአፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vb8BHKA4SpkAKHBs6M0H
ኢንስታግራም https://www.instagram.com/amhara415?igsh=MTh1Nzd3dnNpaWRxMg==
ቲክቶክ https://www.tiktok.com/.finance.bureau?_r=1&_t=ZS-98Pv19CAtHA
ዌብሳይት http://www.amharabofec.gov.com/
ኤክስ (ትዊተር) https://twitter.com/

የምዕራብ ጎጃም ዞን  አስተዳደር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጠ።የዞኑ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ አፈጻጸምን ከዞኑ የመምሪያና ተ...
04/08/2026

የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተዳደር የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጠ።

የዞኑ አስተዳደር የ2018 በጀት ዓመት የአሻጋሪ እድገትና የዘላቂ ልማት እቅድ አፈጻጸምን ከዞኑ የመምሪያና ተጠሪ ተቋማት ጋር ገምግሟል።

በማጠቃለያ ግምገማው ላይ በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጥቷል።

በዚህም ፣ ፣ በመያዝ እውቅና ተሰጧቸዋል።

እውቅናው በተቋማት የተመዘገቡ ውጤታማ አፈጻጸሞችን ለማበረታታትና በቀጣይ የተሻለ የልማት ውጤት ለማምጣት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

#እውቅና #ውጤታማነት

ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን  ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበበተጠናቀቀው በጀት አመት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን  ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የምዕራብ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለፀ።የመምሪያ ኃላፊው አቶ ግ...
23/07/2026

ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

በተጠናቀቀው በጀት አመት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የምዕራብ ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ገለፀ።

የመምሪያ ኃላፊው አቶ ግዛቸው ካሴ እንደገለፁት በ2018 በጀት አመት ከመደበኛ ገቢ 2 ቢሊዮን 544 ሚሊዮን 442 ሺህ 102 ብርና ከከተማ አገልግሎት ደግሞ 612 ሚሊዮን 324 ሺህ 726 ብር በድምሩ 3 ቢሊዮን 156 ሚሊዮን 766 ሺህ 828 ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ከመደበኛ ገቢ 1 ቢሊዮን 996 ሚሊዮን 578 ሺህ 661 ብር የተሰበሰበ ሲሆን ከከተማ አገልግሎት 378 ሚሊዮን 996 ሺህ 460 ብር በድምሩ 2 ቢሊዮን 367 ሚሊዮን 575 ሺህ 120 ብር መሰብሰብ እንደተቻለ ገልፀዋል።

የበጀት አመቱን የገቢ ዕቅድ ለመፈፀም የፀጥታ ችግሩ ዕንቅፋት ቢፈጥርም አሰቻይ ሁኔታዎች ባሉባቸው ወረዳዎችና ከተሞች በአዲሱ የግብር አዋጅ 16/2018 መሰረት የአመቱን ግብር በየሩብ አመቱ ግብር ከፋዩ እንዲከፍል በማድረግ፣ ከደረሰኝና ከቫት ገቢ በመሰበሰብና ባለፉት አመታት ከፀጥታ ችግሩ ጋር ተያይዞ ያልተከፈለ ከመንገድ ስራ ተቋራጮችና ከሌሎች ግብር ከፋዮች ውዝፍ ግብር በመሰብሰብ የዕቅዱን 75 በመቶ መፈፀም መቻሉን አንስተዋል።

በፀጥታ ችግሩ ምክንያት በንዑስ የወረዳ ከተሞ ገብቶ ገቢ መሰብሰብ ባለመቻሉና ነጋዴዎች አካባቢውን እየለቀቁ በመሄዳቸው ዕቅዱን ሙሉ በሙሉ ማሳካት እንዳልተቻለ ገልፀዋል።

ደምበጫ ከተማ፣ ፍኖተ ሰላም ከተማና ሽንዲ ከተሞች የተሻለ የግብር አፈፃፀም ሲኖራቸው ከወረዳዎች ደግሞ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ 91 በመቶ ገቢ በመሰብሰብ የተሻለ አፈፃፀም ማሳየቱን ጠቁመዋል።

ሌሎች ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች በፀጥታ ቸግሩ ምክንያት የሚጠበቅባቸውን ገቢ መሰብሰብ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

በ2019 በጀት አመት እንደ ዞን የታቀደውን ገቢ ለመሰብሰብ የዕለት ገቢ ደረሰኝና ቫት አንፃራዊ ሰላም ባለባቸው ወረዳዎችና ከተሞች በትኩረት በመሰብሰብ፣ ከመደበኛና ከከተማ አገልግሎት የግብር አርስቶችና ውዝፍ ግብር በተደራጀ መንገድ በመሰብሰብ የበጀት አመቱን የገቢ ዕቅድ ለማሳካት የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራቱን አመላክተዋል።

#ልማት #ግብር #ግልጽነት #ተጠያቂነት #ብልጽግና #ኢትዮጵያ

23/07/2026

Address

Finote Selam

Telephone

+251587750907

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when West Gojjam Zone Finance posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share