09/10/2026
የጋራ ዕድገት ምሰሶ ወንድማማችነት፣እህትማማችነት እና የህዝብ አብሮነት ነው !
በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት፣ ዘላቂ ልማት እና እውነተኛ ብልጽግና እውን ሊሆን የሚችለው በህዝቦች መካከል ያለው የወንድማማችነት፣የእህትማማችነት እና የአብሮነት ማህበራዊ እሴቶችን በፅኑ መሰረት ላይ ሲገነባ ብቻ ነው። የልማት ጥረቶች የማህበራዊ መሠረተ ልማት ብቻ ሳይሆን የሰውን ልጅ አብሮነት የሚያጠናክሩ አጠቃላይ ሂደቶች ናቸው።
በተለይም ማህበራዊ ትስስርን እና የጋራ መከባበርን ማጠናከር የኢኮኖሚ ዕድገትን ከማፋጠን ባለፈ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ዋስትና ይሰጣል። አንድነታችንን በልዩነት ውስጥ በማጽናት፣ በጋራ ልማት ጎዳና ላይ በአብሮነት መጓዝ የነገ ብልጽግናችን ማረጋገጫ ነው። የጋራ ዕድገት የሚረጋገጠው ማህበረሰቦች ሀብትንና ዕውቀትን በመጋራት፣ እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ሲያረጋግጡ ነው።
ዛሬ የምንገነባው የልማት መሰረት የነገውን የትውልድ ዕጣ ፈንታ የሚወስን በመሆኑ ወንድማማችነታችን፣እህትማማችነታችንና አብሮነታችንን ይበልጥ በማጠናከር በጋራ መስራት ይጠበቅብናል።
የኢኮኖሚ ልማታችን የህዝቦቻችንን ማህበራዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጸና፣ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ እና የጋራ ዕድገትን የሚያፋጥን መሆን አለበት።
በመሆኑም ለክልላችን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልጽግና መሳካት የህዝቦች አብሮነት፣ወንድማማችነትና እህትማማችነት ሊደራደር የማይችል ዋነኛ ምሰሶ ነው። ልዩነቶቻችንን እንደ ጸጋ በመጠቀም፣ በጋራ ኃይልና በመተሳሰብ የተሻለች እና የበለጸገች ክልልን እውን ለማድረግ ሁላችንም የድርሻችንን መወጣት አለብን።
የጋራ ዕድገታችን በወንድማማችነት፣በእህትማማችነትና በህዝብ አብሮነት ይረጋገጣል!
ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር