01/10/2026
የክረምት በጎ ተግባራት አገልግሎት እቅድ አፈፃፀም መድረክ ተካሄደ ።
ዳንሻ ፦መስከረም 21/2019 ዓ.ም በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የዳንሻ ከተማ አስተዳደር በሴቶች ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ሲካሄድ የቆየው ''በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ቃል የክረምት በጎ ተግባራት መዝጊያ ፕሮግራም ተካሄዷል።
የክረምት በጎ ተግባር እንደ ከተማ አስተዳደር በተለያዩ የልማት ስራዎች በመንግስትም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት መመሪያ በማውረድ መጠነ ሰፊ የበጎ ስራዎች መከናወናቸውን በሪፖርት ቀርቧል።
በተለይም ተቋማት በቁጥር በመሳተፍ የህብረተሰቡን የጋራ ጥቅም በሚያገለግሉ ተግባራት ላይ ያሳዩት ተሳትፎ በጎ ተግባራት በማህበረሰቡ ዘንድ ያላቸውን ሚና ያሳዩበትና የተከናወኑት ተግባራት በአንድ ወቅት ተወስነው የሚቀሩ ሳይሆኑ፣ የበጎ ፈቃድና የማህበራዊ ተሳትፎ ባህልን በማጠናከር በቀጣይም እንዲቀጥሉ ክቡር ከንቲባው አብድልዉሃብ ማሙ ገልፀዋል።
በተሰራው የክረምት እንቅስቃሴ የአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቤት ማደስ እንደ አዲስ በመስራት፣ የተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስ መሰብሰብ ፣በተጨማሪም የደም ልገሳ ሂደቶችን ያከናወነ ሲሆን የተገኙ ግብዓቶችን ፍትሀዊ በሆነ መልኩ ለተፈለገው አላማ እንዲውል በልዩ ክትትል መሄድ እንዳለበት ተብራርቷል።
ተቋማት ስራውን እንደ ባህል ወስደው መሰራት እንዳለባቸው ሀላፊነት ተሰምቷቸው በተግባርና ውጤት በመለካት ሂደቱ በሪፖርት ብቻ እንዳይሆን ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት በተዋረድ ተፈፃሚነቱን ማረጋገጥ ተገቢነት እንዳለው በመድረኩ ተመላክቷል።
በተጨማሪም በተከወኑ ስራዎች ሳይረኩ በታዩ ክፍተቶች እርምት ወስዶ ለቀጣይ ተግባራት የመፍትሄ አቅጣጫ እያስቀመጡና እየገመገሙ መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን ተሳታፊዎቹ አንስተዋል።
በበጎ ተግባሩ የተለያዩ የማህበረሰብ አባላት፣ ወጣቶችና በጎ ፈቃደኞች በመሳተፍ የአካባቢ ጽዳት፣ የችግኝ ተከላ፣ቤት መስራትና መደስ ፣የህዝብ መገልገያ ቦታዎችን ማሻሻልና ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል።