Shagiiz.Abebe

Directions Contact the organization

Shagiiz.Abebe Social News Service
መረጃ ሙሉ ሰው ያደርጋል‼

በትግራይ በህወሓት የጦርነት ትንኮሳ መሰረት  ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ በነገው ዕለት ይጀምራል። መከራና ጦርነት ጠሪ የሆነው የሻዕቢያ አገልጋይ ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ...
02/02/2026

በትግራይ በህወሓት የጦርነት ትንኮሳ መሰረት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ በነገው ዕለት ይጀምራል። መከራና ጦርነት ጠሪ የሆነው የሻዕቢያ አገልጋይ ከትግራይ ህዝብ ጫንቃ ለማውረድ ትግራዋይ ተደራጅተህ ታገለው።

በግምት የሚፀድቁ የብልፅግና ህግና ደንቦች‼========ማንኛውም አይነት የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም ከተከለከልን አንድ ቀን ሆኖታል። ጋዜጣ፣ መጽሐፍትና መጽሔት እንዲሁም ቀለም የታተመባቸው ወ...
01/02/2026

በግምት የሚፀድቁ የብልፅግና ህግና ደንቦች‼
========
ማንኛውም አይነት የፕላስቲክ ከረጢት መጠቀም ከተከለከልን አንድ ቀን ሆኖታል። ጋዜጣ፣ መጽሐፍትና መጽሔት እንዲሁም ቀለም የታተመባቸው ወረቀቶችና የማደበርያ (Polypropylene) ምርቶች በስፋት ለመጠቅለያነት ገበያ ላይ እንደሚውሉ ገምቼ ነበር። ሁሌም ስራን ጥርትና ጥንቅቅ አድርጎ በጥናት ላይ ተመስርቶ መስራት አለመቻልና አለመፈለግ ውጣ ውረዱ ብዙ ነው።

ዛሬ ጠዋት ዳቦ ስገዛ ዳቦው የተጠቀለለበት ወረቀት የአንድ ባንክ (ፎቶ ይመልከቱ) የገንዘብ ወጪ ማዘዣ ነው። የጨነቀው እርጉዝ ያገባል እንዲሉ መፍትሔ በግድ ፈገግ አሰኝቶኛል። ከፌስታል ወደ ውዳቂ ወረቀት ይሄ ነገር ከፍታ ነው ዝቅታ ግራ የሚገባ ነው።

ከፌስታል ኬሚካል ወደ ሕትመት ቀለም ኬሚካል ተሸጋግረናል ማለት ነው ?! ከአካባቢ ብክለት ባሻገር የኬሚካል ይዘታቸው ለካንሰር በማጋለጥ የትኛው እንደሚብስ ለጤና ባለሙያዎች ትቼዋለሁ።

በደርግ ዘመን በቂ የወረቀት አቅርቦት ስላልነበር። ስጋን ጨምሮ ሸቀጥ የሚጠቀለልው በጋዜጣ ነበር። የሕትመቱ ቀለም ለካንሰር ያጋልጣል በሚል የጋዜጣ መጠቅለያ መከልከሉን አስታውሳለሁ።

ሌላው ያስደመመኝ ነገር የተከለከለው የፕላስቲክ ከረጢት ምን ዓይነት እንደሆነ አለመታወቁ ነው። በየገበያውና በየሱፐር ማርኬቱ የሚሸጡ አብዛኛዎቹ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሀገር ምርቶች ዘይትን ጨምሮ ከፕላስቲከሰ ከረጢት በማይሻልና በሚቀራረቡ የፕላስቲክ ምርቶች የማይታሸግ ነገር የለም። ከሆነስ ዘንዳ አማራጩ ምንድን ነው ?! የፕላስቲክ ከረጢትን የሚተካ በቂ የወረቀትና አማራጭ አቅርቦትስ አለ?

የተከለከለው በጅምላ የፕላስቲክ ማሸጊያና መያዢያዎች ከሆኑ ዘይትን ጨምሮ ከውጭ የሚመጡና ሀገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ማሸጊያቸው ወደ ወረቀት ይለወጥ ይሆን? ወይስ ከፕላስቲክ ማሸጊያዎች ውስጥ የተከለከለው ዓይነት ይታወቃል ?! ጥያቄ የሚያጭር ጉዳይ ነው ?! ደንብ አስከባሪው አካልስ ማነው ፖሊስ፣ የወረዳ ደንብ? ሚሊሺያ? ... እንካ ሰላምታና ውዝግብ እንደሚፈጥር ጥርጥር የለኝም። ለማንኛውም ስራን ጥርትና ጥንቅቅ አድርጎ በጥናት ላይ ተመስርቶ መስራት አለመቻልና አለመፈለግ ውጣ ውረዱ ብዙ ነው።

በነገራችን ላይ በተለምዶ ማዳበርያ የሚባለው ማሸጊያ (Polypropylene) ከረጢት የሚመረተው ከፕላስቲክ ነው።
semu

31/01/2026

ወያኔ በህዝብ ደረጃ ጠላት አድርጎ በብቸኝነት የፈረጀው የአማራን ህዝብ ነው‼
==========
ወያኔ የአማራን ህዝብ በጠላትነት የጀመረው ገና በደደቢት በረሀ ሲመሰረት ጀምሮ ነው ። ለወያኔ የአማራ ህዝብ ትምክህተኛ ነው ፤ ገዢና ጨቋኝ መደብ ነው ፤ ተስፋፊና ወራሪ ህዝብ ነው።

ወያኔ ይህንን ቋጥሮ ላለፉት ሰላሳ አመታት የአማራን ህዝብ በተለየ መልኩ የመምታት ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርፆ ሲተገብር ኖሯል። በዚህም እንደየትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ሁሉ ከየትኛውም አገዛዝ ተጠቅሞ የማያውቀው የአማራ ህዝብ ከፍተኛ ገፈት ቀማሽ ሆኖ አልፏል። ወያኔ በፈጠረው የአማራ ህዝብ በዝባዥነት ተረክ የአማራ ህዝብ የገንጣይ ብሔርተኞች ሁሉ የጥቃት ኢላማ ሆኖ በአራቱም አቅጣጫ ተጠቅቷል። እየተጠቃም ነው!

የወያኔ በአማራ ላይ የያዘው ቂም ዘመን የማይሽረው ሁኔታ የማይለውጠው ነው። የትግል መዝሙሩን ሳይቀር አማራን ስለመምታት ስለማንበርከክ ነው ወያኔ ከአማራ ህዝብ ላይ ምላጩን ነቅሎ አያውቅም።

ወያኔ ከስልጣኑ ከተወገደ በሗላ በመከላከያ ሰራዊት ላይ በፈፀመው የክህደት ጦርነትና ከዚያ በሗላ ለደረሰው ያ ሁሉ ሰብአዊ እልቂት ዋና ተጠያቂ የሚያደርገው የአማራን ሀይል ነው። የወያኔ አመራሮች የሚሉት በትግራይ ላይ ለተፈፀመው "ጄኖሳይድ" ዋና ተጠያቂው የአማራ ሀይል ከዚያም የሸእቢያ ሰራዊት ነው። መከላከያ ሰራዊት ጄኖሳይድ ፈፀመ ሲሉ ብዙ አይሰማም። አብዛኛው የጦር ወንጀሎች የተፈፀሙት በአማራ ፋኖና በሸእቢያ ነው ብለው ነው ይፋ የሚያደርጉት። ከትግራይ ይውጣልን ሲሉ የነበሩትም የአማራ ሀይልን እና ሸእቢያን ነበር።

ለዚያም የወያኔ አመራሮች የዘወትር ዛቻ " ከአማራ ተስፋፊ ሊሂቅ ጋር ሂሳብ እናወራርዳለን" የሚል ነበር።
ይሄንን ቃል በኦሮሞውም ሆነ በየትኛውም የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ አልተጠቀሙትም።
ተገላባጩ ወያኔ የብልፅግናን የሀይል ሚዛን ለማመጣጠን ከሻእቢያ ጋር ጥምረት ከፈጠረ በሗላ ግን አማራን በወያኔ ሀይል ከመበቀል ይልቅ አማራን በአማራ መበቀልና አማራን የማይወጡበት የውድመት ቀጠና ማድረግን መረጠ። በርግጥ አዋጭ ስትራቴጂ ነው።
ክልሉን አወደመው ከየትኛውም ጦርነት በላይ አደቀቀው። ወያኔ በርግጥም የአማራን ህዝብ ተበቅሏል።
ወያኔ በመከላከያ ሰራዊትና በፋኖ ሀይል መካከል በሚደረገው ፍትጊያ ሁለቱም ከተዳቀቁና ከተዳከሙ በሗላ የአማራ ክልልን ለመውረር ነበር ሲዘጋጅ የከረመው።

እንግድህ የወያኔ ህልም ወልቃይትንና ራያን ጠቅልሎ ሀገረ ትግራይን መመስረት ነው።

የማን ህልም ይሳካል?
የምናየው ይሆናል!

29/01/2026

ልዩ መረጃ

ወደ ትግራይ ክልል የሚደረጉ መደበኛ የአየር በረራዎች ከዛሬ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ተቋርጠዋል‼️

29/01/2026

አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ወጣቶች ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ ጥሪ አቀረቡ

ራሳቸው የጫሩትን እሳት ራሳቸው ይሙቁት! ሲሉ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፈዋል

የፕሪቶሪያን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እንደ ፖሊሲ ይዘነው የነበረው ከግጭት ውጪ ተፅዕኖ መፍጠር የሚያስችሉን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እና ከፌዴራል መንግስት ጋር በተደጋጋሚ የተካሄዱ መድረኮች ወደ ተግባር እንዳይቀየሩ ከግል እና ከቡድን የስልጣን ጥም ጋር በማያያዝ እንቅፋት የሆኑ የህዝባችንን ስቃይ ያራዘሙና በወንጀል ሊጠየቁ የሚገባቸው አካላት የክልላዊ አንድነትን የማረጋገጥ እና ተፈናቃዮችን የመመለስ ስም በመላከክ በድጋሚ ወደ ጦርነት ለማስገባት የሚችሉትን ሁሉ እያደረጉ ይገኛሉ።

ተፈናቃዮችን መመለስ በታማኝ መንገድ በዘላቂ ሰላም እና መተማመን ላይ የተመሰረተ ህዝባችንን ማቋቋም እና የመልሶ ግንባታ ፍላጎቶቹን ለማሟላት የውጭ እና የውስጥ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎንና ከፍተኛ የፋይናንስ ድጋፍ የሚጠይቅ ተግባር መሆኑ ይታወቃል።

ምንም እንኳን ብዙ ችግሮች ቢኖሩም የአፈፃፀም መንገዱ ሙሉ በሙሉ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በፕሪቶሪያ ስምምነት መሰረት መሆን ይጠበቅበታል።

ሁሉንም ዓይነት እድሎች አጥፍታችሁ የብሔሩን አቅም በትናችሁ የሰላም በር የሚዘጋበትን እና ወደ ግጭት የምንመለስበትን ሁኔታ አመቻችታችሁ በተፈናቃዮች ጥያቄ ስም አጃቢዎቻችሁን ለማስደሰት ስትሉ የጀመራችሁት የት መቼ እና እንዴት እንደሚያልቅ ለመገመት የሚያስቸግር ነገር ግን በእርግጠኝነት ትግራይን የጦርነት አውድማ የሚያደርግ ትንኮሳ ልታቆሙ ይገባል።

የሚገርመው አሁንም የወጣቱን ህይወት እንደ ዋና የጦርነት መሳሪያ መጠቀም በመቀጠል እንደተለመደው በከባድ መሳሪያ አስቀድሞ ሽፋን በመስጠት የሚከፈለውን ዋጋ መቀነስ የሚለው የጦርነት ስልት ጠፍቷችሁ ነው ክላሽ የያዘ እግረኛ አስቀድማችሁ የምታስጨርሱት?

እነዚያ መድፎችስ ለመቼ እና ለማን ሊሆኑላችሁ ነው? የከበረ የወጣት ህይወት "አለሁ" ለማለት ብቻ ትሰዋለህን?
ያም ሆነ ይህ ተጋዳላያችን ህመምህ እና ህዝባዊ መርህህ ለርካሽ ፖለቲካዊ ንግግራቸው እንዳይጠቀሙበት ተጠንቀቅ።

በትግልህና በከፈልከው በማንኛውም ዓይነት መስዋዕትነት እንዲፈረም ያደረግኸው የፕሪቶሪያ ስምምነት ፖለቲካዊ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ መፈታት የሚያስችል የዚህ ወቅት መድረካዊ ተልዕኮ መሆኑን ተገንዝበህ ተጨማሪ ከንቱ መስዋዕትነት አልከፍልም በማለት ተቃውሞህን አሰማ።

መስዋዕትነትህን ደጋግመው ያረከሱ የፖለቲካና የጦር መሪዎች አሁንም የወጣቶችን መስዋዕትነት መሰረት ያደረገ ከጦርነት በታች ያለ ፍጥጫን ወደ ሙሉ ጦርነት ለመውሰድ የጀመሩትን ትርጉም አልባ እንቅስቃሴ እንዲያቆሙ የሚቻልህን ሁሉ አድርግ።

ራሳቸው የጫሩትን እሳት ራሳቸው ይሙቁት!

29/01/2026

ኢራን ወታደራዊ እርምጃውን መቋቋምና መመከት ትችል ይሆናል ኢኮኖሚዋ ግን በአስጊ ደረጃ እየወደቀ ነው።
በአሁኑ ሰአት አንድ የኢራን ሪያል ምንም መገብየት የማይችል ገንዘብ ሆኗል። አንድ የአሜሪካ ዶላር በ 1.51 ሚሊዮን የኢራን ሪያል የሚመነዘር ሲሆን ወደ ዩሮ ቢመነዘር ደግሞ ወደ ዜሮ የተጠጋ አሀዝ ይኖረዋል። ይህም የኢራንን ገንዘብ ዋጋ አልባ ያደረገው ሲሆን ከወረቀትም ያነሰ ሆኗል። እስከዛሬ ከተጣሉት ማእቀቦችም በላይ ሌሎች ጠቅላላ እግዶችን ምእራባውያን እየጣሉ ይገኛሉ።

አሜሪካና እስራኤል ኢራንን ይህን ጊዜ እንደተዳከመች እንጨርሳት ብለው ቆርጠው የተነሱ ቢሆንም ወታደራዊ ምላሿ አስፈርቷቸው አሁንም ፈራ ተባ እያሉ እያደቡ ነው።

ኢራን ቆስላለች። ብቸኛዋ አጋር አልባዋ ጎረቤትም የሩቅ አጋርም የሌላት ኢራን ለአመታት ስትታገለው የኖረቺው ህልቆ መሳፍርት የሌለው ጠላት ክንዷን አዝሏታል።
ኢራንን ደህና እንድትሆን አልፈቀዱላትም። እንድታድግ አልፈቀዱላትም።
ሀብታሟና የስልጡኖች ሀገር ጥንታዊቷና ፐርሺያዊቷ ሀገር ፤ አለምን በእውቀት ያበራቺው ፤ ፍትህ ምን ማለት እንደሆነ ነፃነትና እኩልነት ምን እንደሆነ ከሺህ አመታት በፊት ለአለም ያስተዋወቀቺው የእውቀት ካዝናዋ፤ ኢራን የጥበብ ምንጯ ኢራን ፤ የነ አልጎሪዝም አልጀብራ እና ሌሎች ተነግረው የማያልቁ የሳይንስ ግኝቶችን በልጆቿ ያበረከተቺው ኢራን ዛሬ እስላሙም ክርስቲያኑም አይሁዱም ጠላት ሆኖባት እዚያ ዙሪያዋን በጠላት ተከባ የአልሞት ባይ ተጋዳይ ትግል ልታደርግ ምላጯን ስባ እየተጠባበቀች ነው።

አለም ለውለታ ደንታ የለውምና አበርክቶዋ ሳይገዳቸው አይንሽን ላፈር እያሉ ጥፋቷን የሚመኙት እጅግ ብዙ ናቸውና ካንዣበባት ሀይል ልትተርፍ ወገቧን እያጠባበቀች ትገኛለች።
ትፀናለች ወይንስ ትሰበራለች?
እናየዋለን!
tm/Shagiz.Abebe

Address

Gondar
DEBRETABOR

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Shagiiz.Abebe posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Shagiiz.Abebe:

Shortcuts

Share

Category